cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗ ║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣ ╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩ አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶች የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡ @ethio_leboled ✥--------------------✥ For your comment,feedback and promotion @Meki3 Thank you!

Больше
Рекламные посты
256
Подписчики
+224 часа
+47 дней
+1430 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
የዛሬው combo ላልጀመራቹ ጀምርዋት https://t.me/hamster_kombat_bOt/start?startapp=kentId5875888757
Показать все...
👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
⚡️HamsteKombat ✅ከNotcoin ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነው መልቲ ታፕ ስላላው እንደ Tapswap አሪፍ ነው ይሄኛውም ⚡️ በቅርቡ እስከ 50$ Reward ይኖራል ከአሁኑ ጀምሩ 🔗 https://t.me/hamster_kombaT_bot/start?startapp=kentId6405623892 ✅Bot ውስጥ እንደገባቹ play in 1 click የሚለውን ነክታቹ አስጀምሩ ✅ታስኮችን በመስራት ኮይን ማሳደግ ትችላላችሁ። ✅ትንሽ ኮይን እንደሰበሰባቹ Boost የሚለው ውስጥ በመግባት ታፕ የምትደረገው እና Recharge Speed አሳድጉ። ✅ Premium user 25k coin 😊 Normal user 5k coin @ethioleboled
Показать все...
.              ♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️             💞እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💞                     #የመጨረሻው_ክፍል ...🖊ፊርደዉስ የተሰማኝን መሰበር ስለተረዳችዉ ያን ሰሞን ከጎኔ አትጠፋም ነበር። ትምህርት እየቀረች ሁላ እኔ ትምህርት የሌሉኝን ሰዓቶች አብራኝ ታሳልፋለች። የኢክራም መንፈስ እየለቀቀኝ ነዉ መሰል ግጥም ፃፍኩ! ለፊርዱ አነበብኩላት "ፀሀዩ ጠቋቁሮ ፣ ሰማይ ጠል ለበሰ፣ የክህደትሽ ክፋት ብዕሬን ነቅንቆ ጉድሽን አዳረሰ። ዱላ አልማዘዝም ከድታኛለች ብዬ፣ እችልበታለሁ በብዕር መቅጣቱን በፍቅር አባብዬ" . እኔ ከጀርባዬ ሲሰራ የነበረዉን ድራማ እንዳወቅኩ ብሩኬም ሆነ ኢክራም እንዲያዉቁ አልፈለግኩም። ትንሽ ጊዜ ብሩኬ እና ኢክራም ላይ መዝናናት ፈለግኩ። ብሩኬን እንደድሮዉ በስርዓቱ አገኘዋለሁ! ቤቱ ሳይቀር እየሄድኩ አብሬዉ አሳልፋለሁ። የማዉቃቸዉን ነገሮች እጠይቀዋለሁ፣በዉሸቱ እዝናናለሁ። ኢክራምን ፌስቡክ ላይ እንደድሮዉ አወራታለሁ። ልክ ምንም እንዳልተፈጠረ! በነገራችን ላይ ፊርዱ የኢክራምን የፌስቡክ ፓስወርድ አሳይታኝ ስቄ አላባራሁም። "ብሩክ" ነበር ፓስወርዷ! ብሩክ የሚል ስም ይዞ አሁን ሰዉ እንደዚህ አይነት ተግባር ይፈፅማል? ለነገሩ በስም ከተባለ የነብይ ስም ይዘዉ እንዲህ ርካሽ ተግባር የሚፈፅሙም አይጠፉም። እምነት አንዴ ከተሸረሸረ መልሶ ማምጣት አይቻልም። ፈረንጆቹ እምነት እንደ ድንግልና ነዉ አንድ ጊዜ ከጠፋ መልሶ ማምጣት አይቻልም! የሚሉት ለዚህ ይመስለኛል። ጊዜዉ እየገፋ ሲመጣ ህመሙን ዉስጤ ማመቁ ስለሰለቸኝ ብሩኬን ላናግረዉ ወሰንኩ። . ብሩኬ ጋር ደወልኩለት! እነ ሄኖክ ሰፈር እንደሆነ እና ሲመለስ እንደሚደዉልልኝ ነገረኝ። እነ ሄኖክ ሰፈር ማለት እነ ኢክራም ሰፈር ማለት ነዉ። ከሷ ጋር እንደሆነ እርግጠኛ ሆንኩ። ሲመለስ ደወለልኝ። አገኘሁት። ሳየዉ ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ። እየሳቅኩ "የት ነበርክ?" አልኩት። በጥርጣሬ አይን እያየኝ "እዚሁ ነበርኩ ባክህ ማደያዉ ጋር!" ምናምን ብሎ ቀባጠረ። ዛሬ እዉነት እዉነቷን እንድናወራ ስለፈለግኩ በአይኔ የት እንደነበረ እንደማዉቅ የሚያሳይ ምልክት ሰጠሁት። የስነ አእምሮ ተማሪ ነኝ! ሰዉን በንግግሩ ዉስጥ ችግሩን ተረድቶ ማከም ነዉ የምማረዉ። ያወቅኩ መሆኑን ስለጠረጠረ እየሳቀ! "ባክህ ከሚስትህ ጋር ነበርኩ!" አለኝ። የሚስትነት ስሟን ለኔ፣ ተግባሩን ደግሞ ለሱ ከፋፍሎት መሆን አለበት ከሚስትህ ጋር ያለኝ! "ሚስትህ ስትል አስታወስከኝ ባይዘዌይ ሰሞኑን የሆነ ሰዉ አካዉንቷን ሀክ አድርጎት ነበርና ከብዙ ሰዉ ጋር ያደረገቻቸዉ ምልልሶች በሶፍት ኮፒ ተዘጋጅተዉ ሊላኩልኝ ነዉ!" አልኩት። ብሩኬ ደነገጠ! "ማነዉ ይሄ ባለጌ የሰዉ አካዉንት ሀክ የሚያደርገዉ?" አለኝ እየተበሳጨ። በዉስጤ እስቃለሁ። "አላወቅኩም ግን የሚጠቅምህን ነገር አግኝተንበታል ነዉ ያሉኝ! እነሱ ከኔ የሚፈልጉት ነገር ስላለ ጊቭ ኤንድ ቴክ መሆኑ ነዉ!" አልኩት ፊቱን እያነበብኩ። ከብሩኬ ጋር እያወራን የነበረዉ ዎክ እያደረግን ነበር። ዎክ እያደረግን እነ ረዊና ቤት አካባቢ ደረስን! ብሩኬ ወሬ ለማስቀየር ይሁን አላዉቅም "አንተ ግን እምነትን ልብላት ስልህ እምቢ አልክ አይደል?" አለኝ። የረዊናን እህት እምነትን ነዉ። ፈገግ ብዬ "ብሩኬ ቆይ ስንቱን ልተዉልህ?" አልኩት! ብሩኬ እንደድንጋይ ደርቆ "ማንን ተዉክልኝ?" አለኝ። እየሳቅኩ "ከእምነት ሌላ ምድር ላይ ያሉትን ሴቶች ሁሉ ትቼልሀለሁ!" ብዬ አስቀየስኩ። . ብሩኬ የኢክራም አካዉንት ሀክ መደረጉ በጣም አንገብግቦታል። "ፈዊዬ ጓደኛህ አይደለሁ! ቢያንስ የኔን እንዳይልኩልህ አድርግ!" አለኝ። "ያንተማ ቢላክልኝም ምንም ሚያስጨንቅህ ነገር የለም። እኔ ነኝ ማነበዉ! አንተ ከኔ ደብቀህ ከኢክራም ጋር የምታወራዉ ነገር ስለሌለ አትጨነቅ።" አልኩት። ከጀርባዬ ጭንቅላቱን ይዞ ቆሞ "ፈዉዛኔ ካነበብከዉ ያጣላናል!" አለኝ። የእዉነት እኔን ከመረጠ መጀመሪያ እሷን እንቢ አይልም ነበር! አንቺዉ ታመጪዉ አንቺዉ ታሮጪዉ አሉ! መጫወቱ ሲበቃኝ ወደ ብሩኬ ዞር ብዬ አይን አይኑን እያየሁ "ግን ምኗን ወደድከዉ?" አልኩት። ብሩክ ሁሉንም ማወቄን አረጋገጠ። "በቃ ሁሉንም እነግርሀለሁ!" አለኝ። ድራማዉ ከጀርባዬ ላለፉት ስምንት ወራት እየተተወነ እንደነበር ነገረኝ። ኢክራም ስለምታሳዝነኝ ነዉ ምናምን