cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ልብ ወለድ (fiction)📚

እንኳን በደህና መጣችው share በማድረግ አበረታቱን 🙏

Больше
Рекламные посты
1 268
Подписчики
Нет данных24 часа
+177 дней
+9030 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ክፍል 10 የመጨረሻው ክፍል ነው ላይክ ያድርጉ 🙏 እንዳይረሱ 💖
Показать все...
🔥 42👍 26👎 1
በቅርብ ቀን አዲስ ልብ ወለድ ይዘን እንመለሳለን 💝
Показать все...
23👍 11🥰 3
ክፍል 10 የመጨረሻው ክፍል ነው 🙏
Показать все...
👍 37🙏 3🔥 1
ክፍል 9 ባለ ታክሲው እቤት ከገባሁ በኃላ ፍጹም የማያውቁኝ ሰው ሆንኩባቸው :: እናቴማ በዚች አጭር ደቂቃ ውስጥ ምን ቀመሰች በሚል አስተያየት ስታየኝ ተመልክቻታለሁ :: ልክ ጣፈጭ ሲበላ ውሎ ሀይፐር እንደሆነ ህጻን ልጅ ስለፈልፍ ስስቅ አመሸሁ :: በተደጋጋሚ "ዛሬ ምን ተገኘ ?' እንኳን ቢሉኝ እራሴን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ ደስተኛ ሆንኩ :: ደስታው አስክሮኝ ያወራሁትን አንዱንም እንኳን አላውታውስም :: ለሊቱንም ትንሽ ናፍቆቱን ሳስብ : መውደዱን ሳልም ከቆየሁ በኃላ በሰላም ተኝቼ አደርኩ :: እንዴት ደስ የሚል ስሜት ነው ያለው ለካ መወደድ : መፈለግ : መናፈቅ ! በውነት በሚወዱት መወደድን የሚያክል ምን ጥሩ ሰሜት አለ በዚች አለም ላይ ? ጠዋት ስነቃ ፊቴ በፈገግታ ደምቆ :: ልቤም የሚፈልገውን በማግኘት ሀሴት ተሞልቶ ተነሳሁ :: ከአሁን በኃላ ምን የሚያስፈራኝ ነገር አለ ? እሱን ማጣት ?........ በተቻለኝ መጠን ከቤት ላለመውጣት ወሰንኩ :: ቤታቸው ሄጄ መሰናበት ያለብኝ ዘመዶችን እንኳን ወይ በጠዋት አለዛም በማታ አንድ አፍታ ደርሼ ጨረስኩ።  የቀን ውሎዬ ግን ጆሮዬ የበሩን መንኳኳትና የስልኩን ጥሪ እንደጠበቀ ይውላል :: በኔ በኩል ሰሞኑን ሁሉ ነገር ጥሩ ይመስል ነበር :: ዛሬ ባያገኙት ነገ ማግኘታቸው አይቀርም የሚለው ተስፋዬ ሳይቀንስ በጉጉት ስጠባበቅ ከረምኩ ቀን አልፎ ቀን በተተካ ቁጥር ልቤ ጥርጣሬ እንዳይገባው ምክንያቶችን እየደረደርኩ ብዙ ትግስት አስጨራሽ ሰአታትንና ቀናትን አሳለፍኩ :: ምንም አዲስ ነገር የለም የሽኝቱ ሽርጉድ እለት ተለት እየጨመረ ከመሄዱ በስተቀር :: "ይህንን እቃ ትያዝ ! ያኛውን ትተወው , በጇ ትያዘው , ሻንጣው ይመዘን , እቃው ካሁኑ ይግባ " ሁፍፍፍፍ የሚያወሩት ነገር ሁሉ ተራ ! ምናለ ቢተውት ! አጭ ! ከቢኒያም ምንም ሳልሰማ አገር ልለቅ አንድ ቀን ቀረኝ :: መቼም የቢኒ እናት ሳይገማቸው አይቀርም እኔን ሲሰለቸኝ እህቶቼን በተራ በተራ እየተመላለስን ስናደርቃቸው።  