ኢት-መጽሐፍት | ETHIO-BOOKS
Открыть в Telegram
👉 "የምታነበው መጽሐፍ ለአንተ የሚያስብልህ ሳይሆን አንተ እንድታስብ የሚያደርግ ነው።" ሃርፐር ሊ Fiction (ልቦለድ), History (ታሪክ), Politics (ፖለቲካ), Psychology (ስነልቦና), Biography (ግለ-ታሪክ), Self-help(ራስ አገዝ),& Philosophy(ፍልስፍና) የሀገር ውስጥ & የውጪ ሀገር መጽሐፎችን ያገኛሉ!አስተያየትዎን እዚህ @Desutech_bot ያድርሱን
Больше1 990
Подписчики
-124 часа
-47 дней
-5230 день
Архив постов
ሥነ-ግጥም
በዮሀንስ ፍሠሀ
ርዕስ=ናፋቂ ዜማዎች
ደራሲ=ዮሐንስ ፍስሀ
Join_us;
👉 @et_books1
👉 @et_books1
📚CHANGE YOUR THINKING, CHANGE YOUR LIFE: How to Unlock Your Full Potential for Success and Achievement
Join_us;
👉 @et_books1
👉 @et_books1
📚ርዕስ:- የብልህነት መንገድ
📝ደራሲ:- ግሬሽያን ባልታሳር
👤ተርጓሚ:- ኤፍሬም ጀማል
📜ዘውግ:- ሳይኮ
📆ዓ.ም:- 2013
📖የገፅ ብዛት:- 180
📚Digital Marketing Handbook: A Guide to Search Engine Optimization, Pay Per Click Marketing, Email Marketing, Social Media Marketing and Content Marketing
✍By Shivani Karwal 📖
⬇⬇⬇⬇
ሰውየው እስራኤላዊ ነው:: የታሪክ ተመራማሪ ነው:: ፕሮፌሰር ነው:: እዛው እስራኤል አገር University of Jerusalem ውስጥ የታሪክ መምህርም ነው:: One of the Brightest Mind on Planet Earth ይሉታል ምዕራባዊያኖች:: ሦስት ተፅዕኖ ፈጣሪ የሚባሉ ሳይንሳዊ መፅሐፎችን ፅፏል::
ፕሮፌሰር Yuval Noah Harari
የዚህ ፕሮፌሰር የመጀመርያው Non-Fiction መፅሐፍ 'Sapiens: A Brief History of Humankind' ይባላል:: ፕሮፌሰሩ በዚህ መፅሐፉ የሰውን ልጅ [ዘረ-ሰብ] በታሪክ ውስጥ ያለፈበትን ረዥም ጉዞ ያስቃኘናል:: የሰው ልጅ ካልሰለጠነበት ዘመን የእንጨት ጦር ከመወርወር እስከ ተመዘግዛጊ ኒውክለር ሚሳኤሎች እስከማስወንጨፍ የሄደበትን ጉዞ ያትታል:: የሰው ልጅ ከጥንታዊ አደንና ቃርሚያ ህይወት እስከ ዘመናችን የካፒታል ስርዓት ያደረገውን ጉዞ ይዳስሳል::
ሁለተኛው Non-Fiction መፅሐፉ "Homo Deus: A Brief History of Tomorrow" ይባላል:: ፕሮፌሰሩ በዚህኛው መፅሐፉ ደግሞ የሚነግረን ስለ ሰው ልጅ የወደፊት ታሪክ ነው:: ዘመናዊው እና ዲጂታሉ ዓለም ሰብአዊነትን እንዴት እንደሚለውጥ ይተነብያል:: አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የሰውን ልጅ የበላይነት ቀምቶ አለምን በቁጥጥሩ ስር እንደሚያውል ፣ እንደ ባዮ-ቴክኖሎጂ እና ጄኔቲክ ኤንጂነሪንግ ያሉ የቴክኖሎጂ ዕድገቶች ሊያስከትሉ ስለሚችሉት ውጤቶችም ይጠነቁላል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም በ2050ዓ.ም ሰዎች ሞትን ያሸንፋሉ:: ገንዘብ ያለው ማንኛውም ሰው ወደ ሆስፒታል እየሄደ ዕድሜውን ቻርጅ እያስደረገ እስኪሰለቸው ዘላለማዊ ሆኖ መኖር ይችላል:: ኢ-መዋዕቲ ነፍስ ይኖራቸዋል ይላል:: [ Humans are Essentially Algorithm, and the focus shifts from individual experiences and subjective values to objective data and accumulation of knowledge ]
