794
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
794
ቴሌግራም የቢዝነስ ሶሻል ሚዲያነት እየተቀየረ እንደሆነ ይታወቃል።
ቴሌግራም በዚህ አመት ካስተዋወቃቸው ፊቸሮች መካከል አንዱ Telegram business ነው ።
እነዚህ ፊቸርች ምን ምን እንደሆኑና ለምትጀምሩትን ቢዝነስ ምን ጠቀሜታ እንዳለው አንድ በአንድ ለማየት እንሞክር።
✅️Location: ቢዝነሳችሁን የምትሰሩበትን አካባቢ ሰዎች በቀላሉ እንዲውቁትና Google map ተጠቅመው እንዲመጡ ፕሮፋይላችሁ ላይ መሙላት ትችላላችሁ።
✅️ Opening houre: ቢዝነሳችሁን የምትከፍቱበትና የምትዘጉበትን ሰአት ሰዎች በቀላሉ እንዲያውቁት ፕሮፋይላችሁ ላይ መሙላት ትችላላችሁ።
✅️ Quick Replies:
ብዙ ሰዎች Contact የሚያድርጓችሁ ከሆነና ለሁሉም ተመሳሳይ አይነት መልዕክት የምትልኩ ከሆነ ሁሉንም አንድ በአንድ መፃፍ ሳይጠበቅባችሁ በshortcut መላክ ትችላላችሁ።
✅️Greeting message:
ሰዎች Contact ሲያደርጓችሁ የመጀመርያውን ቻት እናንተ መመለስ ሳይጠበቅባችሁ automatically በራሱ መልስ እንዲስጥ የምታደርጉበት ነው። ይህን ፊቸር ለመጠቀም የምትፈልጉትን ፅሁፍ አስቀድማችሁ መሙላት አለባችሁ።
✅️Away message:
ለተወሰነ ጊዜ online የማትገቡና ለሰዎች መልስ መስጠት የማትችሉ ከሆነ ሰዎች contact ሲያደርጓችሁ መልሲ እንዲሰጥላችሁ የፈለጋችሁትን መልዕክት መሙላት ትችላላችሁ።
✅️Links to chat:
አዳዲስ ሰዎች ቴሌግራም ላይ contact እንዲያደርጓችሁ ፈልጋችሁ ነገር ግን ዩሰርኔማችሁን ወይም ስልክ ቁጥራችሁን መስጠት ካልፈለጋችሁ ምንም ችግር የለም ይህን ፊቸር መጠቀም ትችላላችሁ። የተለያዩ ሊንኮችን በመፍጠርና ሊንኩን ለሰዎች share በማድረግ ዩሰርኔማችሁንና ስልክ ቁጥራችሁን መስጠት ሳይጠበቅባችሁ inbox እንዲያደርጉላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።
✅️Custom Intro: ሰዎች ለመጀመርያ ጊዜ ሊፅፉላችሁ ቻቱን ሲከፍቱት የሚመጣውን ፅሁፍና sticker እንደተመቻችሁ edit ማድረግ ትችላላችሁ።
✅️ChatBots: ቦት ካላችሁ አካውንታችሁ ላይ በማካተት ለሰዎች automatically መልስ እንዲሰጥ ማድረግ ትችላላችሁ።
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
💡 | @Endre_Techs ® 2024 | ሁሉንም በእጅዎ!
