189
Подписчики
Нет данных24 часа
-57 дней
-1030 дней
- Подписчики
- Просмотры постов
- ER - коэффициент вовлеченности
Загрузка данных...
Прирост подписчиков
Загрузка данных...
┈┈••◉❖◉●••┈
👨🌾 ተወዳጁ🌺
❣ :¨·....................:¨·.❣
♥️ ክፍል ሃያ
ኤልሳ ልትወጣ ስትል ሄኖክ እጇን ያዝ አድርጎ ምንድነው አላት ኤልሳም እየተርበተበተች ባሌ ነው ድምፁ አስፈርቶኛል ምናልባት የሰማው ነገር ይኖራል አለችና ልጇን ና አባይዬ ብላ እጁን ይዛው ወጣች ... ሄኖክም ሁኔታዋ ስላስፈራው ከኋላ ተከተላት እውነትም
ባልዋ ውጪ ላይ ይጠብቃት ነበር ገና ሲያያት ከመኪናው ወርዶ እየቀረባት ... አንቺ የድሃ ልጅ እድፍሽን ባጠራልሽ ደሞ ጎረምሳ አማረሽ አለ በሀይለ ቃል እሷም እንዳቀረቀረች አይ አጋጣሚ ነው አለች ፍርሃት በወረረው አንደበት ዝም በይ አለና ያ የሚያሳሳ ጉንጯን በጥፊ አቀላው ቀጥሎም ስሚ ሰው ያገኩሽ እኔ ነኝ
አትሸውጅኝ ይሄን ጋጠ ወጥ የማላውቀው ይመስልሻል? አለና ወደ
መኪናው ገፈተራት ... በራሴ መኪና እመጣለሁ ስትለው መልስም
ሳይሰጣት የራሱ መኪና ውስጥ አስገባት... ሄኖክ ሁኔታቸውን ሲከታተል ትግስቱ ተፈታትኖታል ግን መታገስ ስለነበረበት ዝም አለ ... የሱ የሆኑ ሰዎች ሁሌም ተፈታኝ ናቸው በዚም እድለቢስ እንደሆነ ይሰማዋል... ኤልሳ መኪና ውስጥ ገብታ ከመቀመጧ ንዴቱ ያልበረደለት ባሏ አንቺን ያገባሁ ቀን
ምናለ ቢደፋኝ አለ ይሄኔ የኤልሳም ትግስት አልቆ ኖሮ... ታድያ ለምን አፈታኝም ...እ... ምን ያዘህ አለችና መኪናውን ከፍታ ስትወርድ ቀድሟት ወርዶ እገልሻለው አንቺንም አባትሽንም ልቹቸን ነው የማስገባቹ አለ ይሄኔ ሰብለ ቀዝቀዝ አለች ለአባቷ ስትል ምንም መሆን እንዳለባት አስታወሰች .... ሄኖክ ግን አላስቻለውም ወደመኪናው በመቅረብ አንተ ማን የሚሉህ ገዳይ ነህ ባክህ እስቲ ይብቃህ... እድሜ ልክህን በቁም የገደልከን ይብቃህ አለው ሰውየውም በንዴት ጦፎ አንተ ወጠጤ ማንነቴን አታውቅም አለና ሄኖክን በቦክስ መታው ይሄኔ ግን ስብለ ትግስቷ ተሟጦ እየሮጠች ወደ ሄኖክ በመሄድ በቃህ ከዚ ቡሃላ የኔና ያንተ ጉዳይ አብቅቷል ዳግም ጫፉን እንዳትነካው እኔ የበደልኩት ይብቃ ብላ ከሄኖክ ጎን ቆመች ባሏም እሺ ዋጋ ትከፍይበታለሽ ሲል ዝቶ መኪናውን አስነስቶ ሄደ... በቆሙበት ጥቂት ከቆዩ በኋላ ኤልሳ ዋ...ይ ብላ ጮኸች ለካ ልጇን ይዞባት ሄዷል ሄኖክም እሷን ለማረጋጋት ጥረት እያረገ አይዞሽ የኔ ፍቅር ልጃችንን ይመልሳል አለና ወደቤት ይዟት ገባ... ሁለቱም በዝምታ ተዋጡ የማይተዋወቁ ይመስል የሚነጋገሩበት ርእስ አጡ ይሄኔ ነበር የኤልሳ የስልክ ጥሪ ዝምታውን ያደፈረሰው ... ስልኩን አውጥታ ስታየው አባቷ ናቸው ስልኩን አንስታ ገና ምንም ሳትል እንባዋ ይወርድ ጀመር ሄኖክም የደወለውን ሰው ለማወቅ እንደጓጓ አተኩሮ ይመለከታት ነበር ... አባቷ በታፈነ
ድምፅ ልጄ ሊገለኝ ነው አሏት ምን አባዬ ብላወጥታ ስትሮጥ ምንድን ነው ኤልሳ ብሎ ሄኖክም ይከተላት ጀመር......