ሦስተኛው መፅለፉ ደግሞ "21 Lessons For the 21st Century" የሚል ነው:: በዚህ መፅሐፉ ደግሞ ፕሮፌሰሩ የሚነግረን የአሁኑ ዘመን ሰው ስለተደቀነበት ተግዳሮቶች እና መከራ ነው:: በዲጂታል ቴክኖሎጂ ፕላትፎርሞች Facebook, Twitter, Instagram, Tik Tok, Youtube ወዘተ የውሸት ዜናዎችና የተሳሳቱ መረጃዎች ይስፋፋሉ ሃገሮች እርስ በእርስ የሳይበር ጥቃት ይከፋፈታሉ:: [ በነገራችን ላይ ከዚህ በኋላ በጦር መሳርያ የሚካሄድ ጦርነት እንዳትጠብቁ ሁሉም ጦርነቶች ሁሉ የሚደረጉት በዲጂታል ነው):: ሌላው የተራቀቁ ማሽኖችና ሶፍትዌሮች እና የኮምፒውተር አልጎሪዝሞቾ በቅርቡ የሰዎን ልጅ አብዛኛውን ዘርፍ ይቆጣጠራሉ:: የቨርችዋል አለም ግዙፋን ካምፓኒዎች - የአንተን ማንነት ለሚፈልጉ ካምፓኒዎች መረጃህን ይሸጡታል:: በአጭሩ እኛ የሰው ልጆች በቀደመው 20ኛው ክፍለ ዘመን የፈጠርነውን የአኗኗር ፣ የአሰራር እና የመንግስት አስተዳደር ስርዓት ይዘን የገባንበትን 21ኛው ክፍለ ዘመንን መሻገር እንደማንችል አስረግጦ ይነግረናል::
ታዲያ ይሄ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር እና የአለማችን ባለብሩህ አዕምሮ የተባለው ሰው ከሰሞኑን The Late Show with Stephen Colbert እና Jimmy Kimmel Live ሾዎችን ጨምሮ በተለያዩ የሚዲያ መድረኮች ላይ እየቀረበ እንደ መጥመቁ ዮሐንስ ብቻውን ከፊታችን ስለሚመጣው ክስተት እየጮኸ እየለፈፈ ነው::
ለምን? ምንስ ብሎ?
We are very near the end of our species because AI is a weapon of mass destruction to Humanity...የሰው ልጅ በታሪክ ሂደት ውስጥ ብዙ አጋዥ ቁሶችን ፣ መገልገያ ማሽኖችን በእጁ ሰርቷል ነገር ግን እነዚህ በሰው ልጅ የተሰሩ ነገሮችን ከድንጋይ ቢላ እስከ አቶሚክ ቦንብ ድረስ ብንመለከት በእኛ ቁጥጥር ስር ያሉ ናቸው እንዴት እና በምን አይነት ሁኔታ መጠቀም እንዳለብን የምንወስነው እኛ ሰዎች ብቻ ነን:: እንጂ እነዚህ ነገሮች በፍፁም በራሳቸው ውሳኔ ማሳለፍ አይችሉም ፣ አዲስ ሐሳብም መፍጠር አይችሉም::
ለምሳሌ የሰው ልጅ አቶሚክ ቦምብን ሰራ ነገር ግን ቦምቡ በራሱ ልፈንዳ ብሎ አይወስንም እኛ የት? እና መቼ? የሚለውን ነገር ካልወሰንን በስተቀር:: በተጨማሪም የሰው ልጅ ፕሪንተር ሜሽን ሰርቷል ነገር ግን ይሄ ፕሪንተር ሜሽን ፕሪንት የሚያደርገው እኛ የሰጠነውን ፅሁፍ ነው:: የእኛን ሃሳብ ነው እንጂ በራሱ አንድ ነጠላ ፊደል እንኳ ፅፎ ማተም አይችልም እኛ ካላዘዝነው::
