uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

የክብሩ ነፀብራቅ✨

የክብሩ ነፀብራቅ✨

Відкрити в Telegram

ልጁም የእግዚአብሔር የክብሩ ነጸብራቅና የአምላካዊ ባሕርዩ አምሳያ ነው፡፡ ወልድ አምላክ በመሆኑም ይህን ዓለም በሥልጣኑ ኃይል ይቆጣጠረዋል ፤ በሥርዓት እንዲመራም ያደርገዋል ። እኛን ከኃጢአት ለማንጻትና የተመዘገበብንን የበደል ደብዳቤ ለመደምሰስ ከሞተ በኋላ ፥ አሁን በአባቱ ጎን ባለው ከፍተኛ ሰማያዊ የክብር ቦታ ተቀምጧል ። [ሕያው ቃል ዕብራውያን 1:3]

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
355
Підписники
+224 години
+197 днів
+11330 днів
Архів дописів
ደህና እደሩ ☺️ የያዕቆብ ሌሊት ይሁንላችሁ ❤ @ShekinnahKBR

Thank you for 343 subscribers, Family! 🙏🏾✨ ​ቁጥሩን ሳየው ግን ድሮ "143" ብለን የጻፍነውን ነገር አስታወሰኝ 😁 (የሚያውቅ ያውቃል እንግዲህ... no explanation needed, right? ☺️🤫) አዕምሮዬ ግን በምን ሂሳብ ሁለቱን እንዳገናኘው እንጃ 🙄😂.....🧐🤔 ​አሁን ደግሞ ወደ 343 አድገናል! "ሕዝብህን አበዛ..." 🙌🏾 እያልን፣ Share እያደረግን መዝሙሯንም አብረን እንዘምር! 🎶 ​
ተባረኩልኝ፣ እወዳችኋለሁ! 🤍
​✨ @ShekinnahKBR

አዲስ የስልክ Wallpapers 🔥. በእርግጠኝነት ትወዱታላችሁ 👌 @ShekinnahKBR
+9
አዲስ የስልክ Wallpapers 🔥. በእርግጠኝነት ትወዱታላችሁ 👌 @ShekinnahKBR

አሁንም ብዛልኝ እንዲረዝም እድሜዬ አብዝቼ ልጠጋህ እንዲደምቅ ማታዬ🧎🧎 @ShekinnahKBR

እኔ እርሱን የማውቀው በመልካምነቱ እኔ እርሱን የማውቀው በመሃሪነቱ . . እኔ እርሱን የማውቀው እንደዚህ ነው እስራቴን ፈትቶ ሲለቀኝ ነው🥹🥹🥹 @ShekinnahKBR

እግዚአብሔር አይዋሽም ግን ያባብላል! እግዚአብሔር ሲያባብል ደግሞ ቀጥሎ የሚመጣው ነገር ምድረ በዳ ነው። 🏜️
​"ስለዚህ፣ እነሆ፣ አባብላታለሁ፣ ወደ ምድረ በዳም አመጣታለሁ፣ ለልብዋም እናገራለሁ።" — (ሆሴዕ 2:14)
​ግን ደግሞ እጅግ ጥልቅ የሆነ የልብ ንግግር የሚጀምረው፣ ማንነታችን የሚሰራው እዛ ምድረ በዳ ውስጥ ነው! This is how God works. 🙌🏾✨ ​በእንደዚህ ዓይነት Season (ወቅት) ውስጥ ካላችሁ፣ ቀጥሎ በሚመጣው ምድረ በዳችሁ እግዚአብሔርን ልትገናኙት ተዘጋጁ! 🔥 ✨@ShekinnahKBR

Голосове повідомлення04:22

“እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኃይላችን ፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።”                 መዝሙር 46:1 @ShekinnahKBR

