cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Orthodox pp,mezmur,getm

የመዝሙር ግጥም ከመዝሙር ጋር፣ የሚገርሙ ኦርቶዶክሳዊ ፎቶዎች ፣ ግጥሞች ፣ምክሮች ወዘተ ታገኙበታላቹ subscribe አድርጉ🙏🙏

Больше
Рекламные посты
228
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

13
#ዘወረደ (የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ) የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ይባላል፡፡ ‹‹ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ›› የሚልና ይህንን የመሳሰለ ጌታ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ሌላም ስም አለው #ጾመ_ሕርቃል ይባላል፡፡ ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን #ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ #ሕርቃል_ማን_ነው? #ለምንስ_በስሙ_ተሰየመ? በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60 ሺህ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3 ሺህ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም ቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል። እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገ*ደ*ለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡ በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡ «#ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «#የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምስጢሩ አምላክ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም በቅዱስ ፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት፣ ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ ይህም የሚታወስበት፣ የሚወሳበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ.3፥13፡፡ ሳምንቱ #ሙሴኒ ይባላል። ይህ የተባለበትም ምክንያት በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት» «ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ» ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚያጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ከአለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው ምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን የሚያስታውስ ነው፡፡ /ዘፀ.24፥18፤ 1ኛ.ነገ.19፥8፤ ማቴ. 4፥1-4/፡፡ @retua_haymanot
Показать все...
👍 6
10
4
አንዳንድ ነጥቦች በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ መከልከል ዙሪያ፦ 1. ለዚህ አሳዛኝ ድርጊት የተቀነባበረ ሽፋን በቅርብ ሲሰጥ እንደምንሰማ የታወቀ ነው። በመንግሥት አካላት ተደርሶ የሚቀርበው ድራማና ዶክመንተሪ አያልቅምና ያልሠሩትን ወንጀል ሲያሸክሟቸውና ሲያጥላሉዋቸው እንሰማ ይሆናል። ስለዚህም ከሚዲያ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ልሳን የሆኑ ሚዲያዎችን ብቻ እንከታተል። 2. መንግሥት ይህን መሰል አንገት ሰባሪና ድፍረት የተሞላበት ድርጊት ሲፈፅምም ብፁዕነታቸው ያሉበትን ኃላፊነት ከግምት አላስገባም። ክብራቸውን የሚወክሉትን ቤተ ክርስቲያንና ሕዝባቸውን አላከበረም። በዚህ ጸያፍ ድርጊቱ እርሳቸውን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኝን እንዳሳዘነ መታወቅ አለበት። 3. ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ፓትርያርኩን ሸክም ጎንበስ ብለው የሚሸከሙ አባት ናቸው። የዛሬው የመንግስት ድርጊት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ከሜዳው በማግለል የቅዱስ ሲኖዶስን ማዕከላዊነት የመናድ ሙከራ ነው። 4. ብፁዕነታቸው በእምነታቸው የማይደራደሩ ታላቅ አባት ሲሆኑ እርሳቸውን ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ የማድረግ ርምጃ የቤተ ክርስቲያንን በር የበግ ለምድ ለለበሱ ተኩላዎችና ለእንደ ልቡዎች ክፍት የማድረግ ዕቅድ አካል ነው። ከዚያም ውጪ ሌሎች ውጪ የሚኖሩ አበው ብፁዓን አባቶችንም አፍ የማስያዣ አካሄድ ነው። 5. በሌላ በኩል በውጪ ያሉ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ቁጣቸውን ማሳደር አለባቸው። ምክንያቱም መንግሥትም ሆነ ሕገ ወጥ አካላት በተለያዩ ሚዲያዎች በኩል ይህን ነገር እያራገቡ ጫና ፈጥረው ሌላ ሲኖዶስ እናቋቁም የሚል ሀሳብ እንዲፈጠር መሥራታቸው አይቀርምና በዚህ በኩል ረጋ ብሎ  መጠንቀቅ ተገቢ ነው። ተተኪ ጸሐፊ ይመረጥ የሚል ሤራ እንዳይሸርብም ነቅቶ መጠበቅና መሥመር ማስያዝ እንደሚገባው ሳይረሳ!! 6. ይህ ድርጊት ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል የታሰበ እቅድ ነው። ስለዚህም እንደ ምእመን በበለጠ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ላይ ማተኮርና ቤተ ክርስቲያናችንን በንቃት መጠበቅ አለብን። 7. ይሄ ጉዳይ መሥመር እንዲይዝ የሚያደርጉ አባቶችን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ማገዝና ትዕዛዛቸውንም እንደ ልጅ መፈጸምም ይገባናል። ልዑል እግዚአብሔር ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን #ኢንፈርህሞተ #ሞትንአንፈራውም ብርሃኑ ተ/ያሬድ
Показать все...
ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ እንደተመለሱ ተሰምቷል። ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ ሀገር እንዳይገቡ በመከልከላቸው ወደ አሜሪካ ለመመለስ መገደዳቸውን አሳውቀዋል። ብፁዕነታቸው ከደቂቃዎች በፊት ለማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ፤ " አሁን አሳፍረውኝ ተመለስኩ፤ ወደ አሜሪካ ወደመጣሁበት መለሱኝ ፤ ወደ ስራዬ እንዳልመለስ ከለከሉኝ። " ብለዋል። ለቴሌቪዥን ጣቢያው ቃላቸውን በሰጡበት ወቅት አውሮፕላኑ ሊነሳ እንደነበር ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ የሚደረግበት ምክንያት ምንድነው ? ተብለው ተጠይቀው ፤ ብፅዕነታቸው ፤ " በቃ ግሪን ካርዱን ብቻ ነው የምንፈልገው እኛ ያንተን ፓስፖርት አንፈልግም ግሪንካርድ ብቻ ነው የምንፈልገው ብለው ወሰዱ በሩን ዘጉ !! " ሲሉ ተናግረዋል። ይህን ያደረጉት የደህንነት ሰዎች ናቸው ብለዋል። ብፅዕነታቸው ወደ አውሮፕላን እንዲገቡ ከመደረጋቸው በፊት ውጭ ላይ ሲጉላሉ እንደነበር ተናግረው አንድ የኢሚግሬሽን ሰው " የማውቀው ነገር የለም ግሪንካርዱ ትክክል አይደለም " እንዳላቸውና እሳቸውን ግሪንካርዱ ገና 3 ዓመት እንደሚቀረው እንደነገሩት አስረድተዋል። ይህን ሲያስረዱ ከግለሰቡ መልስ እንዳልተሰጣቸውና " ሌሎች ሰዎችንም #ዲፖርት እያደረግን ነው " በማለት እንደነገራቸው ገልጸዋል። ብፅዕነታቸው የአሜሪካ ፓስፖርት እንዳላቸው ገልጸው ፤ " እሱን ምንም ለማድረግ ስላልቻሉ ግሪንካርድ እንወስዳለን በማለት ወስደዋል " ሲሉ ተናግረዋል። ከሳምንታት በፊት ለአገልግሎት ከሀገር ሲወጡ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ጨምሮ ሌሎችም " ሊያስቀሩህ ይችላሉ " የሚል ነገር ሰምተው እንደነገሯቸው ነገር ግን በአሜሪካ የያዙትን አገልግሎት መተው ስላልፈለጉ ወደ አሜሪካ መሄዳቸውን ገልጸዋል። ብፅዕነታቸው ወደ አሜሪካ በሄዱበት ወቅት " ኮበለሉ " የሚሉ መረጃዎች ተሰራጭተው እንደነበር ይታወሳል። በኃላም ቤተክርስቲያኗ በሰጠችው መግለጫ ፤ በህጋዊ መንገድ በቤተክርስቲያን እውቅና ከሀገር እንደወጡ ፤ የሚደበቁም ሆነ የሚኮበልሉ የወንጅል ሰው እንዳልሆኑ አሳውቃ ነበር።
Показать все...