በአጠቃላይ የሰው ልጅ ከዚህ በፊት የሰራቸው ቁሶች እና ሜሽኖች በእኛ ውሳኔ የሚመሩ እና የእኛን ሃሳብ የሚያስተጋቡ ነበሩ:: አሁን ግን ይሄ ሁሉ ነገር በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ በአደገኛ ሁኔታ ተለውጧል:: ምክንያቱም በራሳቸው ውሳኔ ማሳለፍ የሚችሉ ፣ አዲስ ሃሳብ የሚፈጥሩ እና ከሁኔታዎች ጋር ራሳቸውን በፍጥነት የሚያላምዱ እንደ ሰው ማሰብ የሚችሉ ንቃተ-ህሊና ያላቸው Artificial General Intelligence (AGI) ስለተፈጠረ:: ብሏል:: ይሄም ከፍተኛ እንደሰው የማሰብ ፣ የመረዳት አቅም ያለው ሰው ሰራሽ አስተውሎት በጣም እጅግ በጣም በቅርብ ጊዜ ውስጥ Exist ማድረጉ አይቀርም:: በጣም አስጊ ነው:: ብሎም አክሏል::
Of Course
ዋና መቀመጫውን San Francisco, California, USA ያደረገውና December 2015 የተቋቋመው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር ተቋም ወይም 'OpenAI' በበኩሉ የመጨረሻ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር ግብ የሆነውን ከፍተኛ ሰው ሰራሽ የማሰብ አቅም ያለውን ሮቦት ወይም AGI Achieved አድርጊያለው ብሏል:: የዚህ ተቋም ዋና ስራ አስፈፃሚ Sam Altman ስዊዘርላንድ በተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ባዘጋጀው ወይይት ላይ ተገኝቶ
"ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ ያለው ሮቦት ወይም AGI በጣም ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ በአስደናቂ ሁኔታ አለምን ይቀይረዋል" ብሏል:: እነዚህ AGI በተቆጡ ጊዜ የሰው ልጅ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያደርሱና የሰው ልጅም በቀላሉ ታግሎ እንዲጥላቸው ከቀላል ማቴሪያል የተሰሩ ናቸውም:: ብለዋል የግብር አጋራቸው እነ ኤለን መስክ በበኩላቸው::
እውነት ግን እንደ ፕሮፌሰር ዮቫል ኖህ ሃራሪ ስጋት የሰው ልጅ በተፈጥሮ እና በሌሎች ፍጥረት ላይ የተሰጠውን የመሰልጠን እና የበላይነት ስልጣን በእነዚህ ሰው ሰራሽ አስተውህሎቶች ይነጠቅ ይሆን??
እኔ እንጃ እስኪ አብረን የምናየው ይሆናል በመጨረሻም በ1999 ለዕይታ በበቃው ሳይንሳዊ ልቦለድ ዘውግ ባለው 'The Matrix' ከተሰኘው ፊልም ላይ በተዘገነ ቃለ-ተውኔት (Dialogue) ልሰናበት::
"We marveled at our own magnificence as we gave birth to AI.....Singular consciousness that spawned an entire machine"
ከእንግዲህ 'I'm Not A Robot' ብለን የምንሞላው የCaptcha ቦክስም አይኖርም ማለት ነው:: Let's Strive For Peace on Earth 🙏
Youakin
"ጃኩሊን" የተሰኘው የአጋታ ክርስቲ መጽሐፍ ስትጀምሩት ውስብስብ ያለ ታሪክ ነው። ግን ገለጥ እያረጋችሁ ወደ መሀል ስትጓዙ ስሜት እየሰጣችሁ ይመጣል።
እኔ ከዚህ መጽሐፍ የተረዳሁት «ቅርባችን ያለን ሰው ማወቅ እስከማንችል ድረስ ደካሞች መሆናችንን ነው»። በዚህ ምክንያት ብዙዎቻችን ልባችን ይሰበራል። ማንነታችን ይበላሻል። ክብራችን ይወርዳል። የመኖርን ትርጉም እስክናጣም ድረስ እንደክማለን። ፀፀታችንም ገደብ እስከማይኖረው ድረስ እንዝላለን።
ስለዚህ "ሰዎችን ወደ ህይወታችሁ ስታቀርቡና ስታስጠጉ በማስተዋል ይሁን፤የዋህነታቹም ላለመጎዳትና ላለመታመም የሆነ ገደብ ይኑረው!"
