cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/የሰ/ት/ቤ/ማ/መ/ማኅበረ ቅዱሳን ሚዛን አማን ማዕከል መርሐ ግብራት ፥ #የቅዱሳን_ታሪክ #መጽሐፍ_ትረካ #መጽሐፍ_ጥቆማ #ብሒላተ_አበዉ #የየበዓላት ዋዜማ እና ማኅሌት #መዝሙር https://t.me/n_i_k_o_d_i_m_o_s መወያያ

Больше
Рекламные посты
218
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

🌼​​​​ቅዱስ ጳውሎስ 🌼 =============== 🌹ጳውሎስ ማለት ንዋይ ህሩይ ማለት ነው። ሐዋ. ፱፡ ፲፭ (9፡15) አንድም ብርሃን ማለት ነው። ዘዳ.፲፬፡፪ አንድም መድቅዕ ማለት ነው። ቀዳሚ ስሙ ሳዖል ነው። ሳዖል ማለት ጸጋ እግዚአብሔር የበዛለት ማለት ነው። ትውልዱ ከነገደ ቢኒያም ነው። ፊሊ. ፫፡፭ አባቱ ዮስአስ ይባላል። 🌹የተወለደው ጌታ በተወለደ በ፭ (5) ዓመት በጠርሴስ ነው። ከ፲፭ ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም በታላቅ እህቱ ቤት ተቀምጦ ከመምህር ገማልያል ሕገ ኦሪትን ተምሯል። በወንጌል ያመነው ጌታ ባረገ በ፰ኛው ዓመት ነበር። ጌታም በደማቆ መብረቅ ጥሎበት ሳኦል ሳኦል ስለምን ታሳደኛለህ ብሎ ታርቆታል። ከ፸፪ (72) አርድእት አንዱ የሆነው ሐናንያ ጌታ በራዕይ ታይቶት ጳውሎን አስተምረህ አሳምነህ አጥምቀው አለው። እርሱም በእጁ ገና አይኑ በዳሰሰው ጊዜ አይኑን አሳውሮት የነበረው እንደ ቅርፊት ወድቆለታል። ሐዋ.፱፡፩-፲፱ (9፡1¬-19) 🌹ከዚያ በኋላ በክርስቶስ እመኑ እያለ አስተምሯል። ብዙዎችንም አስተምዎ አጥምቋል። ሐዋ. ፲፬፡፰-፲፰ ብዙውንም አሳምኗል። በወይኒም ታስሮ በነበረበት ወቅት ብዙ ሰዎችን አሳምኗል። ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱ፤ ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ። 🌹ጌቶችዋም የትርፋቸው ተስፋ እንደ ወጣ ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ወደ ገበያ በሹማምት ፊት ጐተቱአቸው፤ ወደ ገዢዎችም አቅርበው። እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ከተማችንን እጅግ ያናውጣሉ። እኛም የሮሜ ሰዎች ሆነን እንቀበላቸውና እናደርጋቸው ዘንድ ያልተፈቀደልንን ልማዶች ይናገራሉ አሉ። 🌹ሕዝቡም አብረው ተነሡባቸው፥ ገዢዎቹም ልብሳቸውን ገፈው በበትር ይመቱአቸው ዘንድ አዘዙ፤ በብዙም ከደበደቡአቸው በኋላ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፥ የወኅኒውንም ጠባቂ ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት። እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው። በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ። 🌹የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ። መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤ ወደ ውጭም አውጥቶ። ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው። እነርሱም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት። 🌹ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገሩአቸው። በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ፤ ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው ፥ በእግዚአብሔርም ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ። ሐዋ. ፲፮፡፲፰-፴፬ (16፡18-34) ሕሙማንንም ሕሙም መስሎ አስተምሯል። ፩ቆሮ.፱፡፳፪ (1ቆሮ.9፡22) ፲፬ መልዕክታትንም ጽፏል። 🌹ከዚህ በኋላ በ69 ዓ.ም ሮም ሲያስተምር ኔሮን ቄሣር አስጠሩት ሲል በንጉሱ ፊት ሲቀርብ መስቀሉን ይዞ ቀረበ። ንጉሱ ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡ አለ። በመጎናጸፊያም ሸፍኖ ሰይፎታል። ደሙም ሰማየ ሰማይ ወጥቶ ቀተሉኒ በዓመጻ እያለ ተካሷቸዋል። ሲያልፍም የ72 ዓመት አረጋዊ ነበር። ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር የሞቱት በአንድ ቦታ በአንድ ቀን ነበር። ይህም ሐምሌ ፭ ነው። 🌼ምንጭ፡- ገድለ ሐዋርያት፣ ዜና ሐዋርያት፣ ነገረ ቅዱሳን ቁጥር ፪፣ መዝገበ ታሪክ 🌹የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡ 🌹ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡ አነሳስቶ ያስጀመረኝ አስጀምሮ ያስጨረሰኝ የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን፡፡🌹
Показать все...