ብሎ ቀባጠረ! የእዉነት ቢያዝንላት የኔን ዉሳኔ እንድትተገብር ነበር ሊያበረታታት የሚገባዉ። "ብሩኬ እኔ ይቅርታ አድርጌልሀለሁ! ኢክራምን የምትወዳት ከሆነም ግንኙነታችሁን መቀጠል ትችላላችሁ!" አልኩት። ብሩኬን ላለፉት አስር አመታት አዉቀዋለሁ! በአንድ ሴት ምክንያት በቃኸኝ ልለዉ አልችልም። ምንም ዛሬ ቢከዳኝም ብዙ ከባባድ ጊዜዎቼን አብሬዉ አሳልፌያለሁ። ለኔ መልካም ሰዉ ነበር። ግን አንድ ፈተና ማለፍ አቃተዉ። . በቀጣዩ ቀን ከብሩኬ ጋር ተገናኝተን ስናወራ ስለሷ አዉርቶ መዘባረቅ ሲጀምር "ቆይ ግን እኔን እንደዛ እወድሀለሁ እያለች የከዳችኝ ኢክራም አንተን ዞራ እወድሀለሁ ስትልህ ነገ ወደ ሌላዉ እንደማትዞር በምን እርግጠኛ ሆንክ? ቢያንስ በኔ አትማርም?" አልኩት። "ባክህ እኔ አልወዳትም!" አለኝ። "ታዲያ ለምን እሺ አልካት?" "እሷ እወድሀለሁ አለችኛ!" በጣም ተበሳጨሁ! ቢያንስ ኢክራምን ወዷት ሴትነቷ አሳስቶት ቢከዳኝ እሺ! ግን እንዲሁ ለመንዘላዘል ነዉ ክህደት የሰራብኝ? ከምር አበሳጨኝ! እምቢ ማለት አለመቻል ትልቁ ዝቅጠት ነዉ። ጠጣ እሺ! ቃም እሺ! ጓደኛህን ክዳ እሺ! በጣም ያሳፍራል። ከብሩኬ ጋር እንደድሮዉ ለመሆን ብሞክርም በፍፁም ሊሳካልኝ አልቻለም። እምነት ከተሸረሸረ ትልቅ አደጋ ነዉ። . ኢክራም ያደረገችዉ ነገር ምንም አስቀያሚ ቢሆንም ልቤ ዉስጥ ቅንጣት ጥላቻ ሊፈጠር አልቻለም። አሁንም በጣም ታሳዝነኛለች። ምናልባት ፈጣሪዬ ከሱ ቀድቼ ለኢክራም የተናገርኩትን ወዶልኝ ይሆን? "ያለፈዉንም የሚመጣዉንም ጥፋትሽን ይቅር ብዬሻለሁ!" ያልኳትን። አይ እንደዉም የወደፊቱን ይቅር ማለት ከሱ ሌላ ማንም እንደማይችል እያሳየኝ ነዉ የሚሆነዉ! ግን አሁንም ለኢክራም ያለኝ እዝነት አልቀነሰም። አንድ ቀን ሁሉንም ነገር ማወቄን ፌስቡክ ላይ ነገርኳት። በጣም ደነገጠች። እኔ አሁንም የድሮዋን ጨዋዋን ኢክራም ለመሆን ብትሻ ላግዛት ዝግጁ ነኝ። ግን ኢክራም ክህደቷን መቋቋም አቃታት መሰለኝ ከፌስቡክ ብሎክ አደረገችኝ። የተበደልኩት እኔ! ዘራፍ ባዩ ሌላ! ይገርማል። ፈጣሪዬ ግን ማገናኘት ካሻዉ ማንም አያግደዉምና ብሎክ ባደረገችኝ በነጋታዉ መንገድ ላይ ተገጣጠምን። ዉስጤ ላይ ምንም ጥላቻ የለም። ልክ እንደድሮዉ ፈገግ አልኩላት! ፈገግታዬን ስታይ ወደኔ መጣች። ሰላም ከተባባልን በኋላ ስለትምህርቷ አወራን! እሷ ግን ከመወዛገቧ የተነሳ ስለያዝኩት ቦርሳ ዘባረቀች። ኢክራምን ከረጅም ጊዜ በኋላ በአካል አገኘኋት! እንደሚሉት የተጋነነ የአለባበስ ለዉጥ አላስተዋልኩም! በርግጥ ጅልባቡ ወልቆ ቀሚሱም ጠቧል። የጠበቅኩት የተጋነነ ስለነበር ነዉ መሰለኝ ብዙም አልደነገጥኩም! . አሁን የሚቆጨኝ እኔ ስበላሽ ከጎኔ ሆና ያረመችኝን ኢክራምን ዛሬ የክህደት እና የስነ ምግባር ዝቅጠት ዉስጥ ስትዘፈቅ ልታደጋት አለመቻሌ ነዉ። ለሰዉ ልጅ ክብር ወሳኙ ነገር ከማንነት መስመር የወጣን አፈንጋጭነት እንቢ ማለት መቻል ነዉ።
Показать все...
4 any comment @Meki3
Показать все...
1.61 KB