◎◎◉◉ ተወዳጁ የፍቅር ታሪክ ሊፈፀም አንድ ክፍል ብቻ ቀረው💔
ꜰᴇʟʟɪɴɢꜱ🥀
❤ 2
ያይኔ አበባ መታለጭ ሰበር ሰካ እያለች
ያጥቢያ ኮከብ ነሽ ወይ አንቺ የንጋት ጸሀይ
ያይኔ አበባ አንቺም ለኔ ሆነሽ እኔም ላንቺ ሆኜ
ከዚህ በላይ አለም ደስታስ ምን ተገኘ
ምን ተፈለገና ልቤ ብዙ ያስባል
ጥንትም በመውደድሽ ባንቺ ፍቅር ሰክኗል
አንኳንስ አኩርፈሽ ሳትነጋገሪ
ስቅ ስቅ የለኛል አንድ ቀን ስትቀሪ ላንድ ቀን ስትቀሪ
የተስተካከለ የፍቅር መዓዛ አሟልቶ ሰቶሻል የመወደድ ለዛ
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏
Tsegaye_Eshetu_ፀጋዬ_እሸቱ_የአይኔ_አበባ.mp36.89 MB
Get up, get up
Kiddominant on the beat, better run it back
Fuckin' Robitussin
I don't know why this shit got me lazy right now, yeah
Can't do Percocets or Molly
I'm turnin' one, tryna live it up here right, right, right
Baby, you can
Ride it, ooh, yeah
Bring it over to my place
And you be like
"Baby, who cares?"
But I know you care
Bring it over to my place
You don't know what you did, did to me
Your body lightweight speaks to me
I don't know what you did, did to me
Your body lightweight speaks to me.
Under The Influence - Chris Brown.mp32.84 MB
Watch the sunrise along the coast
As we're both getting old
I can't describe what I'm feeling
And all I know is we're going home
So please don't let me go, oh
Don't let me go, oh-oh-oh
And if it's right
I don't care how long it takes
As long as I'm with you
I've got a smile on my face
Save your tears, it'll be okay
All I know is you're here with me.
ɪɴ ᴍʏ ғᴇᴇʟɪɴɢs™
d4vd - Here With Me.mp39.34 MB
┈┈••◉❖◉●••┈
👨🌾 ተወዳጁ🌺
❣ :¨·....................:¨·.❣
♥️ ክፍል አስራ ዘጠኝ
ተወዳጁ 🌺ልብ አንጠልጣይና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ ሊፈፀም ሁለት ክፍል ብቻ ቀረው💔
ሄኖክ ሲነቃ ራሱን ያገኘው ሆስፒታል አልጋ ላይ ነበር ካጠገቡ ኤልሳ ነበረች አልጋው ጫፍ አቀርቅራ ታለቅሳለች ሄኖክም እዚ ለምን መጣው? አንቺስ እኔጋ ምን ትሰርያለሽ አለ በሚያሳዝን
አንደበት ኤልሳም ይበልጥ እንባዋን መቆጣጠር እየተሳናት የፀሎት አባት ነግረውኝ ነው አለች ከዛም መልስ ሳይሰጣት የሆነው ትዝ አለው ፀሎት በህይወት የለችም! ይህን ሲያስታውስ
ከመቅፅበት ብድግ አለ ኤልሳም ደንግጣ የኔ ውድ እዛው ተኛ እስኪሻልህ እባክህ አትነሳ አለች ... ሄኖክም እንባው ሳያቆም
በምፀት ፈገግ ብሎ አያትና የተሰካለትን ግልኮስ ነቅሎት ካልጋው ወረደ ይሄኔ ኤልሳ አይሆንም ዶክተር ብላ ጮኸች ወድያው ዶክተሮቹ ገቡና ወደ ፀሎት አባት ተደውሎ እንዲመጡ ተደረገ ...