«ሁለት ነገር አስታውሱ፦ ለብቻችሁ ስትሆኑ የምታስቡትን ነገር ተጠንቀቁ፤ ከሰው ጋር ስትሆኑ ደግሞ የምትናገሩትን ነገር ተጠንቀቁ።»
(Quote From "The Wise You")
📚"Trump: How to Get Rich"
✍️Author: Donald J.Trump
#business
Summary:
This book outlines Donald Trump's business philosophy, emphasizing strategic thinking, negotiation skills, and seizing opportunities. He advises on leveraging branding, deal-making, and building a personal brand. Trump emphasizes perseverance, risk-taking, and learning from failures as key components of success. He advocates for self-promotion and creating a persona of success. The book emphasizes the importance of networking, hiring the right people, and maintaining a positive attitude. Overall, it offers insights into Trump's approach to wealth accumulation and entrepreneurial success.
Pages: 259
📖This novel tells the story of Aminata Diallo, who captured by slave traders in Africa and brought to America. 📖
Join_us;
👉 @et_books1
👉 @et_books1
ቋንቋ 🗣
****
ቋንቋ ሰዎች ሐሳባቸውን የሚገልጹበትና እርስ በእርሳቸው የሚግባቡት መሣሪያ ነው፡፡ ቋንቋ መሠረቱ ትርጉም ያለው የድምፅ ቅንብር ሲሆን፣ የቅንብሩ ትርጉም የሚወስነው በማኅበራዊ የእድገት ሂደት ነው፡፡
ድምጾች በምልክቶች ሲወከሉ ቋንቋው የሚጻፍ ወይም ፊደል ያለው ነው እንላለን፡፡ ቋንቋ የተፈጥሮ ግንዛቤ ነጸብራቅ ነው፡፡ በዚህ ግንዛቤ መሠረት ረቂቅ ጽንሰ ሐሳብ የሚቀረጸው፣ ቁሳዊ ህልውና የሚኖረውና ለሌላ ሰው ሊተላለፍ የሚችለው በቋንቋ አማካይነት ነው፡፡
ቋንቋ ለሰው የውስጥ ስሜቱ መግለጫና የዕለት ተዕለት ኑሮው ማከናወኛ መሣሪያ ከመሆኑም በላይ ባሕሉን፣ ታሪኩን፣ ክንዋኔውን፣ የዕውቀቱንና የልምድ ክምችቱን፣ በአጠቃላይ ማንነቱንና ምንነቱን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያስተላልፍበት መሣሪያ ነው፡፡
የተቀነባበረ የሰው ንግግር (Articulated Human Speech) ሊዳብር የቻለው በሥራ ሂደት ነው፡፡ የተቀነባበረ የሰው ንግግር ከመፈጠሩ በፊት ሰዎች በሥራ ሂደት በጫጫታና ጩኸት ሐሳብ ይለዋወጡ ነበር፡፡ ከጊዜ በኋላ ጫጫታና ጩኸቱ በሰውነት አካል ክፍሎች በጉሮሮ ላይ ጭምር ለውጥን ፈጠሩ፡፡ ጉሮሮም ቀስ በቀስ ለተቀነባበረ ንግግር መፈጠር ምቹ ሆነ፡፡
የተቀነባበረው ንግግርም የሐሳብ መለዋወጫ ቋንቋ (መሣሪያ) ሆነ፡፡ ቋንቋ ሰዎችን በሥራ ሂደትም ሆነ ከዚያ ውጭ የሚያገናኝ መሣሪያ ለመሆን በቃ፡፡ የሰው ልጅ በተፈጥሮ ግፊት መሥራትን ሲማር፣ መሥራት ደግሞ በተራው በሰውነቱ ክፍሎች ቅርጽና ተግባር ላይ ለውጥን እያስከተለ መጣ፡፡