👍 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር እንዳይገቡ ተከለከሉ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል። ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና መስጠታቸው ይታወቃል። ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው እንደሚገኙ ታውቋል።
Показать все...
👍 2
Repost from N/a
ናብሊስ ዜና #የቀጠለ " የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ጵጥሮስ " አቋቁመናል ካሉት ውስጥ ሶስቱ #መታሰራቸውን የእንቅስቃሴው አስተባባሪ ነኝ ያሉ ዲያቆን አክሊሉ ዓለሙ የተባሉ ግስለሰብ ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል ተናግረዋል። ሶስቱ አባቶች የታሰሩት " መንበረ ጴጥሮስ " አቋቁመናል የሚል መግለጫ ከሰጡ በኃላ ሸገር ከተማ አስተዳደር በሚገኘው ቢሯቸው እንደሆነ እኚሁ አስተባባሪ ተናግረዋል። የታሰሩት ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማዕረጋቸውን ገፍፌዋለሁ ያለቻቸው አባ ገብረማርያም ነጋሳ፣ አባ ወልደ ኢያሱስ ኢፋ እንዲሁም አባ ወልደኢየሱስ ተስፋዬ እንደሆኑ ለመረዳት ተችሏል። ሌሎችም አብረው የነበሩ ግለሰቦች መያዛቸውም ተነግሯል። የሸገር ከተማ አስታዳደር ፖሊስ ስለጉዳዩ ምንም ያለው ነገር የለውም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትላንት ተቋቁሟል የተባለውን " መንበረ ጴጥሮስ " አውግዛ ፤ አሁን በሕገወጥ ድርጊታቸው የቀጠሉትን ቡድኖች በፍርድ እንደምትጠይቅ አሳውቃለች። በኦሮሚያ ክልል ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት በእነ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የተመራ የ26 የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ተሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል። ይህንን ሹመት ተከትሎም ቤተክርስቲያኗ በከፍተኛ ሁኔታ ያወገዘችና ግለሰቦቹንም የለየች ሲሆን ህገወጥ ባለችው ሹመት ላይ የተሳተፉ አካላትም ላይ እገዳ እና ማዕረጋቸውን የማንሳት ውሳኔ አሳልፋ ነበር። እነ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በወቅቱ ቤተክርስቲያን " ህገወጥ ነው ! " ላለችው የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ያደረሳቸው ፤ " ቅዱስ ሲኖዶስ የተዋቀረው 85% ከአንድ ወገን በመሆኑ፣ ያለው የውስጥ አሰራር ችግር፣ አባቶችን ከየአካባቢው ከማፍራት ይልቅ ከአንድ ወገን ብቻ የመሾም ችግር ፣  የሚመደቡት አባቶች የህዝቡን ባህል እና ቋንቋ ባለማወቃቸው ለምእመናን እምነት መዳከም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገ መሆኑ ... " የሚሉና ሌሎች ምክንያቶች እንደነበሩ ይታወሳል። ረጅም ጊዜ ከፈጀ አለመግባባት በኃላ በተደረጉ ሰፊ ውይይቶች፣ ምክክር እና መግባባት፣ መንግሥትም ገብቶበት በቤተክርስቲያን በቀረበ ጥሪ እነ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን ጨምሮ ሎሎችም ብፁዓን አባቶች ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሰው አሁን ላይ በስራ ላይ ይገኛሉ። ከተወገዙት እና ከተለዩት ውስጥ ግን 4 አባቶች ጥሪውን ተቀብለው ያልመጡ ሲሆን አሁን 2015 ዓ/ም የተቋቋመ ነው ባሉት " የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ " መንበር መሰየም በማስፈለጉ " የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መንበረ ጴጥሮስ " አቋቁመናል ሲሉ በይፋዊ መግለጫ አሳውቀዋል። ይህንን መግለጫ በሸገር ከተማ ከሰጡ በኃላ #መታሰራቸውን የእንቅስቃሴው አስተባባሪ ነኝ ያሉ ግለሰብ ተናግረዋል። @Eotc @Nablis midea center NBC Midea @የተለያዩ ስለ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ እና ፈጣን መረጃ ለማግኘት የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
Показать все...
