299
Подписчики
Нет данных24 часа
+27 дней
-530 дней
- Подписчики
- Просмотры постов
- ER - коэффициент вовлеченности
Загрузка данных...
Прирост подписчиков
Загрузка данных...
አትምጪ
ተስፍ እየሰጠሽ ዘመናት አሰርሺኝ
በፍቅር ስም ገብቸሽ ሞኝ ጅል አረግሽኝ
እመጣለው እያልሽ አመታት ሰረቅሽኝ
ዳግመኛ አትምጪ ዳግመኛ አትጉጂኝ
👍 5😢 4🔥 1
ድምጽ አልባ ፊደላት
፨፨፨፨
ፀጉሩን አንጨብሮ ፂሙን አጎፍሮ
ጥግ ተቀምጦ ለሚታየኝ ወጣት
ሂድና ታዘዘው ስጠው አንድ ድራፍት
ቅዳለት ደብል ጂን ሃሳቡን ይርሳበት
በፂሙ መጎፈር በፀጉሩ መንጨብረር
ቁጥር ፈታ በሚል በግንባሩ መስመር
ይታየኛል ቋንቋ ይታየኛል ነገር
እዛም ከጨለማው ብቸኝነት ውጧት
ሲጋራዋን ይዛ ለቆመችው ወጣት
ሂድና ታዘዛት የሚጠጣ ስጣት
ምጋ በተፋችው በጭሶቹ መሃል
ሴትነት ሲበደል እህትነት ሲጣል
እናትነት ሲጎድል
ይታየኛል ቋንቋ ይታየኛል ፊደል።
፨፨፨
ምንጭ 👉
ኤፍሬም ስዩም
ሶልያና ከሚለው የግጥም ሲዲ የተወሰደ
@infinity_poems
@infinity_poems
👍 4
እኔ ወድሻለሁ
፨፨፨
እኔ ወድሻለሁ
ታስሮ እንደመፈታት
እንደጣኦስ ውበት
እንደዝሆን ብርታት
ዳዊትን ከጎልያድ
ደርቦ እንደመምታት
እኔ ወድሻለሁ
ጦም ውሎ እንደመጉረስ
ወልዶ እንደመታረስ
ቶምቦላ እንደመድረስ
ካላሙዲ ንብረት
ግማሽ እንደመውረስ
እኔ ወድሻለሁ
እንደመቅደስ እጣን
እንዳፍለኛ ስልጣን
እኔ ያንች ቡዳ
ያንች ልዝብ ሰይጣን፡፡
....
በዕውቀቱ ስዩም
(የማለዳ ድባብ)
@infinity_poems
@infinity_poems
👍 10
Выберите другой тариф
Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.