cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ምክር ለሙስሊም ሴቶች☀️

Больше
Эфиопия9 295Амхарский7 528Категория не указана
Рекламные посты
311
Подписчики
+124 часа
+67 дней
+2930 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ብዙ ህልሞችንና መልካም ተስፋዎችን የሰነቀች ብሩህ ነፍስ... በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ተስፋ አትቆርጥም...🌿
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
📨መልዕክቱ: ማንኛዋም ተሸፋኝ እንስት ከክፍያ ይቅር የተባለች ናት ይላል። "كثر الله أمثال هؤلاء السائقين"
Показать все...
👍 1
💎ሷሊሇ ሴትና በድን ላይ ያላት ኢስቲቃማ🌷                   ~ክፍል ➋ ➖➖➖➖➖➖➖➖ ➴#ሷሊኋ_ሴት_ማናት! ሷሊሇ ሴት ከሴቶች በላጯ ናት ። የአላህ መልእክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንደህ ሲሉ በላጯን ሴት ያመላክቱሃል!               👇 ﻋﻦ ﺃﺑﻲ ﻫﺮﻳﺮﺓ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﻗﺎﻝ : ‏( ﻗِﻴﻞَ : ﻳَﺎ ﺭَﺳُﻮﻝَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ! ﺃَﻱُّ ﺍﻟﻨِّﺴَﺎﺀِ ﺧَﻴﺮٌ ؟ ﻗﺎﻝ : ﺍﻟﺘِﻲ ﺗَﺴُﺮُّﻩُ ﺇِﺫَﺍ ﻧَﻈَﺮَ ﺇِﻟﻴﻬَﺎ ، ﻭَﺗُﻄِﻴﻌُﻪُ ﺇِﺫَﺍ ﺃَﻣَﺮ ، ﻭَﻻ ﺗُﺨَﺎﻟِﻔُﻪُ ﻓِﻲ ﻧَﻔﺴِﻬَﺎ ﻭَﻻ ﻓِﻲ ﻣَﺎﻟِﻪِ ﺑِﻤَﺎ ﻳَﻜﺮَﻩُ ‏) ﺭﻭﺍﻩ ﺃﺣﻤﺪ ‏( 2/251 ‏) ﻭﺣﺴﻨﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ﻓﻲ " ﺍﻟﺴﻠﺴﻠﺔ ﺍﻟﺼﺤﻴﺤﺔ " ‏( 1838 ‏) ከአቢ ሑረይረት(አሏህ ስራውን ይውደድለትና ይህን ብሎ አለ:(አንተ የአላህ መልእክተኛ በላጯ ሴት ማናኛዋ ናት ተባሉ? ብለው አሉ: ያች ወደ እርሷ ሲመለከት የምታስደስተው፣ (አሏህ በሚወደው) ያዘዛት ጊዜ የምትታዘዘው፣ በነፍሷም ሆነ በገንዘቡ በሚጠላው ነገር የማትቃረነው ናት") ሲሉ በሚማርክ ሁኔታ ይገልፇታል። እዚህ ላይ ሲያት የምታስደስተው ሲባል ብዙ ጊዜ ከብዙዎች አዕምሮ የሚቀረፀው የፊት ገፅታ ውጫዊ ቅርፅ ላይ የሚያተኩሩ ብዙዎች ናቸው። ይህ ትክክል ያልሆነ እይታ ነው። " ሲያት የምታስደስተው" ሲባል የብዙ ነገሮች ድምር የሚያመጣው ትክክለኛ የልብ ደስታ ነው። አንድት እንስት ትክክኛ ደስታ ልታስገኝ ዘንድ ቀጣይ ያሉ ባህሪዎችና ተግባሮች ሲንፀባረቁባት ነው          👇 1, ለጌታዋ ትእዛዝ በዒባዳዋ እጅ ሰጥታ ስትገኝ በሶላቷ፣ በፆሟ … 2, ለባሏ ታዛዥና ቅን ሆና ስትገኝ፣ በአቀባበሏ ፈገግታዋ ፣ በንፅህናዋ በቤቷ ጠንቃቃ ሆና ስትገኝ ባል ይደሰታል 3,ልጆቿን በኢስላማዊ ተርቢያ ስትንከባከብና ስትኮተኩት ሲያይ ባል ይደሰታል 4,በሁለ መናዋ አለባበሷ ስነምግባሯ ቁጥብና ጨዋ ሆና ሲያት ባል ይደሰታል 5, ያለፍቃዱ ቤቷን ለቃ የማትወጣ፣ እርሱ የሚጠላውን ሰው ከቤቷ እንድገባ ባለመፍቀድ ቤቱንም ገንዘቡንም ጠብቃ ሲያገኛት ባል ይደሰታል 6, ከሃሜት ነገር አሳባቂነት ቁጥብ ሆና ከጎረቤቶቿ ዘንድ በመልካም ገድል ስትወሳ ሲሰማ ባል ይደሰታል እንግድህ የሷሊሇ እንስት መደሰቻዋ ከብዙ ጥቂቶችን ገለፅኩ እንጅ ብዙ አስደሳች ባህሪና ተግባር አሏት።  እንደህ ነው የደስታ ምንጭ መገኛው!! ግን በተቃራኒው ያች የውጭ የፊት ገፅታ የውጭ ሞደሊስት ሆና ለጊዜው አይኑ እይታው ያረፈባት ሁሉ ለአይኑ የምትስብ መስላ የምትታይ ፣ በባህሪዋና ተግባሯ ግን          👇 1, የአሏህን ዒባዳዎች ላይ የምትዘናጋ ችላ ባይ ሆና ስትገኝ 2, በአለባበሷ ግደለሽ ሂጃቧን የማትጠብቅ አጅነቢ ፊት የምትገላለጥ ያገኘ የሚያያት ሆና ስትገኝ 3,ለባሏ ግደለሽ በተኮሳተረ ፊቷ የምትቀበለው ነጭናጫ ባህሪ ያላት ባሏ በሰጣት የማታመሰግን በማማር የተሞላች  ሆና ስትገኝ 4, በቤቷና በልጆቿ ግደለሽ ዝርክርክ የሆነች በመልካም የማታዛቸው ከመጥፎ የማትከለክላቸው ሆና ስትገኝ 5, ከቤቷ ውስጥ ለባሏ የማትበጃጅ ከእርሱ ጋር የምታደረገው ጨዋታ ግንኙነት የማይደንቃት ፣ ከቤት መውጣት በፈለገች ጊዜ ተበጃጅታ ማንነቷን የሚያጋልጡ ልብስ ለብሳ ሽቶ ተቀባብታ ወጥታ እውኝ እውኝ የምትል ሆና ስትገኝ 6,በማንነቷ ስነምግባሯ ከጎረቤቷ ዘንድ የተጠላችና የምታስደበው የምታስወቅሰው  ሌሎች ጥፉ ባህሪያትና ምግባር የምታንፀባርቅ ሆና ስትገኝ እንግድህ ይህ ባል የዚች ውጫዊ ሃራው በለል መልክና ፀጉር ተክለ ሰውነት ምኑ ላይ ላይ ነው የውስጥ ደስታን የምታስገኝለት ?ምኑ ላይ ነው የአይኑ ማረፊያ የምትሆንለት? በፍፁም በሂዎቱ እንደ ሚጥሚጣ እያቃጠለችው፣ እንደ ጭስ እየቆጠቆጠችው እያስለቀሰችው፣ እንደ ኮሶና ሬት እየመረረችው፣ ምቾት አሳጥታ ሸክም ሆና እያስቃሰተችው ፣ እንደት ሆኗ የአይን ማረፊያ ሆነችው!!????? ይቀጥላል……… ⚠️لانسمح بحزف الرابط القناة!⚠️ ((*أنشر معنا الدال على الخير كفاعله! *)) للإنضمام إلى قناتنا اضغط الرابط أسفل 👇👇 واهلاً نسعد بكنَّ
Показать все...
👍 7🍓 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
👍 1
﴿ كُلوا مِن طَيِّباتِ ما رَزَقناكُم وَلا تَطغَوا فيهِ ﴾.
Показать все...
voice_1685616574.opus8.72 KB
👍 1
﴿ كُلوا مِن طَيِّباتِ ما رَزَقناكُم وَلا تَطغَوا فيهِ ﴾.
