cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

❤️ islamic ቻናል❤️

Рекламные посты
352
Подписчики
Нет данных24 часа
+17 дней
-1230 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

🌹ቁርዐን🌹 ቁርዐን ማለት የአላህ ቃል ነው፤ ለኡመቱ የተላከው፣ ቁርዐን ማለት የአላህ ቃል ነው፤ ድብርት ጭንቀትን የሚያስለቅቀው፤ የሙስሊሞች የህይወት ፋና፤ የሚያስገኝ የብርሃን ጎዳና፤ የወረደው ከአረህማኑ ከአርሽ በላይ ካለው ጌታ፤ በነብዩ ሙሀመድ የተሰጠን ስጦታ፤ በራህመቱ በእዝነቱ የተሰጠን በእውነቱ፤ በብርሀን እንድንኖር የምንወጣበት ከማቁ፤ ባዕድ አምልኮን የሚያስቀር የሚያስገባን ከጀነቱ፤ ቁርዐን ማለት የአላህ ቃል ነው፤ በብርሃን ጎዳና የምንጓዝበት፤ ችግርን መከራን የምንረሳበት፤ ከችግር መከራ የምንሸሽበት፤ አላህ በእዝነቱ የሰጠን መማሪያ፤ ከሱ የተላከ የሱ ቃል የሆነ የህይወትን መምሪያ፤ ቁርዐን ማለት እኮ ወላሂ ፍቅር ነው፤ ቢያነቡት ቢያነቡት ማይሰለች ነው፤ ከአለም ጫፍ እስከ ጫፍ የተሸመደደው፤ በቢሊዮኖች ልብ ሰርጎ የገባ ነው፤ የስንቶችን ህይወት ብርሀንን የሞላው፤ የእውነቱን ጎዳና እስልምናን መርጠው፤ የነብዩን ሱና የያዙ አጥብቀው፤ ኧረ ስንቶች አሉ በፍቅሩ የታወሩ፤ ጧት ማታ ቀንም ሌት ቁርዐንን ሚቀሩ፤ የእውነቱን ብርሀን ሰጥቷቸው ጀባሩ፤ የጌታዬ እዝነት እጅጉን ገረመኝ፤ እሱን ብቻ እንዳመልክ አብዝቶ ነገረኝ፤ አልሃምዱሊላሂ ሙስሊም አደረገኝ፤ ከሚወዳቸውም ባሪያው አደረገኝ፤ ቃሉንም እንዳነብ ገር አደረገልኝ፤ እስልምናን ሰጥቶኝ ሂወቴም በራልኝ፤ አልሃምዱሊላሂ ሙስሊም ላደረገኝ። አልሃምዱሊላህ አላ ኒዕመተል ኢስላም @Rihu_islamic_post
Показать все...
Repost from ŘÏHÜ TUBE🌹
አንድም ሙስሊም ቁርአነን ሳያዉቅ መሞት የለበትም!!! የ Rihu Tube አላማ ነው https://t.me/Rihu_Tube/402 ኢንሻ አላህ @Rihu_Tube
Показать все...
*#በዕርግጥም ወንድ ነሕ#*~~ ቀጥ ባለው መንገድ በተውሂድ ጎዳና መንገድ የጀመርከው በነብዩ ሱና የነዛ ምርጦቹ ረሱል ተከታዮች ተውሂድ ያነገሱ ምርጦቹ ሰለፎች የሄዱበት ይዘህ መንገድ ላይ ያለኸው የተውሂድ ቀበቶ ወደህ የታጠከው ወለም የማትል ለጊዜያዊ ደስታ ሀራም ሳትቀላውጥ ከቶ ሳትረታ ቀጥ ያልከው አንተ በተውሂድ በሱና በቀደምቶች ፈለግ እንደነዛ ጀግና ጉዞ ላይ ያለኸው ለረጅሙ መንገድ በጀሊሉ ዘንዳ እጅግ ለመወደድ ፂምህ አስረዝመህ ሱሪ የቆረጥከው በረሱልም ዘንዳ ተወዳጅ የሆነው ጀለቢያ ነበር እሱን የለበስከው በንግግር ሳይሆን ሰርተህ ምታሳየው የረሱል ወዴታ በተግባር ለውጠህ ፊዳክ ኡሚ ወአቢ ሳትል አስቀድመህ ራስህ ፊዳ ያረክ ቀድመህ ለሱናቸው እጅ እግር የሰጠህ ለትዕዛዛቸው መጥፎ ስታይ ምትርቅ ጥሩን ምተከተል ሱና በሌለበት ፈፅሞ ማትውል አላህ ከጠላቸው ከሀራም ነገሮች ከሰውም ሆና ከሼይጧን ወስዋሾች በሩን ዘጋግተኸው አላህን ምትለምን ከሀራም አርቆ ሊሰጥህ ሀላሉን ዘውትር ምትማፀን በሱና ተውበህ ሱና ወዳጅ ጀግና በርዕግጥም ወንድ ነሕ 🎀🎀🎀🎀🎀🎀🎀🎀 @Rihu_islamic_post
Показать все...
