4-3-3 Crypto³
Открыть в Telegram
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @bboyessey Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...
Больше1 636
Подписчики
-1024 часа
-237 дней
-11330 день
Архив постов
1 637
▫️ Real token placement
ከንግድ derivative (የፋይናንሺያል instruments) በተለየ መልኩ እውነተኛ ቶከኖች በቅድመ ማርኬት ይቀርባሉ ይህም ኢንቨስተሮች የ Digital crypto ባለቤት እንዲሆኑ ያስችላቸዋል።
በ premarket ውስጥ መሳተፍ,ጠቀሜታው ▫️▫️▫️
🔑 በይፋ list ከመደረጉ በፊት ቶከኖችን በአነስተኛ ዋጋ የመግዛት እድል ይፈጥራል
🔓ይፋዊ ግብይት ከመጀመሩ በፊት የገበያውን ስሜትን ለመገምገም እና አወጭነቱን ለመረዳት ይጠቅማል
🔷 የተሳካ list እና የዋጋ ጭማሪ ካለው ከፍተኛ ትርፍ የማግኘት እድል ይፈጥራል
PREMARKET
1 637
Premarkets ምንድን ነው?
premarket ወይም ቀድሞ መገበያየት ቶክኑ ወይም Crypto በዋና ዋና Exchange ላይ ይፋ ከመደረጋቸው በፊት ቶከኖቹ ለንግድ ወይም ለኢንቨስትመንት እንዲገኙ ለማድረግ ነው premarket የተጀመረው። premarket ወይም ቀድሞ መገበያየት ባለሀብቶች ቶክኖቹን ለሰፊው ህዝብ ከመድረሳቸው በፊት ቀድመው እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።
key aspect of crypto premarket
📌 ቶከንን ቶሎ ማግኘት ፡- premarket ባለሀብቶች ቶከን በመገበያያ ገንዘብ ከlist ከመደረጋቸው በፊት እንዲገዙ እድል ይሰጣቸዋል ይህም list ከተደረጉ በኋላ ዋጋው ቢጨምር ጥቅም ሊያገኙ ይችላሉ።
🔷 Demand evaluation፡
Premarket ወይም ቀድሞ መገበያየት የባለሀብቶችን ፍላጎት እና የገበያ ስሜት ለመገምገም ያመቻል በቅድመ ማርኬት ውስጥ ያለው ከፍተኛ ፍላጎት ከlist በኋላ የተሳካ እንደሚሆን ሊያመለክት ይችላል።
🔷Risk እና Volatility፡-
Premarket ኦፊሻላዊ ያልሆነ የግብይት ስለሆነ ቶከኖች ከፍተኛ የዋጋ ተለዋዋጭነት ሊያጋጥማቸው ይችላል ዋጋዎች በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ላይ ወይም ወደ ታች ሊወርድ ይችላል እና ሁልጊዜም እና ጥቅም እንዳለው ሁሉ riskም አብሮ ይኖረዋል
📢 public እና private premarket
ማንኛውም ባለሀብቶች ቶከኖችን የሚያገኙበት ወይም የግል እንደ ተቋማዊ ባለሀብቶች ወይም በcrypto ላይ ያሉ ሰራተኞች እና የተመረጡ ባለሀብቶች ቡድን ብቻ የሚገኙባቸው premarket ይዘጋጃል ።
1 637
የባንኮች አንጀራ የተመሰረተው በዚሁ የሦስተኛ ወገንነት ሚና ላይ ነው። የCypherpunks አመለካከት ደግሞ ይህ የሶስተኛ ወገንነት ሚና በጥቂት ኃያላኖች እጅ መወደቅ ሳያስፈልገው በየትኛውም ቦታ ሥራውን ለመስራት ፍቃደኛ በሆኑ ሰዎች አማካኝነት (decentralized ሆኖ) መከናወን ነው ያለበት መሆንም ይችላል በሚል መነሻ ነው ቢትኮይንን የወለደው።
በቢትኮይን የሚፈጸሙ ክፍያዎች ትክክለኛነት የሚረጋገጠው በMining እንደመሆኑ የዚህን የገንዘብ ዝውውርና የማረጋገጡን ሂደት እዚህጋ በድጋሚ ማንሳት ይጠበቅብናል።አንድ ተጠቃሚ ኮምፒውተሩ ወይም ሞባይሉ ላይ ባለው Wallet ውስጥ በጥሬ ገንዘብ ገዝቶም ይሁን በክፍያነት ተቀብሎ ያገኛቸውን ቢትኮይን ያስቀምጣል። ክፍያ ሊፈጽምለት የፈለገውን ሰው የWallet አድራሻ ኮምፒውተሩ ወይም ሞባይሉ ላይ በመጻፍ Send የምትለዋን በመጫን ይልካል። በዚህ መልኩ ዲጂታል ገንዘብን በመጠቀም የሚፈጸም ክፍያ የሚመዘገበው አንድ መዝገብ (ledger) ላይ ሲሆን ከዚህ የሚመነጩ ክፍያዎችን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ጥቅም ለማግኘት በመላው ዓለም ልዩ የMining ኮምፒውተራቸውን ይዘው የሚሰሩ የዚሁ መዝገብ ግልባጭ ስላላቸው ትራንዛክሽኑ መፈጸሙ ወዲያው መዝገባቸው ላይ ይታያቸዋል። እዚህ ጋ 'ማረጋገጥ' የምንለው ለክፍያ የዋለው ገንዘብ ከዚህ ቀደም ከፋዩ ለሌላ ክፍያ የተጠቀመው (double spent) አለመሆኑን እና ከፋዩ እየከፈለ ያለው በርግጥም ከቦርሳው ያለውን እና የራሱ የሆነን ገንዘብ መሆኑን እርግጠኛ ሆኖ መመስከርን ነው። ይህ የማረጋገጥ ስራ ጥብቅ የሆነ የCryptography ሕግን እንዲከተል በሲስተሙ የሚገደድ በመሆኑ በማረጋገጥ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ሊያጭበረብሩ የሚችሉበት ምንም አይነት እድል የለም። ይህ ሂደት በአማካይ ከ10 እስከ 30 ደቂቃ ይፈጃል። ክፍያው ተረጋገጠ የሚባለው ሥራውን ከሚሰሩ ወገኖች በቅድሚያ የተቀመጠለትን የማረጋገጫ ስሌት በትክክለኛ መንገድ ሰርቶ በማጠናቀቅ ውጤት ሲያስረክብ ነው። ቀድሞ ውጤት ያስገኘው አረጋጋጭ ትራንዛክሽኑ የተፈፀመ ጊዜ ለማረጋገጫ ይከፈላል ተብሎ የተገለፀው የቢትኮይን መጠን ሲከፈለው ሌሎቹ አረጋጋጮች ደግሞ ቀድሞ ባረጋገጠው ወገን መረጃ መሰረት የየራሳቸውን ሌጀር እንዲያስተካክሉ (Update እንዲያደርጉ) ይገደዳሉ። በባንክ ቋንቋ ስናስቀምጠው Mining በቢትኮይን ለሚፈጸም ግብይት data center ነው። ሆኖም በማዕከል የተቀመጠ እና በአንድ ተቋም ቁጥጥር ሥር ያለ ሳይሆን በመላው አለም የተሰራጨ እና በተሳታፊ ወገኖች ሙሉ ዕይታ ሥር ሆኖ የሚንቀሳቀስ አስተማማኝነቱም ማንም ሊያስታቸው በማይችሉ የሒሣብ አልጎሪዝሞች አማካኝነት የተረጋገጠ እንጂ በሰራተኞች ታማኝነት ላይ ያልተመሰረተ ነው። ይህ የዲጂታል ገንዘብ የመቆጣጠሪያ ስልት ዕውን እንዲሆን ያስቻለው ቴክኖሎጂ Blockchain ተብሎ ይጠራል። ቢትኮይን በአፍሪካ ያለው ተቀባይነት ምን ያህል ነው? ቢትኮይን በመግዛትና መሸጥ ግብይት ብዛት፤ ቢትኮይንን መሰረት አድርገው አዳዲስ ብቅ ብቅ ባሉ የስራ ፈጠራዎች ብዛት፤ እንዲሁም በጋራ በመሰባሰብ በጉዳዩ ዙሪያ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ብዛት ጋና፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ መሪ ናቸው። ዝምባብዌ እና ቦትስዋናም በዚሁ ተግባር የተሰማሩ ጥቂት የማይባሉ ዜጎች አሉዋቸው። ቢትኮይን በዓለም አቀፍ ገበያ ከሚሸጥበት ዋጋ ይልቅ በአፍሪካ የሚሸጥበት እና የሚለወጥበት ዋጋ የ45 በመቶ ብልጫ አለው። ለዚህም ለምክንያት የሚጠከሱት አቅርቦት ከፍላጎት ያነሰ መሆኑ፣ የአፍሪካ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ አቅም አናሳ መሆን፣ ወደ አፍሪካ ምርት የሚልኩ ላኪዎች ክፍያን በቢትኮይን ለመቀበል ፈቃደኛ መሆን፣ ከውጪ የሚመጣ ካፒታል እና እርዳታም ጭምር በቢትኮይን እየሆነ መምጣት (ለምሳሌ ያህል Save the Childern እና American Red Cross እርዳታ በቢትኮይን ይቀበላሉ) እንዲሁም በአህጉሪቱ ያለው የኤሌክትሪክ ሀይል እጥረት በ mining ሥራ ቢትኮይን የሚገኝበትን እድል ማጥበቡ ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ሥራ አጥነት እና የመግዛት አቅማቸው በየጊዜው የሚቀንስ የአፍሪካ ሀገራት ገንዘቦችም ዜጎች ቢትኮይን በመግዛትና በመሸጥ ገቢ ለማግኘት የሚፈልጉ እንደሆኑና ያገኙትንም ገቢ በቢትኮይን ለማስቀመጥ እንዲመርጡ ምክንያት እንደሆነም ይነገራል። በሌላ በኩል ሲታይ የአፍሪካ የፋይናንስ ዘርፍ የቁጥጥር ደንብ ከጠቀስናቸው አዳዲስ ሥራዎች እኩል ሊራመድ አልቻለም።
1 637
Bitcoin ምንድነው?
በአጭሩ ለኢንርኔት ዓለም የተዘጋጀ እና ከየትኛውም ሀገር መንግሥት ጋር ግንኙነት የሌለው ገንዘብ ነው። ይህ ገንዘብ ሊገኝ የሚችለው እርሱኑ በጥሬ ገንዘብ በመግዛት፣ ለምርት/አገልግሎት በክፍያ መልክ በመቀበል ወይም mine በማድረግ ነው። በዚህ ገንዘብ አማካኝነት የተከናወኑ ልውውጦችን ትክክለኛነት በኮምፒውተር በታገዘ የCryptography ስሌት አማካኝነት የማረጋገጥ ስራ Mining ይባላል። ይህን ሥራ ለሚሰሩ ሰዎች ሲስተሙ አዲስ ቢትኮይን እያተመ ይከፍላቸዋል። አዲስ ቢትኮይኖች የሚታተሙትም በዚህ መንገድ ብቻ ነው።
Mining ለዚሁ ተብለው የተዘጋጁ ልዩ ኮምፒውተሮችን እና ከፍተኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ፍጆታ የሚፈልግ ስራ ሲሆን አፍሪካ ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ይህንን ስራ በመስራት ሲስተሙ የከፈላቸወን ቢትኮይን ወደ ሀገራቸው ጥሬ ገንዘብ እየቀየሩ በማስቀመጥ ስራ ላይ የተሰማሩ በርካታ ድርጅቶች እና ግለሰቦች አሉ። ለሚሸጡት ምርት ወይም አገልግሎት በቢትኮይን የሚፈፀምን ክፍያ የሚቀበሉ በርካታ የምግብ ቤቶች፣ የህግ አገልግሎት ሰጪዎች፣ አምራቾች ... ወዘተ ስላሉም ለነዚህ ነጋዴዎች በቢትኮይን የተቀበሉትን ክፍያ ፕሮሰስ አድርገው ወደ ጥሬ ገንዘብ በመቀየር ወደ ባንክ ሒሳባቸው ገቢ የማድረግ ስራ ብቻ የሚሰሩ ድርጅቶች አሉ። የመጀመሪያው ዲጅታል ገንዘብ በመሆኑ እና በዚሁ ጽሁፍ ለሚነሱ ተዛማጅ ሀሳቦች መነሻ በመሆኑ መረጥነው እንጂ በአሁኑ ጊዜ በዚሁ ጽንሰ ሀሳብ ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጡ ከ 1500 በላይ ዲጂታል ገንዘቦች አሉ።
በኢንተርኔት የሚፈጸም ገቢ እና ወጪ ምን ያህል ያስተማምናል?
