cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ያሲራ(ታጋሽ ሴት)

ለሁሉም ጊዜ አለው... 🙏🙏 ፩) አጫጭር ታሪኮች ፪) ግጥሞች . . .

Больше
Рекламные посты
261
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
+130 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ዋጋ በኤልሳ[FB] ክፍል - 87 ................ ከሀይስኩል ጀምሮ ስትቀልድ እንደዚህ እያለች ነው የምትምለው ይሄስ አጋጣሚ ነው? እንዴት ሊሆን ይችላል? እንዴት ፊዮሪ ልትሆን ትችላለች? እንዴትስ ልትሆን አትችልም? ባንዴ ፈገግታዬ ጠፋ " ምን ሆንክ? " አለችኝ " ምንም... መሀላሽ ያልተለመደ ሆኖብኝ ነው " አልኳት " ሀሀ አዎ በአንድ ብሬ ድርድር ስለማላውቅ ነው " አለችኝ በድጋሚ? ፊዮሪም "በአንድ ብሬ ድርድር የለም" ነበር የምትለው የወረቀቱ አንድ ብር ላይ ያለው ወጣት ቆንጆ ነው ብላ ስታምን ስለምንስቅባት ነበር እንደዛ የምትለው " የምን አንድ ብር ነው ግን ማለት እንዴት እንደዚህ ብለሽ ልትምዪ ቻልሽ? " አልኳት " እንዴ አንተ የምር አመረርክ እንዴ? " ብላ ሳቀችብኝ ፈገግ ብዬ አየኋት የሚያምር በዲምፕሎች የታጀበ ውብ ሳቅ ዲምፕል በ ሰልጀሪ ይሰራል እንዴ? ራሴን ጠየኩት " ይልቅ አሁን ተራው ያንተ ነው " አለችኝ " ጥሩ የተጠየኩትን እመልሳለሁ " አልኳት " ብቻህን ነው የምትኖረው? " አለችኝ " አደለም ከወንድሜ ጋር ነው " አልኳት " ወንድም አለህ? ታድለህ" አለችኝ " አዎ ዮኒ እኮነው ትላንት አብረን ያመሸነው " አልኳት " ኦ... ጓደኛህ መስሎኝ ነበር " አለች " አዎ ጓደኛዬም ወንድሜም ብቻ ምድር ላይ ያለኝ ብቸኛ ዘመዴ ቤተሰቤ ነው " " ደሲላል... ታድለህ.. አትከዳም " አለችኝ " እንዴት " አልኳት " እኔ ምንም የሴት ጓደኛ የለኝም በማይገባኝ ይከዱኛል መጥፎ ይሆኑብኛል " አለች " አብሮ አደጌ ያልሻትስ? " አልኳት " ከሷ ጋር ብቻ ነው የምንግባባው ግን አሁን ተራርቀናል እሷም ልጇን ልጇን ስትል እኔም ጠቅልዬ እዚህ ስመጣ ተረሳሳን " አለችኝ " አይዞን አሁን ደግሞ እኛ አለን " አልኳት " አመሰግናለሁ የምር አንተም ቀና ሰው ነህ " አለችኝ " ምን አደረኩ? " አልኳት " ባሁን ጊዜ እኮ እንዳንተ አይነት ባለሀብቶች ለሰዎች ጊዜ ሰጥተው እንደዚህ ከሰዎች ጋር አያወሩም " አለችኝ ረጅም ሰአት ዝምታ በመካከላችን ሰፈነ " ታውቃለህ? ልጅ እያለሁ አስመራ ነበር የተማርኩት ከ 1 እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ..... " ከልጅነቷ ጀምሮ የነበራትን ህይወት ዝክዝክ አድርጋ ስታወራኝ መሽቶ ተለያየን የአስመራ ልጅ መሆኗም ከፊዮሪና ጋር ያመሳስላቸዋል