የመጀመሪያዉ ስህተት የኔ ነበር! ከፈጣሪ ትዕዛዝ ዉጪ ሴት ስተዋወቅ! ህይወቴ ዉስጥ ልጨምራት ከፈጣሪ ተጋፍቼ ያመጣኋት ኢክራም የነበረኝን ብሩክንም አሳጣችኝ። ጌታዬ ልክ ነበር! ተሳስቶም አያዉቅም! አይሳሳትምም! ኢክራም ዛሬም መልካም ለመሆን ቅንጣት እንኳ አልረፈደባትም። ወደለመዱት መልካምነት መመለስ ለኢክራም አይከብድም። ዛሬም የኢክራምን መልካም ስብዕና እናፍቃለሁ። የጋብቻ የጥሪ ካርዷን ስትልክልኝ አልማለሁ! እሷ ራሷ ከዘቀጡበት ፈልጋ ሰብስባ ያፀዳቻቸዉ ነብሶች ዛሬ እሷን እንደመታደግ ሲጠቋቆሙባት ሳይ እበሳጫለሁ። ኢክራም ከነክህደቷ ብዙ ንፁሀንን አፍርታለች። በጨዋዋ ኢክራም እጅ ንፅህናን የተቀበሉ በሙሉ ኢክራምን ወደነበረችበት ከፍታ የመመለስ ግዴታ አለባቸዉ። ብሩኬም መልካም ለመሆን ጊዜዉ አልረፈደበትም። ብሩኬ ለመበላሸቱ ምክንያት የሆኑትን ነገሮች ለማጤን ሞክሬ ነበር። ዋናዉ ፊልም ነዉ። ፊልሞቹን በከፊል ወስጄ ተመለከትኳቸዉ። ስሜት ተኮር ናቸዉ። "የሰዉ ልጅ የተመለከተዉን ነገር ይተገብራል" ይላል ስነ አእምሮ! የሰዉ ልጅ ባህሪዉን የሚገነባበት አንዱ መንገድ ሲደረግ ያየዉን በመማር (imitation) ነዉ። ብሩክ ለመበላሸቱ ይመለከታቸዉ የነበሩት ፊልሞች ግንባር ቀደም ምክንያት ናቸዉ። ሁለቱም ሰዎች ናቸዉ ተሳሳቱ! እኛ ስህተት ባይኖርብን ፈጣሪ እኛን አጥፍቶ ሌሎች የሚሳሳቱ ህዝቦችን ይፈጥር ነበር። ግን ዋናዉ ነገር ጥፋትን ተረድቶ ለመፅዳት መሞከር ነዉ። ጥፋቱ ክህደት ሆኖ ወንጀላቸዉን አገዘፈዉ እንጂ ብዙ መልካም ነገር ይኖራቸዋል። . ብርጭቆ መሬት ላይ ወድቆ ሲሰበር ከነበርኩበት የሀሳብ ሰመመን ነቃሁ! አንዱ ጠረዼዛ ላይ ያሉት ጥንዶች ናቸዉ የሰበሩት። ካፌዉ ዉስጥ አራቱ ቴብሎች ላይ ጥንዶች ተቀምጠዋል። ረሂማ እየሳቀች ወደኔ መጣች! ከኪሴ ልከፍል ብር እያወጣሁ ነበር። ረሂማ እየሳቀች "ወተቱስ?" አለችኝ። ወይኔ ለካ ቅድም ልታሞቀዉ ወስዳዉ ነበር እርስት አድርጌዋለሁ። "እሺ የታለ?" አልኳት እየሳቅኩ! "አሙቄዉ እዛ ቴብል ላይ ወተት ታዞ ነበር እና ለሱ የታዘዘ መስሏቸዉ ወሰዱት! አንተም ሙድህ ስለወረደ አዉቄ ነዉ ዝም ያልኩህ!" አለችኝ እየሳቀች። . ካፌዉ ዉስጥ ያሉትን ጥንዶች ተመለከትኳቸዉ! ይስቃሉ ፣ይጎነታተላሉ! እስከሚጣሉ ይጎነታተሉ አልኩ በልቤ! አዎ ተዋደዱ፣ከነፉ፣ተጣልተዉ አረፉ! ነዉ ከትዳር ዉጪ ያለ ፍቅቅሮሽ መዳረሻ። ሲከፋም የወንዱም የሴቷም ክብር በዝሙት ይገፈፍና ለንፁሀን የተከለከሉ ቆሻሻ መሆንን ነዉ የሚያተርፈዉ። . ፊርደዉስ ደወለችልኝ። አነሳሁት! "አንተ እዛ መቆዘሚያ ካፌህ ነህ አይደል?" አለችኝ። "አዎ ምነዉ ፊርዱ?" አልኳት "በዚህ ስሜት ዉስጥ ሆነህ መጠየቁ አግባብ ይሁን አይሁን አላዉቅም! ግን ፈዊ ፈቃደኛ ከሆንክ ካንተ ጋር ኒካህ ማሰር እፈልጋለሁ! ገንዘብ ምናምን የሚለዉ አያሳስብህ ነብዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) የመጀመሪያ ሚስታቸዉን ኸዲጃን(ረዐ) ሲያገቡ እሷ በጣም ሀብታም ነበረች! የእዉነት ሀይማኖተኛ ከሆንክ ይሄ አይጠፋህም" አለችኝ። የኔ አንበሳ ይሄን ታሪክ ማወቋ በራሱ አስገርሞኛል። እንዴት እንዴት ነዉ ያገናኘችዉ? ቆንጆ ፖለቲከኛ ይወጣታል። ደሞ ለሷ ኒካህ ምን አላት? እድሜ ለአባቷ! ገንዘብ እንደልቧ ነዉ። እኔ የማስተዳድራት እንጂ የምታስተዳድረኝ ሴት ማግባት አልፈልግም። "ፊርዱዬ ከኔ ጋር ወንድምነቱ ይሻለናል እሺ! እኔ ለጋብቻ ብቁ ነኝ ብዬ አላምንም!" አልኳት። ለጋብቻ ብቁ ሆኜ ቢሆንማ ኢክራምን