ru
Feedback
ESS Study Tips

ESS Study Tips

Открыть в Telegram

Daily study tips, exam strategies & note-taking methods that actually work. 🎯 For students who want higher scores with less stress. 📞Contact us:@ess_cbot 📙የእኛን መፅሐፍ(PDF) ለማግኘት:https://t.me/ess_study_tipsbot

Больше
3 202
Подписчики
-724 часа
-257 дней
-8030 дней
Архив постов
😇የ 5 ደቂቃ ዕረፍት

1⃣የመጀመሪያ ዙሪ1⃣ 👍START

ዛሬ እንደተለመደው የጥናት ቻሌንጃችን ሰዓቱን ጠብቆ 3:00 ላይ ይጀምራል። የምትፈተኑ ልጆች ነገ የምትፈተኑትን በሚገባ መከለስ እንዳትረሱ። 🙏 መልካም ጥናት ይሁንላቹ 🙏

☀️ መልካም የፈተና ጠዋት! ☀️ የዛሬው ፈተና እውቀትህን የምታሳይበት እንጂ የምትጨነቅበት መድረክ አይደለም። የደከምክበት ጥናት ፈጽሞ ከንቱ አይሆንም። 💡 ጥቂት ማስታወሻዎች፦ 1. ፈጣሪን አትርሳ፦ በፀሎት ጀምር። 🙏 2. ረጋ በል፦ ጭንቀት መልስ ያጠፋል፣ መረጋጋት ግን ትውስታን ያድሳል። 🧠 3. ሰዓትህን ተጠቀም፦ በአንድ ጥያቄ ላይ ብዙ አትቆይ። ⏱️ አንተ ለዚህ ቀን ብቁ ነህ! ትልቅ ውጤት እንደምታመጣ አንጠራጠርም። 🌟 መልካም እድል! 🍀

🎉 እንኳን ደስ አላችሁ! የ2 ሰዓቱ የጥናት ቻሌንጅ ተጠናቋል! ✅ለዛሬው የ2 ሰዓት የPomodoro የጥናት ቻሌንጅ ራሳችሁን ሰጥታችሁ፣ በትጋት ለተሳተፋችሁ ሁሉ ትልቅ ምስጋና እና አክብሮት ይገባችኋል። ዛሬ ያሳያችሁት ጽናት ለነገው ትልቅ ስኬታችሁ አንድ እርምጃ ወደፊት አስጠግቷችኋል። አስታውሱ፣ ስኬት ማለት በየቀኑ የምናደርጋቸው ትናንሽና ተከታታይነት ያላቸው ጥረቶች ድምር ውጤት ነው። የPomodoro ዘዴን በመጠቀም ትኩረታችሁን ሰብስባችሁ በማንበባችሁ ውጤታማ እንደነበራችሁ ተስፋ እናደርጋለን። ጥቂት ማሳሰቢያ፦ • አሁን አእምሮአችሁ እረፍት ያስፈልገዋል። • ከስክሪን ራቅ ብላችሁ ለዓይናችሁና ለአእምሮአችሁ እረፍት ስጡ። • በዛሬው ማንነታችሁ ኩራት ይሰማችሁ! ነገ ደግሞ በበለጠ ተነሳሽነትና በታደሰ ጉልበት እንገናኛለን። የዛሬው ጥረታችሁ ነገ በውጤት ይከፈላል! 🌙 መልካም የዕረፍት ምሽት ይሁንላችሁ! #ESS_Study_Tips #Pomodoro_Challenge #Consistency #Success #GoodNight

😇የ 5 ደቂቃ ዕረፍት

4⃣አራተኛ ዙሪ4⃣ 👍START

😇የ 5 ደቂቃ ዕረፍት

3⃣ሶስተኛ ዙሪ3⃣ 👍START

😇የ 5 ደቂቃ ዕረፍት

2⃣ሁለተኛ ዙሪ2⃣ 👍START

😇የ 5 ደቂቃ ዕረፍት

1⃣የመጀመሪያ ዙሪ1⃣ 👍START

ዛሬ እንደተለመደው የጥናት ቻሌንጃችን ሰዓቱን ጠብቆ 3:00 ላይ ይጀምራል። የምትፈተኑ ልጆች ነገ የምትፈተኑትን በሚገባ መከለስ እንዳትረሱ። 🙏 መልካም ጥናት ይሁንላቹ 🙏