794
🔰 በአለማችን ትልቁ ዲጂታል የጠፈር ካሜራ
የሌሊት ሰማይን በበለጠ ለመቃኘት እና በከርሰ-ምድር ላይ ያሉ አስትሮይድስ ለመለየት ዝግጁ የሆነው የመጪው የቬራ ሩቢን ኦብዘርቫቶሪ ካሜራ ለእይታ በቅቷል። ይህ 3,200 ሜጋፒክስል አቅም ያለው ለሥነ ፈለግ ጥናት በዓለም ትልቁ ዲጂታል ካሜራ ሲሆን በቺሊ በሚገኘው ሩቢን ኦብዘርቫቶሪ ውስጥ ይገኛል።
#space #digitalcamera #camera #tech #technews
📣 | @TechBamargna
794
⚡️⚡️ Telegram
🌐Telegram ክፍያ ሊጀምር ነው።🌐
ቴሌግራም ቻናሎች ላይ ማስታወቂያዎችን ማስተላለፍ ሊጀምር ነው።
ከነዚህ ማስታወቂያዎች የሚገኘው ገቢም ለቻናል ባለቤቶች ግማሽ የሚያካፍል ይሆናል።
ለማስታወቂያው ብቁ የሚሆኑ public ቻናሎች ሲሆኑ ቢያንስ 1000 ሰብስክራይበሮች ሊኖራቸው ይገባል።
ክፍያው የሚፈፀመው በTON coin ሲሆን ያለምንም ክፍያ ወደ ton ዋሌታቸው መላክና ማውጣት እንደሚችሉ ተገልጿል።
የቻናሉን monetization states የቻናሉ owner channel settings > Statistics > minitization ውስጥ ገብቶ ማየት ይቻላል።
ለመመዝገብና የሰራነውን ገንዘብ ለማየት
✅1. fragment.com ላይ መግባት
✅2. Connect Telegram የሚለውን በመምረጥ telegram አካውንታችንን connect ማድረግ
✅3. Telegram Ads የሚል አዲስ የተጨመረ ምርጫ አለ እሱን በመንካት ማስታወቂያ ማስነገር ወይም በቻናላችን የሰራነውን ማውጣት እንችላለን።
የማስታወቂያው አይነት ከሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች ለየት ያለ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።
ይህም
✔️ በuser data ላይ መሰረት አያደርግም።
✔️ቪዲዮና ረዘም ያለ ፅሁፍ አይኖረውም።
✔️ፕሪምየም ቴሌግራም ያለው ሰው እነዚህን ማስታወቂያዎች አያይም።
ማስታወቂያ የሚተላለፍባቸው ቻናሎች እንደሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች የተለመደውን የኮፒራይት ህግን ማሟላት ይኖርባቸዋል።
✔️ ቻናሉ ላይ የሚተላለፈው original content መሆን አለበት።
❌ ከሌሎች ቻናሎች ወይም ሲሻል ሚዲያዎች ቀጥታ የተገለበጡ ኮንቴንቶች monetize አይሆኑም።
❌ ወሲብ ነክ ይዘት ያላቸው፣ የተሳሳተ መረጃና የጥላቻ ንግግር የሚያስተላልፉ ቻናሎችም ለማስታወቂያ ብቁ አይሆኑም።
✍️ምን ተሰማችሁ?
ልክ እንደ ▶️Youtube ብዙ ሰው በቴሌግራም ህይወቱ የሚቀየር ይመስላችኋል?
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
💡 | @Endre_Techs ® 2024 | ሁሉንም በእጅዎ!
794
✅ለ ቴሌግራም ቻናል ባለቤቶች መልካም ዜና
➡️የ Telegram ቻናል ባለቤቶች ክፍያ መቀበል ሊጀምሩ ነው Telegram ለሊቱን አዲስ Feature Monetization ክፍት አርገዋል የቻናል performance እየታየ ነው ክፍያው 👍
➡️Statics ነክታችሁ Monetization ያልመጣላችሁ Telegram Update አርጉ።
💎💎💎💎💎💎
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
💡 | @Endre_Techs ® 2024 | ሁሉንም በእጅዎ!
794
👉 PYTHON ለመማር ሚጠቅሙ መንገዶች
❇️ Python ከ high-level programming language ሚመደብ አንዱ ሲሆን በከፍተኛ ደረጃ እያደገ የመጣ ነው ።
❇️ It was founded in 1991 by developer Guido Van Rossum.
▶️ Learn Python Basics
╰┈➤ Syntax
╰┈➤ Variables
╰┈➤ Operators
╰┈➤ Loop
╰┈➤ Condition
╰┈➤ Function
▶️ Python Intermediate Level
╰┈➤ Object Oriented Programming
╰┈➤ Data Structures
╰┈➤ File Handling
╰┈➤ Error and Exception Handling
╰┈➤ Custom Exception
▶️ Python Advanced Level
╰┈➤ Working with modules
╰┈➤ Decorators
╰┈➤ Lambda Functions
╰┈➤ Comprehension
╰┈➤ SQLite Database
╰┈➤ API
▶️ Learn about Git/Github
╰┈➤ Version Control System
╰┈➤ Code Management
╰┈➤ Understanding Git/GitHub
╰┈➤ Preparing Github Repositories
╰┈➤ Uploading Projects on Github
▶️ Do some Python Projects
╰┈➤ Calender
╰┈➤ Alarm Clock with GUI
╰┈➤ Web Scrapper
╰┈➤ Bacon Desktop Apps
╰┈➤ Python Snake Game
━━━━━━━━━━━━━
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
💡 | @Endre_Techs ® 2024 | ሁሉንም በእጅዎ!