ግብይት በሚያያደርጉ ሁለት ወገኖች መካከል መተማመን ሳይኖር ሲቀር የገቢና ወጪ ክፍያዎችን ትክክለኛነት የሚያረጋግጥ ሶስተኛ ወገን ያስፈልጋል።
1 637
🔷Crypto mining እንዴት ይሠራል?
ቢትኮይን እና ሌሎች cryptocurrency ለማግኘት ሶስት ዋና መንገዶች አሉ። እንደ Coinbase, binance ባሉ Exchange platform ላይ ልትገዙዋቸው እና በdefi እንደ ብድር ልታገኟቸው ትችላላችሁ አሁን የምናየው 3ተኛውን መንገድ ነው እንደ ምሳሌ Bitcoinን እንጠቀማለን
ቢትኮይን mining እራሳቹ ለመሞከር ብትፈልጉ በBitcoin የመጀመሪያ አመታት ጥሩ የቤት ኮምፒውተር ያለው ማንኛውም ሰው መሳተፍ ይችል ነበር በ mining ላይ ነገር ግን ኮይኑ እያደገ ሲሄድ ለማቆየት የሚያስፈልገው የ processing ኃይል እየጨመረ መቷል ምክንያቱም ሁሉም ሰው በቀላሉ ማይን ቢያረገው አሁን ያለበት የዋጋ ደረጃ ላይ ባልደረሰ ነበር ባሁን ሰዐት አንድ ቢትኮይን ማይን ለማረግ የሚያስፈልገው የ Computing ሃይል በ2009 የመጀመሪያዎቹ የBitcoin ብሎኮች ከተመረቱበት ጊዜ የበለጠ - በ6 እጥፍ ገደማ ይበልጣል ይህም ላለፉት 15 አመታት በmining ላይ በተመዘገበው ጉልህ እድገት ምክንያት ነው ማይነሮች ወደ ኔቶርኩ ስለተቀላቀሉ በዚ የተነሳ ማይን ለማረግ Super computer ያስፈልጋል ማለት ነው አሁን ላይ
Mining የሚከናወነው በትላልቅ Companies ወይም ሀብቶቻቸውን በአንድ ላይ በሚያሰባስቡ የትሬደሮች ቡድን ነው።
👉Miners ምንድናቸው?
Miners ማለት ሰዎች ናቸው የነሱ ስራ Transaction ሲፈፀም Verify ማድረግ ነው ለምሳሌ ከዋሌታችሁ 1 crypto ለሰው ለመላክ ብትንቀሳቀሱ Miners ዋሌታችሁ ላይ ልትልኩ የፈለጋችሁት crypto መኖሩን ያረጋግጣሉ ከዛም Transactionኑን Verify ያደርጉታል። Transaction Verify እንደሆነ ወዲያው ወደ Blockchain መዝገብ ይገባል። Miners ለሚሰሩት ስራም ሲስተሙ 'ኮይን' ይከፍላቸዋል ይህን የማይኒንግ ስራ ለመስራት መቀዳደም ስለሚኖርና በጣም የተወሳሰቡ ኮዶችን መፍታት ይኖርብናል።
🔹Mining ለምን አስፈላጊ ሆነ?