የፀሎት አባት መተው ልክ እንደ ልጃቸው ሲያረጋጉት ለተመለከተ የሱ አባት ነበር የሚመስሉት ሄኖክም ፀሎትን አይኗን ሳላያት ፍቅሬን ሳልገልፅላት አፈር አለበሳችኋት አይደል አባባ እስቲ ንገሩኝ
ፀሎትን ለዚ ያበቃኋት አውቄ እንዳልሆነ ገብቷታል ? አለ እንባው ያለማቋረጥ እየወረደ አባትየውም ልጄ ተው በቃ እሷን ፈጣሪ ስለሚወዳት ነው የወሰዳት አይዞህ ደሞ ልጄ አንተንም እንደልጄ እንዳይህ አደራ ብላኛለች አሉ ፀጉሩን አያሻሹ... አይ አባባ ያ ቢሆን ጥላኝ አትሄድም ነበር አለ የፀሎትን አባትና ሄኖክን ተመልክቶ ያላነባ አልነበረም ኤልሳም ይህን ማየት ተስኗት ተነስታ ውጪ ቁጭ አለች...
ሁሉም ከተረጋጉ ቡሃላ ዶክተሮቹ ሄኖክን ዳግም እንዳይጨናነቅ አስጠንቅቀውት መውጣት እንደሚችል ገለፁለት ... ኤልሳም በመኪናዋ የፀሎት አባትና ሄኖክን ይዛቸው ሄኖክ የሚኖርበት ቤት
ወሰደቻቸው ከዛም ልጇን ከትምህርት ቤት ማውጣት እንዳለባት ገልፃ ብቻቸውን ትታቸው ሄደች ሁለቱም በየራሳቸው የትዝታ ማእበል ይዋኙ ጀመር ... ከዛም
የፀሎት አባት ከኪሳቸው አንድ የተጣጠፈ ወረቀት አውጥተው ወደ ሄኖክ እየዘረጉ እንካ ይሄ ልጄ የላከችልህ መልክት ነው አንብበው እናም የኔ ልጅ እኔም እንግዲ እዚ መቆየት አልፈልግም ከዚ ቡሃላ
ለነብሴ መኖር እጀምራለው ወደ ትውልድ ቦታዬ አምርቼ ገዳም እገባለው ... አሉ ሄኖክ በቅጡ ያደመጣቸው አይመስልም
እየተቻኮለ ወረቀቱን ገልጦ ያነብ ጀመር
ሄኖኬ እንደምን አለህ እኔኳ ደና አይደለሁም መሞቴም አይቀርም ግን የኔ ውድ ሁለም ቢሆን ሞቼም ሳይቀር አፈቅርሃለው ይሄን አትርሳ የኔ ውድ በመጨረሻዋ ሰአት ደርሰህ ደስታዬን
እጥፍ ድርብ አርገህልኝ ነበር የኔ ውድ ሁሌም ለኔ እንዲ መሆን እራስህን ተጠያቂ ታደርግ እንደነበር አውቃለው ግን ተሳስተሃል አንተ ምንም አላደረክም ወደ ህንድ የመጣሁትም የልብ በሽታዬን ለመታከም ነበር የልብ ህመም የነበረብኝ
ደግሞ ገና ልጅ ሆኜ ነው እንጂ ባንተ አይደለም!! ሌላው ውዴ አደራ የምልህ ኤልሳ ታፈቅርሃለች አንተም እንደዛው በዛ ላይ ልጅ አላቹ ስለዚህ አብራቹ ሁኑ እሷን ከዛ አስቀያሚ ትዳር አውጣት!! መላካም ህይወት የኔ ውድ። ይላል ይሄን ተመስጦ እያነበበ እንባው ይወርድ እንደነበር
ያስተዋለው ደብዳቤው በስብሶ ሲያየው ነበር ... ከዛም ቀና ብሎ ሲያይ የፀሎት አባት የሉም ... ኤልሳም ልጇን አውጥታ ቀጥታ ወደ ሄኖክ ተመለሰች ገና ገመግባቷ ስልኳ ጠራ ባሏ ነበር አንስታም ወዬ አለች ነይ ውጪ አንቺ ተራ አላት ልቧ ስንጥቅ አለ የልጇን ምሳቃ በቁሟ ለቀቀችው ይሄኔ ትንሹ ልጇና ሄኖክ
በሁኔታዋ ደንግጠው ቆሙ እሷ ልጇን አውጥታ ስትሄድ ባሏ ለካ ይከታተላት ነበር......