794
✅በApple እና Google መካከል AI ላይ መሰረት ያደረገ ስምምነት ሊደረግ ነው።
⚡️እንደ ብሉምበርግ ገለፃ Apple ከ Google ጋር በመተባበር የGemini AI ሞዴልን በ iPhone ስልኮች ላይ ለማካተት እየፈለገ ነው። ጎግል ከዚህ ቀደም ለSafari browser በ iPhones ላይ እንደ ተመራጭ የSearch engine አቅራቢነት ከአፕል ጋር ውል አለው።
⚡️Bloomberg ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎችን ጠቅሶ እንደገለጸው አፕል በዚህ አመት መጨረሻ ላይ ከIOS Update ጋር ተያይዞ በ AI የጎለበተ ባህሪያትን ለማስተዋወቅ የ Google AI ቴክን ፍቃድ ለመስጠት ይፈልጋል በተጨመሪም ኩባንያው የጂፒቲ ሞዴሎችን ለመጠቀም ከOpenAI ጋር ውይይት አድርጓል ተብሏል።
⚡️Apple አዲሱን የ Gemini AI ለተጠቃሚዎች መቼ ይፋ እንደሚሆን እና የትኞቹ ሞዴሎች ላይ እንደሚካተት ባይገለፅም በቅርቡ ተጨማሪ መረጃዎች እንደሚወጡ ይጠበቃል።
══════❁✿❁═══════
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
💡 | @Endre_Techs ® 2024 | ሁሉንም በእጅዎ!
794
✳️ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ያጋጠመዉ ችግር የሲስተም ጃር ፋይል ሶርስ ኮድ ላይ የፕሮግራሚንግ ቅደም ተከተሉ የተዛባ ሆኖ በመገኘቱ ነዉ ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታወቀ❗️
🔺በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ የተፈጠረው ክስተት ባንኩ በሞባይል ሲስተሙ ላይ ባደረገው የማሻሻያ ስራ የተከሰተ እንጂ ፤ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገር የተሰነዘረ የሳይበር ጥቃት አለመሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ አስታዉቋል፡፡
🔺የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ
ችግሩ የተፈጠረው ባንኩ የሲስተም ማሻሻያ በሚያደርግበት ወቅት ፤ ቀደም ብሎ የተጫነው ኮር ባንኪንግ ሲስተም ጥቅም ላይ የዋለ የስሌት ሞጁል በመውሰድ በሞባይል ባንኪንግ ሲስተሙ ላይ በቀጥታ ለመተግበር በተደረገ ሙከራ መሆኑን ባደረግነው ምርመራና ትንተና ደርሰንበታል ብለዋል።
🔺አስተዳደሩ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲስተም ጃር ፋይል ሶርስ ኮድ ላይ በተደረገው ምርምርና ትንተና የፕሮግራሚንግ ቅደም ተከተሉ የተዛባ ሆኖ በመገኘቱ ሲስተሙ ገንዘብ የሚያወጡ ደንበኞች ገንዘብ ሲያወጡ መቀነስ የነበረበትን የገንዘብ መጠን ሳይቀንስና ባላንስ ሳይሰራ ክፍያ በመፈፀሙ ነው፡፡ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ባንኩ የሳይበር ጥቃት እንደደረሰበት የሚናፈሱ መረጃዎች ከእውነት የራቁ መረጃዎች ናቸው ተብሏል፡፡
🔺በቀጣይ ተጨማሪ ምርመራና የፎረንሲክ ስራዎችን በማከናወን ውጤቱን ለህብረተሰቡ ይፋ ይደረጋልም ተብሏል፡፡
ምንጭ:- ዳጉ ጆርናል
