cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

FDRE TVT Institute

ይህ የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው። This is FDRE TVT Institute official Telegram cannel

Больше
Рекламные посты
1 073
Подписчики
+524 часа
+427 дней
+13630 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የኢንስቲትዩቱ ሐዋሳ ካምፓስ ክልል አቀፍ የክህሎት ውድድርን እያስተናገደ ይገኛል፡፡ ***ሰኔ 23/2016 ዓ.ም*** በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አዘጋጅነት ከሰኔ 20-24/2016 ዓ.ም እየተካሄደ በሚገኘው ዓመታዊ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ፣ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር እንዲሁም ስራ ፈጠራ ውድድር እና ኤግዚቢሽን በሰልጣኝ እና አሰልጣኝ ምድብ በብየዳ፣ መካኒክስ እና የእንጨት ስራ (Welding, Mechanics እና Furniture making) ሙያዎች የክህሎት ውድድር በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የሀዋሳ ካምፓስ ወርክ ሾፖች እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዳኝነት የካምፓሱ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን በቀጣይም ትብብሩን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡ የካምፓሱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዌብሳይት http://www.ftveti.edu.et/ ፌስቡክ https://www.facebook.com/TVTI.EDU.ET ቴሌግራም https://t.me/fdretvtinstitute ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.me/tvtinstitutehawassa
Показать все...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

የኢንስቲትዩቱ የሥራአመራርና አስተዳደር ፋካሊቲ የመጀመሪያው ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ሴሚናር በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ልህቀት ለማምጣት የአመራርና አስተዳር ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ተካሔደ፡፡ *****************ሰኔ 21/2016************* የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የሥራአመራርና አስተዳደር ፋካሊቲ ከጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ጋር በትብብር ያዘጋጁት የመጀመሪያው ዓመታዊ የጥናትና ምርምር Striving for Excellence; Leadership and Management in TVET በሚል መሪ መልዕክት አምስት ጥናትና ምርምሮች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ብሩክ_ከድር ሴሚናሩን በንግግር ሲከፍቱ ኢንስቲትዩቱ ቴክኒክና ሙያ አመራሮችን የማፍራት ተልዕኮ የተሰጠው በመሆኑ እንደዚህ አይነት በዘርፉ ላይ ያሉ ምሁራንን፣ ተመራማሪዎችን፣ ተማሪዎችን፣ ባለድርሻዎችን አሰባስቦ በጉዳዮ ላይ መምከር ዘርፉን የበለጠ ለማሳደግ አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡ በአገራችን ከ2ሺ በላይ የስልጠና ተቋማት መኖራቸውን ያነሱት ዶ/ር ብሩክ በየተቋማት በየዓመቱ በሚሊየኖች የሚቀጠሩ ዜጎችን በብቃት ያወጣሉ፡፡ መንግስትም እነዚህን ተቋማት ለማብቃት ትልቅ ተነሳሽነት ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህ ኮንፍረንስ መካሔዱ ለኢንስቲትዩቱ ብቻ ሳይሆን ለእነዚህ በመላ አገሪቱ ለሚገኙ ተቋማት ልህቀት የሚኖረው ሚና ጉልህ ነው ብለዋል፡፡ የእለቱ የቁልፍ መልዕክት አቅራቢ ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የሥራአመራር እና መልካም አስተዳደር ትምህርት ክፍል የመጡት ዶ/ር #ብርሀኑ_በላይነህ ሲሆኑ ለተቋማት ልህቀት የአመራር ሚና ላይ ተመስርተው ንግግር አድርገዋል፡፡ ተቋማዊ ልህቀት ቴክኖሎጂ፣ መሰረተ ልማት፣ በግለሰቦች ዘንድ ያለ አንድ አይነትና የተቀራረበ አመለካከት አስተሳስሮ መያዝን ይመለከታል ብለዋል፡፡ ተቋማዊ ልህቀት ሲባል የአመራሩ ቁርጠኝት የማይተካ እና ለድርድር የማይቀርብ መስፈርት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ ውሳኔ ሰጪነት፣ ግብ የመቅረጽ ብቃት፣ ለውጥን የማይፈራ/የማትፈራ መሆን፣ የተግባቦት ችሎታ ከብዙ በጥቂቱ ከአመራር የሚጠበቁ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ በዕለቱ የቀረቡ ጥናት ጽሁፎችም Reconfiguring Technical and Vocational Education Training: Leveraging Multi-Stakeholder Partnership in Ethiopia by #Samson _Melesse (PhD), Leadership Practices: Emphasizing on Additive Effects of Transformational and Transactional Leadership Styles in Selected Polytechnic Colleges of Addis Ababa by #Adane_Abeje (PhD), Challenges influencing the acquisition of practical skills by trainees in TVET College at Basketo Special Woreda in S.N.N.P.R State, Ethiopia by Mr. #Nassir_Kanso, Can Professional Development Intended for Teacher Educators Influence Roles of Academics in Leadership? Lesson from Ethiopian Public Universities by #Tewodros_Asmare (Asis. Prof.), Leaders Role in Managing Training Resources: The Case of Tegbare Id Polytechnic College Insights from KfW Project By #Bekretsion_H/Silassie (PhD) ናቸው፡፡ ዌብሳይት http://www.ftveti.edu.et/ ፌስቡክ https://www.facebook.com/TVTI.EDU.ET ቴሌግራም https://t.me/fdretvtinstitute
Показать все...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
👍 1
Перейти в архив постов
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.