◎◎◉◉ ክፍል 20 ይቀጥላል ◎◎◉◉
ꜰᴇʟʟɪɴɢꜱ 🥀
👍 3
It's 4 am
I can't turn my head off
Wishin' these memories would fade
They never do
Turns out people lie
They say, "Just snap your fingers"
As if it was really that easy for me to get over you
I just need time
Snapping one, two
Where are you?
You're still in my heart
Snapping three, four
Don't need you here anymore
Get out of my heart
'Cause I might snap
ꜰᴇʟʟɪɴɢꜱ🥀
baf30eab-9e03-44b9-8222-169ddf469467.mp36.83 MB
❤ 1
┈┈••◉❖◉●••┈
👨🌾 ተወዳጁ🌺
❣ :¨·....................:¨·.❣
♥️ ክፍል አስራ ስምንት
💢ልብ አንጠልጣይና አሳዛኝ ታሪክ
ፀሎት ያባቷን ቁጣ ስትሰማ ይበልጥ ውጪ ቆሞ ፀሎት የሚለውን ሰው ለማየት ጓጓች አባቷ ግን በአይናቸው ሄኖክን እንዲሄድ ይነግሩት ጀመር ሄኖክ ትግስቱ ተሟጠጠበትና አባቷን እስኪ
እባኮትን አንድ እድል ብቻ ስጡኝና ያበላሸሁትን ላስተካክል ብሎ በሩን ግፍቶ አባቷን ገፍትሯቸው ገባ ፀሎትም ሄኖክን ስታይ እውን አልመስልሽ አላት ደንግጣ ፈዛ ቀረች ይሄኔ ሄኖክ እግሯ ስር ተደፍቶ ይሄ ላንቺ አይገባሽም ፀሎትዬ እያለ ያለቅስ ጀመር ፀሎት ማመን ትስኗት
ፈዛ ቀርታለች ከዚ ቡሃላ ላንቺ እኖራለው እንደንግስት አነግስሻለው እንደ እናት እጦርሻለው የኔ ውድ እንደ ልጅ
እንከባከብሻለው አለ ከልቡ እንደተፀፀተ እያስታወቀበት... አባትየውም ለሄኖክ ለመጀመርያ ግዜ አዘኑለት እሱ ሲያወራ
እሳቸው አይናቸው እምባ አቅርሮ ነበር...
ከዛ ቀን ቡሃላ ሄኖክ ስራ ለመቀየር ማፈላለግ ጀመረ በፀሎት ግፊትም ትምህርቱን በማታው መርሃግብር ቀጠለ ሁሌም ከስራና ከትምህርት ውጪ ባሉት ሙሉ ሰአቶቹ ፀሎትን ያዝናናታል እሷም
ከሷ ውጪ ደስተኛ የሌለ እስኪመስላት ድረስ ደስታዋ ወሰን አጣ... ኤልሳም አካሏ ባሏ ጋር መንፈሷ ሄኖክ ጋር እንደሆነ ህይወቷን ቀጠለች ...
ሄኖክ ትምህርቱን ጨርሶ ተመረቀ ፀሎት ሀኪሞቿ ከግዜ ወደግዜ ተሽሎሽ መራመድ ትችያለሽ ቢሏትም እስካሁን ግን አልቻለችም ስለዚህም ወደ ህንድ አገር ሄዳ እንድትታከም ተደረገ ስትሄድ
ሄኖክም ያለችውን በሙሉ አባቷም ቤታቸውን ሳይቀር ሽጠው አልበቃ ብሏቸው ሄኖክ የመጀመርያ ፍቅረኛውን ኤልሳን እንድታግዛቸው ጠይቋት እሷም ያለምንም ማቅማማት ነበር እሺ ያለችው... በዚ መልኩ ፀሎት ከአባቷ ጋር ህንድ ሀገር ሄዳ ህክምና ጀመረች ...