794
✅የቴሌግራም🌐 መስራች Pavel Durov አስገራሚው የህይወት ታሪክ ።
- ክፍል 1
⚫️ የልጅነት ህይወት
🤔ፓቨል ቬልሪቪክ ዱሮቭ ጥቅምት 10, 1984 አ.ም እ.ኤ.አ በሌኒንግራድ ከተማ ሩስያ ውስጥ ተወለደ። በአባቱ ሩስያዊ በእናቱ ደግሞ ዩክሬናዊ የሆነው ፓቨል አብዛኛውን የልጅነት ጊዜውን ያሳለፈው የህክምና ዶክተር የሆነው አባቱ ተቀጥሮ በሚሰራባት የጣልያኗ ቱሪን ከተማ ሲሆን በ2006 አ.ም ከቅዱስ ፒተርስበርግዩኒቨርስቱ በፊሎሎጂ ተመረቀ።
⚫️ VK
🤔በ2006 አ.ም ፓቨል ከፕሮግራመር ወንድሙና ኢቭጌንቪክ ፔርኮፕስኪ ከተባለ ሌላ ኢንተርፕረነር ጋር በመሆን VK የተባለ የማህበራዊ ድረገፅ ፈጠሩ። ከፌስቡክ ጋር ተመሳሳይነት የነበረው ይህ ማህበራዊ ድረገፅም በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅና ስኬታማ በመሆኑ ፓቪልን ሩሲያዊው ዙከርበርግ የሚል ቅፅል ስም ሊያሰጠው ቻለ።
🤔ይህ ማህበራዊ ድረገፅም 3 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ያለው ትልቅ ድርጅት መሆን ቻለ። እስከ 2014 ድረስም VKን ባለቤትነትና በዋና ሃላፊነት በማገልገል ለትልቅ ስኬት አብቅቶታል።
🤔የዚህን ማህበራዊ ድረገፅ ተፅኖ ፈጣሪነት የተረዳው የሩስያ የስለላ መስርያ ቤት የተቃዋሚ ግለሰቦችን ገፅ እንዲዘጋና የዜጎችን ሚስጥራዊ መረጃዎች ለመንግስት አሳልፎ እንዲሰጥ ድርጅቱን መጠየቅ ጀመረ። ይህን ጥያቄም ፓቨል ፍፁም የሚቀበለው ጉዳይ ስላልሆነ ከሩስያ መንግስት ጋር አለመግባባት ተፈጠረ።
🤔በ2014 አ.ም የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በመጀመሩና የሩሲያ መንግስትም የዩክሬን ተቃዋሚዎችን መረጃ አሳልፎ እንዲሰጠው ድርጅቱን በመወትወቱ በዚሁ አመት april 1 ፓቨል ከመሰረተው ድርጅት የመልቀቂያ ወረቀት አስገባ። ድርጅቱም ደብዳቤውን ተቀብያለሁ ፓቨልም April 21 በይፋ ድርጅቱን ለቋል በማለት አሳወቀ።
(ፓቨል ቆይቶ በሰጠው ቃለመጠይቅ የመልቀቂያ ደብዳቤ ያስገባው ከምር ድርጅቱን ለመልቀቅ አስቦ ሳይሆን april the fool ለማለት እንደሆነና አጋጣሚውን በመጠቀም የፑቲን ሰዎች ህነ ብለው እንዳባረሩት ተናግሯል።)
🤔ዲሮቭ ሩስያ ውስጥ የኢንተርኔት ቢዝነስ በነፃነት ለመስራት እንደማይመች በመግለፅ ሃገሪቷን በፍጥነት ለቆ በመውጣት ድጋሚ ወደሩስያ የመመለስ ሃሳብ እንደሌለው ተናገረ።
⚫️ የቴሌግራም አመሰራረት
🤔ሩስያን ከለቀቀ በኋላ Saint Kitts and Nevis ከተባለች አነስተኛ ራስ ገዝ ደሴት ዜግነት አገኘ።
በጣም የሚያስገርመው የዚችን ደሴት ዜግነት ያገኘበት ምክንያት ለአንድ የደሴቲቱ የስኳር ፋብሪካ 250ሺ ዶላር እርዳታ በመስጠቱ ምክንያት ነው።
ከዚህ በኋላ በነጻነት ሌላ የማህበራዊ ሚዲያ መመስረት ላይ ትኩረት ማድረግ ጀመረ።
ይሄንም encrypt የሆነ የመልዕክት መላላኪያ አፕ በዚሁ አመት እውን አደረገ።
ክፍል 2 ይቀጥላል.... 🚨
©Big habesha
══════❁✿❁═══════
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
💡 | @Endre_Techs ® 2024 | ሁሉንም በእጅዎ!
794
#ለጥንቃቄ⚠️
እንዲህ ካሉ አጭበርባሪዎች ተጠንቀቁ።
ከላይ የምትሰሙት የድምፅ ቅጂ ከአንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተላከ ነው።
አጭበርባሪው ደዋይ ግለሰብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ #ዋናው_ቢሮ እንደደወለ በማስመሰል በኦንላይን ዘረፋ ለመፈፀም ሞክሯል።
የደወለው #የባንክ_ሰራተኛ ጋር መሆኑን አላወቀም ነበር።
ሰራተኛው ግለሰቡ የሚለፈልፈውን ሁሉ እስከ መጨረሻ ድረስ አዳመጠው።
በኃላም የአንድ የባንኩን ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ ስምን ይጠይቀዋል።
በዚህ ግዜ ከዋናው መ/ቤት ነኝ ያለው አጭበርባሪ ምን ይዋጠው ? መቀባጠር ይጀምራል።
በመጨረሻ ውርደቱን ተከናንቦ ስልኩን ዘግቷል።
እንዲህ ያሉ የማጭበርበር ስልቶች አንድ ሰሞን እንደጉድ ተበራክተው ነበር። አሁን ደግሞ ሰሞነኛውን የንግድ ባንክን ሁኔታ ተከትሎ እንደ አዲስ ተስፋፍተዋል።
ውድ ቤተሰቦቻችን ፦
* የማታውቋቸው የግል ስልኮችን ባለማንሳት ፣
* #የሚስጥር_ቁጥሮችን ባለመስጠት እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ። የሚመለከታቸው አካላትም ይህን ነገር እንደ ቀላል ከማየት የማጭበርበር ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች #በደወሉበት_ስልክ ክትትል በማድረግ ወደ ህግ ማቀረብ አለባቸው።
(የድምፅ ቅጂውን ለላከው የቤተሰባችን አባል ምስጋና እናቀርባለን)
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
|@Endre_Techs
@Endre_Techs
@Endre_Techs ® 2024 | ሁሉንም በእጅዎ
794
🧩Latest Tech News.
✳️Apple
🔺Apple አውሮፓ ውስጥ ለሚገኙ ተጠቃሚዎቹ ከWebsite ላይ Application ማውረድ እንዲችሉ ማድረጉን አሳውቋል።
🔺 Elon Musk X /Twitter ላይ በሚገኙ ፓስቶች ላይ የሚኖሩትን የ Reaction እና Retweet ቁጥር ማሳየት ሊያቆም እንደሚችል አሳውቋል።
✳️Microsoft
🔺ባሳለፍነው ሳምንት ሲዘገብ ከነበሩ ዜናዎች መካከል ማይክሮሶፍት በ ራሽያ ሀከሮች የተለያዩ ሶርስ ኮዶች እንደተሰረቁ አሳውቀዋል። እነዚ ቡድኖችም መረጃዎችን ከመውሰዳቸው በፊት የማይክሮሶፍት ስራ አስፈፃሚዎችን ሲሰልሉ ቆይተው ነበርም ብለዋል።
ምንጭ- Bloomberg
794
Repost from Enat Jobs
በአንድ የሀገራችን ባንክ ላይ ባጋጠመ የሞባይል ባንኪንግ ሲስተም ችግር ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ደረሰ።
ችግሩ የተከሰተው መጋቢት 6 ሌሊት ሲሆን የችግሩ መንስኤም በሞባይል አፕሊኬሽኑ update ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል። የሞባይል ባንኪንጉ ተጠቃሚዎች ገንዘብ በሚያዘዋውሩበት ጊዜ ከአካውንታቸው ተቀናሽ ባለማድረጉ ምክንያት ባንኩን ኪሳራ ላይ ሊጥል ችሏል።
በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎችም ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በነፃ ወደ ሌሎች ባንኮች ገንዘቦችን ሲያዘዋውሩ አድረዋል።
ይህ ዜና እስከተሰራበት ጊዜ ድረስ የዚህ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ ሲስተም አገልግሎት መስጠት ያቆመ ሲሆን ባንኩ የደረሰውን ችግር ወደነበረበት ለመመለስ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።
✅ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት📥
╔════════════╗
📚JOIN: @Endre_Academy
📚JOIN: @Endre_Academy
╚════════════╝
For Gread 12 students
@Ethio_High_School
@Ethio_High_School
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
794
#ተጠንቀቁ ⚠️
ከኦንላይ ዘራፊና አጭበርባሪዎች እራሳችሁን ጠብቁ።
ነገሩ እንዲህ ነው ...