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ተማሪወች ዛሬ በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ቡራኬ በቤተክርስቲያን ተመርቀዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ት/ቤት ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የወልድያ ማዕከል ባለፉት ዓመታት በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዋናውና መርሣ ካምፓስ ያሥተማራቸውን 140 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ዛሬ ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም አስመርቋል። ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በወልድያ ደብረ ሲና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ለተመራቂ ተማሪዎች አባታዊ የአደራ መልእክት አስተላልፈዋል። መማር የሕይወት ምንጭ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው በተማራችሁት ሳይንሳዊና መንፈሳዊ ትምህርት መሠረት እንዲታገለግሉ ቤተክርስቲያን፣ ሀገርና ቤተሰብ ከእናንተ ብዙ ይጠብቃሉ ብለዋል። የጠቢባን (የምሁራን) መብዛት የዐለም መድኀኒት ነውና በተማራችሁት ትምህርት ሀገርንና ወገንን እንዲያገለግሉ አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል። ባለፉት ዓመታት በተለይ በሰሜን ወሎ በተከሰቱ  ችግሮች ምክንያት ብዙ ፈተናና ውጣውረድ ማሳለፋችሁ በተግባር አስተምሯችኋል ያሉት ብፁዕነታቸው ፈተናዎቹን ተቋቁማችሁ ለስኬት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። ከሳይንሳዊ እውቀት ባሻገር እግዚአብሔርን መፍራት በመማራችሁ የለውጥ ሐዋርያ እንደምትሆኑ ተስፋ ተጥሎባችኋልም ብለዋል ብፁዕነታቸው። ሳይንሳዊ እውቀታችሁ ፍሬ የሚያፈራው እግዚአብሔርን መሪ በማድረግ ስትሠሩ በመሆኑ በሥራችሁ ኹሉ እግዚአብሔርን ከፊት አስቀድሙ ብለዋል። በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ጌዜን በአግባቡ በመጠቀም ቤተክርስቲያንን እያገለገሉ በሳይንሳዊ ትምህርታቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ተሰጥቷል። join and share Via ሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE 🇪🇹👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇🇪🇹 🕊@mizanamangibigubae🕊      🕊@mizanamangibigubae🕊      🕊@mizanamangibigubae🕊 🇪🇹👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆🇪🇹     🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪       ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧       ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
Показать все...
ምስባክ ዘነግህ አመ ፲ወ፪ ለሰኔ 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚     🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪       ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧       ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
Показать все...
ይትአየን.mp31.98 MB
ሶበ ትሬእዮሙ.mp32.30 MB
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 የሰኔ ቅዱስ ሚካኤል #ሥርዓተ_ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋራ አብረን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 👉Share ያድርጉ ሥርዓተ ነግሥ:- ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 መልክዐ ሥላሴ፦ ሰላም ለጒርኤክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ፤ብዑላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ፤ከመ ትትኃየዩኒሰ ወኢትኅድጉኒ ጽኑሰ፤ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ስጋየ ጌሠ፤ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ዚቅ ኢይጽሕቅ ዘይመክሮ ወኢየኀሥሥ ዘይረድኦ፤አልቦቱ ጥንት ወኢተፍጻሜት፤ኢየኃልቅ መንግሥቱ ወአልቦ ዘይክል መዊዓ ኀይሉ፤ወአልቦሙ ኁልቊ ለሠራዊተ መላእክት እለ ይትለአክዎ፤አንተ ውእቱ አቡሃ ለጥበብ፤ገባሬ ኲሉ ፍጥረት ወገባሪሃ ለሕግ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ነግሥ ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል፤እንበለ ባህቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ዚቅ አመ ይነፍህ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ፤አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን፤ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ፤በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 መልክዐ ሚካኤል፦ ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ፤ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ፀሃፈ፤ሶበ እጼውእ ስመከ ከሢትየ አፈ፤ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ፤ለረዲኦትየ ነዓ ሠፊሐከ ክንፈ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ዚቅ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ዓቢተነ በመድኃኒትከ፤ጸግወነ ንጸውዕ ስመከ፤ኖላዊነ ኄር ትጉሕ ዘኢትነውም ሰላመከ ሀበነ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ወረብ ሀበነ ሰላመከ ንጸውዕ ስመከ/፪/ ዘኢትነውም ትጉሕ "ኖላዊነ ኄር"/፪//፪/ 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 መልክዐ ሚካኤል፦ ሰላም ዕብል ለአስናኒከ ዘመንፈስ፤ዘኢይረክቦን ጥረስ፤ሚካኤል ረዳኢ ለእለ ውስተ ባሕር ወየብስ፤እስመ ረሰይከ ካህነ ምሥዋኡ ክርስቶስ፤መፍትው ሊተ ትተንብል