cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Ministry of Agriculture-Ethiopia

All agri related news and updates

Больше
Рекламные посты
1 337
Подписчики
+224 часа
+727 дней
+17530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

በአፈር አሲዳማነት የተጠቁ መሬቶችን በማከም ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር እየተሰራ ነው። -የግብርና ሚኒስቴር ሚንስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) (አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2016 ዓ.ም፤ ግብርና ሚኒስቴር) በአፈር አሲዳማነት የተጠቁ መሬቶችን በማከም ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ። የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኦሮሚያ ግብርና ቢሮ የጉደር ኖራ ማዘጋጃ ፋብሪካን ጎብኝተዋል። የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በጉብኝቱ ወቅት፤ በኢትዮጵያ ከሚታረሰው መሬት ውስጥ 43 በመቶ የሚሆነው በአሲዳማነት የተጠቃ መሆኑን ተናግረዋል። ይህን የአፈር አሲዳማነት በማከም ምርታማነትን ለመጨመር የተለያዩ ሥራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። ለአብነትም የኖራ ፋብሪካዎችን አቅም የማሳደግና አዳዲስ ፋብሪካዎችን በተለያዩ ቦታዎች ለማስፋፋት ዕቅድ ተይዞ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። በሌላ መልኩም የአፈር አሲዳማነትን ለመቀነስ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ኖራን እንዲያመርቱ መግባባት ላይ መደረሱንም ጠቁመዋል። አሁን ላይ በኦሮሚያ ክልል የጉደር ኖራ ማዘጋጃን ጨምሮ በአማራ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በአጠቃላይ ሦስት የኖራ ማዘጋጃ ፋብሪካዎች መኖራቸውን ገልፀዋል። የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ግብርና የሀገር ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት በመሆኑ ዘርፉን ማገዝ የሁሉም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል። የገንዘብ ሚኒስቴር በአፈር አሲዳማነት የተጠቁ መሬቶችን ለማከም አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ገመቹ፤ በክልሉ ከ1 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት በላይ በአፈር አሲዳማነት የተጠቃ ነው ብለዋል። የዘገባ ምንጫችን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ነው።
Показать все...
👍 4
በምርት ዘመኑ የበልግ አዝመራ 82 ሺህ 441 ሔክታር መሬት በዘር መሸፈኑን የቡርጂ ዞን የግብርና መምሪያ አስታወቀ *************** (አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቡርጂ ዞን የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ህርቦ ቤጦ ወቅታዊ የበልግ ተግባራት የሚገኙበትን ሁኔታ አስመልክተው መረጃ ሰጥተዋል። የመምሪያ ኃላፊው በምርት ዘመኑ ወቅቱን የጠበቀ ዝናብ በመገኘቱ የበልግ አዝመራ ሥራው በተያዘለት መርሃ-ግብር ተጀምሮ እየተፈፀመ እንደሚገኝ አመልክተው በአዝርዕት ሰብሎች 82 ሺህ 399.5 እንዲሁም በሆርቲካልቸር ሰብሎች 40.375 ሔክታር በድምሩ 82 ሺህ 441 ሔክታር መሬት በዘር ተሸፍኖ እየለማ ይገኛል ብለዋል። በአዝመራው 38 ሺህ 554 ወንድ እና 1 ሺህ 601 የዞኑ አርሶ አደሮች በንቃት እየተሳተፉ ናቸው ያሉት አቶ ህርቦ ከማሳ ዝግጅት፣ እስከ ተባይ በሽታና አረም ቁጥጥር ተግባራትን በተደራጀ መንገድ ተፈፃሚ እያደረጉ እንደሚገኙ አስረድተዋል። በዞኑ እየለማ ከሚገኘው ሰብል በበልግ 1 ሚሊየን 262 ሺህ 685 ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ እና አማካይ ምርታማነትን ከማሳደግ አኳያም በአዝርዕት 10.8 እንዲሁም በሆርቲካልቸር 80 ኩንታል በሔክታር አማድረስ እየተሠራ ነው ብለዋል። የመምሪያ ኃላፊው በዞኑ ጤፍ፣ በቆሎ፣ ቦሎቄ፣ እንሰትና ሌሎች የሆርቲካልቸር ሰብሎች እየለሙ ሲሆን አርሶ አደሩ በጊዜ የለኝም መንፈስ ከአዝመራው ሳይነጠል እየታተረ እንደሚገኝ መግለፃቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘውን መረጃ ዋቢ አድርጎ ኢ.ፕ.ድ ዘግቦታል።
Показать все...