ቀናት ተቆጠሩና ወደ ሳምንታት ተቀየሩ ከዛም ወደ ወራት ሄኖክ ቢጠብቅም ሳይደወልለት ቀረ አባቷ ገና የገቡ ቀን ብቻ ነበር መግባታቸውን የተናገሩት ከዛ ግን ድምፃቸው ጠፋ ... ሄኖክም ጠንክሮ እየሰራ ነው ፀሎት ድና መታ አንድ ላይ መኖር የሚጀምሩበት ግዜና ሰርጋቸው ተደግሶ ፀሎት የምትመኘውን ሙሽራ ቀሚስ ለብሳ ማየት ይፈልጋል ....
ልክ በስድስተኛው ወር ሄኖክ ከዚ ወዳላከቸው ሆስፒታል አምርቶ
መረጃ መጠየቅ ጀመረ ስለፀሎት በጠየቀ ግዜ ሁሉም ደነገጡ ፊታቸው የሀዘን ጥላ አጠላ... የሆነውን መገመት አልፈለገም
እስኪሰማ ድረስ ጓጓ መዳን አልቻለችም እናም ከሰሞኑ ትመለሳለች ነበር መልሳቸው ሄኖክ ይሄ ቢያሳዝነውም ይሄን ያህል ወር ያለምንም መፍትሄ የመቆየቷ እንቆቅልሽ ሳይፈታለት ይጠብቅ ጀመር ይህ በሆነ በ4ኛ ቀኑ ሄኖክ ስልኩ ጠራ አንስቶ ሀሎ ከማለቱ
ኤርፖርት ተቀበለን አሉ አንድ ትልቅ ሰው በደከመ ድምፅ ሄኖክም ደስታና ድንጋጤ ተቀላቅለውበት የፀሎት አባት ፀሎቴ ደና ናት አለ ግን ምላሽ ሳይሰጠው ስልኩ ተቋረጠ.... ግዜ ሳያጠፋ ኤርፖርት ደረሰ እሱ ከደረሰ ከደቂቃዎች ቡሃላ በቁጥር 10 አካባቢ የሚሆኑ ሰዎች ወይኔ ልጄ እኔ አፈሩን ልብላልሽ እያሉ ጥቁር ለብሰውና ነጠላ ዘቅዝቀው ያለቅሳሉ
ሲያያቸው በጣም አሳዘኑት ሰው ሊቀበሉ እንደመጡ ያስታውቃሉ ... እያያቸው በልቡ ሲያሳዝኑ በህይወት ሸኝቶ እሬሳ መቀበል ምን ያህል አለመታደል ነው ይላል ... ልክ ከ1ሰአት ቡሃላ የፀሎት
አባት ጥቁር በጥቁር ለብሰው ብቅ አሉ ፀሎት የምትባል ልጅ ባካባቢው አትታይም እሳቸው ብቅ ሲሉ ለቅሶው ይበልጥ ይሰማ ጀመር ግራ ገብቶት ማንን ምን መጠየቅ እንዳለበት አያውቅም ይሄኔ የፀሎት አባትም ከለቀስተኛው ጋር ተደምረው ልጄ ልጄ ሲሉ አንዴ ብቻ ሰማቸው ከዛ እራሱን ስቶ ወደቀ......
◎◎◎◉◉ ክፍል 19 ይቀጥላል ◎◎◉◉
ꜰᴇʟʟɪɴɢꜱ🥀
❤ 2
Bebe Rexha - Meant to Be (feat. Florida Georgia Line)
@Music_4_3_3
Bebe_Rexha_Meant_to_Be_feat_Florida_Georgia_Line_Offic_zDo0H8Fm7d0.m4a2.75 MB
00:14
Видео недоступноПоказать в Telegram
I wanna be your favourite boy.
ɪɴ ᴍʏ ғᴇᴇʟɪɴɢs™ ✨🛒
ogSH19phuhIjIEnIcAfyAF2zo9kJcgQUN4QCNI.mp45.41 KB
❤ 1