ታሪካቸው ግን ፍፁም አይገናኝም ስታወራ ከወሬዋ ይልቅ ስሰማ የነበረው ድምፀቷን ነበር ፊዮሪ ስታወራኝ የዋለች እስኪመስለኝ ድረስ ደስታዬን መቆጣጠር እያቃተኝ ነበር የሰማኋት ቤት ስገባ ዮኒ ሶፋ ላይ እግሩን ዘርግቶ ተኝቶ የሆነ የቢሮ ፋይል እያነበበ ነው " ሰላም ሰላም " አልኩት ቀና ብሎ ተቀመጠ " ኧኸ አንበሳዬ... ቢሮ ዘግተህልኝ ዋልክ? " አለኝ " መተህ ነበር እንዴ? " አለኝ " አዎ ሴክሬታሪህን አጊንቻት ከ ሲፈን ጋር ምሳ ሰአት ወጡ አለችኝ " አለ " አዎ ቤቷ ነበር ያመሸነው " አልኩት ቀና ብሎ በሹፈት አስተያየት አየኝ " ሳምኳት እኮ " አልኩት ከተኛበት ፍንጥር ብሎ ተነስቶ ተቀምጦ ቀና ብሎ እያየኝ " የምርህን ነው? " አለኝ ቅንድቤን ከፍ አድርጌ የሹፈት ሳቅ ሳኩበት " ዱሮስ ካንተ ቁም ነገር መጠበቄ... እግሬን አስበረድከኝ " ብሎ እግሩን አውጥቶ መልሶ ተኛ "ቆይ አዎ ብልህ ልታምነኝ ነበር እንዴ? " አልኩት " ለምንድነው የማላምንህ ? ከድምጿ ፍቅር እንደያዘህ ነግረኸኛል ድምፅ ደሞ በአፍ ነው የሚወጣው "አለ " እና? " አልኩት " ድምጿን መሳም ፈልገህ ካደረከው ብዬ ነዋ " አለኝ " ያምሀል እንዴ? " አልኩት " ምን ያመኛል እኔማ አያመኝም እንደውም ራስህ ነህ እንጂ የሚያምህ ለምን ግን ፀበል አትሞክርም ወይ ደግሞ መንን... በቃ መንን ልደትዬን አምስት አመት አለፈህ እኮ ከዚህ ቦሀላ ሰይጣን ራሱ ኮ ፊዮሪን መስሎ ካልመጣ አያሳስትህም.. ወይ ከነፍስህ ሁን " አለኝ የንዴት አነጋገሩ ሳቄን የመቆጣጠር እድል አልሰጠኝም እሱ ሲናደድ እኔ ከት ብዬ እየሳኩ ነበር ስስቅ ደግሞ ባሰበት መጨረሻ ላይ " ባክህ ዝምብለህ አታግጥ " ብሎኝ ተነስቶ ለራሱ ብቻ መጠጥ ቀዳ " ለኔስ " አልኩት " መቼ እራት በላህ " አለኝ " በልቻለሁ " አልኩት " እንኳን በላህ " አለኝ " እና ልጠጣአ " አልኩት " ቅዳና ጠጣአ ማን ከለከለህ ? " አለኝ ሳቄ እየመጣ ተነስቼ ብርጭቆ ይዤ መጥቼ ቀዳሁ ለምን እንደሆነ አላውቅም ዮኒ እንደዚህ ሲናደድና ሲያኮርፍ እኔን ከጀርባዬ የሚኮረኩረኝ ሀይል ያለ ይመስለኛል ዝምብሎ ሳቅ ሳቅ ይለኛል " ይልቅ የተዘረጋው ለምቦጭህን ሰብስበውና የሆነውን ልንገርህ " አልኩት አሁንም እንዳኮረፈኝ ነው " ሲፈን የምትኖረው የበፊቱ የፊዮሪ ቤት ውስጥ ነው " አልኩት " ምን? " አለኝ ከኔ በላይ ያስደነገጠው ይመስላል.... ኩርፊያውንም ረስቶት " የምርህን ነው? " አለኝ " አዎ......... " የሆነውን ሁሉ ታሪኳን ሳላስቀር ነገርኩት " እንዳትጠራጠር ወንድሜ ራሷ ፊዮሪና ናት" አለኝ " ለምን በአንድ ነገር አናረጋግጥም? " አልኩት " በምን?" አለኝ " ንቅሳት ፊዩ ጀርባ ላይ እኮ የኔ ስም ንቅሳት አለ "............... ይ...ቀ...ጥ...ላ...ል.... @yoakinnn
Показать все...
🥰 3👍 1
ዋጋ በኤልሳ[FB] ክፍል - 86 ...... ይሄም አጋጣሚ ይሆን? " ይሄን ይመስላል እንግዲህ " አለችኝ ወደ ነበርንበት ሶፋ እየተመለስን " ቆንጆ ቤት ነው " አልኳት ከፊቷ ከችኩልና ከተጫዋችነቷ የተረዳሁት የዋህነት ልቤን አስደነገጠው ግን ደግሞ ራሴን " አስታውስ ካወካት 3 ቀን እንኳን አልሞላህም " አልኩት " እና መቼም ይሄን የሚያክል ቤት ይዞ ለብቻ መኖር ይከብዳል " አልኳት " መልመድ ነው እንግዲህ እዛስ ብቻዬን አልነበርኩ? " አለችኝ " ቤተሰብ የለሽም እዚህ? " አልኳት " አንድ አባት ብቻ አለኝ " አለች " ዱሮስ ስንት አባት ሊኖርሽ ነበር? " አልኳት ፈገግ ብዬ " ማለት የቀረኝ ብቸኛ ዘመድም ቤተሰብም አባቴ ነው... ሳሪስ ነው የሚኖረው በፊት የሚኖርበት ከናቴ ጋር የተጋቡበት ቤት ከቤቱ ምን እንዳለው አላውቅም ሌላ ቤት ልግዛልህ እምቢ!.. እሺ አብረን እንኑር እምቢ!... እሺ ላሳድስልህ እምቢ!.. ከነትዝታዬ ልሙት የሚለው ነገር አለ" አለችኝ ... አባቷን በዚች ምድር ከኔ በላይ የሚረዳቸው ያለም አልመስል አለኝ አጊንቼ ትዝታቸውን ተጋርቼ ትዝታዬን ባጋራቸው ብዬ ተመኘሁ " ካልሆነ ማግባት ነዋ " አልኳት " ኸ ሰርግ? " አለች " አዎዋ መቼም ያለሰርግ አታገቢ " አልኳት ተነስታ አዲስ ወይን ከነመክፈቻው አምጥታ ሰጥታች ተመልሳ ሄዳ ብርጭቆ ይዛ እስክትመጣ ወይኑን ከፍቼ ጠበኳት ለሁለታችንም ከቀዳች ቦሀላ ብርጭቆውን ሰጥታኝ የራሷንም ይዛ ተቀመጠች "እ...ሺ ሰርግ ላይ ነበርን " አልኳት " ጨዋታ እንቀይር " አለች ወዲያው ተነስታ ወይን የቀዳችው ጨዋታ ለማስቀየር መሆኑ ገባኝ ግን ደግሞ ብዙ ጊዜ ጥያቄዎችን የሚሸሹ ሰዎች ከጀርባቸው ልባቸውን የሰበረ እውነት የያዙ ናቸው የሚል ነገር አንብቢያለሁ ወይም ሰምቻለሁ ይበልጥ ለመስማት ጓጓሁ " ለምን? " አልኳት " በቃ ማስታወስ የማልፈልገውን ነገር ያስታውሰኛል... ይልቅ አንተስ ብቻህን ነው የምትኖረው? " አለችኝ "ኖ ኖ ኖ.. ስለኔ በደምብ በሰፊው እነግርሻለሁ አሁን ግን ስላንቺ ብቻ እናውራ " አልኳት ዝም ብላኝ ቆየች.. አይን አይኗን እያየሁ በትግስት ጠበኳት " ስለ ሰርግ ማውራትም ማሰብም አልፈልግም " አለችኝ " እኮ ለምን? " አልኳት " ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ ላገባ ነበር " አለችኝ " እና ምን ተፈጠረ? " አልኳት " ሁለቱም ሳይሳካ ቀረ የመጀመሪያው የሽምግልናው ቀን ቀረ ሁለተኛው ደግሞ ሽምግልናው አልፎ የሰርጉ ቀን... አባቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ግፊት የያዘው የመጀመሪያው ሽምግልና ቀን ነበር.. በሁለተኛው የሰርጉ ቀን ሲቀር ግን ራሱን ስቶ ወደቀ ከዛ ቦሀላ ለረጅም ጊዜ መንቀሳቀስ አይችልም ነበር.. ውጪ ድረስ ሄዶ ታክሞ እንኳን እንደበፊቱ አይደለም ቢያንስ ግን በክራንችም በሰውም ተደግፎ ይራመዳል " አለችኝ "ኦ.. ያሳዝናል " አልኳት " ከዛ ቦሀላ ትዳር እና ሰርግ ስለሚባል ነገር ማሰብ ይከብደኛል ለማግባት መሞከር ማለት የአባቴን ነፍስ አሲዤ እንደመቆመር ነው ለኔ ከዚህ ቦሀላ እንደዛ አይነት ነገር ቢፈጠር አባቴ ይሞትብኛል " አለችኝ ዝም ተባብለን