Repost from N/a
ናብሊስ ዜና ዝርዝር መረጃ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ከዚህ ቀደም አውግዛ የለየቻቸው ግለሰቦች አሁንም በሕገወጥ እንቅስቃሴያቸው እንደገፉበት አመልክታ ግለሰቦቹን በፍርድ እንደምትጠይቅ አስታወቀች። ግለሰቦቹን አሁንም አውግዛ ፤ ድርጊታቸውን ተቃውማለች። የለበሱት ልብስም የቤተክርስቲያን በመሆኑ #እንዲያወልቁት እንደምታደርግ ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያን " ሕገወጥ " ባለችው መንገድ በጵጵስና ተሹመናል ካሉት እና በኃላም በእርቅ ወደቤተክርስቲያን ሳይመለሱ ከቀሩት መካከል አባ ገብረማርያም ነጋሳን ጨምሮ 4 አባቶች ትላንት በሰጡት መግለጫ " የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት መንበረ ጴጥሮስ " አቋቁመናል ብለዋል። ይህ በ2015 ዓ/ም ተቋቁሟል ላሉት የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መንበር መሰየም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቋሚና ጊዜያዊ ፕሮጀክት መምሪያ ኃላፊ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ወ/ኢየሱስ ሰይፉ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህ መግለጫ ፤ " ግለሰቦቹ በሌላቸው ክህነት ነው መግለጫ እየሰጡ ያሉት " ብለዋል። እነዚህን አካላት ያደረጉት ከቀኖና ውጭ ስለሆነ ዛሬም ቤተክርስቲያን አጥብቃ ታወግዛለች ሲሉ ተናግረዋል። " ቤተክርስቲያን በሕግ በፍርድ ቤት ትጠይቃችለች ፤ በፍትህ መንፈሳዊ ከዚህ ቀደም እንዳወገዘችው አሁንም ህጌ፣ ስርዓቴ፣ ልብሴ ፣ ዶግማዬ ይከበር ትላለች " ሲሉ አክለዋል። " ከዚህ ቀደም በፍ/ቤት ከቤተክርስቲያን እውቅና ውጭ የትም እንዳይንቀሳቀሱ ፣ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደው ነበር ያንን ተላልፈዋል ከዚህ በኃላ በፍርድ እንጠይቃቸዋለን፤ የለበሱት ልብስም የቤተክርስቲያን ስለሆነ እናስወልቃቸዋለን፤ ህገወጥ ናቸው " ብለዋል። " ከዚህ ባለፈ ይህ የሕገወጥ የሹመት እንቅስቃሴ ጉዳይ ከኦሮሚያ ወገን የተነሱትን ብቻ ሳይሆን ከትግራይ ወገን የተነሱትንም የሚመለከት ነው " ያሉ ሲሆን ሲመቱ ትክክለኛ አይደለም ቅዱስ ሲኖዶስም አይቀበለውም ብለዋል። የቤተክርስቲያንን ውሳኔ ማስፈፀም የሚችል አካል ሌላ በመሆኑ እንዲያስፈፅም በትዕግስት እየጠበቅን ነው ሲሉም ተናግረዋል። ኃላፊው ፤ ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት አባቶች በቤተክርስቲያን ጥሪ ተመልሰው መጥተው ፣ ከመንግሥት ጋር በተደረግው ውይይት ፣ ወደቀድሞ ስራቸው እንዲመለሱ ተደርጎ በስራ ላይ ናቸው ብለዋል። አራቱ እንዳልተመለሱና በሕገወጥ እንቅስቃሴ መቀጠላቸውን ገልጸው " የቤተክርስቲያንን ስም ማንሳት አይችሉም ፣ ስሟን ማጠልሸት አይችሉም " ሲሉ አሳስበዋል። " እራሱ ህገወጥ ቡድን የ ' 5 ኪሎ ህገወጥ ' እያለ መጥራቱ ትልቅ ድፍረት ነው " ያሉት ኃላፊው ፤ " ይህን ድፍረት የሰጣቸውም ወቅትና ጊዜውን እየዋጁ መነሳታቸው ነው ብለዋል። " #ሃይማኖት እና #ፖለቲካም ተቀላቅሎባቸዋል " ሲሉ አክለዋል። " የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ምዕመናኖቿ ይህንን ህገወጥ ተግባር አይቀበሉትም ፤ ስለተወገዛችሁም ምዕመኑንም ከእናተ መስቀል አይባረክም " ሲሉ አሳውቀዋል። ከዚህ ባለፈ ቤተክርስቲያኗ አውግዤ የለየኋቸውን አካላት መግለጫ ልክ እንደ ህጋዊ እያደረጉ ያቀርባሉ ያለቻቸውን #ሚዲያዎች ' ከቤተክርስቲያን ላይ እጃችሁን ፣ ሚዲያችሁን አንሱ ' ስትል አስጠንቅቃለች። @Eotc @Nablis midea center NBC Midea @የተለያዩ ስለ ቤተ ክርክቲያን ወቅታዊ እና ፈጣን መረጃ ለማግኘት የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
Показать все...
👍 1
ባለፈው ዓመት በሕገወጥ መንገድ "ጵጵስና  ተሹመናል በማለት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት በዛሬው ዕለት በዚሁ ሕገወጥ መንገድ በመቀጠል "መንበረ ጴጥሮስ" የተባለ ሕገወጥ ቤተ ክህነት መሥርተናል አሉ !
በኦሮሚያ ክልል ፖለቲካዊ ካባ የደረበ አጀንዳ ይዘው የኢትዮጵቻ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል እየተንበሳበሱ የሚገኙት በቀድሞ ስማቸው "አባ" ገ/ማርያም ነጋሳ እና ግብረ አበሮቻቸው ሕገወጥ ተግባራቸውን በመቀጠል "መንበረ ጴጥሮስ" የተባለ ቀኖናዊ መሠረት የሌለው እና ሕገወጥ የሆነ ቤተ ክህነት መሥርተናል ሲሉ ስትራቴጂክ አጋሮቻቸው በሆኑ የሚዲያ ተቋማት አማካይነት በሰጧቸው መግለጫዎች አስታውቀዋል።   በቋንቋችን ለመማር እና በነጻነት ለማምለክ ለዘመናት ተከልክለናል በሚል ሀሰተኛ ሽፋን ይህን እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙት ነውጠኛ መነኮሳት በመንግስት አደራዳሪነት ችግሩ ተፈትቷል ከተባለ በኋላ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ስምምነቱን የጣሰ እና በሚዲያዎች እና ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት በሚጥሩ ኃይሎች ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ማሳያ ነው። ልክ የዛሬ ዓመት ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም ሕገኸጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት በመፈፀም የኦሮሚያና የብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ በሚል "አብዮታዊ ዴሞክራሲን" እናት ፍልስፍና አድርጎ ተመሠረተ የተባለው የመነኮሳት ስብስብ በአሁኑ ወቅትም ከ5 በማይበልጡ የቀድሞ መነኮሳት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማፍረስ የውክልና እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል። "ለትግራይና ለአማራ ሲኖዶስ እንዲቋቋም ተፈቅዷል" በማለት ሀሰተኛ እና በቤተ ክርስቲያኒቱ ያልተደረገን ነገር ማስተላለፋቸው ሳያንስ "ለ5 ኪሎ ሲኖዶስ" እንዳትገዙ በማለት ጭምር ሕዝብን በሕዝብ ለማነሳሳት ከፍተኛ ቅስቀሳ እና የጦርነት አዋጅ እያወጁ ይገኛሉ። 🚀ተ.ሚ.ማ
Показать все...
1
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.