እስከአሁን አግብቼ ነበር። "ፈዉዛን እኔ ምን ያንሰኛል? ዉበት ከፈለግክ ማንም አይጠጋኝም ታዉቃለህ! ገንዘብ አለኝ እንደፈለግክ አድርገዉ! ከማንም እኔ እሻልሀለሁ።" አለች እየተነጫነጨች። በራስ መተመመኗ እና ግልፅነቷ በጣም ደስ ይለኛል። "ፊርዱ እኔ አንቺ ምንም ይጎድልሻል አላልኩም ግን እኔ ብቁ አይደለሁም! ለሌላ ጊዜ ብቁ ስሆን ግን ከዉበትሽ እና ከገንዘብሽ በላይ ሀይማኖትሽ ላይ ያለሽን አቋም ስለምፈልገዉ እሱን አሻሽይ!" አልኳት እየሳቅኩ። "እሺ በቃ እንደድሮዉ!" አለችኝ እንዳንኮራረፍ ፈርታ። "እሺ ፊርዱ ፈታ በይ!" አልኳትና ስልኩን ዘጋሁት። ረሂማ ሚስተናገድ ሰዉ የለም መሰለኝ አጠገቤ መጥታ "አንተ ግን ዛሬ ምን ሆነህ ነዉ?" አለች። መልሴን ሳትጠብቅ ወዲያዉ ስልኬን ከጠረጴዛ ላይ አንስታ ሰዓት አየች። እግረ መንገዷን ሰሞኑን የፃፍኩትን ግጥም ዋልፔፐር አድርጌዉ ስለነበር አየችዉ። እየሳቀች ጮክ ብላ አነበበችዉ "ስምሽ ጎዳደፈ አነሱሽ በክፉ፣ ከንፈር ማሳበጤ ይሄ ነዉ ወይ ትርፉ? ደግሜ ብስምሽ ይፀዳ ይሆን ወይ የህሊና እድፉ!" አሽኮረመመችኝ! ረሂማ ወዲያዉ ተስተናጋጅ ስለመጣ ትታኝ ሄደች። ወዲያዉ ስልኬ ጠራ! ረዊና ነበረች። አነሳሁት። "ፈዉዛኔ የት ነህ? አዲስ አበባ መጥቻለሁ!" አለችኝ። ረዊና ንፁህ እህቴ ናት! ሁሉንም ነገር ለሷ መተንፈስ ነበር የሚቀለኝ። "ስማ ከትምህርት ቤቱ ጀርባ ያለዉ ልብስ ቤት ነኝ! አትመጣም?" አለች! "መጣሁ!" ብያት ከካፌዉ ተነስቼ ወጣሁ። ከመሸሸጊያዬ ወጣሁ! የወዳጅ ጦር ቅርብ ርቀት ላይ ነዉ። ንፁህ እህትነት! ረዊና!           ♾#ተፈፀመ♾ እውነተኛ ታሪክ ስለሆነ  እንደድርሰት ልቦለዶች መጨረሻቸውን  አላሳመርነውም ምክንያቱም እውነተኛ ታሪክ  የእውነት ስለሚቀመጥ   ሁሉም ታሪኮች ፍፃሜያቸው አያምርም  ከታሪኩ የምንማረውን እንማራለን የምንቀስመውን እንቀስማለን። አንብባችሁ ከወደዳችሁት  ያላችሁን ሀሳብ አስቀምጡልኝ Like አርጉልን እኛ ሺ ፊደል ተጭነናል ፡                       ,,, ✦━━
Показать все...
👍 1
እሱም የቀድሞ ፍቅረኛዉን የሪሀናን ጓደኛ እና የአስር አመታት ጓደኛዉን የእኔን የትዳር ቅዠት ሲያማግጥ ህሊናዉ እንዴት ዝም አለዉ? ደግሞ እኮ ቃል በቃል "ኢክሩ እንድታገባ እንጂ ከማንም ወንድ ጋር እንድትንዘላዘል አይደለም የተዉኳት!" ብዬዋለሁ። አደራ ብዬዉም ነበር! ጌታዬ ሆይ በከለከልከኝ መንገድ ላይ ተጉዤ የነገድኩት ንግድ ኪሳራን እንጂ አላተረፈልኝም! . ፊርደዉስ ቁርሱን ሰርታ አቀራርባ እንድንበላ ልትጠራኝ ስትመጣ አልጋዉ ላይ ተዘርሬያለሁ። ከአይኔ እንባ ይጎርፋል። እንሰቀሰቃለሁ። "ፈዉዛኔ ምን ሆንክብኝ?" አለች እየተንደረደረች መጥታ አንገቴን ቀና እያደረገች። በጣቶቼ ላፕቶፑን ጠቆምኳት። ሄዳ አነበበችዉ። ፊቷ ደም እንደለበሰ ወደኔ ዞራ "ብሩክ አንተን ከዳህ?" አለችኝ ስለ ብሩክ ታዉቅ ነበር። ፊርደዉስ ከኔ በላይ መበሳጨት ጀመረች። "ለኢክራም እኮ መልአክ ነበርክ ፈዊ! ምላሿ ይሄ ነዉ?" አለችኝ ንዴቷ ይበልጡኑ እየተቀጣጠለ። አልጋዉ ላይ ከወገቤ ቀና ብዬ ተስተካክዬ እየተቀመጥኩ "ብዙ ጊዜ ያለመድሽዉ ዉሻ ነዉ የሚነክስሽ!" አልኳት። "ፈዊ ኢክሩን ቆንጆ ቅጣት ልትቀጣት ይገባል!" አለች ፊርደዉስ ግድግዳዉን