ቆየን " የቀረ ጥያቄ አለ? " አለችኝ " በጣም ብዙ " አልኳት " ጥሩ ቀጥል " አለችኝ ከፈገግታ ጋር ወይኗን እየተጎነጨች " በምን ምክንያት ከዱሽ? " አልኳት ብርጭቆዋን አስቀምጣ በረጅሙ ተነፈሰች " የመጀመሪያው ውጪ መውጣት በሚል ሰበብ ነው የሚገርምህ አግብቶ የወጣው እኮ የገዛ ጓደኛዬን ነው ያውም የቅርብ ለሚዜነት ሳዘጋጃት የነበረች... ሁለተኛው ምንም አላለኝም ዝም ብሎ ቀረ ቀረ... ቦሀላ ቆይቼ ከብዙ ጊዜ ቦሀላ ካፌ ውስጥ ባጋጣሚ አገኘሁት ምንም አላልኩትም ምክንያቱን ጠየኩት የተጣላችውና ከልጅነቱ ጀምሮ የሚያፈቅራት ሴት ይቅርታ ስላደረገችለት ነበር ሰርጉን በሰርጉ ቀን የተወው እና ከበፊት ፍቅረኛው እንደተጋቡና እንደወለዱ ጭምር ነገረኝ " አለችኝ " ይገርማል.. ማለት እንደዚህ የተደረጉ የማውቃቸው ሰዎች ወይ በቀለኛ ሆነው ሰዎችን ወይም ሴት ከሆንሽ ወንዶችን ይበቀላሉ ወይም ሰዎችን በፍፁም አይቀርቡም.. አንቺ ግን ደስተኛ ሳቂታ ተግባቢና የዋህ ነሽ በጣም ባላውቅሽም በነዚህ ሁለት ቀናት ውስጥ ካየሁት" አልኳት " በቀል የፈጣሪ ነው... ምናልባትም በነሱ ቦታ ብሆን እኔም የማደርገውን ነገር ይሆናል ያደረጉት... መፍረድ አልፈልግም ግን ራሴን ለራሴም ለአባቴም ስል ማራቅ ካለብኝ ነገሮች አርቃለሁ " ብላ በትካዜ ስራችን ያለውን ጠረጴዛ ማየት ጀመረች " አይዞን!... ግን አባትሽስ ብቻቸውን በዛ ሁኔታ ብቻቸውን አይከብዳቸውም? " አልኳት " ብቻውን አይደለሞ ሁለት ሞግዚቶች አሉት እኔም ቢያንስ በሳምንት ከ4ቴ በላይ አየዋለሁ " አለችኝ " አባትሽስ ስለ ሰርግ ምን አይነት አመለካከት አላቸው ? " አልኳት " እሱማ ያው ነው... አሁንም አግቢ.. አግቢ ነው ጭቅጭቁ " አለች "ምክር ላይ ጎበዝ አደለሁም ግን ለራስሽ እድል ብትሰጪና የምትተማመኚበትን አይነት ወንድ ብትፈልጊ አይጠፋም " አልኳት " ከዛ ቦሀላ ትዳርም ፍቅርም ወንድም ስለሚባል ነገር አስቤ አላውቅም ስራ ስራዬን ሳሳድድ ይሄው ሳላስበው የወጣልኝ ቢዝነስ ማን ሆንኩ " አለች " ደሲላል መቼም ካገባሽ በባልሽም ቢሆን እኔን ነው ስር ሚዜ የምታስደርጊኝ " አልኳት " ሀሀሀ ልክ ጓደኛዬ እንዳለችኝ.... ይገርምሀል ቺካጎ እያለሁ የልጅነት አብሮአደጌን አጊንቻት አብረን ብዙ ጊዜ አሳልፈን ነበር እና እሷም ካገባሽ ስር ሚዜ ልታደርጊኝ ቃል ግቢልኝ ብላ ቃል አስገብታኝ ነው የመጣሁት " አለችኝ ስለውጪ ስታነሳ ጓደኛዋ ፊዮሪ ብትሆንና ብታገናኘን ብዬ ተመኘሁ ባዶ ቅዠት የተምታታ ሀሳብ እሷም ፊዮሪ ብትሆን ብዬ እያሰብኩ ነው ስለ ውሸቱ ምንም አልቀየማትም ነበር " ግን አንተ እንኳን ሙሽራነት ነው የሚያምርብህ እንጂ ለሚዜ አትሆንም" አለችኝ " ለምን? " አልኳት " ኧኸ ሙሽራውን ታስንቀዋለሀ " ብላ ሳቀች " አትይኝም " አልኳት ሳቋ እየተጋባብኝ " አልኩህ አልኩህ " አለች " እስኪ ማይ " ብዬ እጄን ዘረጋሁላት " አንድ ብሬን ይንሳኝ! " ብላ እጄን መታች ውሀ ተቸልሶበት ከእንቅልፉ እንደተቀሰቀሰ ሰው ቀልቤ ተገፈፈ ይሄ የፊዮሪ ብቸኛው መሀላ ነው... ከሀይስኩል ጀምሮ ስትቀልድ እንደዚህ እያለች ነው የምትምለው.. ............. ይ..ቀ..ጥ..ላ..ል...... @yoakinnn
Показать все...