ቀሲስ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ዚቅ ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ ምስሌሁ፤ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ፤ዮም ሰማያዊ በምድር አስተርአየ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ወረብ ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ/፪/ ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ ስዕንኩ/፪/ 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 መልክዐ ሚካኤል ሰላም ለእስትንፋስከ ቁሱላነ ነፍስ ለአጥዕዮ፤ዘይነፍሕ ፄና አንህዮ፤ሚካኤል ነዓ ኲናተከ በተረስዮ፤ለገቢር ከመ ቀዳሚ ለአርዌ አመፃ ደርብዮ፤እስመ ኢኃደገ እንከ ዘትካት እከዮ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ዚቅ ወከሢቶ ረከበ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ፤ወእስብክ ሎሙ ግዕዛነ ለጺውዋን፤ወእፈውሶሙ ለቁሱላነ ልብ፤ወእስምዮ ለባሕራን ኅሩየ፤ዝኬ ውእቱ ዘተነግረ በመዋዕለ ትካት፤ለ፳ኤል ኅብስተ መና ዘአውረደ በገዳም፤ወርእየቱ ከመ ተቅዳ፤ወከመ አያያተ መዓር ጥዑም ፈድፋደ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ወረብ "ወከሢቶ ረከበ"/፪/ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ/፪/ ወእስብክ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን ወእስምዮ ለባሕራን ኅሩየ/፪/ 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 መልክዐ ሚካኤል፦ ሰላም ለአጻብኢከ መጽሐፈ እለ ለክዑ፤ዕጒለ አባግዕ እምኖሎት በጊዜ ተመልዑ፤ሚካኤል አንተ ለንጉሠ ነገሥት ካህነ ምሥዋኡ፤አሣዕነ መድኃኒት ለእገርየ አጻብኢከ ይቅጽዑ፤ከመ በፍናውየ የኀዝ ለሰላም ቅብዑ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ዚቅ ቅዱሳት አጻብዒከ ለጽሒፈ መጽሐፍ እለ ተቀንያ፤ወብፁዓት አዕይንቲከ ምስጢረ መለኮት ዘርእያ፤ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ወረብ ምስጢረ መለኮት ዘርእያ አዕይንቲከ/፪/ ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ "ሚካኤል መልአክ"/፪//፪/ 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 መልክዐ ሚካኤል፦ አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክዕከ ኲሉ፤ለለአሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ፤ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ፤ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኃ ሰማያት ዘላዕሉ፤ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ዚቅ መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል፤ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ፤አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዓቢይ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ወረብ መልአከ ሰላምነ/፬/ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ/፪/ 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 አንገርጋሪ አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ፤ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ፤ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ፤ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ምልጣን ዘዜማ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ፤ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 አመላለስ ወሪዶ እመስቀሉ/፪/ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ/፬/ 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ወረብ አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ/፪/ ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ/፪/ 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 እስመ ለዓለም፦ ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ፤አዓርግ ሰማየ ኀበ አቡየ ወአቡክሙ፤ኀበ አምላኪየ ወአምላክክሙ፤ዘንተ እንከ ይቤሎሙ ዓርገ ውስተ ሰማያት፤ካዕበ ይመጽእ በዘዚአሁ ስብሐት፤ሠርጎሙ ለሐዋርያት ብርሃኖሙ ለእለ ውስተ ጽልመት፤መድኃኔ ነገሥት ክብሮሙ ለመላእክት ኖላዊሆሙ ለአህዛብ ለከ ስብሐት። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ዓዲ እስመ ለዓለም፦ እምድኅረ ተንሥአ እሙታን ዓርገ ውስተ ሰማያት በስብሐት አምላከ ምሕረት፤ወተቀብልዎ አዕላፈ አዕላፋት፤ወሚካኤል ሊቀ መላእክት በንፍሐተ ቀርን ዘእምኀበ እግዚአብሔር፤ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 አመላለስ፦ በንፍሐተ ቀርን ዘእምኀበ እግዚአብሔር/፪/ ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር/፪/ 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ቅንዋት፦ ተሰቅለ ወሐመ ከመ እቡስ ማዕከለ ክልኤ ፈያት፤ዘይትዓፀፍ ብርሃነ፤ከመ ልብስ አክሊለ ሰማዕት ሠያሜ ካህናት፤ማ፦ዓርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት አእኰትዎ መላእክት። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 አመላለስ፦ ዓርገ  በስብሐት ውስተ ሰማያት/2/ አእኰትዎ መላእክት/4/ 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 =>✍እመሒ ስሕተኩ አንትሙ እለ በመንፈስ አርትዕ(የተሳሳትኩት ቢኖር እናንተ በመንፈስ ያላችሁ አቃኑት)🙏🙏🙏  💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 join and share Via ማህሌታውያን
Показать все...
👍 1
ሰላም እንዴት ናችሁ ሞክሩት
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.