የቋንቋ ድምፅ ሲፈጠር የሚሳተፉ የሰውነት ክፍሎች ከንፈር፣ ጥርስ፣ የውስጥ ድድ፣ ምላስ፣ ትናጋ፣ የአፍ በዓት፣ የአፍ ጫፍ በዓት፣ ጉሮሮ፣ ሥረ ድምፅ (ቮካል ኮርድ) እንዲሁም ሳምባ ናቸው፡፡ እነዚህ የሰውነት ክፍሎች መጀመሪያ ሲፈጠሩ ከቋንቋ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡ ማለትም የሰው ልጅ በቋንቋ ለመጠቀም እንዲያስችሉት ተብለው አይደለም የተፈጠሩት፡፡
አፈጣጠራቸው ከምግብ አጠቃቀምና ከሌሎች መሠረታዊ የህልውና (ሰርቫይቫል) ተግባራት ጋር በተያያዘ ሁኔታ ነው፡፡ ቀስ በቀስ ግን የሰው ልጅ በህልውና ትግል በአስገዳጅነት በቋንቋ መጠቀም ሲጀምር እነዚህ የሰውነት ክፍሎች መሠረታዊ የህልውና ተግባራትን እያከናወኑ በተጨማሪ ቋንቋ የመቅረጽ ሥራንም ማከናወን ጀመሩ፡፡
ለምሳሌ ምላስ ከመሠረታዊ ሥራዎቹ አንዱ አፍ ውስጥ የገባን ምግብ በጥርስ ወፍጮ በሚገባ እንዲፈጭ እያገላበጠ ማከፋፈልና ሲደቅ እንዲዋጥ ለጉሮሮ ማቀበል ነው፡፡ በቋንቋ የመጠቀም ተግባር ሲመጣ ደግሞ ወደ ጥርስና ወደ ውስጥ ድድ እየተወነጨፈ፣ ጭብጥ ዘርጋ በማለት ከትናጋ ጋር እየተገናኘ የተለያዩ ድምጾች እንዲፈጠሩ ይረዳል፡፡
ሌሎችም ክፍሎች እንደዚሁ በቀድሞ ሥራዎች ላይ ተጨማሪ ዐዲስ ሙያ አፍርተዋል፡፡ ሳምባ ከሥር አየር ሲስብና እየመጠነ ሲገፋ ሥረ ድምፅ (ቮካል ኮርድ) ሲርገበገብ ጉሮሮ ዐጠር ረዘም፣ ጠበብ ሰፋ እያለ የሰው ልጅ የተለያየ ትርጉም ያላቸውን ድምጾች ለመፍጠር ያስችሉታል፡፡ እነዚህ የሰውነት ክፍሎች በዚህ ድምፅ የመፍጠር ተግባር ይበልጥ በቀጠሉ መጠን የውስጥ ተፈጥሮአቸውም ለዚሁ ተግባራቸው በሚስማማ ሁኔታ እየተደራጀና እየሰለጠነ ይሄዳል፡፡
በኅብረተሰብ ውስጥ የሚወለድ ሕጻንም እነዚህን የሰለጠኑ የድምፅ መፍጠሪያ የሰውነት ክፍሎች ስላሉት ውስጣዊ የመናገር ችሎታን ይዞ ይወለዳል፡፡ ሆኖም ይህ ውስጣዊ ችሎታ ሕጻኑ ከማኅበራዊ ግንኙነት በቋንቋ ግብአት (ኢንፑት) ካልተቀሰቀሰ በቀር ለንግግር አያበቃውም፡፡ ተዳፍኖ ይቀራል፡፡ ይህም ማለት አንድ ሕጻን በአካባቢው ቋንቋን ካልሰማና ካላየ (የቋንቋን ግብአት ካላገኘ) ውስጣዊ የመናገር ችሎታ ይዞ ቢወለድም ሊናገር አይችልም ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ሕጻናት ከመጀመሪያ ጀምሮ ለቋንቋ መጋለጥ ወይም አለመጋለጥ ወይም የመጋለጣቸው መጠን በኋላ በቋንቋ ችሎታው ላይ ወሳኝ የሆነ ተጽእኖ እንደሚኖረው ለማየት አያዳግትም፡፡
እያንዳንዱ ቋንቋ ለተናጋሪው ማኅበረሰብ የተሟላ አገልግሎት የሚሰጥ መሣሪያ ነው፡፡ ቋንቋዎች ሁሉ ለያሉበት ኅብረተሰብ የሚመጥን አገልግሎት የሚሰጡ እስከሆኑ ድረስ በባሕሪያቸው ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ቋንቋዎች ሁሉ የተሟላ ሰዋስው አላቸው፡፡ ሆኖም ኅብረተሰቦች በእድገት ደረጃ ስለሚለያዩ ይህ ልዩነት ከቋንቋ አንጻር የሚንጸባረቀው በያንዳንዱ ቋንቋ የቃላት ብዛትና ጥልቅ ጽንሰ ሐሳብ የመግለጽ ችሎታ ነው፡፡
••• ቋንቋና ሐሳብ•••