👍 3🤗 1
አንዳንድ ሰዎች ዝም ስትላቸው እነሱ ብቻ ትክክል የሆኑ ይመስላቸዋል ግን አይደለም👐🏾 እኔ በዝምታየ አስተሳሰብህ ምን ያህል ትንሽ እንደሆነ እየነገርኩህ ነው። ማውራትህን ቀጥል። ዝም ማለቴን ቀጥላለው።
Показать все...
🥰 3🤝 1
😍 ቤተሰቦቼ አንድ መልካም ሀሳብ ይዤ መጥቻለው የስነፅሁፍ ችሎታ ያላችሁ @myholehearttt ቤተሰቦቼ ግጥም ፣ አጭር ወይ ረጅም የtg ልቦለዶች፣ እንዲሁም ወግ ያላችሁ በውስጥ አውሩኝ አብረን እንሰራለን። ሌሎች ቤተሰቦች ደሞ እስካሁን ለነበሩት ስራዎችና ለወደፊቶቹም ሀሳብ አስታየታቹን ማጋራት እንዳትረሱ 👍እወዳቹሀለው።😘😊
Показать все...
😏😏😏 አይታወቅ ብለህ የወንድ ብራንባሩ ቆንጆ ገላን መርጠህ ስትቀብጥ ከአስሩ አካሏ ካማረህ የሳበህን ሁሉ በመሸታ ቦታ ቤርጎ ስትዋልሉ ከርመህ ከርመህ ከርመህ በዝቅጠት ጎዳና ዛሬ ብታስተውል የህይወትክን ኦና በሚስት ልታደምቅ ጎዶሎን ልትሞላ ጠንስሰህ ወስነህ ልታገባ ቆርጠህ መስፈርት ደርድረህ ብዙ እንስት መርጠህ ከብዙሀን ቆንጆ የኔ ሴት መግለጫ ክብሯን የጠበቀች ናት የኔ ምርጫ ትሁንልኝ ስትል ጨዋ አንገት ደፊ ሚገባህ ብትደርስህ ቢጤህን ቀጣፊ ለምን? ብለህ አትሞግት ሮሮ አታብዛ ያቺ የተመኘኻት ያጣሀት ያኔ ነው ስትዘል እንደዋዛ የማንነት ስበት ሌላውን ሲጠራ ከመሰሉ እንጂ ከሌላ አያመራ ጥሩ ከጥሩ ነው ክፉውም ከክፉ ዘላልና ጨዋም ርቀው ተላለፉ ለአህያም ነውር ነው ማርን ማቀራረብ ድርሻ ደረጃህን ፋንድያህን ክበብ ይልቅ ምክር ቢጤ ልለግስህ ስማ የእድልህን አጥብቅ ምሬት አታሰማ ያለፈው ቢጠፋ ነገ ይፃፋልና ካለፈው ተምረህ ቀሪን ጊዜ አቅና ✍️ የተክልዬዋ @semetenbegtm @semetenbegtm @semetenbegtm
Показать все...