በተለይ ደሞ በኔ ምክንያት ልጃቸው አስፋልት ላይ ቀኑን ሙሉ ፀሀይ ሲቀቅለው መዋሉን ቢሰሙ ይገሉኝ ነበር :: እንዲሁ ስልክ በጮህ ቁጥር ልቤ ሲተረተር ተሽቀዳድሜ ሳነሳ ሌላ ሰው ሲሆን :: አቤትትት ! እንደምኞቴማ ቢሆን ያንን ጎርናና ድምጹን ብሰማ ነበር የምናፍቀው:: ያኔ ምናለበት ረዘም ያለ ወሬ ቢያወራ ? አጭር አጭር መልስ ከሚሰጥ ! እያልኩ ከጎኑ ቁጭ ብዮ ታክሲውስጥ ስበሳጭ የነበረውን :: ገና መናገር ሲጀምር ወንዳወንድ ድምጹን ተሸክመው ወደጆሮዬ የሚዘልቁት ቃላቶች ሳላውቀው እንደሰመመን ቀስ ብለው አይኔን ያስከድኑኝ ነበር :: እንደገደል ማሚቱ ውስጤ ሲያስተጋባና በደም ስሬ ሲሰራጭ እሰማውና ንግግሩን ሲያቆም ከቀን ቅዠቴ እባንን ነበር... ቅዠቴ እባንን ነበር ልቤ ጥርጣሬ አዝሏል። ለራሴ እየደጋገምኩ የማይታመን ነገር ነው አጣነው ቢሉኝ መቼም እላለሁ።  እንዴት ግን ለመጨረሻ ጊዜ አንዴ እንኳን ደግሞ አይመጣም ? ምን ሊለኝ ይሆን የመጣው ? ያ ልጅ ምንሽ ነው ? ሊለኝ :: መቼም ከኔ ሳይሰማ እርግጠኛ መሆን አይችልም :: ኡፍፍፍ ምናለ ሰአቱን ወደኃላ የመመለስ ልዩ ችሎታ ቢኖረኝ ! ቢያስ አንድ ወር ግደማ ወደኃላ አጠነጥነው ነበር እሱ ተፈልጎ እስኪገኝ :: እቤት ውስጥ የሚተራመሰው ዘመድ አዝማድ : ጓደኛና ጎረቤት ከአንገት በላይ በሆነው አቀራረቤ በደንብ ላናግራቸው አልቻልኩም። እንዲያውም ሁሉም ወደየቤታቸው ሄደው ብቻዬን ብሆን ደስታውን አልችለውም ነበር :: ኤዲያ ! የትኛው ክፍል ልደበቅ ሰው የሌለበት ! ማታም መኝታቤቴን አጣበው ያድሩት ያጎቴ : ያክስቴ ልጆች : ጓደኞቼን ጨምሮ እረፍት አሳጥተውኝ እንቅልፍ ባይኔ ሳይዞር ነጋ :: ለነገሩ ምን እንቅልፍ አለኝ ! ሲነጋም ከጠዋት ጀምሮ ምን ይታውቃል መጨረሻ ላይ የሚፈጠረውን በሚል የተሟጠጠ ተስፋ በር በሩን ሳይ አረፈድኩ :: የልቤ መሰቀል በአይምሮዮ መሰብሰብ ስላልቻልኩ የምናገረው የምሰራው ሁሉ ለሌሎች ግራ አጋብቷቸው ዋለ :: በፍጹም ከልቤ እንዳልሆንኩ ስለተረዱ ግማሾቹ "ምን ሆነሻል "? በሚል ጥያቄ ሲያደርቁኝ :: የተቀሩት ደሞ መሄዴ እረብሾኝ ስለመሰላቸው ሊያጽናኑኝ ይሞክራሉ :: ቢቸግራቸው እናቴና አንዷ በጣም የምቀርባት ያጎቴ ልጅ ብቻዬን መኝታቤት አስገብተው ምን እንደሆንኩ ሲጠይቁኝ አፌ እንዳመጣልኝ ዛሬ መሄድ አልፈልግም ! ብዮ ለስንት ጊዜ አፍኜው የነበረው እንባዬ ከቁጥጥሬ ውጪ አምልጦ ዝርግፍ አለ :: እናቴ "ምን ?" ስትለኝ :: ያጎቴ ልጅ ደሞ "እየመጣሽ ተኚ " አለ ሰውየው ! ብላ መሳቅ ጀመረች.... ................ #ይቀጥላል...እረ Like ኡኡኡኡኡኡኡ ደሞ እንኳን አደረሳችሁ Eid Mubarak 💝 🌺🌺
Показать все...
40👍 20🥰 1👌 1
ክፍል 9 ምርጡ ክፍል ሊለቀቅ ነው ዝግጁ ናችው 🙌🙌🙌 አላችው ወይ
Показать все...
🔥 46🥰 9😡 5👍 3
ክፍል 9 በቅርብ ቀን 🙌 ሞቅ ሞቅ ደመቅ አድርጉ 🙏
Показать все...
42👍 18
መልካም ቀን 🙌
Показать все...
