cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ሚራህ ✍️✍️✍️

እዚህ ቤት ረቡል አለሚን በብዛት ይወሳል እናም ጠቃሚ ሃሳቦች ግቡ ተሳተፉ 🤗 @Mirahtypingbot

Больше
Рекламные посты
552
Подписчики
-124 часа
-77 дней
+3330 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ሃጃዎች አሉብን ጌታችንን ጥሩልን 😊
Показать все...
🥰 1
ሃሳቡና ጭንቀቱ አኼራ ያደረገ ሰው ሴትየዋ የፈጅር ሶላት ኣምልጧት ልቧ ተቃጥሏል ጭንቀት ያዛት መጨረሻ ላይ ራሷን ለመቅጣት ወሰነች ሙሉ ቀን ሱጁድ ለአላህ ወርዳ ልትለምን። ባሏ ለስራ ሲወጣ መስገጃዋ ላይ ኣያት ከስራ ሲመለስ ሱጁድ ላይ ነች ታለቅሳለች ቀይሉላ ተኛ ሲነሳ ኣሁንም ሱጁድ ላይ ታለቅሳለች መግሪብ ለመስገድ መስጅድ ሄደ ሰግዶ ሲመለስ ወደ ሚስቱ ሂዶ እቅፍ ኣድርጎ ግምባርዋ እየሳመ ወደዛች ኣልሄድም ኣልሄድም ይላል በመደጋገም ለሷ ሳይነግር ሌላ ሴት ኣጭቶ ነበር እናም በዛች ቀን ኒካሕ ሊያስር ነበር:: የሚስቱን ለቅሶ የልቧ መሰበር ያየ ጊዜ ወደዛች ላለመሄድ ቆረጠ ሃዘንዋና ጭንቀትዋ ወደዛች ይሄዳል በሚል መስሎት። ከጊዜ በህኃላ ሲነገራት ቂሳው ይሄን የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሓዲስ ኣስታወሰች {ሃሳቡና ጭንቀቱ አኼራ ያደረገ ሰው ኣላህ ነገራቱን ሁሉ ይሰበስብለታል ሃብቱ በቀልቡ ላይ ያደርግለታል ዱንያ ተገዳም ትመጣለች። ሃሳቡና ጭንቀቱ ዱንያ ያደርገ ሰው አላህ ነገሩን ይበታትንበታል ድህነት በሁለት አይኖቹ መሃል ያደርግበታል ዱንያም ኣያገኛትም አላህ ከፃፈለት ዉጭ} አላህ ሀሳባችንና ጭንቀታችን አንተው በጥበብህ አስወግድልን። صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ)፡፡
Показать все...
👍 2
the result of sab’r is always worth it.🎀
Показать все...
1🥰 1
ሰዎችን ሊፈትን በሚችል ሁኔታ በእውነትም ቢሆን አታሞካሻቸው። ጭራሽ ያልደረሱበት ደረጃ ላይ ከሰቀልካቸው ደግሞ ድርብ ጥፋት ውስጥ ወድቀሃል። በአንፃሩም ስለጠላሃቸውም ብቻ መልካም ጎናቸውን አትካድ። እነርሱን ለማጠልሸት ብለህ የስነምግባር እሴቶችን አትናድ። ስለማንም በሚኖርህ አቋም ላይ በጭፍን አትነዳ፤ በመፈክርም አትሸንገል። በጥቅሉ አንተነትህን በግለሰቦች ማንነት ላይ አታንጠልጥል። በማይመለከትህ ጉዳይ ውስጥም ዘው አትበል፤ ስለ ሁሉም ነገር አስተያየት መስጠት አይጠበቅብህም። በሚከሰቱ ውዝግቦች ላይ ሁሉ ለአንዱ ለመወገን አትቻኮል፤ በጥልቀት ባልተረዳኸው ሀሳብ ላይ የፍርድ ቃላትን ከመሰንዘር ተቆጠብ። እውነተኝነት መቼም ቢሆን አይለይህ፤ ፍትኸኝነት እስትንፋስህ ይሁን፤ መረጋጋት ከደምህ ጋር ይዋሃድ! ይህን ሁሉ መተግበር የምትችለው የአላህ ፍራቻ በልብህ ሲሰርፅና ንግግርህ በመዝገብ ሰፍሮ በታላቁ የፍርድ እለት እንደምትጠየቅበት ዘውትር ስታስታውስ ብቻ ነው። ✍ ኢልያስ አሕመድ @ustazilyas
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
لَعَلَّكَ بَٰخِعٌۭ نَّفْسَكَ أَلَّا يَكُونُوا۟ مُؤْمِنِينَ አማኞች ባለመኾናቸው፤ (በቁጭት) ነፍስህን ገዳይ መኾን ይፈራልሃል፡፡ (25 : 3)
Показать все...
በሱ ምክንያት ስንት ሸሮች እንደተወገዱልኝ አላወቁ በሱ ምክንያት ስንት መልካሞችን እንደተወፈቅኩ አልገባቸው በሱ ሰበብ ምን ያህል እምነት እንደጨመርኩ መች ተረዱ በሱ በሂጃቤ ብዙ ከፍታዎች የውበት የክብር የሃያዕ የአስተሳሰብ የማይገለፁ ኒዕማዎች ☺️🤍 አላህ ሆይ እስካገኝህ በሂጃቤ አፅናኝ አላሁመ ሶሊ 🤲
Показать все...