ዛሬ ፈተና ወስዳችሁ ነገ ሌላ ፈተና ላለባችሁ ተማሪዎች ጠቃሚ ምክሮች! 📝✨ አንዱን ተወጥታችኋል! አሁን ትኩረታችሁን ነገ ላይ ለማድረግ እነዚህን ነጥቦች ተከተሉ፦ 1. የዛሬውን ፈተና እዚያው ይተውት! 🚫 ከፈተና ወጥታችሁ መልስ ለማመሳከር አትሞክሩ። ትክክልም ይሁን ስህተት አሁን ምንም ሊቀየር አይችልም። መልስ መፈለግ ጭንቀትን ስለሚጨምር ለነገው ፈተና ትኩረት እንዳይኖራችሁ ያደርጋል። 2. አጭር የጭንቅላት እረፍት (Break) ይውሰዱ 🧘‍♂️ ከፈተና እንደወጣችሁ ወዲያውኑ ወደ ቀጣዩ ጥናት አትግቡ። ለ30-60 ደቂቃ ያህል አእምሮአችሁ እንዲያርፍ አድርጉ። የሚወዱትን ምግብ ይብሉ ወይም ንጹህ አየር ይተንፍሱ። 3. ለነገው ፈተና ዋና ዋና ነጥቦችን ብቻ ይከልሱ 📚 ጊዜው አጭር ስለሆነ ሁሉንም መጽሐፍ ለማንበብ አይሞክሩ። ይልቁንም፦ • በክፍል ውስጥ የተሰጡ ማስታወሻዎችን (Short notes) ይመልከቱ። • ዋና ዋና ቀመሮችን እና ርዕሶችን ይከልሱ። • ከዚህ በፊት የሰሯቸውን ጥያቄዎች በድጋሚ ይዩ። 4. ውሃ በደንብ ይጠጡ እና ጤናማ ምግብ ይብሉ 💧🍎 አእምሮአችሁ በደንብ እንዲሰራ ጉልበት ያስፈልገዋል። ከልክ በላይ ጣፋጭ ወይም ከባድ ምግብ ከመመገብ ይቆጠቡ። 5. ቀደም ብለው ይተኙ! 😴 ለነገው ፈተና ትልቁ ዝግጅት እንቅልፍ ነው። አእምሮአችሁ ያጠናችሁትን ነገር እንዲያቀናጅ እና ነገ በፈተና ሰዓት ንቁ እንዲሆን ቢያንስ ከ 6-7 ሰዓት መተኛት አለባችሁ። 6. ቁሳቁሶችን ቀድመው ያዘጋጁ 🖊️ ለነገ የሚያስፈልጉዎትን እስክሪፕቶ፣ እርሳስ፣ መታወቂያ እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ዛሬውኑ ቦርሳችሁ ውስጥ በማስገባት ጠዋት የሚፈጠር መደናገጥን ያስቀሩ። በርቱ! የዛሬው ጥንካሬያችሁ ለነገው ስኬት መሰረት ነው! 💪🌟