****
ቋንቋ የሰዎችን ግንኙነትና የዕውቀት ተግባር በምልክት፣ መልክና ሥርዓት ባለው ሁኔታ የሚያስፈጽምና የሚገልጽ ነው፡፡ በፍልስፍና ታሪክ ውስጥ ቋንቋ ሁለት መሠረታዊ ጥያቄዎችን አስነስቷል፡፡ አንደኛው ቃል ማለትም ስያሜ ተፈጥሮአዊ ወይም ነባራዊ መሠረት አለው ወይም ከስምምነት ብቻ የሚመነጭ ነው የሚለው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ዕሳቦት ካለቋንቋ፣ ቋንቋ ካለ ዕሳቦት የማይገኝ በመሆኑ የተለያየ ህልውና አላቸው ወይንስ አንድ ናቸው የሚል ነው፡፡
በነባራዊ ሐሳባዊያን አመለካከት ቃላት የሚገልጹት ሐሳብን ሲሆን፣ ሐሳብ ደግሞ የነገሮች ውስጠ ምንነት በመሆኑ ቃላት ሰው ሠራሽ አይደሉም፡፡ ሆኖም ዕሳቦትና ቋንቋ የተለያዩ ናቸው፤ ቋንቋ የዕሳቦት ውጫዊ ገጽታ በመሆኑ ነፍስ ከሥጋ እንደሚለይ ሐሳብም ከቋንቋ ይለያል፡፡ በኅሊናዊ ሐሳባዊያን አስተሳሰብ ግን ቋንቋ አስፈላጊ ሲሆን ከነባራዊ ነገሮች ምንነት የሚመነጭና እነሱን የሚገልጽ አይደለም፡፡ የቃላት ምንጭ ስምምነት ነው፤ ሰው ስንል ለነገሩ በስምምነት የምንሰጠው ስም እንጂ ምንነቱን የሚገልጽ አይደለም፡፡ለዚህም ማስረጃ የሚሆነው አሁንም ቢሆን ከተስማማን በሌላ ቃል ልንጠቀም የምንችል መሆናችን ነው ይላሉ፡፡
በእርግጥ በቋንቋ ውስጥ ስምምነት እንዳለ ሊካድ አይችልም፡፡ ሆኖም ስምምነት ሲባል በግለሰብ ደረጃ የሚፈጸም ወይም የሚፈጠር አለመሆኑ በትክክል የሚያስረዳን ቋንቋ ማኅበራዊ መሠረት እንዳለው ነው፡፡
ንቃተ ኅሊና ከቋንቋ ውጪ ሊኖርና ሊዳብር አይችልም፡፡ ምክንያቱም ቋንቋ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፈውን ዕውቀት የሚያጠራቅም በመሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ካለሱ ዕሳቦት ከረቂቅ ሐሳቦች ላይ ለመድረስ ስለማይቻለው ነው፡፡ ማንኛውም ቃል (ወንበር፣ ሰው ወዘተ…) አጠቃላይ ነው፡፡ ማለት ነባራዊ ሐሳባዊያን እንደሚሉት ቋንቋ የሐሳብ መግለጫ ብቻ አይደለም፤ ቋንቋ የራሱ ሕጎች ያሉት መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ሁለቱን አንድ ማድረግ የነባራዊውንና የኅሊናዊውን ልዩነት መሰረዝ ይሆናል፡፡
ቋንቋ ቁሳዊ ሲሆን፣ ሐሳብ ነጸብራቅ ነው፡፡ የቋንቋ ዓይነተኛ ተግባር የሰውን ንቃተ ኅሊና ማኅበራዊ ማድረግ ነው፡፡ የሰዎችን እንቅስቃሴና አስተሳሰብ የሚያገናኝና የሚያቀናጅ በመሆኑ ቋንቋ የማኅበራዊ ኑሮ ዋንኛው አካል ነው፡፡
•••ቋንቋና ፍልስፍና•••
****
አንዳንዴ የሕዝብ አካል ሆነን ግን «ይኼ ሕዝብ!» እያልን እንደምንናገረው ሁሉ ፍልስፍና ውስጥም ሆነው ፍልስፍናን የሚሞልጩ ፈላስፎች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል እንደ ሉድዊግ ዊትገንስቴይን ዐይነቶቹ ይገኙበታል፡፡ ቋንቋ ስር የተደበቀውን ፍልስፍና መዞ በማውጣት ከተጨባጭ እውነታው ጋር እንዲፋጠጥ ካደረጉት አንዱ ዊትገንስቴይን ነው የሚሉለት አሉ፡፡
What's more, when the old man finally called the little boy to tidy up the fishing gear and fight again, he had no fear, no hesitation, even though his body was so painful that he was about to explode, he was still so determined and decisive. Such courage and confidence are so worth touching.