🥰 5👍 3
ኒቃብ 😊 የፊትሽን አውጪው እንዲህ ታምሪያለሽ... አታካብጂ አ... ሱና ኮ ነው... የመሳሰሉት ድምፆችን የምታስተናግዱ እህቶች አላህ የሁለት ሀገር ስኬትን እንካችሁ ይበላቹ አላሁመ ሶሊ
Показать все...
😢 2
የተሸፈነ ነገር አይገለጥም። በተለይ አንድ ባርያ በርሱና በጌታው መካከል ስላጠፋው ጥፋት ለሰዎች እንዲታያቸው የምንገልጠው መጋረጃ አይኖርም። ደብቀንለት ለመምከር ካልሆነ በቀር ጌታው ጋር ይጨርስ ዘንድ መተው የደጋጎች መገለጫ ነው። ሁሉም ሰው ከራሱ ጋር እንኳን የሚተፋፈርበት መጥፎ ጎን ይኖረዋል።  ለራሳችን እንኳን ደግመን ለመንገር የሚቀፈን ስንት ኃጥያት አለን?  በቃ ሰዎች አክብረውን እንኳ ጥሩ ጎናቸውን ካሳዩን ይበቃናል። የጥፋት መዝገባቸውን ሙሉ ለሙሉ ብናውቅ እንኳን ከጌታቸው ዘንድ ያወሩ ዘንድ እድል እንሰጣለን እንጂ ለሰው ምላስ አሳልፈን አንሰጥም። እየተሸፋፈንን የምንመካከርበት ሜዳ ናት… ዱንያ።
Показать все...
ያሳሰቦት ሀጃ አለን? ረሱልﷺ እንዳሉት "በጁመዓ ቀን አንዲት ሰዓት አለች ሙስሊም የሆነ ሰው አላህን አይጠይቅም ቢቀበለው እንጂ" አብዛኞቹ ዑለሞች እንዳሉት ይህች ሰዓት ከዓስር በኋላ ያለው ሰዓት ነው በተጨማሪም ፆመኛም እስከሚያፈጥር ድረስ ዱዓው ተቀባይነት አለው በዚህ ወቅት በዱዓ ላይ እንበርታ
Показать все...
#ጁመዓዬ ዛሬ በጠዋቱ ወደ መርካቶ ሰባተኛ አካባቢ ገበያ ወጥቼ ነበር።ታዲያ በመንገዴ ላይ አንዲት ቃሪያ በችርቻሮ የምትሸጥ ሴት ጮክ ብላ''ያረቢ በኪሎ ሚገዛውን''ብላ ዱዓ ታደርጋለች።አጠገቧ ያሉት እያዩዋት ይስቃሉ።ምናልባትም በችርቻሮ ሲያስቡት በኪሎ መጥቶ የሚገዛ ማለሟ ይሆናል ያሳቃቸው።እኔም ስለ እሷም ስለዱዓዋም እያሰብኩኝ ወደ ጉዳዬ አቀናሁ። ከምሄድበት ስመለስ እንደገና በአይኔ ፈልጌ አየኋት። ድንገት ያሰበችውን ብገዛትስ?የሚል ሀሳብ መጣልኝና ጠጋ ብዬ''በኪሎ የምትሸጪ ከሆነ እስኪ አንድ ኪሎ ስጪኝ''አልኳት ደስ ብሏት በኪሎ መዝና ሰጠችኝ።ልሄድ ስል መቼስ አላህ ዱዓዋን ስለተቀበላት ነው ራሴው እንድገዛት ያደረገኝ አልኩና ለሌላ ቀን እንድታሳምረው በማሰብ ቅድም ሳልፍ ጮክ ብለሽ''ያረቢ በኪሎ ሚገዛውን''ብለሽ ዱዓ ስታደርጊ ሰምቼሽ ነው የመጣሁት''አልኳት እየተሽኮረመመች ሳቀችና ተሰነባበትን። ወደ ምሄድበት ስመለስ በዱዓዋ ዱዓዎቼን ፈተሽኩኝ። አላህ ለሚሰጠው በእኛ ልክ ትልቅ የመሰለንን ብቻ ወይንም የአሁን መሻቶቻችንን ላይ የሙጥኝ ብለን ምንጠይቀው ለምንድነው ግን? አልኩ።ለሁላችንም መሻታችንን ቢሰጥ መርፌ ባህር ገብቶ ሲወጣ ሚቀንሰውን ያህል ማይቀንስበትን ጌታ ለምን አጥብበን እንጠይቀዋለን? ለምሳል ያቺ ሴት''እጄ ላይ የያዝኩትን ሁሉ ገዝቶኝ ሚሄድ''ወይንም ሌላ ማይመስል የመሰላትን ትልልቅ ነገር መጠየቅ እየቻለች ይህንን ጠየቀች።የጠየቀችውንም ተሰጠች።እኛም እንዲሁ ነን።ትላንት የጠየቅነውን ነገር በጠየቅነው ልክ ብዙውን ተሰጥተናል።ከዛ በላይ አስፍተነው የነበር ቢሆንም ይሰጠን ነበር። ዛሬም ዱዓዎቻችን ምላሽ የሚያገኝበት ሰአትን የያዘችው ውዷ ጁመዓ ላይ ነን የማይሆኑ የሚመስሉን ህልሞቻችንን ሁሉ ጠይቀነው አል ሙጂቡ'ሁን'ይበልልን🤲 Zinirah
Показать все...
3
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.