Показать все...
voice_1685616574.opus8.72 KB
Фото недоступноПоказать в Telegram
💎ሷሊሇ ሴትና በድን ላይ ያላት ኢስቲቃማ🌷                   ~ክፍል ❶ ➖➖➖➖➖➖➖➖ ሷሊኋ ሴት ማናት?? ﻗﻮﻟﻪ تعالى[ ‏( ﻓﺎﻟﺼﺎﻟﺤﺎﺕ ﻗﺎﻧﺘﺎﺕ ﺣﺎﻓﻈﺎﺕ ﻟﻠﻐﻴﺐ ﺑﻤﺎ ﺣﻔﻆ ﺍﻟﻠﻪ ‏) "ሷሊኋ (እንስት) በድኗ ላይ ቀጥ ያለች፣ (ለጌታዋ ደግሞም ለባሏ) ታዛዥ የሆነች፣  (ባሏ ከእርሷ በራቀ ጊዜ) አሏህ እንድጠበቅ ያዘዘውን የምትጠብቅ ናት" )] ሷሊኋ ሴት በመጀመሪያ ወደ ዱኒያ አለም የመጣችበትን አላማ ጠንቅቃ የምታውቅና መጨረሻዋ ወደ የት እንደሆነ አውቃ ለቀሪ ሃገሯ ታላቅ ዝግጅትን ስንቅን በመሰነቅ ላይ የተጠመደች ናት። #ሷሊኋ ሴት ዱኒያ ላይ የመጣችው የተፈጠረችው ጌታዋን እርሱ እንዳዘዛትና እንደሚወደው እስከመጨረሻዋ  ተገዝታው አምልካው ዱኒያን አጠናቃ ወደ አኼራ ተሸጋግራ  የጀነትን ስኬት ለመጎናፀፍ ደፋ ቀና የምትል ውድና ብልህ እንስት ነች።  ሷሊኋ ሴት አላማዋን ግቧን ጠንቅቃ ስለምታውቅ ከደመነፍስና ጭፍን ጉዞ ታቅባ  ድነል ኢስላም በሚያዛት መልኩ ራሷን ለመቅረፅ የምትተጋ ቁጥብና ጨዋ የሆነች እንስት ናት። ~➴ አዎ ሁለ መናዋ ማራኪ ናት በቁጥብነቷ ፣ በስነ— ምግባሯ ፣ በአለባበሷ ለልጆቿና መሰል እንስቶቿ ምርጥ ሞደል ነች………… ይቀጥላል✍                        (ተውጂሐት)
Показать все...
👍 10🥰 1
≈>#ውድ_እህቴ! እጆቼን  አንቀሳቅሼ  በአንድ  ጉዳይ ላይ መፃፍን  ፈለኩኝ እናም አንቺ   ውድ ሆንሺው  እህቴ  ሆይ! ≈>ስለ ወደፊት ኑሮሽ እና በዚህ የህይወት ክፍልሽ የሚጋራሽን ሰዉ  ስትፈልጊ፣ስታስፈልጊ፣ስትመርጭና ስታሰመርጪ ብዙን አሳልፈሽ ይሆናል ≈>አንዳንዴም  በፆዎታሽ  ፈተናዎች  ሲደራረቡብሽ  መሸሸግና  መርጋት  እጅጉኑ ይናፍቅሻል። በተላይ  ከቤተሰብ  ርቀሽ  እና  በባአድ  ሀገር በባዳ  ቤት ስትኖሪ  ሁሌም  የራሴ  የምትይው  አካልን  ፍለጋ  አንዳንድ  ምልክቶችን ታንፀባርቂያለሽ ≈>እህቴ  ምክሬን  እዚህ  ጋር  ያዝ  አድርጊልኝ ፍላጎትሽ  ወሰንን  አይለፍ ፣ ማንነትሽን  ዝቅ አታድርጊው  ሰዎች  ቢሰበሰቡ  አሏህ  ያልሰጠሽን  አይሰጡሽም  እንዲሁም አሏህ  የሰጠሽን  አይቀሙሽም። ≈> ይልቁንስ እህቴ  በርሽን  ለሌባ  አትክፈቺ፣  ቁስልሽን  ለዝንብ  አታጋልጪው ፣ክብርሽን  ክብር  ለሌላቸውና የማንነትሽን  ትርጉም ለማይረዱ  አታዝቅጪው። ≈> ዛሬ  ስትጠይቂ  ሰለመስፈርትሽ ብትባይ ማሻ አሏህ  መልስሽ  ሰለፊይ  የሆነ እና  ዲን  ያለው  ስነምግባሩ  ያማር  የሚል መልስ   ከብዙዎቻችን  አንደበት  ቀድሞ ይወጣል ። ≈>ወድ  እህቴ  ስለ  ሰለፊይነቱ  በ post ላይ  ስላንፀባረቀው  