👍 1 1
ቀለበት እንዲያስር ጣቷን ለገሰችው ያገባኛል በሚል ክብሯን ገለጠችው ተገልጦ ቢያገኘው ያን ስውር ገላዋን የገዛት ይመስል ይፈርዳል ዕጣዋን ዛሬ ነገ እያለ ሲያሻው እየከዳ ታምኖ የተገኘን ልብ ያረጋል ባለዕዳ ተጎጂው አማኙ ሁሉን የገለጠ ያሉትን በማመን የተረጋገጠ በቃላት ጨዋታ ሁሉን አሳልፎ ብቻውን የሚቀር ህመም ተደግፎ
Показать все...
3
ሂድ🥺 ሂድ እንዳሻህ ሁን እኔ ልፍቀድልህ አካሌ ሁን ብዬ በግድ አላስቀርህ ፍቀደኝ ልፍቀድህ በሚል መሠረት ነዉ የፍቅር ማገሩ ምሰሶ ሚቆመው ልቤን ስከፍትልህ ፍቅርን በመለገስ በድክመትህ ስገኝ ለህልሜ ስትደርስ 🚶‍♂ሂድ እንዳሻህ ሁንባይሆንም ከልቤ ❤️ፍቅር ውዴታ ነው በግዴታ እሾህ አላጥርህ ከብቤ🤷‍♀ 🥹የእንባ ሣቅ ስቄ      👋🙌 ልሸኝህ አርቄ በል እንግዲ ዉዴ የሀሣብ ዘመዴ በሄድክበት ቦታ ባረፍክበት መንደር ፍቅርን ምትቀበል መዋደድን ምትችር ይስጥህ ይለግስህ የፍቅሩ እግዜር
Показать все...
ሆይ ሆይ... ቅድም አዲስ የተከፈተው "አዶ ቡና" ቁጭ ብዬ (የሚገኘው ጎፋ ገብርኤል አደባባዩ ጋር ፤ ባላንስ ህንፃ በፓርኪንጉ ሥፍራ ነው። ማስታወቂያ አይደለም።) እና የንዋይን ዘፈን እየሰማኹ ነበር።አንዱ የግጥም ስንኝ ቀልቤን ሳበውና ደጋግሜ አሰብኹት... "ንብ ሆኜ መጥቼ እንዳይሽ ፈገግ ብሎ ይቆየኝ ጥርስሽ ።" ምን አሰብክ አትሉኝም? ቆይ ነገሩን ከስር ዠምሬ ልንገራችኹ። Teenage እያለኹ ዝም ብሎ ነበር "ፍቅር" የሚይዘኝ i mean sight love. ትክክለኛው ፍቅር ነው ወይ? የሚለው ሌላ ጥናት ይፈልጋል።(እኔ ጉንፋን ይመስል ቶሎ ቶሎ ነበር የሚይዘኝ...) እኛ ሰፈር ያሉትን አብዛኛዎቹን ቆንጆ ሴቶች ተራ በተራ አፍቅሬያቸዋለኹ። እንዴት ? እሱ ለእኔም ጥያቄ ነው ። ማለት እኔ ሲደብረኝ "አሁን ደግሞ ማንን ላፍቅር ?" እያልኹ ነበር የማስበው።ከዛም በዛ ሰሞን ነጋዴ የገበያ ጥናት እንደሚያደርገው ፤ አካባቢዬን አጠናና በወቅቱ የፍቅር ገበያ ልቤ ያተርፍበታል ብዬ የማስባትን ላፈቅር እወስናለኹ። "ፍቅር" ነው የሚለው በትምህርተ ጥቅስ እንደ ተቀመጠ ሆኖ ማለት ነው። እናላችኹ አፍቅሬ አፍቅሬ አስራ ሰባተኛዋ ላይ ደረስኹ።( አያችሁልኝ ? እንዴት ያለኹ ስራ ፈት ብሆን ነው ጎ'በዝ?) የሚገርመው ነገር አንዳቸውንም አናግሬ አለማወቄ ነው።በቃ ሰፈር ውስጥ ፈፅሞ ከሴት ጋር የማልቀራረበው ልጅ ነኝ። አስራ ሰባተኛዋ የቤት ልጅ ናት።