cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

መዝሙረ ማህሌት

✔ ይህ ትክክለኛው የቴሌግራም ቻናላችን ነው ። ➾ የእለት የእለቱን ምስባክ ፣ ➾ ለፕሮፋይል የሚሆኑ ፎቶዎች ፣ ➾ የእሁድ መዝሙር ፣ ➾አና ሌሎችም ያገኛሉ። join and share.

Больше
Рекламные посты
1 656
Подписчики
+524 часа
-27 дней
+4530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

አርውዮ ለትለሚሃ.mp35.78 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
ግጻዌ ዘሰንበት 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹     t.me/mezmur1999 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
Показать все...
መዝ ዎ በ፩ ይሰጠዎ-1625071538293.mp32.83 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
ግጻዌ ዘሰንበት 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹     t.me/mezmur1999 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
Показать все...
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 መዝሙር ይሰጠዎ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ከሐምሌ ፫ እስከ ሐምሌ ፱ ሃሌ ሉያ፤ይሠጠዎ ወይሰምዖ ጸሎቶ፤ለኲሉ ለዘሰአሎ፤እግዚአ ለሰንበት አምላከ ምሕረት፤ያርኁ ክረምተ በበዓመት፤ይሰምዑ ቃሎ ደመናት። አመላለስ፦ ያርኁ ክረምት በበዓመት/፪/ ይሰምዑ ቃሎ ደመናት/፬/ ትርጉም፦ ይመልስለታል የለመነውን ሁሉ ጸሎቱን ይሰማዋል የይቅርታ አምላክ የሰንበት ጌታ በየዓመቱ ክረምትን ይከፍታል (በጋና ክረምትን ያፈራርቃል) ደመናት ቃሉን ይሰማሉ። የዕለቱ ምንባባት ዕብራውያን ፮፥፯-ፍ:ም ፩.ጴጥ ፫፥፰-፲፭ ግብ:ሐዋ፲፬፥፰-፲፱ የዕለቱ ምስባክ፦ አርዊዮ ለትለሚሃ፤ ወአሥምሮ ለማዕረራ፤ ወበነጠብጣብከ ትበቊል ተፈሢሓ።መዝ ፷፬፥፲ ትርጉም፦ ትልሟን አርካው፤ መከሯንም አብጀው፤ በነጠብጣብህም ደስ ብሏት ትበቅላለች። ምሥጢር፦ የኢየሩሳሌም ትልሟን አርካው መከሯን የበጀ/የሚጠቅም አድርገው እንዲህ የሆነ ጠብ ጠብ ብሎ በሚዘንመው ዝናም ደስ ብሏት ተካክላ ትበቅላለች። ብርቱ ዝናም የዘነመ እንደሆነ ከነመሬቱ ድሶት (ጠራርጎት) ይሄዳል፤ ለሰስ ብሎ የወረደ እንደሆነ ደስ ብሏት ተካክላ ትበቅላለችና አንድም ልቡናዋን ደስ አሰኘው ሚጠተ ሥጋውን የበጀ አድርግላት በዘሩባቤል ደስ ብሏት ተካክላ ትወጣለች አንድም ነፍሷን ደስ አሰኘው ሚጠተ ነፍሷን የበጀ አድርገው ከቀኝ ጎንህ በፈሰሰ ጽሩይ ማይ ተጠምቃ ደስ እያላት ከሲኦል ወደገነት ትወጣለች የዕለቱ ወንጌል፦ ማቴ ፲፫፥፩ - ፴፩ ቅዳሴ፦  ዘእግዚእነ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹     t.me/mezmur1999 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
Показать все...
መዝሙረ ማህሌት

✔ ይህ ትክክለኛው የቴሌግራም ቻናላችን ነው ። ➾ የእለት የእለቱን ምስባክ ፣ ➾ ለፕሮፋይል የሚሆኑ ፎቶዎች ፣ ➾ የእሁድ መዝሙር ፣ ➾አና ሌሎችም ያገኛሉ። join and share.