ገንዘባቸውን ኦንላይን ተጭበርብረው የተበሉ ግለሰቦች መጀመሪያ በማያወቁት የውጭ ሀገር ስልክ ቁጥር በ #ዋትስአፕ / በ #ቴሌግራም መልዕክት ይደርሳቸዋል። ስልካቸውን / username እንዴት እንደሚያገኙት ባይታወቅም።
የሚደርሳቸው መልዕክት " ጥሩ የስራ እድል እንደሆነ ፣ በትንሽ ስራም ብዙ ትርፍ እንደሚያገኙ ፣ ይህ እድል ለነሱ የተመቻቸ " እንደሆነ የሚገልጽ ነው።
ቅድመ ክፍያ እንደሌለው ፤ ከ100 ብር አንስቶ እስከ 50 ሺህ ብር በቀን የሚያስገኝ እንደሆነም መልዕክቱ ይገልጻል።
እነዚህ አጭበርባሪዎች የሚያጭበረብሯቸው ሰዎች የሚያናግሩበት መንገድ ፍፁም ትህትና የተሞላበትና ፕሮፌሽናል በሆነ መንገድ ስለሆነ በተበዳይ ዘንድ ጥርጣሬ እንዳይጫር ያደርጋሉ።
ልክ የማግባባት ስራቸውን ከሰሩ በኃላ ትንሽ ተልዕኮ ሊሰጧቸው እንደሆነ በመግለፅ ወደ " ጎግል ማፕ/ ሎኬሽን " ገብተው ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አድራሻ ስር ጥሩ አስተያየት እንዲሰጡ ያዟቸዋል። (ይህ ከማጭበርበሪያ መንገድ አንዱ እንጂ ብቸኛው አይደለም)
የሚጭበረበረውም ሰው እጅግ በጣም ቀለል ያለ ስራ ስለሆነ የተሰጠውን ተልዕኮ መወጣቱን የሚገልጽ screenshot ለአጭበርባሪዎቹ ይልካል። እነሱም አካውንቱን ይጠይቃሉ።
ከዚህ በኃላ ነው ዋናው ጨዋታ የሚጀመረው።
ሰዎቹ ለተሰራው ስራ ክፍያ በሚል ከ300 - 1,000 ብር ከዚህም ከፍ ያለ ገንዘብ ያስገባሉ። ይህ ሰዎችን የማሳመኛና እንዳይጠራጠሩ ማድረጊያ መንገዳቸው ነው።
ይቀጥሉና ታስክ ይሰጣችኋል ስሩ ይላሉ። በተሰራው ስራ ልክም የተወሰነ ገንዘብ ይልካሉ። ይህ እንደ ሰውየው የመክፈል አቅም እየተገመገመ የሚደረግ ነው።
በዚህ መኃል ላይ " ኮሜርሻል ቤኔፊት " የሚል ነገር ያመጣሉ ይኸውም ከ1,000 ብር እስከ 1,000,000 ብር ሰዎች እንዲያስገቡ የሚጠይቅ ነው። ሰዎች ባስገቡት ብር ልክም በሰሩት ቀላል ስራ በፐርሰንት ትርፍ እንዳለው ይነገራቸዋል።
ለምሳሌ ፦ የሚጭበረበረው ሰው በዚህ ማታለያ ተታሎ 1000 ብር ቢያስገባ ሰዎቹ መልሰው በደቂቃ ውስጥ 1500 ብር አድርገው ያስገባሉ። (ይህ አንዱ የማሳመኛ መንገዳቸው ነው)
በዚህም የሚጭበረበረው ሰው ብሩን ከፍ በማድረግ ብዙ ትርፍ ለማግኘት ሲል በዛ እያደረገ ብር ይልካላቸዋል።
የተጭበርባሪውን ሰው የመክፍል አቅም ገምግመው አጭበርባሪዎቹ የተላከው ብር ላይ 500ም ይሁን 5000 ብር ጨምረውበት መልሰው ይልካሉ። (ይህን እድታምኗቸውና ብዙ ብር እንድታስገቡ ማሳመኛ ነው)
ድጋሚ ሌሎች ስራዎዥ ይላሉ በዚህም ከፍ ያለ ብር እንድታስገቡ ያደርጋሉ። የላካችሁትን ብር እንዳታጡ የሚሳጣችሁን ስራ እንድትወጡ ይጠየቃል። እናተም ብራችሁ ተበልቶ እንዳይቀር የብሩን መጠን ከፍ ወደማድረግ ትሄዳላችሁ። (በዚህ ሁሉ ሂደት ግን ሰዎቹ የምክፈል አቅማችሁን እያጠኑና ከፍ ያለ ብር ከቻሉ እስከ #ሚሊዮን ለመቀበል ጥረት ያደርጋሉ ስለሆነም በመሃል በመሃል የሰራችሁበትን እያሉ ያራሳችሁን ብር መልሰው ይልኩላችኃል)
የመክፈል አቅማችሁንም አይተው ለዚህ ማጭበርበር ስራ ታልሞ ብቻ ወደ ተከፈተው ግሩፕ እንድትገቡ ይደረጋል። (ሁሉም ግሩፑ ውስጥ ያለው አካውንት የአጭበርባሪዎቹ ነው)
እንዲህ እንዲህ እያለ በዛ ያለ ብር ከፈፀማችሁ በኃላ ስህተት ሰርታችኋልና እሱን ለማረም ስራችሁን ቀጥሉ ይላሉ። እናተም ብራችሁን ላለማጣት ውስብሰብ ችግር ውስጥ ትወድቃላችሁ።
በመጨረሻም እየተጭበረበራችሁ እንደሆነ ስታውቁ ታቆማላችሁ። ብራችሁም መና ሆኖ ይቀራል። ሰዎቹ ግን ብር አስገቡ ያኛውን ብር ለማስመለስ ማለታቸውን ይቀጥላሉ።
ብር የሚያስልኩት ኢትዮጵያ ባለ ሰው አካውንት ነው።