👉 reward reduction ፡- ከተቀነሰ በኋላ ማይነሮች አ በአንድ ብሎክ በጣም ትንሽ ቢትኮይን ነው ሊያገኙ የሚችሉት
👉 እጥረት መፍጠር የአቅርቦት መቀነስ ዋጋውን ይበልጥ ይጨምራል ልክ እንደምታዩት።
1 637
👉Crypto mining ምንድነው?
Mining ልዩ የኮምፒውተሮች ኔትወርኮች አዲስ Bitcoin የሚያመነጩበት እና (አዲስ ሲባል በማይኒንግ መልክ ሚገኝ እንጂ አሁን ካለው የቢትኮይን ቁጥር ለመጨመር አደለም) አዲስ ግብይቶችን ወይም transaction verified የሚያረጉበት ሂደት ነው።
Mining Bitcoin እና ሌሎች በርካታ cryptocurrency አዳዲስ ኮይኖችን ለማምረት እና አዲስ ግብይቶችን verified ለማረግ የሚጠቀሙበት መንገድ ነው በዓለም ዙሪያ ያሉ ግዙፍ Decentralized የኮምፒዩተር Networks ያካትታል blockchain ን Verified እና ደህንነቱ የተጠበቀ የክሪብቶ ግብይቶችን የሚመዘግቡ ምናባዊ ሂደት ናቸው በኔትወርኩ ላይ ያሉ ኮምፒውተሮች የ processing ኃይላቸውን በማበርከት በምላሹ በአዲስ ኮይኖች ይሸለማሉ Miners blockchainን ደህንነቱን ጠብቀው ከሌሎች cyber ጥቃት ይጠብቃሉ ብሎክቼይንም ለነዚህ ማይነርስ ኮይኖቹን ይሸለማሉ ኮይኖቹ blockchainን እንዲጠብቁ ማበረታቻ ይሰጣሉ ማለት ነው Crypto mining።
1 637
🚨 ከመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ጋር ተያይዞ ኢራን በእስራኤል ላይ የሳይበር ጥቃት መደረጉ ተነገረ
ኢራን በእስራኤል ላይ የDistributed Denial of Service (DDoS) የተባለ የሳይበር ጥቃት እንደፈጸመ ተገልጿል።
በዚህ ጥቃት ከ110 በላይ የእስራኤል ድር ጣቢያዎች ተጎድተዋል፣ በአጠቃላይም 149 የሳይበር ጥቃቶች መመዝገባቸው ተጠቅሷል።
ከእነዚህ ጥቃቶች ውስጥ፦
• 47.8% የDDoS ጥቃቶች
• 11.9% የድር መተግበሪያ ጥቃቶች
• 6.7% ሌሎች የሳይበር ጥቃቶች ናቸው።
ይህ ሁኔታ በክልሉ ያለው ግጭት ከመደበኛ ጦርነት በላይ ወደ ሳይበር ጦርነት እየተስፋፋ መሆኑን ያመለክታል።
1 637
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በ ኢራን ላይ የሚያካሂዱትን ጦርነት ለመገደብ የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ
በUnited States ምክር ቤት ፕሬዝዳንት Donald Trump በIran ላይ የሚወስዱትን ወታደራዊ እርምጃ ለመገደብ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በ53 ተቃውሞ እና 47 ድጋፍ ውድቅ አደረገ።
ዴሞክራቶች ፕሬዚዳንቱ የምክር ቤት ሥልጣን እየተሻሩ ነው ሲሉ ተችተዋል፤ ሪፐብሊካኖች ግን ውሳኔው የተሳሳተ መልዕክት ይላካል ብለው ተቃውመዋል።
1 637
👋 ሰላም ውድ የቻነላችን ቤተሰቦች!