Фото недоступноПоказать в Telegram
🕊                    💖                     🕊 [       ምን ልታዩ ወጣችሁ ?       ]                         🕊                        ❝ ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ ? ነቢይን ? አዎን እላችኋለሁ ፥ ከነቢይም የሚበልጠውን። እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና። እውነት እላችኋለሁ ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም ፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል። ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች ፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል። ❞ [ ማቴ . ፲፩ ፥ ፱ ] 🕊                        💖                     🕊 ❝ የአዋጅ ነጋሪ ቃል። የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ። ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል ፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል ፤ ጠማማውም ይቃናል ፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል ፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል ፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና። ❞ [ ኢሳ . ፵ ፥ ፫ ] [      🕊   እንኳን አደረሳችሁ   🕊      ] 🕊                        💖                       🕊
Показать все...
👍 7
🕊 † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † [ † እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ] † 🕊 ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ 🕊 †    ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: [ሉቃ.፩፥፮] የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ [አድናቆት] ይገባል ! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ ፺ [90] የዘካርያስ ፻ [100] ደግሞ ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት [ኢሳ.፵፥፫] (40:3) , [ሚል.፫፥፩] (3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው:: ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም ፳፮ [26] ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ፮ [6] ወራት ራሷን ሠወረች:: በ፮ [6] ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው:: የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ በዚህች ቀን [ሰኔ ፴] (30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል:: መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ + የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ + በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት + በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ + እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ + የጌታችንን መንገድ የጠረገ + ጌታውን ያጠመቀና + ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው:: ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች:: †  🕊  አባ ጌራን ሕንዳዊ  🕊  † ዳግመኛ በዚህች ቀን ሕንድ ካፈራቻቸው ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት ጻድቁ አባ ጌራን ይታሰባሉ:: የእኒህ ቅዱስ ታሪክ አሳዛኝ ነው:: ቅዱሱ በሕንድ ተወልደው: በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድገው: ገና በወጣትነታቸው መንነው: ደሴት ውስጥ ወደሚገኝ አንድ በርሃ ገብተዋል:: ከገድላቸው ጽናት: ከቅድስናቸውም ብዛት የተነሳ በሃገረ ሕንድ ሰይጣን እንዳይገባ: ጠብ ክርክር እንዲጠፋ: ሰው ሁሉ በፍቅርና በሰላም እንዲኖር ማድረግ ችለው በጣም ተወዳጅ ነበሩ:: በዚህ የተበሳጨ ሰይጣን ግን ባልጠረጠሩት መንገድ መጣባቸው:: አንዲት ሴት ወደ እርሳቸው መጥታ [የንጉሡ ልጅ ነኝ በሚል] አስጠግተዋት ነበር:: አንድ ሌሊት ላይ ግን አውሬ ያባረራት በመምሰል ሩጣ ወደ ቤታቸው ገብታ አቀፈቻቸው:: በዚያ ቅጽበት ፍጡር ደካማ ነውና ታላቁ አባ ጌራን ተሰነካከሉ:: ከአፍታ በሁዋላ የሆነውን ሲያውቁ ደም አለቀሱ:: ልብሳቸውን ቀደው: እንባቸው እንደ ዥረት እየፈሰሰ አለቀሱ:: ራሳቸውን በትልቅ ድንጋይ እየቀጠቀጡት የጭንቅላታቸውና የደረታቸው አጥንቶች ተሰባበሩ:: እርሱ እግዚአብሔር መሐሪ ነውና ይቅር ብሎ: የቅድስና ስም ሰጥቶ በዚሕች ቀን ወደ ገነት አሳርጉዋቸዋል:: ለዚህ ነው መጽሐፉ "ጻድቅ ፯ [7] ጊዜ ይወድቃልና: ይነሣማል" ያለው:: [ምሳ.፳፬፥፲፮] (24:16) አምላካችን ከቅዱሱ ቤተሰብና ከጻድቁ አባ ጌራን በረከት ይክፈለን:: 🕊 [ † ሰኔ ፴  [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት [ልደቱ] ፪. ቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ [ወላጆቹ] ፫. አባ ጌራን መስተጋድል [ሕንዳዊ] ፬. ቅዱሳት ደናግል ማርያና ማርታ [ከ፴፮ (36) ቱ ቅዱሳት አንስት-የአልዓዛር እህቶች] [ †  ወርኀዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ [ሐዋርያ] ፪. አባ ሣሉሲ ክቡር ፫. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት ፬. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት " ደግሞም አንተ ሕጻን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ:: መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሔዳለህና:: እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ:: ይሕም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው::" [ሉቃ.፩፥፸፮] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Показать все...
👍 3
ዘይገለብቦ ለሰማይ በደመና .mp37.33 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
ግጻዌ አመ በአተ ክረምት መዝሙር ደምጸ እገሪሁ ለዝናም 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹     t.me/mezmur1999 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
Показать все...
👍 2
መዝ ኒ በ፪ ደምፀ እገሪ-1625070566733.mp33.29 MB
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.