እየደበደበች እንደ እብድ ጮክ ብዬ እየሳቅኩ "ኢክራም እኮ ቅጣት አያስፈልጋትም እኔን ከድታ ብሩኬ ላይ የወደቀች ቀን ራሷን ቀጥታለች። ንፁህ ልቤን ረግጣ ፊልም ላይ ስትመለከተዉ የኖረችዉን ዝቅጠት ለመተግበር ስትሞክር እና ከቅዱሳን ተራ ስትወጣ ያኔ ራሷን ቀጥታለች። እኔ መቅጣት አይጠበቅብኝም። የሚታዘንላት ለንግስትነት የታጨች ዉብ ከመሆን ማንም እንዳሻዉ የሚጨልፋት ርካሽ መሆንን ስትመርጥ ያኔ ራሷን ቀጥታለች።" ንግግሬ ሲያልቅ ሰዉነቴ መንዘፍዘፍ ጀመረ። እየተንሰቀሰቅኩ አለቀስኩ። በህይወቴ እንዲህ ያለቀስኩባቸዉ ቀናት ዛሬ እና ኢክሩ ልታገባ ስትል ናቸዉ። ሁለቱም በኢክሩ ምክንያት! ደካማ ጎኔ ሴት ናት! ከሴት ደግሞ ኢክራም! ፊርደዉስ ለቅሶዬ ሲበረታ አልጋዉ ላይ ከጎኔ ቁጭ ብላ ማባበል ጀመረች። በእጆቿ እንባዬን ጠረገችልኝ። ደንዝዣለሁ። ብደበደብም የሚሰማኝ አይመስለኝም። ፊርደዉስ እጆቿን ወደ አንገቴ ወሰደቻቸዉ። ከንፈሬ ላይ ተለጠፈች። እኔ አያታለሁ ላስቆማት አልቻልኩም ደንዝዣለሁ! አይኔ እያየ ስልኳን አዉጥታ ከንፈሬ ላይ እንደተጣበቀች ሰልፊ ፎቶ አነሳች። ፊርደዉስ ዉርርዷን ፈፀመችብኝ። አደነቅኳት። ምንም የስነ አእምሮ ምሁር ብትሆን ሴት ልጅን ተንኮል አትበልጣትም። ዛሬ ካፌ ሳይሆን ቤት እንድንገናኝ ያደረገችዉ አጋጣሚዉን ለመጠቀም ብላ ነበር። በንፁህ አእምሮ ብሆን ኖሮ ሁሉም ይገባኝ ነበር። ግን የኢክራምን ጉድ ለማየት መጓጓቴን ፊርዱ ተጠቀመችበት። ፊርዱ ባደረገችዉ ነገር ምንም አልተቀየምኳትም። እልህ ተያይዘን ነበር! እሷ አሸነፈች አለቀ! አእምሮዬ ሲረጋጋ ፊርዱን በአክብሮት እንድታቆም ጠየቅኳት። ወዲያዉ አቆመች። አየኋት ቆንጆ ናት! ከኢክራምም የበለጠች ቆንጆ! ግን በሰዓቱ በፍፁም ስለሴት ማሰብ ስላልፈለግኩ ትቻት ወደ ሳሎን ሄድኩ። ፊርዱ የሰራችዉ ቁርስ ላይ እልሄን ተወጣሁበት! ፊርዱም መጥታ አብረን በልተን ተያይዘን ከቤቱ ወጣን!
Показать все...
♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️             💞እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💞                           #ክፍል_16 ኢክሩ እኔ ጋር አትደዉልም ግን ብሩኬ ጋር ትደዉላለች። እሱም ይደዉልላታል። አንድ ቀን እነ ብሩኬ ቤት ሆነን ብሩኬ ኢኩን ችላ ሳይል እንዲያማክራት አደራ አልኩት። እሱም አደራዉን ተቀበለ። ኢክራም ወደ ትዳር ህይወት እንድትገባ ብዬ እንደተዉኳት ያዉቃል። ስለዚህ ከማንም ጋር እንዳትንዘላዘል መምከር አያቅተዉም ብዬ አስባለሁ። . በቀጣዩ ሳምንት ልጆቹን ለመተዋወቅ ወደ ተቀጣጠርንበት ከስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ዋናዉ በር ፊት ለፊት ወዳለዉ መናፈሻ ሄድኩ።