🔥 23👍 11
ክፍል 8 ባለ ታክሲው የናቴን ፌስታል ተቀበላት። " እረ አይከብድም እኮ ብትለውም " እኔ እይዘዋለሁ ማዘርዮ " ብሎ እንቢ አለ :: ትንሽ እንደተራመድን ቀስ እያለ እየዞረ ሲያየኝ ሀሳቤን ሰረቀውና የሰፈነውን ዝምታ ለማደፍረስ ያህል እሺ ቢኒዬ እንዴት ነህ ታዲያ አልኩት ? "አለሁልሽ " አለና ወደኃላ ቀረት እንደማለት ብሎ በአንድ አይኑ እናቴን እንደምታየውና እንደማተየው እየተከታተለ እኔን ድምጽ በሌለው ንግግር "እ ፈ ል ግ ሻ ለ ሁ " አለኝ :: በአይኔ እሺ ብዮው ወሬ እንደያዘ ሰው ቀስ ማለት ጀመርን :: እናቴ ከፊት ከፊት ፈጠን ፈጠን እያለች እቃ የተሸከመውን ልጅ ስትከተል :: "እረ የሆነ ልጅ ፈልጎሽ ነበር ! ቤት መጥቼም ነበር :: አልነገሩሽም ?" እረ ነግረውኛል ቢኒዬ እረስቼው ነው እንጂ :: ማነው ? "የሆነ ሚኒባስ ታክሲ የያዘ ልጅ " ሲለኝ ለካ ሰው ወዶ አይደልም እጢዮ ዱብ አለ የሚለው :: እኔ ደሞ በቂጤ ቁጭ ልል ምንም አልቀረኝም። ውይ ! ቢኒዬ ምን አይነት ልጅ ነው ? "በቃ ረዘም ያለ ጠየም ያለ ! አለ አይደል ጀንትል ነገር " አይኔ ተጎልጉሎ እንዳፈጠጥኩበት ቆምኩ ! መቼም ሳይፈራኝ አይቀርም :: "ምነው ትፈልጊው ነበር "? ብሎ አባነነኝ አዎ በጣም እፈልገው ነበር ብዮ ቁዝም አልኩና መቼ ነበር የመጣው ? "እ ....መቼ ነበር ? ብቻ ሁለቴ ነው የመጣው :: እኔና መስፍኔ እዛ ድድ ማስጫው ላይ ቁጭ ብለን መጥቶ አንቺን በምልክት ጠየቀን "ምን አላችሁ ? "በቃ በቅርቡ ከኮሜርስ የተመረቀች ልጅ ብሎ ያንቺን ምልክት ሲሰጠን አወቅንሽ " "ምንሽ ነው ግን ? ብሎ በጥያቄ አስደነገጠኝ እ .... የጓደኛዬ ወንድም ! አልኩ ከየት እንደመጣልኝ እግዜር ይወቀው :: "እህ ! ስምሽን እንኳን እኮ አያውቀውም ?" ሌላ አስደንጋጭ ጥያቄ እኔጃ እረስቶት ይሆናል ! ለነገሩ በደንብ አንተዋወቅም ጕደኛዬ ከቤቷ ስለወጣች እንዳንድ ነገር ለመነጋገር ነው የፈለገኝ :: ቅርብ ቀን የሰማሁት የአንዷ ልጅ ታሪክ ነበር :: "ግራ በመጋባት አንቺ ግን እንደዚህ አይነት ጓደኛ አለሽ "? ውይይይይ ቢኒዬ ምናለ ብትተወይ አልኩ በሆዴ ? በቃ እረጅም ታሪክ ነው :: አሁን እሱን ተወውና ምን አለ ታዲያ ? ብዮ ሳልጨርስ .... "በነገራችን ላይ አሜሪካ ልትሄጂ ነው አሉ :: ታድለሽ ! ብሎ ሞቅ ባለ ፈገግታ እቃ ያልያዘ እጁን ዘረጋ ሊያቅፈኝ :: እሺ ብዮ ታቀፍኩ ሁፍፍፍ እኔ የምፈልገው እንዲያወራልኝ ! ቆይ ቢኒዮ ግን ምን አለ ታዲያ ? እመጣለሁ ብሏል ? "አይ በቃ ስምሽን ከነገርነው በኃላ ስልክሽን ሲጠይቀን ... ብሎ ሳይጨርስ ".... ተንቀዥቅዤ ሰጣችሁት ? አልኩት ! ኖ ! አልሰጠነውም ! አናውቅም አልነው !" አይይ ! በሰጣችሁት ኖሮ ብዮ ቅር አለኝ :: እና በምንድነው የሚገኘው ታዲያ ? አየህ ቢኒዬ ከመሄዴ በፊት የፈለገ ቢሆን መገናኘት አለብን ስለው "ጠ ! በሰጠነው ኖሮ ! ይሄ መስፍኔ ነው ደሞ አይሆንም ያለው :: ምናባቱ ! ይሄ ባሪያ ! አልኩ በሆዴ ::.......