በዚህ መንገድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባጣራው ብቻ ከ150 ሺህ ብር እስከ 600 ሺህ ብር የተበሉ አሉ። ይህም የሰዎችን ህይወት አመሰቃቅሏል።
ለምሳሌ ፦ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ሆነው ስማቸውን በይፋ መግለፅ የሚያስፈልግ ሰዎች #የተጭበረበሩት የገንዘብ መጠን እንደሚከተለው ቀርቧል ፦
1. 600 ሺህ ብር
2. 470 ሺህ ብር
3. 300 ሺህ ብር
4. 300 ሺህ ብር
5. 150 ሺህ ብር
6. 150 ሺህ ብር
7. 100 ሺህ ብር
8. 80 ሺህ ብር
9. 80 ሺህ ብር
10. 65 ሺህ ብር
ይህ እጅግ በጣም ጥቂቱ ነው።
በመሆኑንም ፦
1ኛ. ማንኛውም የቴሌግራም ሆነ የዋትስአፕ የውጭ የማይታወቅ መልዕክት አትመልሱ።
2ኛ. በምንም ተአምር በትንሽ ብር ኢንቨስት አድርጉና ትርፍ አግኙ የሚሉ ሰዎችን አታናግሩ አትመኑ ተጠራጠሩ።
3ኛ. አሁንም በዚህ ውስብስብ ነገር ውስጥ ያላችሁ ተጨማሪ ብር እንዳትበሉ አቁሙ።
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
💡 | @Endre_Techs ® 2024 | ሁሉንም በእጅዎ!
794
✳️ዓባይ ባንክ 7 ሚሊዮን ብር ያወጣበትን አዲሱን የንግድ ምልክት (Logo) ይፋ አደረገ።
🔺ባንኩ ነባሩን የንግድ ምልክት እና መገለጫ የቀየረው በተለየ መልኩ የደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት እና ለእድገት እና ለፈጠራ ያለውን ትጋት ለማስረዳት በማሰብ ነው ተብሏል።
🔺አዲሱ የንግድ ምልክት የዓባይ ወንዝ ዋና መገለጫ ከሆነው የጢስ ዓባይ ፏፏቴ የተነሳ እና በሰባት አራት ማዕዘናዊ ቋሚ መስመሮች የተወከለ መሆኑን ተጠቅሷል፤ለስራውም 7 ሚሊዮን ብር ተከፍሏል ተብሏል።
🔺አዲሱ የንግድ ምልክት መገለጫው የደንበኞቹ ትልቅ የመሆን ተስፋ፣ ምኞት እና እቅድ ምንጭ በመሆን፤ ወደ ከፍታ ለመድረስ በሚደረግ ጉዞ የማያለሰልስ የባንኩን የፋይናንስ ድጋፍ መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ዓባይ ባንክ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ ሀብቱ 60 ቢሊዮን ብር፣ የተቀማጭ 48.6 ቢሊዮን ብር፣ የተከፈለ ካፒታል 5.8 ቢሊዮን ብር ፣ አጠቃላይ ካፒታሉ 8.7 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተነግሯል።ዓባይ ባንክ እስከ አሁን ድረስ ከ533 በላይ ቅርንጫፎች እና 3.2 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችም አሉኝ ብሏል።
ምንጭ-ሸገር FM
794
✅YouTube Premium Features ምንድነው ?
⚡️እንደ Normal የYoutube App ሳይሆን Premium ላይ ምንም አይነት Advertisement (ማስታወቂያ) ሳይመጣባችሁ መጠቀም ያስችላቹሃል።
⚡️በ Normal Youtube ላይ Music እያዳመጣችሁ ከ መተግበርያው ስትወጡ ሙዚቃው ይቋረጣል/Background ላይ play አያደርግም፤ በPremium Youtube ላይ ግን የፈለጋችሁትን Music ካስጀመራችሁ በኋላ ከ App ብትወጡ Background ላይ መስራቱን ይቀጥላል።
⚡️በተጨማሪም በPremium Youtube ላይ በNormal Youtube ላይ የማታገኟቸውን Series Film & Movies ማግኘት ትችላላችሁ።
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
💡 | @Endre_Techs ® 2024 | ሁሉንም በእጅዎ!