ከአንድ ዛፍ ስር ያለ ወንበር ላይ የተቀመጠች ቀይ ሴት እጇን አዉለበለበችልኝ። እኔ ሁለት ሴቶች እንደሚጠብቁኝ ነበር የተነገረኝ። "ፈዉዛን ዌልካም!!" አለችኝ ከመቀመጫዋ ተነስታ እንድቀመጥ እየጋበዘችኝ። "ሁለት ሰዉ እንደሚጠብቀኝ ነበር የተነገረኝ!!" አልኳት። "አዎ ነዉ ግን ዛሬ ለምናወራዉ ነገር የሜሮን መኖር አስፈላጊ ስላልሆነ ነዉ ብቻዬን የመጣሁት!!" አለችኝ። "ባይዘዌይ ፊርደዉስ እባላለሁ!!" አለች የአክብሮት ፈገግታ እያሳየችኝ። አየኋት በጣም ቆንጆ ናት! በጣም!! ከኢክሩ ሌላ ቆንጆ ነበር እንዴ? የእዉነት በጣም ዉብ ናት። የለበሰችዉ ቀሚስ ሰፋ ያለ ነዉ። አይጨንቅም!! በጣም ልብሱን አሳምራዋለች። "እና እንደዚህ ዉብ ሆነሽ ፊርደዉስ ካላሉ ምን ብለዉ ስም ሊያወጡልሽ ነበር?" አልኳት እየሳቅኩ ፊርደዉስ ሳቋን ለቀቀችዉ!! ጉንጯ ላይ ስርጉድ አለ። ወይኔ በቃ ይህቺ ልጅ ልቤን ልታሰረጉደዉ ነዉ። ፊርደዉስ ከጀነት በጣም ያማረዉ ጀነት ነዉ። ጀነት እንደሆቴል ባለ4 ባለ5 ኮከብ እንደምንለዉ ይለያያል። ሰው እንደስራዉ ምርጡ ላይ ይገባል። ስሟ እና ዉበቷ በጣም የተስማማ ነዉ። ፊርደዉስ ስቃ ስትጨርስ"ፈዉዛን መንገድ ላይ ነበር ያየሁህ! ከዛም ከሰዎች ስላንተ አንዳንድ መረጃዎችን አገኘሁ!!" አለችኝ። ፈገግ አለችና እጇን እየዘረጋችልኝ ያዘዉ አለችኝ። ይሄ ነገር ወዴት ወዴት እየሄደ እንደሆነ ግራ ገባኝ። "ይቅርታ ሴት አልጨብጥም!!" አልኳት "ለምን?" አለችኝ የእዉነት የእስልምና እምነት ተከታይ አልመስልህ አለችኝ። ሙስሊም ሆና ይህን አለማወቋ አሳዘነኝ። "ቁርዓን ላይ ማን ማንን መንካት እንደተፈቀደልሽ ተፅፏል አንብቢዉ!!" አልኳት። "እሺ ለዛሬ ብቻ ጨብጠኝ!!"አለችኝ በአይኖቿ እየተለማመጠችኝ። አለንጋ ጣቶቿን ፊቴ ድረስ አስጠጋቻቸዉ። የአይኗን እንቅስቃሴ በሚገባ አጤንኩት ይዞር ይዞርና ወደ ግራ እየሰረቀ ያያል። የስነ አእምሮ ተማሪ እንደመሆኔ በግራ በኩል የሚያየን ሰዉ እንዳለ ገመትኩ። ዞር ስል አንዲት ሴት የስልኳን ካሜራ አነጣጥራ እየቀረፀችን ነዉ። . ያላየሁ መስዬ "ፊርደዉስ ሪያሊቲ ሾዉ ለመስራት አስበሽ ነዉ እንዴ የጠራሽኝ?" አልኳት ወዲያዉ እንደባነንኩ ስለገባት ጓደኛዋ መቅረፅ እንድታቆም በእጇ ምልክት ሰጠቻት። . "ፈዉዛን በጣም ይቅርታ!! በቃ እዉነቱን እነግርሀለሁ!"አለችኝ የመሸነፍ ስሜት እየታየባት እኔ የሰዉነቷን እንቅስቃሴ እና የምትመርጣቸዉን ቃላት በማዳመጥ የምታወራዉ እዉነት መሆን እና አለመሆኑን ለማጤን ተዘጋጀሁ። "ፈዉዛን እኔ የሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ተማሪ ነኝ። እኛ ባች ዉስጥ "አይ ዊል ዱ ኢት" የሚባል ሙድ አለ።አንድ ቀን ጓደኛሞች አንድ ላይ ሆነን የኛ ጓደኛ ልትጨብጥህ ስትል ሴት አልጨብጥም ስትላት አየሁ። እና እኔ "አይ ዊል ዱ ኢት" አልኩ። እኔ አንተን በግድ እንድትጨብጠኝ ላደርግህ ከነሱ ጋር ተወራረድኩ።"አለችኝ። "ዉርርዱን ባትፈፅሚ ምን ይከተልሻል?" አልኳት በጣም አሳዘነችኝ! "ለኔ ዉርደት ነዉማንንም የሚያንበረክክ ዉበት አለኝ!! ጓደኞቼ መቀለጃ ነዉ የሚያደርጉኝ የምፈራቸዉ እነዚህን ነዉ ሲቀጥል ሁሉንም ሸራተን እራት ለመጋበዝ እገደዳለሁ።" አለችኝ። ሁለት ነገሮች አስገረሙኝ በዉበቷ እርግጠኛ መሆኗ እና ሀንዳዉት ኮፒ ማድረጊያ ያጡ በሞሉባት ሀገር ለቀልድ ሸራተን ራት የሚገባበዙ ተማሪዎች መኖራቸዉ። ደግሞ እኮ እራት መጋበዙ ለሷ ቀላል ነዉ። ያስፈራት ሙድ መያዣ መሆኑ ነዉ። "ልትጨብጪኝ ብቻ ነዉ የፈለግሽዉ?" አልኳት ድርድሩ ለመጨባበጥ ብቻ የተደረገ አለመሆኑን ከመቀጮዉ ስለተረዳሁ። እንደማፈር እያለች"አይደለም ከንፈርህን መሳም ነዉ ዉርርዱ አለችኝ።" ከወንበሬ እየተነሳሁ "እንዳታስቢዉ!!" አልኳት። ፊቷ በእልህ እየቀላ "ፈዉዛን ታደርገዋለህ!!"