👍 1
እንሰት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚኖረው ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡ /አዳማ፣ ግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር/ እንሰት የዝናብ እጥረትን በተወሰነ መልኩ በመቋቋም በድርቅ አመታት የብዙ ህብረተሰብና እንስሳትን ህይወት ማትረፍ በመቻሉ “ነፍስ አድን” ሰብል በሚል ቅጽል ስም ጭምር ይታወቃል፡፡ ከጥቂት የእርሻ ማሳ ብዙ ምርት በመስጠቱ እንሰት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አሰተዋፅዖ ያደርጋል፡፡ ከእንሰት የሚጣል የለም፤ ሁለመናው ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ እንሰት በዋነኛነት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣  በኦሮሚያና   በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ይለማል፤ ይመረታል፡፡ ግብርና ሚኒስቴር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደ ሌሎች የሰብል አይነቶች ለእንሰት ልማትም ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ የእንሰት ልማትን ውጤታማ ለማድረግም  ግብርና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን ረቂቅ ሀገራዊ የእንሰት ልማት ፍላግሺፕ ፕሮግራም አዘጋጅቷል፡፡ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ከዘርፉ ተዋንያኖችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በውይይት ሰነዱን ለማዳበር ከአሜርካ የልማት ተራድኦ ድርጅት ጋር በመቀናጀት  የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ በግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) እንሰት ከ25 ሚሊዮን ህዝብ በላይ በምግብነት የሚደግፍና  ለብዙ ስራ ፈላጊዎች የስራ ዕድል የሚፈጥር ከመሆኑም ባሻገር ለገቢ ምንጭነት፣ ለእንዱሰትሪ ጥሬ ዕቃነት፣ ለመኖነት፣ ለመድኃኒትነት፣ ለአፈር ጥበቃ እና ለሌሎች ጠቀሜታ ስለሚውል አስፈላጊነቱን ግምት ውስጥ በማስገባት በትኩረት እየተሰራበት ነው ብለዋል፡፡ ካሜራ፦ ማቲዎስ ተገኝ ዘጋቢ፦ ሸምሱዲን ዩሱፍ
Показать все...
👍 9 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የተሻሻለ መኖ በማልማት የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የባለድርሻ አካላትን አቅም መገንባት ያስፈልጋል (ሐዋሳ፥ 16 ግንቦት 2016፥ ግብርና ሚኒስቴር) ግብርና ሚኒስቴር የመኖ ልማትን ለማሳደግ ግብ ጥሎ በዘርፉ የተሰማሩ የመኖ ባለድርሻ አካላትን አቅም የመገንባት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። የመኖ ባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት በሚደረገው ሂደት በመኖ ልማት ዙሪያ ለተለያዩ ክልሎች የተለያዩ ስልጠናዎች ተደራሽ እያደረገ ነው። በመሆኑም ከሲዳማ፥ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ለተውጣጡ 56 ተሳታፊዎች በተሻሻለ የመኖ ዕጽዋት የዘር ብዜት ላይ ስልጠና ተሰጥቷል። ይህ በተግባር የተደገፈው ስልጠና የመኖ ዕጽዋት ልማት አዘራር፥ አተካከልና የአረንጓዴ መኖ (hydroponic) ልማት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። እነዚህ ከየክልሉ የተውጣጡ ሰልጣኞች ከ20ሺ በላይ አርሶአደሮችን በመኖ ልማት ላይ በጓሯቸው በተግባር ያሰለጥናሉ። ይህም ከአርሶአደሩ ዘንድ ያልደረሱ የተሻሻሉ የመኖ ዝርያዎችን ተደራሽ ለማድረግ ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ስለዚህ የተሻሻለ መኖ በማልማት የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የቤት ሥራ ነው። የካሜራ ባለሙያ፥- ያሬድ አሰፋ ዘጋቢ፥- ባህሩ ሰጠኝ
Показать все...
👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
2016/17 ምርት ዘመን የበልግ እርሻ ወቅታዊ መረጃ
Показать все...
👍 8
የጤፍ ሰብል ካለው አገራዊ ፋይዳ አንጻር ምርታማነቱን ማሳደግ ይገባል! /አዳማ፣ ግንቦት 16፣ 2016 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር/ ኢትዮጵያ በእርሻው ዘርፍ ለሰብል ልማት በተለይም ለጤፍ ሰብል ምቹ ስነ-ምህዳር፣ ሰፊ አቅምና የጤፍ ሰብል የማምረት ባህልና ልምዱም ያላት አገር ነች፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝቧም የጤፍ ምርት ተመጋቢ ነው፡፡ ይህን ትልቅ አገራዊ ፋይዳ ያለውን ሰብል ምርታማነቱን ለማሳደግ ከግብዓት ጀምሮ እስከ አመራረት ሂደት ባለው ሰንሰለት በርካታ የምርምር ስራዎች በየጊዜው እየተሰሩበትና ውጤትም እየተመዘገበ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ጤፍ ካለው ፋይዳ እና አገሪቱ ካላት አቅም አንጻር ምርታማነቱ በሚፈለገው ልክ አድጓል ማለት አይቻልም፡፡ በመሆኑም የጤፍ ምርት ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝና ምርታማነቱን በአገር አቀፍ ደረጃ ለማሳደግ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል የጤፍ ዘር ምርምር ውጤቶችን መልቀቅና በየደረጃው ላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ሙሉ ዜናውን ለማንበብ ሊንኩን ይንጫኑ፦ http://www.moa.gov.et/.../36-news/256-2024-05-24-07-12-37 ካሜራ ዮዲት እንዳለው ዘጋቢ ተዋበ ጫኔ
Показать все...
የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ግብርና ተሞክሮ ላይ ከጋና የመጡ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ልምድ ቀሰሙ፡፡ (አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር) የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መለሰ መኮንን (ዶ/ር) በፅ/ቤታቸው ልዑካን ቡድኑን ተቀብለዋቸዋል፡፡ የኢትዮጵያን የአየር ንብረት ለውጥ የሚቋቋም ግብርና ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው፤ አረንጓዴ አሻራ፣ የመስኖ ስንዴ ልማትን እና የሌማት ትሩፋት ፕሮግራምን በአብነት ጠቅሰዋል፡፡ የአየር ንብረትን የሚቋቋም ግብርናን ለማስፋፋት የተለያዩ ፖሊሲዎችን፣ ዕቅዶችን እና ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ የአየር ንብረትን የሚቋቋም ግብርና ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ ሚ/ር መ/ቤቱ ከኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ ቆላማ አካባቢዎች ላይ በስፋት የመስኖ ስንዴን በማልማት የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሆነ የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው በልማቱ ለረጅም ጊዜ ከውጭ የሚገባውን የስንዴ ምርት ማስቀረት እንደተቻለም አስገንዝበዋል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ፖሊሲ፣ የአየር ንብረት ለውጥ የሚቋቋም ግብርና አተገባበር፣ በሃገሪቱ ያሉ መልካም ዕድሎች፣ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ጋር በተያያዘ ሰነዶች ለልዑካን ቡድኑ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ የልዑካን ቡድኑ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ የሚቋቋም የግብርና ልማት እየተገበረች ያለውን ስራ አድንቀዋል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ የሚቋቋም ግብርና አተገባበር ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችን የልዑካን ቡድኑ ያነሱ ሲሆን መለሰ መኮንን (ዶ/ር) ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የካሜራ ባለሙያ፡- ማቲዎስ ተገኝ ዘጋቢ፡- ዮሐንስ ደመቀ
Показать все...
🕊 8
የመኖ ልማቱ በእውቀት እንዲመራ የባለድርሻ አካላትን አቅም መገንባት ይገባል፡፡ (ሀዋሳ፣ግንቦት 15 ቀን 2016፣ ግብርና ሚኒስቴር) ለሰው ልጅ የተመጣጠነ ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለእንስሳትም የተመጣጠነ መኖ ያስፈልጋል። በሌላ በኩል የሰው ልጅ የተመጣጠነ ምግብ ይመገብ ዘንድ የእንስሳት ተዋጽኦዎችን ማካተት ይኖርበታል። ለዚህ ደግሞ የገጠርም ሆነ የከተማ ነዎሪዎች የተሻሻለ መኖን በማልማት የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የበኩሉን አስተዋጽዎ ሊያበረክት ይገባል። በተሻሻለ የመኖ ዕጽዋት የዘር ብዜት ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ከሲዳማ፥ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ለተውጣጡ 56 ተሳታፊዎች እየተሰጠ ይገኛል። በስልጠናው ላይ የተገኙት የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ዮሐንስ ግርማ (ዶ/ር) የእንስሳትን ዘርፍ ለማሳደግ የአቅም ግንባታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። ሙሉ ዜናውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፥ http://www.moa.gov.et/.../36-news/255-2024-05-23-12-40-12FB የካሜራ ባለሙያ፥- ያሬድ አሰፋ ዘጋቢ፥- ባህሩ ሰጠኝ
Показать все...
🕊 3
የተሻሻለ የንግድ ስራ ክህሎት ስልጠና የእንስሳት መኖ እሴት ሰንሰለት ሚናን ለማሳደግ ያግዛል፡፡ (አዳማ፣ ግንቦት15 ቀን፣ 2016 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር) በግብርና ሚኒስቴር እና በላንድ ኦሌክስ ቬንቸር 37 ፕሮጀክት የጋራ ትብብር ከተለያዩ ክልሎች፡ ከእንስሳት መኖ የግል አምራቾች፣ ከግብዓት አቅራቢዎች፣ ከእንስሳት መኖ ነጋዴዎችና ከወተት ማህበራት ለተውጣጡ ባለሙያዎች ለዘላቂ እንስሳት መኖ ልማት የሚያግዝ የክህሎት ስልጠና ተሰጠ፡፡ ስልጠናው የተሳታፊዎችን የንግድ ስራ ክህሎትን ለማሳደግ እና የእንስሳት መኖ እሴት ሰንሰለት ላይ ያላቸውን ሚና በመጨመር ትርፋማና ዘላቂ የሆነ የእንስሳት መኖ ንግድ ስራ እንዲኖራቸው የሚያስችል ነው፡፡ በተጨማሪም ስልጠናው ሴቶችና ወጣቶች በእንስሳት መኖ እሴት ሰንሰለት ውስጥ የሚኖራቸውን ተሳትፎ ለማሳደግና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማገዙም ባሻገር የተሻለ የግብዓት ትስስር እንዲፈጥሩ ያደርጋል፡፡ የካሜራ ባለሙያ፡- ጌታቸው ምትኩ ዘጋቢ፡- ራቤያ ፈንታው
Показать все...
🕊 2