ፅሁፉን  ሰለመወደድሽ ሰፍሰፍ  አትበይ  በፆታሽ  አንቺ  ላይ ከመጫወት ወደ  ኋላ  የማይሉ  ስነ-ምግባር የጎደላቸው  እንዳሉ  አትዘንጊ {አሏህ  ካዘነላቸው  በሰተቀር}‼️ ≈>እቺን  በስተመጨረሻው  ልበልሽ  የምትናፍቂው  አካል  ከዘገየብሽ  የትም ፍለጋ አትሂጂ  በዱዓሽ  ፈልጊው  የሁሉ ነገር  ባለቤት  የሆነው  ተንከባካቢሽን  አል-ረህማንን  ጠይቂ! ≈ላንቺ  ያለው  ማንም  አይወሰደውም  ሁሉም ተከትቦ  ብእሩም  ደርቋል። ≈>አትዘኝ  ሌሎች  ስለቀደሙሽ  እነሱ  ተራቸው ስለደረሰ  እንጂ  ከማንም  በምንም  አንሰሽ አይደለም፣  ሌላዋ  ጋር  የሌለ  አንች ጋር ይኖራል   አንቺም  ተፈላጊ  እና  ወድ  ነሽ‼️ ≈> (ኒካህ)  ያሰረው  ሁሉ ደስተኛ  ይመስልሻልን?  አትሳሳች  ምን  መሰለሽ  ወደ  ኒካህ  መሮጡና  መገስገሱ  የተወደደና መልካም  ከመሆኑም   ባለፈ  አንገብጋቢ  ነው  በል በዚህ ባለንበት  ዘመን  አንፃር  ሲታይ  አንገብጋቢነቱ  ያመዝናል‼️ ≈>ግን  ማነው  እሱ   አንዳንዴ   ዲን  ካለው  ብቻ  በቂዬ  ነው  ስንል  ይስተዋላል አይደል!? ወላኪን  አንድ  ነገር ዘንግተናል  እርሱ  ስታያት  ምታስደስትህን  ሴት  አግባ  ሚለው  ወንዶች ብቻጋ  ይመስለናል! አንችስ  ስታይው  ሚያስደስትሽ  ካልሆነ  ኢልም ብቻ  ስላለው  እንዴት  ልብሽ  ለእርሱ  ቀልብሽ  ወዴ   እርሱ  ሊሆን  ይችላል? አዎ  ዲኑኮ  ከሁሉም  በፊት  ቁ1 ላይ  የሚሰፍር  የመጀመሪያው  መስፈርት  ሊሆን  ሚገባ  ነው። ግና  ዲን  ስላለው  ብቻ  ልብሽ  ባልደነገጠች  ለት ሰው  ላይ  አንዴት  ልብሽ  ለልቡ ትሆናለች?! ≈> ዲኑ  የመጀመሪያ   ምርጫሽ ነው  ሊህም ያለበት  ነው ግና ሳታይውና  ሳትደሰችበት  በዳፈናው  መግባትሽ  ከኒካህ  በኋላ  መደናገርንጂ  መቃናትን  አታገኝም  ነዓም  ፍቅርም  ውዴታም  ከኒካህ  በኋላ ሚመጡ የአሏህ ፀጋዎች  ናቸው አሏህ ልብሽን  የዛን ሰው  ሙሀባ  በቀልብሽ   ሊዘራው  ይችላል ሚቸግረው  የለም  ስለሆነም  ሰበቡን  በማዴረስሽና  በማስተዋልሽ  ተጠቃሚ  ነሽና  አስተውይ‼️ ≈> አትቸኩይ  ረጋ  በይ  ራስሽን  ከፊትና  አርቀሽ  በማስተዋል  መሄድ  ወደ ፈለግሽበት ከመሄድሽ  በፊት በደንብ  አስቢበት  አስተንትኚ  በደንብ  አስተውይ   ወዴ  አሏህ ተጠጊ  እርሱኑ   ያዢ  እሱ  የሚበጅሽን ና  የሚያስደስትሽን  ያውቃልና በእርጋታ  ተሞልተሽ   ለእያንዳንዱ  እርምጃዎችሽ አማክሪው  እርሱ  ከመራመድሽ  በፊት  ምትራመጅባቸውን  ሁሉ  አዋቂ  ነውና‼️                   ⤵️🌸⤵️🌸⤵️ ምክር ለሙስሊም ሴቶች Sher ጆይን፦ https://t.me/muslimahcom https://t.me/muslimahcom
Показать все...