አለችኝ። በተቀመጠችበት ትቻት ሄድኩ።. ሰዓታት ምንም የሰዉ ልጅ ለዉጥ ቢፈጥርም ባይፈጥርም ከመቁጠር አይወገዱም። ተኝተንም እንዋል በስራ ተጠመድን ቀን ይነጉዳል።እንደቀልድ አመት አለቀ ይባላል። ከኢክራም ጋር የፍቅር ግንኙነታችንን ካቋረጥን ከሶስት ወራት በላይ ተቆጠሩ። በወንድምነት የነበረንንም ትስስር ኢክሩ ካቆረፈደችዉ ሁለት ወር ሆነ። የዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ አመት ትምህርቴን አጠናቅቄ ክረምቱን እየቦዘንኩ ነበር አንዳንዴ እዚህ ካፌ እየመጣሁ ከረሂማ ጋር እጫወታለሁ።አንዳንዴ ብሩኬ ጋር እየሄድኩ እደበራለሁ።በዛ ሰሞን ግን ለተለያዩ ተቋሞች የስነ ፅሁፍ ስራዎችን ድህረ ገፃቸዉ ላይ በመስራት ተጠምጄ ስለነበር ኢንተርኔት ላይ ተጥጄ እዉል ነበር። አንድ ቀን እንደተለመደዉ ኢንተርኔት ላይ ተጥጄ ከማላዉቀዉ ሰዉ መልዕክት ደረሰኝ። ልጁ ሰላምታ እንደተለዋወጥን "ፈዉዛኔ እኔ ሰፈር አካባቢ አዉቅሀለሁ። ከኢክሩ ጋርም ግንኙነት እንደነበራችሁ አዉቃለሁ። አሁን የፍቅር ግንኙነት ዉስጥ ናችሁ እንዴ?"የሚል መልዕክት ላከልኝ። ወዲያዉ "እኔና እሷ መገናኘት ካቆምን በጣም ቆይቷል። በመካከላችን ምንም አይነት ግንኙነት የለም።"አልኩት። ልጁ አመስግኖ ተሰናበተኝ።ትንሽ ቆይቼ አሰብኩና በመልሴ ተፀፀትኩ። ፍቅረኛዬ ናት ነበር ማለት የነበረብኝ።ኢክሩን ከዚህ በኋላ አግብታ እንጂ ከማንም ወንድ ጋር ስትንዘላዘል ማየት አልፈልግም። ልጁ ጥያቄ ደግሞ ከተዉካት ልዉሰዳት አይነት ነዉ። ማንም የጣለዉን ሲያነሱበት አይወድም። ሊያዉም እንድታገባ የምመኝላትን ሴት አብራዉ ስትንዘላዘል ማየት ያመኛል። ዉስጤ ሰላም አጣ።የኢክሩን የፌስቡክ ገፅ ለመጎብኘት ገባሁ አንፍሬንድ እንደተደረግኩ ነዉ።ላወራትና ከልጁ ላስጥላት ፈለግኩ። . ከኢክሩ ጋር ከሶስት ወራት በኋላ ድጋሚ ፌስቡክ ላይ አወራን።ስላለችበት ሁኔታ አንዳንድ ነገሮችን ጠየቅኳት።እንደድሮዉ በመካከላችን ሰላም አዉርደን በወንድምነት እንድንቀጥል ጠየቅኳት። መልዕክቱን የላኩላት በእንግሊዘኛ ስለነበር የፍቅር ግንኙነታችንን ድጋሚ መልሰን እንቀጥል ያልኳት መስሏት እንዲህ አለችኝ ፦"እኔ ስትፈልግ የምትጥለኝ ስትፈልግ የምታነሳኝ እቃ አይደለሁም።አሁን ከሌላ ሰዉ ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምሬያለሁ።" ደነገጥኩ!እሞትልሀለሁ ስትለኝ የነበረችዉ ኢክሩ ናት በሁለት ወር ዉስጥ ከህይወቷ ማህደር ፍቃኝ ከሌላ ወንድ ጋር ፍቅቅሮሽ የጀመረችዉ?ወይስ ሲጀመርም አፈቀርን ሲሉ ሰምታ እንጂ ፍቅር ምን እንደሆነ እንኳ አታዉቅም? እንዴ እኔ እኮ ኢክሩ ግጥም ስለማትወድ ብዬ ግጥም መፃፍ ያቆምኩኝ ይኸዉ እስከአሁን ግጥም አልፃፍኩም።ቆሻሻ ላይ የተወለደ ፍቅር ንፅህና ሊኖረዉ እንደማይችል ግልፅ ነበር።ትዳር ላይ ያልተመሰረተ ግንኙነት ፍሬ ሊያፈራ አይችልም። ኢክሩ እንዴት እኔን ረስታ ሌላ ወንድ ጋር ለመሄድ ደፈረች?እኔ እኮ እንኳን ልረሳት በጣም ስትስቅ የሚሸበሸበዉ አፍንጫዋ አሁንም አይኔ ላይ አለ።ኢክሩ እኮ እየተኮላተፈች 'ደ' ስትል አሁንም ጆሮዬ ላይ ይደጋገማልነጠብጣብ ዛሬ ማታ 3 ሰአት ላይ ፍፃሜው ያገኛል
Показать все...