ለወንድሞቼ ➡️ያንተ ወንጀል የቱንም ያህል ቢገዝፍ ከ አላህ ምህረት አይበልጥም 💧 አንተ ሺ ጊዜ ድንበር ብታልፍ አላህ አንድም ቀን ቃሉን አያጥፍም 💧 የሠው ልጅ እያፈቀርከው ጥሎህ ይሄዳል፣ አላህ ግን እያመፅከው ይጠብቅሃል ✿ የወንጀለኛነት ስሜት ከተሰማህ የኢማን ብርሃን ልብህ ውስጥ አለ ማለት ነው ምክንያቱም ያ ብርሃን ባይኖር የጥፋተኝነት ስሜት ባልተሰማህ ነበር፡፡ ✿አንተ ለመመለስ እስካልሰለቸህ ድረስ አላህ ለማርታ ዝግጁ ነው፡፡ ✿ ሸይጣን ሁለት ጊዜ እንዲያሸንፍህ አትፍቀድለት አንደኛ ወንጀል አሰርቶ ሁለት በአላህ ላይ ያለህን ተስፋ አስጠፍቶ Join us👇 @Rihu_islamic_posts @Rihu_islamic_post
Показать все...
📚ኡሱሉ ሰላሳ ሶስት አን ኳር ነጥቦች اعْلَمْ رَحِمَكَ اللهُ أَنَّه يَجِبُ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ وَمُسْلِمَةٍ، تَعَلُّمُ هَذِهِ المَسَائِل الثَّلاثِ، والْعَمَلُ بِهِنَّ: እወቅ! አላህ ይዘንልህና፡- በእያንዳንዱ ሙስሊም ወንድ እና ሙስሊም ሴት ላይ እነዚህን ሶስት ጉዳዮች ማወቅ እና በነሱም መስራት ግዴታ ነው፡፡1 . الأُولَى: أَنَّ اللهَ خَلَقَنَا، وَرَزَقَنَا، وَلَمْ يَتْرُكْنَا هَمَلًا، بَلْ أَرْسَلَ إِلَيْنَا رَسُولًا، فَمَنْ أَطَاعَهُ دَخَلَ الجَنَّةَ، وَمَنْ عَصَاهُ دَخَلَ النَّارَ، 📚የመጀመሪያዉ አላህ ፈጠረን፡፡ ሲሳይም ሰጠን፡፡ ልቅ አድርጎ አልተወንም፡፡ ይልቁንም መልእክተኛን ወደኛ ላከ፡፡ (መልእክተኛውን) የታዘዛቸው ጀነትን ይገባል፡፡ ያመፃቸው ደግሞ እሳትን ይገባል፡፡ وَالدَّلِيلُ قَوْلُهُ تَعَالَى:- إِنَّا أَرْسَلْنَا إِلَيْكُمْ رَسُولًا شَاهِدًا عَلَيْكُمْ كَمَا أَرْسَلْنَا إِلَىٰ فِرْعَوْنَ رَسُولًا ( 16 )   فَعَصَىٰ فِرْعَوْنُ الرَّسُولَ فَأَخَذْنَاهُ أَخْذًا وَبِيلًا [المزمل: ١٥ - ١٦] እኛ በእናንተ ላይ መስካሪ የሆነ መልእክተኛን ወደ እናንተ ልከናል፣ ወደ ፊርዐውን መልእክተኛን እንደላክን፡፡ ፊርዐውንም መልእክተኛውን አመፀ፡፡ ስለሆነም ብርቱ መያዝን ያዝነው፡፡ [አልሙዝዘሚል፡ 15-16] الثَّانِيَةُ: أَنَّ الله لا يَرْضَى أَنْ يُشْرَكَ مَعَهُ أَحَدٌ فِي عِبَادَتِهِ، لا مَلَكٌ مُقَرَّبٌ، وَلا نَبِيٌّ مُرْسَلٌ؛ 📚ሁለተኛዉ አላህ በአምልኮቱ ላይ ከሱ ጋር አንድም እንዲጋራ አይወድም!! ቅርብ የሆነ መልአክም ይሁን የተላከ ነብይም ይሁን (እንዲጋራ አይወድም)፡፡ وَالدَّلِيلُ قَوْلُهُ تَعَالَى: وَأَنَّ الْمَسَاجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا مَعَ اللَّهِ أَحَدًا [الجن: ١٨] እነሆ መስጂዶችም የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ ስለሆነም ከአላህ ጋር አንድንም አታምልኩ፡፡ [አልጂን፡ 18] الثَّالِثَةُ: أَنَّ مَنْ أَطَاعَ الرَّسُولَ، وَوَحَّدَ اللهَ لا يَجُوزُ لَهُ مُوَالاةُ مَنْ حَادَّ اللهَ وَرَسُولَهُ، وَلَوْ كَانَ أَقْرَبَ قَرِيبٍ؛ 📚ሶስተኛዉ መልእክተኛውን የታዘዘ፣ አላህንም ብቸኛ ያደረገ ሰው፡ አላህንና መልእክተኛውን የሚፃረር የሆነን ሰው መወዳጀት አይፈቀድለትም- እጅግ የቀረበ ዘመድ ቢሆን እንኳን፡፡ وَالدَّلِيلُ قَوْلُهُ تَعَالَى: لَّا تَجِدُ قَوْمًا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ يُوَادُّونَ مَنْ حَادَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَوْ كَانُوا آبَاءَهُمْ أَوْ أَبْنَاءَهُمْ أَوْ إِخْوَانَهُمْ أَوْ عَشِيرَتَهُمْ ۚ أُولَٰئِكَ كَتَبَ فِي قُلُوبِهِمُ الْإِيمَانَ وَأَيَّدَهُم بِرُوحٍ مِّنْهُ ۖ وَيُدْخِلُهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ ۚ أُولَٰئِكَ حِزْبُ اللَّهِ ۚ أَلَا إِنَّ حِزْبَ اللَّهِ هُمُ الْمُفْلِحُونَ  [المجادلة: ٢٢ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑ የሆኑ ህዝቦች አላህንና መልእተኛውን የሚፃረሩ የሆኑ ሰዎችን አባቶቻቸው ወይም ወንድ ልጆቻቸው ወይም ወንድሞቻቸው ወይም ዘመዶቻቸው ቢሆኑም እንኳን የሚወዳጁ ሆነው አታገኛቸውም፡፡ [ ] እነሱ (አላህ) በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ፅፎላቸዋል፡፡ ከእርሱም በሆነ መንፈስ አፅንቷቸዋል፡፡ ከስሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸው የሆኑ ጀነቶችን በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያገባቸዋል፡፡ አላህ ከእነርሱ ወዷል፡፡ ከእርሱም ወደዋል፡፡ እነሱ የአላህ ህዝቦች ናቸው፡፡ አዋጅ! የአላህ ህዝቦች እነርሱ ናቸው ስኬታማዎቹ፡፡ [አልሙጃዲላህ፡ 22] ወንዶቹ ተለይተው የመጠቀሳቸው ሚስጥሩ ይህቺ አንቀፅ የወረደችበት ምክንያት የበድር ጦርነት ላይ የተካፈሉ ወንዶችን አስመልክቶ ስለሆነ እንጂ መልእክቱ ጠቅላይ ነው፡፡ በዚህ ዘመቻ ላይ አቡ ዑበይዳህ አባታቸውን ገድለዋል፡፡ አቡበክር አስሰዲቅ ልጃቸውን ሊገድሉ አስበው ነበር፡፡ ሙስዓብ ኢብኑ ዑመይር ወንድማቸውን ገድለዋል፡፡ ዑመር፣ ሐምዛ፣ ዐልይና ዑበይዳ ኢብኑል ሓሪስ ዘመዶቻቸውን ገድለዋል፡፡ [ተፍሲር ኢብኑ ከሢር፡ 8/84] @Rihu_islamic_posts @Rihu_islamic_posts
Показать все...