ሳላውቀው ምን ይሻላል ታዲያ ቢኒዬ ? ብዮ በሚለማመጥ አይን ሳየው ልክ አሁኑኑ ይዞልኝ ይመጣ ይመስል :: "ቆይ ለምን ጓደኛሽ ቤት አትሄጂም ታዲያ ? እ .... አየህ እሱ እዛ አይኖርም በዛ ላይ ደሞ ቤቷን በደንብ አላስታውሰውም አልኩት እንዳመጣልኝ በሆዴ ግን አቤት ውሸቴ ! ደሞ ሲያስታውቅብኝ ! "እህ ! እንደማሰብ ብሎ ግን እኮ በኛ መስመር መሰለኝ የሚሰራው ! ሳላየው አልቀርም :: አዎ በብዛት ከዚህ ወደ መርካቶ ነው መስመሩ አልኩ ተቀብዮ " "በቃ ታዲያ ሰሞኑን አስፋልት ወጥተን እንጠብቅልሽ ሲያልፍ ካገኘነው ?" አዎ በናትህ ቢኒዮ ! "በቃ ለመስፍኔ እነግረውና እዛ እንቆማለን " ብሎኝ የያዘውን ፌስታል ሰጥቶኝ እንደ መሄድ ካለ በኃላ ዞር ብሎ " ታዲያ ስናገኘው ምን እንበለው ?" አለኝ :: እንደምወደው ንገረው በይው ! ከስንት ጊዜ በኃላ እንደገና ተመልሳ:: ግን አላልኩትም እ .....በቃ ስልኬን ስጡት ! ታውቀው የለ ? "አዎ ማወቁን አውቀዋለሁ ግን እቤት ሀርድ የለውም ?" የቤታችንን ጉድ በከፊል ያውቃል :: ባክህ ምንም ችግር የለውም ስጠው ! አልኩት የቤቴን ህግ በመሰልቸት እጄን አመናጭቄ :: አደራ እሺ ! ስለው :; "እናገኘዋለን አትጨነቂ በቃ " ብሎኝ ሮጠ :: ወደቤቴ እየኔድኩ በውስጤ ለብቻዮ አወራ ነበር :: እኔኮ አሁን ትልቅ ነኝ ደሞ ስልክ ቢደወልልኝ ምን ችግር አለው ! አሁንስ በዛ ! ቅቅቅ ቤተሰቦቼ ምንም ሳይሉ የበፊቱን አሰልቺ ህግ እያስታወስኩ ነበር :: በሌላ በኩል ደሞ ከመጠን በላይ ልቤ ሞልቷል :; ለካ እሱም እየፈለገኝ ነው !!! ሁፍፍፍፍ ጨክኖ አልዘጋኝም ማለት ነው ! ተመስገን አምላኬ ! ግን ለምን እንዲህ ከሚጠፋ ፊቱኑ ቢያናግረኝ ኖሮኮ እንዲህ ችግሩ አይብስም ነበር :; ሁፍ አሁን ደሞ.. ሳላስበው ከመጠን በላይ ናፍቆቱ ተሰማኝ ! ምን አለበት አሁን ቢመጣ እዚሁ እንደቆምኩ ብዮ ለብዙ ደቂቃ በራችን ላይ ቆምኩ :: ታየኝ እኮ ናፍቄው !! አሁን ቢመጣ አንገቱ ላይ ጥምጥም ነበር የምለው ! መላው ሁኔታው አነጋገሩ , አሳሳቁ , ፍጹም ሰላማዊ ገጽታው , ጠይምነቱ , ሰርቆ የሚያየኝ ሳይቀር በሀሳቤ እያመላለስኩ ፈዘዝኩ ከኃላዮ አትገቢም እንዴ የሚለው የህቴ ድምጽ ቆሌዮን እኪገፈው ድረስ :: ውይ ያስደንግጥሽ ! አንቺ ደሞ ቀስ አትይም ? ስላት :: እኅኅ ምን ሆነሻል ? ብላይ ጥላኝ ገባች. #ይቀጥላል... . እንዲቀጥል ከተመቻቹ like ❤️❤️❤️❤️👍👍❤️👍❤️👍❤️👍❤️
Показать все...
👍 41🔥 19 3
ክፍል 8 እንዲለቀቅ እስቲ ሞቅ ሞቅ ደመቅ አድርጉ 🙏
Показать все...
👏 36
በቀን 6 ሚሊየን ምትሰሩት ምንም ታብ ሳታደርጉ አንዴ ገብታችው መውጣት በየቀኑ bonus አለ እንዴት 6 ሚሊየን እናግኛለን ምትሉ በውስጥ አናግሩኝ 150,000,000 ሰዎች እየሰሩ ነው በዓለም ላይ 🔅 https://t.me/hamsteR_kombat_bot/start?startapp=kentId6684450150
Показать все...
Hamster Kombat

Just for you, we have developed an unrealistically cool application in the clicker genre, and no hamster was harmed! Perform simple tasks that take very little time and get the opportunity to earn money!

4👍 2