ጠዋት አባቷ ነው በመኪና ትምህርት ቤት የሚወስዳት ስትመለስም እርሱ የሚያመጣት ይመስለኛል።(ስትመለስ አጋጥሞኝ አያውቅም።) እና የት አይተህ ነው የወደድካት አትሉኝም? የሆነ ፀዴ ድግስ ነበር ቤታቸው አስታውሳለኹ የቅዱስ ሚካኤል ዝክር ልበላ ድንኳን ሰብሬ ገብቼ ተበላኹ ነው የምላችኹ።ሳያት አልቻልኹም እዛው ላፈቅራት ወሰንኹ። ውብ ናት ! ውብ ናት ! ብዬ እንደታምራት ደስታ በልቤ ጮኹ። ከዛም በኋላ አንድ ሁለት ቀን ሱቅ ከሰራተኛቸው ጋር ስትመጣ አየኋት...እኔ ሱቁ ጋር ካሉ ጎረምሶች ጋር ነበር ድድ የማሰጣው ።(ስራ ፈትነቴን እኮ ተንከባክቤ ነው ያሳደግኹት...ሌላ አለም ላይ በእዛ እድሜ ስንት ስራ ይሰራሉ እኔ እቴ...) እናም አስራ ሰባተኛዋን ሌላ በምንም አጋጣሚ ላያት አልችልም።"ፍቅሯ" ፀናብኝ ።ፍቅር ህመም ነው ይላሉ እኔም እንደዛ ይመስለኛል። ናፍቆ አለማያት ህመም ነው ፤ ፈልጎ አለማግኘት ስቃይ ነው ። እስከመፈጠሬ የማታውቀኝን ልጅ ማየት ለእኔ ልዩ የህይወት ትርጉም ይሰጠኝ ነበር። እና ነዋይ ደበበ በዘፈኑ "ንብ ሆኜ መጥቼ እንዳይሽ..." ሲል... እኔም የሆነ ተሳቢ እንስሳም ቢሆን ሆኜ...ወይም የምበር ትንሽ ፍጥረት ሆኜ...ጊቢያቸው ገብቼ ልጅቷን አይቼ የአይኔን ርሀብ ባስታገስኹ እያልኹ እመኝ እንደነበር አስታወሰኝ። ሆይ ሆይ በሉ ሌላ ሳላወራ ሰላም እደሩ። ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ
Показать все...
👍 1
(ተዋት ትገላለጥ) ትገላለጣለች ወግ አጣች ይሉኛል ገሃድ ትውላለች ፣ ትደበቅ ይሉኛል ስታለች እያሉ እንዲያ ያወጉኛል የሳቱስ እነርሱ ወግ ያጡስ እነርሱ (እኔ ግን መልሴ) ተገላለጪ ዋይ ገሃድ፣ ሁሉም ሰው ቢያወራው ተሸፋፍኖ አይደል፣  ተደብቆ አይደል በደል የሚሰራው ተገላልጦ እንዴት ገሃድ ውሎ እንዴት በሃሜት ተጠምዶ፣ በሰው አፍ ይገባል ተገላለጪ እስከላይ፣ የተደበቀ ሰው መች ቅን ያስባል? ተደብቀው አይደል ፣ ዳቦ የሚልሱት ተሸፋፍነው አይደል፣ ካጋራቸው' ጀርባ ትዳር ሚቀልሱት እርስ በርስ ሲያፋጁም ጦርነት ሲያውጁም ሲነዱን በየረድፍ ተደብቀው አይደል መቺ ገሃድ ይሰራል ክፋትና በደል (እኔ የምልሽ) አትሸፋፈኝ ፣ ገሃድ ዋይ ተገላለጪ ግን ደግሞ አደራ ከቤት እንዳትወጪ እንግዳዬሁ ዘሪቱ(የጠፋው ልጅ)
Показать все...
