cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

UNIVERSITY INFO

Больше
Рекламные посты
2 853
Подписчики
+124 часа
+547 дней
+27630 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የ12ኛ ክፍል የተማሪዎች አቀባባል በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች👏👏👏👏👏 መልካም ፈተና 👏😍🙏✌️👌😊😘😘🥰
Показать все...
👍 2 2
ተማሪውን በመድፈር የተከሰሰው የዩኒቨርሲቲ መምህር በ9 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥቷል። ተከሳሽ አየለ ሀይሉ ሞላ  ይባላል። የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከረፋዱ 9፡00 ሰዓት ላይ የሚያስተምራትን የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ተማሪ " የተበላሸብሽን ዉጤት አስተካክልሻለሁ ፤ አሳይመንት ይዘሽ ኢስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ነይ " ሲል ይቀጥራታል። የግል ተበዳይ ተማሪ ነይ ወደ ተባለችበት ቦታ ለመሄድ በጉዞ ላይ ሳለች ተከሳሽ በወልቂጤ ከተማ ጉብሬ ክ/ከተማ ከሚገኘዉ  የመምህራን መኖሪያ አፓርታማ ላይ ሆኖ  የግል ተበዳይን ጠርቶ ወደ መኖሪያ ክፍሉ እንድትገባ ያደርጋታል። ተከሳሽ የግል ተበዳይን ውጤት ለማስተካከል ሴትነቷን ለመጠቀም ያቀረበላትን ጥያቄ " አልቀበልም " ስትል በእምቢታ ትፀናለች። ተከሳሽ ካንተ ጋር አልተኛም ስትል አሻፈረኝ ያለችውን የግል ተበዳይ በጥፊ እያላጋ  ከለፈቃዷ በኃይል አስስገድዶ እንደደፈራት  የተከሳሹ የክስ መዝገብ ያስረዳል። ተከሳሽ የተከሰሰበት ክስ የወልቂጤ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በችሎት ቀርቦ የተነበበለት ክስ የወንጀል ድርጊቱ " አልፈፀምኩም " ሲል ክዶ ተከራክሯል። ዐቃቤ ህግም የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አስቀርቦ አሰምቷል። በዚህም ግለሰቡ የወንጀል ተግባሩን መፈፀሙ አረጋግጧል። ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር አስቀርቦ ቢያሰማም ክሱን ማስተባበል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል። ፍ/ቤቱ መምህሩን በ9 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ፥ " የዚህ መምህር የቅጣት ዉሳኔ በመሰል ችግር ዉስጥ ለተዘፈቁ መምህራን የማስጠንቀቂያ ደወል ይሁን " ሲል አስጠንቅቋል።
Показать все...
👍 5
Фото недоступноПоказать в Telegram
#NationalExam " የኦንላይን ፈተናው አልቀረም። የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጿል። ሚኒስቴሩ ይህ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ መሆኑን አሳውቋል። ፈተናው በሁለቱም በወረቀት እንዲሁም በኦንላይን እንደሚሰጥ አረጋግጧል። ተማሪዎች ይሄን ተገንዝበው ዝግጅታቸውን እንዲቀጥሉ አሳስቧል። ትምህርት ሚኒስቴር " ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት እየሰራን ነው ለዚህም ከፍተኛ ዝግጅት ተደርጓል " ብሏል።
Показать все...
👍 2
#WolkiteUniversity ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ካሉት 51 የቅደመ-ምረቃ ፕሮገራሞች በ50 ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ያስፈተነ ሲሆን በመደበኛ መርሀ-ግብር 85.07% በማሳለፍ በ2015 የነበረውን ከፍተኛ ውጤት በሰፊ ልዩነት ወደ ላቀ ደረጃ አሻሽሏል። በተከታታይ ፕሮግራም የተፈተኑት ተማሪዎችን ጨምሮ የ2016 አማካይ ውጤቱ 82% ሲሆን በ10 ፕሮግራሞች ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ(100%) ማሳለፍ ችሏል።
Показать все...
👍 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
የምርቃት ቀን📍 #2024_Commencement የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ከሳምንቱ መጨረሻ ጀምሮ ያስመርቃሉ፡፡ ☑️ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 👉 ሰኔ 25/2016 ዓ.ም ። ☑️የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ👉 ሰኔ  28/2016ዓ.ም. ☑️ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 👉 ሰኔ 26 እና 27/2016 ዓ.ም ☑️ዲላ ዩኒቨርሲቲ 👉 ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ 👉 ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️ደምቢ ዶሎዩኒቨርሲቲ 👉 ሰኔ 29/2016 ዓ.ም 🧑‍💻እንኳን ደስ አላችሁ✌️👏👏👏👏
Показать все...