የማይሞላ ጉድጓድ የሥጋ ምኞት በቃኝን አያውቅም! መቼም እንደማይሞላ ሲኦል፣ የፍጻሜ ወለል እንደሌለው ጥልቅ ጉድጓድ አይጠረቃም። እንኳን ከሌሎች 7 ቢሊዮኖች ሰዎች ጋራ ተካፍለናት ይቅርና ዓለም ራሷ ተጠቅልላ የእኛ ብትኾን እንኳን የምኞት ጉድጓዳችንን አይሞላውም። እግዚአብሔር ልባችንን የሠራው ነውና የሰራው በራሱ ልክ ነውና ከ እሱ ሌላ አንድ ሊሞላ የሚችል ነገር የለም። እሱ ሲገባበት ግን ጢም፣ ልክክ ይላል፣ ከአፍ እስከ ገደቡ ይሞላል። ያኔ ሰው ስለሚረካ ለራሱ "ኑሮዬ ይበቃኛል!" ይልና የሌሎችን ጉድለት ለመሙላት ያስባል፣ እጁን ይዘረጋል። ጌታ ሆይ፥ ምኞት የኃጢአት እናት፣ የሞት አያት፣ የአሮጌው ሰው መገልገያ፣ የውድቀት ጥግ ማሳያ ናት። እባክኸን ኃጢአተኛ ተፈጥሮዬን ከምኞቴ ጋር ሰቅዬ በትንሳኤህ ሕይወት በአንተ የረካ ኑሮ እንድመራ እርዳኝ። እውነተኛ አምልኮ ከዝማሬ ባለፈ በአንተ ተደስቶ፣ በማንነትኸ ረክቶ መኖር ነውና አንተ ብቻ እርካታችን ኹነልን። አሜን !🙏 ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን እፎይታ ሣልሳይ

የሃጢአተኛው ጽኑ መሸሸጊያ የኢየሱስ ቁስሎች ውስጥ ነው🥰

ለምን እንደሚኾን አላውቅም ፤ አንዳንድ ጊዜ እንደዚኽ ይሰማኛል። የቀረብኳቸው፣ እነርሱም ደጀ ሠላም ብለው የተቀበሉኝ ሰዎች ጋር በዐሳብ እነጉድና ራሴን ረስቼ ስለ እነርሱ ዐስባለኹ። ሰዉ ለወዳጁ ሊኾንለት የሚገባውን በምን ያኽል ልክ እንዲኾን፣ ልቤ ማወቅ ይቃጣውና መለኪያ ሚዛኑን አንግቤ ራሴን እለካለኹ። Am I really important to them? የምር ግን አስፈልጋቸው ይኾንን? ወይስ በእንዲኹ ቀጠሮ እንደተገናኘ ፋይዳ ቢስ እግረኛ፣ ምንም የማላበጅ፣ ምንም የማልፈይድ ብኩንነት ተሸክሜ ሌላ የጀርባ እሾኽ ልኾን የቀረብኩ ክፉ ሰው ነኝ?  እውነት ግን አስፈልጋቸው ይኾን? ወይስ የሰዉ ጊዜ የምሰርቅ፣ ከሕልመኛነት ላይ ጎትቼ በራሴ አልባሌ ሜዳ ላይ ባዶነት የማፋጅ «ሕልም አደናቃፊ» ድንጋይ ነኝ? ‎ ‎ማን ነኝ እኔ ለዕገሌ/ሊት? በራሴ ውስብስብነት ጥያቄ ውስጥ ብቻ ታጅቤ ጎዳናዬ ላይ እማላዝን ችግሬን ብቻ አንጋቢ ስለኾንኩኝ፣ በእኔነት ወጥመድ ተቀፍድጄ ሕልሜን የማሳድድ ስለኾንኩኝ፣ ለቀረብኩት ሰው የዚኹ ዕዳ ተካፋይ ከማድረግ ውጪ ሌላ ፋይዳ የምሰጠው አይመሥለኝም። ይባሱኑ ከመንገዱ ላይ ጎትቼ ሕልሙን የማስረፍደው እንደኾነ ይሰማኛል፤ ከብርቱ ሩጫው ላይ ያስቆምኩት/ያሰናከልኩት ድሉን ነፋጊ መጥፎ አቊሳይ የኾንኩ ያኽል ጥያቄው ያምመኛል። ሠላም ነግቤ ከሠላም የማጎድል፣ ጥሩ መሥዬ መልካምነት የምነፍግ፣ ሰውን ከራሱ መዝገብ ላይ ሰርዤ ውሉን የማሳጣው ክፉ መንገደኛ....። እንደውም አንዳንዴ «ጌታ ሆይ ከክፉ አድነኝ» ብለው የለመኑ ሰዎች እኔን ከማግኘት የሚጠበቊ/የሚድኑ መኾናቸው ይሰማኛል። ለራሱ ብቻ ብዙውን አድራጊ ሌላውን የማይፈይድ፣ ለራሱ የሚፈጥን ሌላው ጋር ዘገምተኛ፣ የሌላውን አተራምሶ የራሱን ቤት ሊያሰናዳ መሰሶ የሚያቆም (ጅራፍ የሚያነሣ).... ብዙ ብዙ... ዕብራውያን 13:‎3 ከእነርሱ ጋር እንደ ታሠረ ኾናችኹ እሥሮችን ዐስቡ፥ የተጨነቊትንም ራሳችኹ ደግሞ በሥጋ እንዳለ ኾናችሁ ዐስቡ።  ይኽ ቃል ደግሞ ባነበብኩት ቁጥር የመንፈስ ቅዱስ ዕረፍት የለሽ ንዝናዜ ያይልብኝና ምነው ሰው ባላወቅኹ.... ሰዎች ባልቀረብኩ?! ያስብለኛል። ለዚህ ኹሉ የተናደና ድፍርስ ጥያቄ በቂ መልስ የለኝም። እሱም ሌላ ፍዳ ነው፤ ለጥያቄ መልሱን አለማግኘት። Find a friend who you can build with, not just chill with. ጥሩ የሰውነት ልጓም መርሕ ይመሥላል። ‎ ‎እንዴት ያምማል በስመ-አብ?! መጥፎ በሽታ፣ ምርቅዝ ቊስል። እውነትም ሰዉ አለማወቅ «ሠላም ነው» ያሰኛል። ሕልም የእውንነት ግማሽ ነው፤ የነገ ሕልም የሌለው ሰዉ እውነቱን ከወዲኹ ጒድጓድ የሚቀብር ቂል ነው። ታዲያ ግን እኔ፣ ለነገዬ ብሎ ሕልሙን ከወዲኹ የሚያሰናዳውን እውነት ፈላጊውን መና የማስቀር፣ ቂል (ሞኝ) የማደርግ ቊስል አዳይ መንገደኛ። ‎ ‎እውነት ያምማል! ጌታ ሆይ መድኃኒት ኹነኝ... በሚያባብል ቃል አልሸነገልኩኽም፣ ነገር ግን ውስጤ ያለውን የተሸነተረ እውነተኛ በሽታዬን እነግርኻለው። ምን አልባት ጌታ ሆይ፣ እንደዚህ ዐይነት ሰው እኾንን? ውስጤን መርምር ልቡናዬን መርምር፤ እኔም ሰዎችም ያላዩብኝን አንተ ዕይ፤ ጥያቄው እንደ ብርቱ ድንጋይ አልቆረስ ያለ ቢሆንም  ከምድሩ አጐንብሶ መፍትሔውን መታገል ትክክል አይመሥለኝም። አባት ሆይ አንተ ጋር ንጹሕ ልብ አለ፤ ቀና ልብ አለ። ከባሕርዮተ-አንተነትኽ ላይ ቆርሰኽ አድለኝ፤ «ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ። » ‎ ‎አቤቱ ፈትሸኝ ፈውሰኝም! ሊያድን እንጂ ሊ'ያድን ብቻ የወጣ ክፉ መንገደኛ አልኹን። ካለኹበት ከዚኽ ዐስተሳሰቤም አድነኝ ቊስሌንም ፈውስ። ‎ ‎ለሰዎች ማን ነኝ? ትልቅ ጥያቄ.... መልስ ያስፈልገዋል!! ‎ ✍ Sam. A.

the Phillips Modern English rendering of 1 Peter 5:7, “
You can throw the whole weight of your anxieties upon him, for you are his personal concern.”

. እግዚአብሔር ፀሎትን ይሰማል! @ShekinnahKBR

.....       መነካት....🫳🫴 የክርስትናን ጉዞ ከጌታችን ከኢየሱስ ጋር ከጀመርን ሕይወት ሰምበትበት ብሏል። አጽናኙ መንፈስ መሪ መሆኑን ስናስብ ዕርግጠኝነታችን ይህ ነዉ አይባልም🔥። አቤት! የኑሮ ጣዕም ፣ የተስፋ ጸዳል ፣ የመኖር ጉጉትና ሕይወትን መዉደድ እንዳልላሱት ማር በጽኑ ያስጎመጃል ።  ያላየናቸዉን ቀኖቻችንን ናፍቀናቸዋል ነዉ ምላችሁ...🙌! በዚህ ክቡር ሕይወት ጎዳና ዉስጥ የተጓዦች አቅም የምወሰነዉ፣ ጉልበታቸዉ የምጎለብተዉ ፣ ለጉዞአቸዉ ቀና አመለካከትና ትጋት የምኖራቸዉ ከመሪዉ መንፈስ ቅዱስ ጋር ባላቸዉ ግንኙነት(intimacy) ልክ ነዉ። በዉስጣችን ካለዉ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጥልቅ ሕብረት የምንጀምርበት፣ በነፍስ ዕዉቀት የገባዉን በሕይወት ልምምድ የምናጎላበት ፣ የጉዞአችንን ቀለብ ሰንቀን የምንነሳበት፣ እግዜር ልባችንን የምያሰናዳበት ትልቁና የተለየ ክስተት መነካት(Encounter) ነዉ። ከጩኼትም ዝም  ከማለትም ፤   ከመንከባለልም  ስሜት ከታከለበት ከአንድ ቀን ዕምባም ያለፈ ነገር ነዉ  ባይ ነኝ መነካት። በርግጥ የሥጋችን ምላሽ መሆን ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን አይገልጹትም። በአዕምሮችን እንደዛ ስለን እነደሆነን ፣  ከመፈለግ እንጎድላለን የረካን ስመስለን።
ቃሉ ያፈራዉ እዉነተኛ መነካት፦ የእግዚአብሐርን መነጽር አጥልቆ አጽናፈ ዓለሙን መመልከት ነዉ።
  ለእግዚአብሔርና ለራሳችን፣  ለወንድሞቻችንና ለክርስቶስ አካል ፤ ለዓለምም እንኳን ባለን ዕይታ  የእግዚአብሔርን አዕምሮ(Godly mind) የምንጋራበት ድንቅ ክስተት ነዉ። የሕይወት ዘመን  ጉዞ እንጅ ሰሞነኛም አይደለም ። ቀምሰዉ እንዳዩ ምላሶች  ፥  የቃሉ ርሃብ ፣ የጸሎት ጥማት ያኃይላል።  የወንድማማች መዋደድና የቤተ ክርስቲያን መታነጽ እንደዶፍ ይዘንቡብናል። መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን ፍቅር በልባችን ያፈስብናል። ፈቃዱን ያስረዳል። መንበርከክ ያጓጓል፣ ነገሮች እንደድሮ normal አይሆኑም። "ኢየሱስ የወደኛልኮ" ማለት  ለቀናት የምናነባበት የምያሳርፈን እዉነት ይሆናል። የነካዉን ለመንካት ርሃብ ይጸናል ፣ ፍለጋውም ይብሳል። ዓለም በጉዳት ትተመናለች ፤ ነፍሱም መሪዉጋር ትከርማለች። ጉዞ ይጣፍጣል ነዉ ምላችሁ...🙌። ካልሆነማ! ምን ልበላችሁ?...👐  በጣም አዳጋችና ታማኝነትን የምጎድል ቁልቁለትና ዳገት ይሆናል ። በዚህ ምድር ከባዱ ሸክም ተደርጎ ይሰላል። ቀድሞ የገባ ዕዉቀት ሁሉ የቤቱ ራስ ይሆናል። የእዉነት መሌክያ የአመክንዮ(logic) ልህቀት ሆኖ ይቀራል። መንፈሳዊ ልምምድ "ለእኔ ዕገለ" ጎራ ይሰጣል።
ሥጋ በብዙ ሰበብ በድሎት ሰፈነጥዝ ፣ ነፍስ ግን ከነጬኼቷ በርሃብ ትጠወልጋለች👐 አድነን!..🙌
ባለ ብዙ መንገድ የሆነ አምላክ በምገባላችሁ መንገድና ቋንቋ ለቀሪ ዘመናችሁ ስንቅ በምሆን መነካት ይንካችሁ....🙌🥰🔥! https://t.me/followhistrace ....

ክርስቲያኖች ኀጢአተኛ ሆነን ለቅድስና የምንታገል ሳንሆን ቅዱስ ሆነን ኀጢአትን የምንታገል ነን። በሁለቱ መካከል እጅግ የሰፋ ልዩነት አለ። ከ ''የፖርኖሲስ ትውልድ'' መጽሐፍ የተወሰደ

. አንዳንድ ሰው ግን ፎሎ ያረገኛል ተመልሶ ሀንፎሎ ፎሎ ያረገኛል ሀንፎሎ ያረገኛል😁😁 ተው እረፉ ተመለሱ @ShekinnahKBR

. ለነፍሳችን "ስኬት ምን ማለት ነው? መኖርስ ምንድነው?" ለሚለው ጥያቄ ቁርጥ ያለ መልስ እስካልሰጠን ድረስ እረፍት ምን ማለት እንደሆነ አናውቅም። ​
እግዚአብሔር አምላክ ከሃሳቡ ጋር ያገናኘን! 🙌🏾
​✨ @ShekinnahKBR

“የፈጠረህ ከማኅፀንም የሠራህ የqሚረዳህም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ባሪያዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም ይሹሩን ሆይ፥ አትፍራ።” — ኢሳይያስ 44፥2 @ShekinnahKBR

በሰላም እደሩ🥰