ይህ ቻነል
👉 የእውቀት ምንጭ ነው
👉 የእድገት መንገድ ነው
👉 የገንዘብ እድል መነሻ ነው 💰
ከዚህ ቻነል ምን ታገኛላችሁ?
📚 እውቀት – አስተሳሰባችሁን እና ክህሎታችሁን የሚያሳድግ ጥራት ያለው መረጃ
💡 ክህሎት – በተግባር ሊጠቅማችሁ የሚችል ችሎታ
💰 ገንዘብ – በትክክል ከተጠቀማችሁበት የገቢ እድሎች
ዛሬ የምትማሩት ነገ ገቢ ሊያመጣላችሁ ይችላል። ዛሬ የምታገኙት መረጃ ነገ የሕይወታችሁን አቅጣጫ ሊቀይር ይችላል።ነገር ግን ውጤት ተሳትፎ ይፈልጋል! ✔️ ፖስቶችን በትኩረት ያንብቡ ✔️ የምትማሩትን በተግባር ያውሉ ✔️ ንቁ ተሳትፎ ያድርጉ ሺ ሰዎች አብረው ሲሰሩ ትልቅ ውጤት ይመጣል 🚀 እውቀት + እርምጃ = ገንዘብ 💪💰
ቀጣይ የያዝናቸው አሪፍ የሆኑ ገንዘብ ማግኛ መንገዶች ይዘን አንመጣለን አስከዛ በ reaction አለን በሉን ✌️✌️✌️አብረን እንማር፣ አብረን እንስራ፣ አብረን እንደግ!
1 637
🚨🇺🇸 'ለመነጋገር ተስማምቻለሁ' - ትራምፕ ከኢራን ጋር ድርድር ሊቀጥል እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለዘ አትላንቲክ እንደተናገሩት፣ የኢራን መሪዎች ድርድር ለመቀጠል እየፈለጉ ሲሆን እርሳቸውም ለመነጋገር ተስማምተዋል።
“መነጋገር ይፈልጋሉ፤ እኔም ለመነጋገር ተስማምቻለሁ፤ ስለዚህ አነጋግራቸዋለሁ። ይህንን ቀደም ብለው ማድረግ ነበረባቸው። በጣም ቀላል እና ተግባራዊ የነበረውን ነገር ቀደም ብለው መስጠት ነበረባቸው። በጣም ዘገዩ፣” ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል።ንግግሩ ዛሬ ወይስ ነገ ይካሄዳል ተብለው ሲጠየቁ፣ “ያንን ልነግርህ አልችልም” ሲሉ መልሰዋል። 👉 ትራምፕ ቀደም ሲል፣ በድርድሩ ላይ ተሳትፎ የነበራቸው አንዳንዶቹ የኢራን ባለሥልጣናት አሁን በሕይወት እንደሌሉም ጠቁመዋል። “አብዛኞቹ እነዚያ ሰዎች የሉም፤ አብረናቸው ስንገናኝ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች የሉም፤ ምክንያቱም ያ ትልቅ ትልቅ ድብደባ ነበር፣” ብለዋል፡፡
“ስምምነት ሊያደርጉ ይችሉ ነበር። ቀደም ብለው ማድረግ ነበረባቸው። በጣም ‘ብልጥ’ ለመሆን ሞክረዋል” ሲሉ ፕሬዝዳንቱ አክለዋል። ስፕትኒክ
1 637
Traderoch adis no deposie bonus miset sewoch eyawetubet yale broker ale yilekek eski belike react argu 50 kederese yilekekal
1 637
JUST IN : 🚨🚨🇺🇸 The U.S. Government just transferred 667.6 $BTC(74.79M) to a new wallet.
1 637
JUST IN: $200,000,000 liquidated from the crypto market in the last 4 hours
📉 BTC: 110k$
Уже доступно! Исследование Telegram 2025 — ключевые инсайты года 