ዛሬ ፈተና የጀመራቹ አላቹ?
Anonymous voting

photo content

📝 የፈተና ቀን ስኬት መመሪያ ዛሬ የለፋህበትን ፍሬ የምታይበት ቀን ነው! በፈተና ሰዓት ውጤታማ እንድትሆን እነዚህን ነጥቦች ተግብር፦ 1. ጠዋት ስትነሳ (Preparation)በጊዜ ተነሳ፦ አጣድፎህ ጭንቀት ውስጥ እንዳይከትህ ቀድመህ ተነሳ። • ቀለል ያለ ቁርስ ተመገብ፦ አእምሮህ በቂ ጉልበት እንዲኖረው ቁርስ መብላትህን አትርሳ። • ቁሳቁሶችህን አረጋግጥ፦ መታወቂያ፣ እስክሪብቶ፣ እርሳስ እና ሌሎች የሚያስፈልጉህን ነገሮች መያዝህን ደግመህ አረጋግጥ። 2. የፈተና ወረቀቱ ሲሰጥህ (At the Start)መመሪያውን በጥንቃቄ አንብብ፦ ብዙ ተማሪዎች የሚሳሳቱት መመሪያ ባለማንበብ ነው። ስንት ጥያቄ መስራት እንዳለብህና ለእያንዳንዱ ጥያቄ የተሰጠውን ነጥብ እወቅ። • ሁሉንም ጥያቄዎች በረባቡ እያቸው፦ የትኞቹ ጥያቄዎች ቀላል እንደሆኑና የትኞቹ ጊዜ እንደሚወስዱ ለመለየት ይረዳሃል። 3. በፈተና ሰዓት (During the Exam)ከቀላሉ ጀምር፦ የምታውቃቸውን ጥያቄዎች ቀድመህ በመስራት በራስ መተማመንህን ጨምር። • ጊዜህን ተቆጣጠር፦ በአንድ አስቸጋሪ ጥያቄ ላይ ብዙ ጊዜ አታጥፋ። ካልመጣልህ አልፈኸው ወደ ቀጣዩ ሂድ፤ መጨረሻ ላይ ትመለስበታለህ። • ጥያቄውን በአግባቡ ተረዳ፦ "አይደለም" (Not)፣ "ከ... በስተቀር" (Except) የሚሉ ቃላትን በትኩረት ተመልከት። 4. ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት (Mindset)ጥልቅ ትንፋሽ ውሰድ፦ ድንገት ከጨነቀህ ወይም የጠየቀው ጥያቄ ግራ ካጋባህ ለጥቂት ሰከንዶች አይንህን ጨፍነህ በጥልቀት ተንፍስ። • በራስህ ተማመን፦ "የቻልኩትን ያህል አጥንቻለሁ፣ ውጤታማ እሆናለሁ" ብለህ ለራስህ ንገረው። 5. ከመጨረስህ በፊት (Final Check)መልስህን ከለስ፦ ጊዜ ካለህ የሰራሃቸውን ጥያቄዎች በድጋሚ እያቸው። ያልመለስካቸው ጥያቄዎች አለመኖራቸውን አረጋግጥ። • ስምህንና መለያ ቁጥርህን አረጋግጥ፦ በወረቀቱ ላይ አስፈላጊ መረጃዎችን መጻፍህን አትዘንጋ። 🌟 መልእክት፦ ፈተና የእውቀትህ መመዘኛ እንጂ የማንነትህ መለኪያ አይደለም። ተረጋግተህ ከሰራህ ውጤቱ ያምራል። መልካም ፈተና ይሁንላችሁ! 🍀📚

🚀 ዛሬ ያንተ ቀን ነው! 🚀 ለረጅም ጊዜ ስትለፋ፣ ስታጠና እና ስትዘጋጅ የነበረው ለዛሬው ቀን ነው። በራስህ ተማመን! የሰራኸው ስራ በሙሉ ውጤት የሚሰጥበት ሰዓት ደርሷል። ✅ አትርሳ፦ • በራስህ
🚀 ዛሬ ያንተ ቀን ነው! 🚀 ለረጅም ጊዜ ስትለፋ፣ ስታጠና እና ስትዘጋጅ የነበረው ለዛሬው ቀን ነው። በራስህ ተማመን! የሰራኸው ስራ በሙሉ ውጤት የሚሰጥበት ሰዓት ደርሷል። ✅ አትርሳ፦ • በራስህ መተማመን ግማሽ ድል ነው! 😎 • በጥልቀት ተንፍስና ረጋ በል 🧘‍♂️ • እያንዳንዱን ጥያቄ በጥንቃቄ አንብብ 📝 አንተ አሸናፊ ነህ! መልካም ፈተና ይሁንልህ! 💪✨

photo content