ጂን {ክፍል አንድ} 🌹ለአላህ ብላችሁ በትኩረት🌹 ሁሉንም ክፍሎች አንብቧቸው በጣም መሰረታዊ የሆነ ርዕስ ነው። بــســم الــلــه الــرحــمــن الــرحــيمــ الحمد الله رب العالمين ጂን;- ማለት ስውር ወይም ድብቅ ማለት ነው፡፡ ጂን የተባሉበት ምክንያት ለእኛ ስለ ማይታዩን እና ከኛ የተደበቁ ስለሆኑ ነው፡፡ በእነሱ ማመን ከኢልመል ገይብ የሚመደብ ሲሆን በእነሱ ማመን ግዳታ ነው፡፡ የእነሱን መኖር ማስተባበል ኩፍር(ክህደት)ነው፡፡ ጂኖች ልክ እንደ ሰዎች አማኞች፣ መልካም እና ጥሩ የአላህ ባርያዎች የሆኑ አሉ ፤ እንዲሁም ካሃዲዎች እና መጥፎዎችም አሉ፡፡ ጂኖች የተፈጠሩት ከእሳትነው፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ ‹‹ጃንንም(ከሰው) በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው፡፡›አል ሂጅር 27 • በቅድምያ እነዚህን ማጤን ይኖርብናል!! وَمَا هُم بِضَارِّينَ بِهِ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ‹‹እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም፡፡ ›› አል-በቀራህ 102 إِنَّ كَيْدَ الشَّيْطَانِ كَانَ ضَعِيفًا ‹‹የሰይጣን ተንኮል ደካማ ነውና፡፡›› አን-ኒሳእ 76 إِنَّمَا ذَٰلِكُمُ الشَّيْطَانُ يُخَوِّفُ أَوْلِيَاءَهُ فَلَا تَخَافُوهُمْ وَخَافُونِ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ ‹‹እንዲህ የሚላችሁ ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ ወዳጆቹን ያስፈራራችኋል፡፡ አትፍሩዋቸውም፡፡ ምእምናንም እንደኾናችሁ ፍሩኝ፡፡ ›› አል-ኢምራን 175 وَإِن يَمْسَسْكَ اللَّهُ بِضُرٍّ فَلَا كَاشِفَ لَهُ إِلَّا هُوَ ۖ وَإِن يَمْسَسْكَ بِخَيْرٍ فَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ‹‹አላህም በጉዳት ቢነካህ ለእርሱ (ለጉዳቱ) ከእርሱ በቀር ሌላ አስወጋጅ የለም፡፡ በበጎም ነገር ቢነካህ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ ›› አል አንዓም 17 إِنَّ عِبَادِي لَيْسَ لَكَ عَلَيْهِمْ سُلْطَانٌ ۚ وَكَفَىٰ بِرَبِّكَ وَكِيلًا «ባሮቼ በእነሱ ላይ ፈጽሞ ላንተ ስልጣን የለህም፡፡ መጠጊያም በጌታህ በቃ፡፡»አል ኢስራእ 65 إِنَّ عِبَادِي لَيْسَ لَكَ عَلَيْهِمْ سُلْطَانٌ إِلَّا مَنِ اتَّبَعَكَ مِنَ الْغَاوِينَ «እነሆ ባሮቼ በእነሱ ላይ ላንተ ስልጣን የለህም፡፡ ከጠማሞቹ የተከተለህ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡»አል ሂጅር 42 አላህ(ﷻ)በቁርአን እንደነገረን ሰይጣን በመልካም ባሮች ላይ ምንም ስልጣን አና አቅም እንደለለው እና በአላህ ፍቃድ እንጂ መጉዳት እንደማይችሉ ማመን እና መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ •ጂኖዎች የሚያደርሱት ጉዳት ጂኖች በሰዎች ላይ የተለያዩ ጉዳቶች ማድረስ ይችላሉ ይህ ስንል ግን በአላህ ፍቃድ እንጂ ምንም አይነት ጉዳት ሊያደርሱ አይችሉም፡፡ •ከትክክለኛው መንገድ ማጥመም ፡- የሰው ልጆችን ትክክለኛውን መንገድ(ኢስላምን)እንዳይዙ፣አላህን በብቸኝነት እንዳያመልኩ በተለያዩ አቅጣጫ በመምጣት ያሳስታሉ ይህም ዋነኛ ስራቸው ነው፡፡ ሸይጧን እንዲህ ሲል ነበር የፎከረው قَالَ رَبِّ بِمَا أَغْوَيْتَنِي لَأُزَيِّنَنَّ لَهُمْ فِي الْأَرْضِ وَلَأُغْوِيَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ إِلَّا عِبَادَكَ مِنْهُمُ الْمُخْلَصِينَ ‹‹ኢብሊስ)አለ «ጌታዬ ሆይ! እኔን በማጥመምህ ይኹንብኝ ለነርሱ በምድር ላይ(ኀጢአትን) እሸልምላቸዋለሁ፡፡ ሁሉንም አጠማቸዋለሁም፡፡ ከነርሱ ፍጹሞቹ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ፡፡» አል-ሂጂር 39-40 قَالَ فَبِمَا أَغْوَيْتَنِي لَأَقْعُدَنَّ لَهُمْ صِرَاطَكَ الْمُسْتَقِيمَ ثُمَّ لَآتِيَنَّهُم مِّن بَيْنِ أَيْدِيهِمْ وَمِنْ خَلْفِهِمْ وَعَنْ أَيْمَانِهِمْ وَعَن شَمَائِلِهِمْ ۖ وَلَا تَجِدُ أَكْثَرَهُمْ شَاكِرِينَ ‹‹ስለአጠመምከኝም ለእነርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ በእርግጥ እቀመጥባቸዋለሁ» አለ፡፡ «ከዚያም ከስተፊቶቻቸው ከኋላቸውም ከቀኞቻቸውም ከግራዎቻቸውም በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ፡፡ አብዛኞቻቸውንም አመስጋኞች ኾነው አታገኛቸውም»(አለ)፡፡ ››አል-አዕራፍ 15-17 (አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው) አካላዊ ወይም ስነ ልቦናዊ ጉዳት ማድረስ 👉በክፍል ሁለት ይጠብቁን 👉 ይቀጥላል👈 ለአላህ ብለው ሼር ማድረግ አትርሱ ይሄን መልዕክት ያነበባችሁ ቢንያስ ከ15 ሰው በላይ ሼር አድርጉት። አላህ ይባርካችሁ በዱዓ አንረሳሳ! Comment @Riihu_bot ይህ በዝሙን አንዘምን የቴሌግራም ቻናል ነው በተለያዩ ርዕሶች አስፈላጊና አንገብጋቢ ርዕሶችን የሚያቀርብላችሁ ቻናል ነው ይቀላቀሉን። join us on telegram channel 👇👇👇👇👇👇👇 @Rihu_islamic_post @Rihu_islamic_post
Показать все...
🎈ሴት ልጅ አንዴ ህጓን ከትዳር ውጭ ካጣችው ለወደፊቱ ከባድ የሆነን ዋጋ እንደሚያስከፍላት ማወቅ አለባት❗️ ይሄም እንዳይሆን መንገዶችን መዝጋት አለብሽ #አላህ (ሱብሃነ ወተዓላ) በተከበረው ቃሉ እንዳለው "ላተቅረቡ" (አትቅረቡት) ነው ያለን እናም እህቴ ከሃራም ፍቅር (ቦይ ፍሬንድ) ከሚባለው በሽታ እራስሽን አርቂ። ከገባሽበትም እራስሽን በተውበት አፅጂው❗️ Join us @Rihu_islamic_post
Показать все...
👍 1
Repost from N/a
Фото недоступноПоказать в Telegram
Agaro muslim student's jemea 🌹ፕሮፋይል እናድርግ 🌹 ነጃሺ የ ሴት በ ሴት ድንቅ ፕሮግራም👌🏿👌 እለተ ጁመአ 9:00 ሰዓት ላይ በ ነጃሺ የሴቶች መስጂድ ወስጥ እንሻላህ 🌹 🍁ኒሳ'አል ሙስሊም 1🍁 የኔ መንገድ @Nisa_Al_Muslim
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.