Join_us;
👉 @et_books1
👉 @et_books1
The Old Man and the Sea is the last major work of American writer Ernest Miller Hemingway, published in 1952. Adapted from a true story, the book tells the story of a fight between an old Cuban fisherman, Santiago, and a big marlin. The book is adapted from a true story that Hemingway learned in 1935. Hemingway considered The Old Man and the Sea "the best work of his life"
The old man didn't complain or get discouraged when he hadn't gained anything for eighty-four days. On the contrary, he was still full of optimism. It's like we have tried our best for one thing, but still haven't got the result we want, so what should we do at this time? Can you maintain an optimistic attitude like an old man? If so, then whatever the outcome, we have at least proven ourselves.
A small fishing boat and an experienced fisherman are struggling to catch a big fish in a vast blue ocean. The story is very simple, it is fishing. But this was another extraordinary fishing, an old man catching a marlin bigger than a skiff. He was the only one in the whole process, fighting against the fish alone. Let's talk about old people. The old man fought with the fish for three days, holding on to the line desperately, his hands and shoulders were worn out, he felt severe pain, but he still did not give up, he was a man who refused to admit defeat. The old man was still rational when he was catching fish. He told himself what to do next, which reflected the old man's rich experience, and the old man was always prepared, which is the reason for his success.
The old man has the romance of a man and the feelings of the sea. He firmly believes that his big fish is somewhere. Even if he has not caught a fish for eighty-four days, this still cannot make the old man despair. Eighty-four days. It's not eight days and four days. If it's someone else, can they hold their breath? The old man sticks to himself and has a romantic date with the sea. He believes in himself and the sea. It can be said that the old man’s dream is to catch fish, big fish. In the article, we can see the marlin caught by the old man. Fish is extremely loved and respected, he even treats it as a brother, but he has to catch it because of his livelihood. The old man is also a confident person. He believes that the big fish will take the bait, and he believes that he can catch the big fish. This confidence also comes from his ability.
In the article, the old man mentioned more than once that "it would be great if the boy was here", which shows that the little boy is also a powerful assistant in his heart. The old man often talks to himself, to the sea, to the fish, to the sky Talking, he once said to himself, people will not be alone in the sea. But I can feel the lonely old man talking to himself alone on the lonely fishing boat. The old man actually doesn't want to be alone, so in the end the old man will say "I miss you very much" to the little boy. No matter what kind of strong man he is, he is a human being after all. When going to sea in the future, I believe the old man will definitely take the little boy with him. And Xiaonan's help is also very good. After all, the strength of the team should not be underestimated, and the strength of a team working alone is definitely not as good as that of a concerted effort. Therefore, we must also make good use of the strength of the team, and really don’t be afraid of sharing the final results, as much as the pie is shared.
In front of the sea of fate, each of us is a fisherman, and it always has countless ways to make us bruised and miserable. Then we should accept it calmly or fight hard, but no matter how we are polished by life and reality, we cannot give up the courage and tenacity in our bones.
Every dream chaser is worthy of admiration, and the process of the dream chaser is also worthy of aftertaste. Even if the dream chaser is covered with bruises, it is so touching and joyful.
Уже доступно! Исследование Telegram 2025 — ключевые инсайты года 