👍 4🤔 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ExitExam #Result የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኳል። በዚህም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። የዘንድሮው የመውጫ ፈተና ለ57 የመንግሥት እና ለ124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐግብሮች መሰጠቱ ይታወቃል። ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን አደረሳችሁ👏👏 ለተማሪዎች የሚሆን በ Online ብር ለመስራት ......... Start the business               Share share🙏🙏 ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇 ╔═══════════╗ ♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️ ♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️ ♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️ ╚═══════════
Показать все...
👍 5
Фото недоступноПоказать в Telegram
Congratulations 🎉🎉🎉🎉🎉🎆🎆🎆 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ከሳምንቱ መጨረሻ ጀምሮ ያስመርቃሉ፡፡ ☑️ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ☑️አክሱም ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ☑️መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ☑️አሶሳ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም ☑️ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም ☑️ወለጋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25-26/2016 ዓ.ም ☑️ሠመራ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 26/2016 ዓ.ም ☑️ቦረና ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 26/2016 ዓ.ም ☑️አምቦ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️ደብረ ብርሃን - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 29/2016 ዓ.ም
Показать все...
👍 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
#Ethiopia ላለፉት ስድስት ቀናት በመላ አገሪቱ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ተጠናቋል። 57 የመንግሥት እና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከመውጫ ፈተናው ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በተለይ ከተነገርን ይዘት እና ከተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው ቅሬታ ካቀረቡት መካከል፦ - የማኔጅመንት -የማርኬቲንግ ማኔጅመንት - የሀይድሮሊክና ውሃ ሃብት - የቬተርነሪ ሜዲሲን -የኸልዝ ኢንፎርማቲክስ ተማሪዎች ይጠቀሳሉ። ከዚህም ባለፈ ፥ " የተሰጠን ሰዓት በቂ አልነበረም ፣ፈተና ዘግይቶ የመጀመር፣ ለፈተናው በቂ ሰዓት አለመመደብ ችግር ነበር " የሚል ቅሬታ ያቀረቡም አሉ። የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ፈተናም በድጋሜ እንዲሰጥ ተደርጓል። አጠቃላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተላኩለትን ቅሬታዎች ይዞ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራርን አነጋግሯል። ከፍተኛ አመራሩ ፤ " የዘንድሮው 2016 የመውጫ ፈተና ከ220 በላይ ፕሮግራሞች ያለምንም ችግር Smoothly ነው የተሰጠው " ሲሉ ገልፀዋል፡፡ " ከፈተናዎቹ ጋር የተያያዘም ምንም አይነት Issue አላጋጠመንም " ያሉት ኃላፊው፤ " አንድም ቅሬታ ለትምህርት ሚኒስቴር አልደረሰም " ብለዋል፡፡
Показать все...
👍 3
#ExitExam "ከዘንድሮው የመውጫ ፈተና ጋር የተያያዘ ምንም አይነት ችግር አላጋጠመንም" - ትምህርት ሚኒስቴር ላለፉት ስድስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡ ለሁሉም የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂዎች በኦንላይን የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመውሰድ 178,000 ተማሪዎች መመዝገባቸውን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል፡፡ በዛሬው ዕለት የጤና ትምህርት መስክ ፈተናዎች ከ30 ሺህ ለሚበልጡ ተፈታኞች በመሰጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከአጠቃላይ የመውጫ ፈተና ጋር የተያያዙ በርካታ ቅሬታዎች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ደርሰዋል፡፡ የተወሰኑ ፈተናዎች በወጣው ብሉ ፕሪንት መሰረት የተዘጋጁ እንዳልነበሩ በርካታ ተፈታኞች ቅሬታቸውን ማቅረባቸው አይዘነጋም፡፡ አጠቃላይ ፈተናዎቹ ከተባሉት ሰዓት ዘግይተው መጀመራቸውና ለተፈታኞች በቂ የፈተና ሰዓት አለመሰጠቱ ሌሎች ተፈታኞች በቅሬታ ያነሷቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ በጉዳዮቹ ላይ አንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራርን የጠየቅን ሲሆን፤ የዘንድሮው የመውጫ ፈተና “ከ220 በላይ ፕሮግራሞች ያለምንም ችግር Smoothly መሰጠቱን“ ገልፀዋል፡፡ “ከፈተናዎቹ ጋር የተያያዘ ምንም አይነት Issue አላጋጠመንም” ያሉት ኃላፊው፤ “አንድም ቅሬታ ለትምህርት ሚኒስቴር አልደረሰም” ብለዋል፡፡ ምስል፦ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ
Показать все...
👍 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
#Update የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ውጤት ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ይፋ እንደሚደረግ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል። የፈተናው ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ በርካታ ተማሪዎች ጥያቄያቸውን አድርሰውናል። የፈተናው ውጤት መቼ ይገለፃል ስንል የጠየቅናቸው የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር፤ "በቅርቡ፥ ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት" ሲሉ መልሰውልናል። የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ከሰኔ 3-11/2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።
Показать все...
👍 3 2
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.