794
Repost from Enat Jobs
✔️አለማችን በቴክኖሎጂው የደረሰችበት❗️
🔵 የሰሞኑን አብይ ዜና:-
♈️በዓመት 30 ሺህ ህጻናትን በAi (በሰው ሰራሽ ክህሎት) ማህጸን የሚያመርተው ፋብሪካ።
🔺ወላጆች በቤተሙከራ የሚያድገው ልጃቸውን የአይን ቀለም፣ ቁመትና ባህሪ ጭምር መወሰን ይችላሉ ተብሏል።የህጻናቱን እድገትም በሞባይል ስልካቸው መከታተል እንደሚችሉ የጀርመኑ ኩባንያ ኢክቶ ላይፍ ገልጿል።
━━━━━━━━━━━
🔵 JOIN AND SHARE
| @Endre_Academy
| @Endre_Academy
🔴 ለHIGH SCHOOL ተማሪዎች
| @Ethio_High_school
⚫️ የቴክ መረጃዎችን ለማግኘት
| @Endre_Techs ® 2024|
━━━━━━━━━━━
794
🔴ትልቅ የ ዋጋ ለውጥ ተጨመረ ።
ገራሚ ዜና ይዘን ተመልሰናል😉 ።ማንኛውንም old group እንገዛለን ። እንገዛለን ስንል በቤተሰብ ዋጋ ነው ።
🔔2017✔️
🔔2018✔️
🔔2019✔️
🔔2020✔️
🔔2021✔️
🔔2022 all months
member አያስፈልግም 0 ቢሆንም እንገዛለን ምን አስጨነቃችሁ ድሮ ቴሌግራም group ከፍታቹሃል ማለት አሁን ሀብታም ናችሁ ማለት ነው። ብዛት ካለው ደሞ አስተያየት ይኖረዋል ።ይሄ ጭማሪ ለትንሽ ግዜ ነው ይፍጠኑ። Two Step verification 7 ቀን የሞላው መሆን አለበት ።
🔃 ለመሸጥ @ENDRE24 🥰 ያናግሩኝ inbox ።
794
✅በ 1 ሲም ካርድ እና የስልክ ቀፎ📲 ላይ ተጨማሪ 4 ቁጥሮችን አስተሳስረው፤ በዋናው ቁጥር የገዙትን የአየር ሰዓትና ጥቅል በማጋራት በራሳቸው ጥሪ፣ የፅሁፍ መልዕክት እና ዳታ መጠቀም የሚያስችልዎን የመልቲ ነምበር አገልግሎት!
📌ቁጥሮቻችሁን #Activate ለማስደረግ *136*2# ላይ ይደውሉ። (2 ቁጥር እንደናንተ የሲም ብዛት ተለዋዋጭ ናት)😊
📌ካልሆነ ደግሞ *136* አክቲቬት የሚሆነው ቁጥራችሁን አስገብታችሁ ከዛም # አድርጋችሁ በመደወል #Activate ማስደረግ ትችላላችሁ።
📌በቀጣዮቹ ቁጥሮች እንዳይደወልላችሁ ከፈለጋችሁ *135# ላይ መደወል ትችላላችሁ።
📌እንዲደዉልላችሁ ለመፍቀድ ድግሞ: *136* አድርጋችሁ መደወል ትችላላችሁ።
📌*138# ላይ ብትደውሉ ያላችሁን ቁጥሮች #በሙሉ ያሳያችኋል።
📌መልቲ ነምበር አገልግሎትን በተመለከተ ጥያቄ❓ ካላችሁ ኮመንት ላይ መጠየቅ ትችላላችሁ።
🦋#Share🦋
👩💻 @ethio_techs 👨💻 @ethio_techs 👩💻
794
💹ቤት ውስጥ ሆነን የተለያዩ ሰራዎችን በRemotely የምንሰራባቸው ዌብሳይቶች
1. UpWork
https://www.upwork.com/
2. TopTal
https://www.toptal.com/
3. Fiverr
https://www.fiverr.com/
4. Hired
https://hired.com/
5. PeoplePerHour
https://www.gettyimages.com/
══════════════════
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ
@Endre_Techs ® 2024
@Endre_Techs ® 2024
@Endre_Techs ® 2024
| ሁሉንም በእጅዎ!