ዘወር ብላችሁ አልቅሳችሁ ታውቃላችሁ ...ወይ ደግሞ ለሊት ተነስታችሁ በእንባ ታጥባችሁ ...ሲቃችሁን ሰው እንዳይሰማው አፋችሁን በእጃችሁ አፍናችሁ ስትንሰቀሰቁ ያደራችሁ....ነግቶ ለጠየቃችሁ እንዲሁ አይኔን አሞኛል ምን እንደሆነ እንጃ ብላችሁ ላለቀሰው አይናችሁ ሰበብ የደረደራችሁ...ብሶተኛ ላለመባል በሆነው ባልሆነው የገለፈጣችሁ.... የፊታችሁ እና የሰውነታችሁ ከለር አራምባና ቆቦ ሆኖ መጎሳቆላችሁን ያሳበቀባችሁ የላችሁም....ልብሳችሁ እስኪሰፋችሁ ድረስ ከስታችሁ መክሳቱን ፈልጌው ነው ብላችሁ የዋሻችሁም...አልያም "ስጋ ለበሬ ነው...እንደ እኔ አትሸናቀጡና..."....የሚል  ውስጠ ወይራው ብሶት የሆነ ቀልድ ቀልዳችሁ ለብቻችሁ የሳቃችሁም ትኖራላችሁ...ዘመድ እንደ ሰውነት የሆነባችሁስ...ሲኖራችሁ የሚቀርብ ስታጡ ደግሞ የሚርቅ....መቼ ነው አልፎልኝ እኔም እንደ ሰዎቹ, "ሂሳብ እኔ ነኝ የምዘጋው...."...ብዬ ምከራከረው ብላችሁ የምትተክዙ....ማጣት...መንጣት የአማርኛ ፊልም ላይ እንደሚታየው  ኮሜዲ እንዳልሆነ የምታውቁ..ለተራበው ሆዳችሁ ስትሉ ውሻ የሆናችሁ.... ተስፋ ያደረጋችሁት ጉም የሆነባችሁ...እኮ እናንተ እንዲህ ሆንኩ ብላችሁ ማስረዳት የሰለቻችሁ...ልባችሁ የሰለለባችሁ...."ለበጎ ነው"..የሚለው ቃል ተራ ዲስኩር የመሰላችሁ..."ደህና ነህ"...ለሚለው ጥያቄ እንዲሁ ስለሚባል ብቻ "ደህና ነኝ" የምትሉ....የደከመው ልባችሁ ደልዳላውን መሬት የተራራን ያህል አግዝፎ ላሳያችሁ ...ለዶፍ ዝናብ የማትበገሩ የነበራችሁና አሁን ካፊያ ድንኳን ለሚያስደኩናችሁ እናንተ.... ማን ያውቃል ገና አፍ ላልፈቱ ልጆቻችሁ  ስትሉ ክብራችሁን የዘነጋችሁም ትኖራላችሁ...እኔስ መቼ ነው "ተደላደለልኝ ህይወቴ.."..ብዬ የምዘምረው ብላችሁ የሰው ደስታ አጃቢ ብቻ ሆናችሁ የቀራችሁ ለመሰላችሁ እናንተ...በሰው ደስታ ግርግር መሀል  ፊታችሁ መጨለሙን የምታስተውሉት "ምነው ፊትህን ጣልከው..."...በሚል የተመልካች ጥሪ የሆነ...ምቀኝነት እንዳችመስልብኝ ብላችሁ በደረቅ ሳቅ መከፋታችሁን የምትደብቁ ....ቁጭ ብላችሁ ለሚነጋባችሁ...እንቅልፍ እንኳን የሸሻችሁ እናንተ.... አይዞአችሁ ትዕግስታችሁ ፍሬ ያፈራል...ከልባችሁ የምትስቁበት ጊዜ ይመጣል...ወዴትም መሄድ አይሻልም...ፈተናው ፀና ብላችሁ ካልተጠራችሁበት አትሂዱ...የሰርግ ድንኳን ሰባሪ የቤተሰብ ፎቶ ላይ ሲገባ አይታችሁ ታውቃላችሁ....?...ያልተጠራችሁበት ለምን ትሄዳላችሁ...አይዟችሁ ይሄ የመጨረሻ ትግላችሁ ይሆናል....ይሄን ሩጫ ለየት የሚያደርገው አበረታች መድሀኒት ብትጠቀሙ የማትከለከሉበት መሆኑ ነው...አበረታች መድሀኒቱ ፀሎት ይባላል...dose በጨመራችሁ ቁጥር ሩጫችሁ እያጠረ ይመጣል😊 የትም አትሂዱ...ፈተናውን ያሳለፋችሁ ፈጣሪ ለሽልማት በመጣ ጊዜ በድናችሁን አያግኘው...አሸነፋችሁ እኮ ኧረ ተሸለሙ😊 በርቱ...ተሸለሙ። የምትሸለሙበት ቀን ይሁንላችሁ😊 ✍Shewit dorka https://t.me/shewitdorka
Показать все...
ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

ለአስተያየታችሁ @Shedorka

🙏 1
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.