ብስራት (graph)
Открыть в Telegram
5 871
Подписчики
+624 часа
+417 дней
-2230 дней
Архив постов
5 870
የማቴዎስ ወንጌል 5:21-24
••••••••••
²¹ ለቀደሙት። አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል።
²² እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።
²³ እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ፥
²⁴ በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ።
@bisrat_graphics
5 870
Repost from Tesfa
የእግዚአብሔር የተወደደ ልጅ ለሚያምኑ አማኞች ሁሉ እውነተኛ ሰላም እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል። ይህ ሰላም ከምድር ያልሆነ :-ከሥራ ፣ ከገንዘብ ፣ ከሰዎች እና ከየትኛውም ሁኔታ የማይመጣ ሰላም ነው። ዓለም የምትሰጠው ሰላም ጊዜያዊና በነገሮች ላይ የተመሰረተ ነው። ነገር ግን ከተወደደው ከእግዚአብሔር ልጅ የምንቀበለው ሰላም ሁኔታዎች ቢቀየሩ የማይቀየር፣ በዙሪያችን ሁሉ ቢወደቅ የማይወድቅ፣ የምታየው ተስፋና አላማ እንኳን ባይኖር የማይናወጥ ሰላም ነው። ከዚያም ኢየሱስ ልብክ እንዳይታወቅ እና እንዳትፈራ አዟል :: ስለዚህ አትረበሽ፣ ልብህ አይታወክ። በዚህ አስተማማኝ ጌታ እና እርሱ በሚሰጠው ሰላም ተማመን።
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
5 870
የማቴዎስ ወንጌል 5:43-44,46
••••••••••
⁴³ ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
⁴⁴ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
⁴⁶ የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?
@bisrat_graphics
5 870
የማቴዎስ ወንጌል 5:14-16
••••••••••
¹⁴ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።
¹⁵ መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።
¹⁶ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።
@bisrat_graphics
5 870
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10:13
••••••••••
¹³ ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።
@bisrat_graphics
5 870
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:4,7
••••••••••
⁴ ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።
⁷ አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
@bisrat_graphics
5 870
የማቴዎስ ወንጌል 6:26-28,31-33
••••••••••
²⁶ ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?
²⁷ ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?
²⁸ ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤
³¹ እንግዲህ። ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤
³² ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።
³³ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።
@bisrat_graphics
5 870
Repost from ማስታወቂያ
🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨
📨የምስራች✉️
📚ለልብ ወለድ ወዳጆች አዲስ ቻናል ተከፈተላችሁ😮
በፈለጋችሁት መልክ ➡️በፅሁፍ
➡️በትረካ
➡️ ተቀላቀሉ
✅Sponsor :- @Albumsongsbot
5 870
እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።
(ኦሪት ዘፍጥረት 28:15)
@bisrat_graphics
5 870
+1
መዝሙረ ዳዊት 23:1-6 (AMH)
••••••••••
¹ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
² በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
³ ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
⁴ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
⁵ በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።
⁶ ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።
@bisrat_graphics
5 870
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:2 (AMH)
••••••••••
² የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
@bisrat_graphics
5 870
🛍የሚሸጥ Active የተለግራም ቻናል 🛍
🚦Content - Spiritual,
✅ 19.8k Subscribers
✅9.2k Subscribers
✅3.4k Subscribers
🌍እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ መግዛት የሚፈልግ በውስጥ መስመር አልያም ደውሎ ያናግረኝ ።
✅እንዲሁም መሸጥ የሚፈልግም ካለ እግዛለሁ አናግሩኝ
አናግሩን | ደውሉልን
☎️ +251916446034
📩 @Abu_nd8
https://t.me/Worlds_reality