👍 5 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
👍 3
#እህቴ!💎 የሰው ልጅ ክብሩን የሚጠብቀው ራሱ ነው። አንድ ሰው ራሱን ሲያዋርድ ሌሎችም በንቀት አይን ያዩታል‼️ #ሚዲያ_ላይ ከሚገኙ አሏህ ካዘነላቸው እህቶች ውጪ! አንዳንድ እህቶች ከማንም ጋር በመለፍለፍ መልካም ነገር የሚገኝ ይመስለናል መሰል?! #ወሬን  በየቦታው መጥለቅለቅን… በመቀነስ ክብርሽን ጠብቂ‼️ #ያው__ወሬ ስልሽ! ከሰዎች ርቄ ነው የምኖረው ልትይ ትችይ ይሆናል! #በአካል ተገናኝቶ ከሚወራው ባሻገር! በሚድያ  በቻት እኔም  እርሷም  እርሱም ሳታውቂ/አውቀሽ ጓደኛውም…ጋር አታውሪ! #የግድ ማውራት አለብኝ ካልሽ/ አስፈላጊ ነው ካልሽ! #የምታወሪውን ወሬ አስፈላጊነቱን መዝኝ አገናዝቢ! #የህይወት ታሪክሽን እኔ  እኔ …ማለት እያለሽ ጥሩውን መጥፎውን አዘርዝሪ! #ምናልባት ያወራሻቸው ሰዎች የአንችን አቋም ፈታኝ / የሚተዋወቁ ጓደኛሞች ይሆኑና ባንች ላይ መቀለድ ይጀምራሉ! #የዛኔ ክብርሽ ቅጥ ያጣና የሰዎች መሳለቂያ ሆነሽ ታርፊያለሽ! ይህ ነው ውርደት  ይህ ነው ቅሌት! በቅርብ ሰዓት የተከሰተ ነገር ላካፍልሽ! ትምህርት ይሆንሽ ይሆናል! #ልጂቷ በሚድያ በሚታየው ጠንካራ ጥሩና መልካም መካሪ ነች!  የቻት ወሬን ታወግዛለች ያው በምክሯ ነው! እናም ከምክሯ ካላት የሚድያ ጥንካሬ አንፃር! በቻት ትገኛለች የሚባለውን ለማመን ይከብዳል! #ባጠቃላይ! ቻት ታወራለች! #ግን ማንን ነው የምታወራው! እህቶቿን ላ አይደለም! #አጂነብይ_ወንዶችን_ነው! ከዛ እኔ ማለት በቂርዓት እንዲህ  እንዲህ የቀራሁ! እኔ ማለት… ወንድ የማላናግር ሴት ነኝ!  እኔ ማለት…… እንዲህ እንዲህ ነኝ ቀጥላለች አላቆመችም! #ከዛ_ወንድ_ሆዬ! እንዲህ አይነት ሴት ማግኘትማ እድለኛነት ነው ይልና! #በቃ እውነት ጠንካራ ከሆነች እያለ  በጓደኛው #ማስፈተን ጀመረ! ለጓደኛውም… ለርሱ የተባለው ተደገመ! #ፈተናው__በዚህ_አላቆመም! #ከዛም ቀጠሉ እርሷም እነርሱም (ሶስቱም ማዋራትን አላቆሙም! ሶስቱንም ለመተያየት ቀጥራቸው እስካዯት እስካቆሙበት/ እስከተዋት ድረስ!! #በርግጥ ለምን ተሳሳተች እያልኩ አይደለም! የሰው ልጂ ነች ትሳሳታለች! ይሄ ለሁሉም መዕሩፍ ነው!! #ግን__ተግባር_ላይ የሌለንበትን ነገር ባንፅፍ ባናወራ መልካም ነው! ለውርደት ከመዳረጋችን በፊት! #ስለዚህ__እህቴ! ለሀጃ/ለዶርርይ ማውራት ከፈለግሽ ሀጃሽን ብቻ አውርተሽ መሰናበት! ተገቢ ነው! የህይወት ታሪክሽን አውርተሽ ምን ትጠቀሚያለሽ??? #ወንዶች እንደ ልምድ ሆኖ ስማቸው በትንሽ ነገር  አይጠፋም! ሴቶች ግን ………በትንሽ ነገር ይጠፋል! #ስለዚህ! እህቶች ራሳችሁን ልባችሁን ሚስጥራችሁን  ክብራችሁን ጠብቁ!!! #ኋላ ከመነፋረቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ!!! "ይላሉ መካሪዎቻችን"        Sher ጆይን፦ https://t.me/muslimahcom https://t.me/muslimahcom
Показать все...
👍 10
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.