cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

💒ቤተ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ⛪️💒💒

ዘየአቅበነ፡፡ኢይነውም ወኢዴቅስ፡ የሚጠብቀን፡አይተኛም፡አያንቀላፋም።

Больше
Рекламные посты
198
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
-530 дноК

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ    ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ✍የዛሬው ትምህርት ስለ መራኁት ነው።መራኁት የሚለው ቃል መርኆ ከሚለው የግዕዝ ቃል የመጣ ሲሆን መርኆ ማለት መክፈቻ ማለት ሲሆን መራኁት ማለት ደግሞ መክፈቻዎች ማለት ነው። መራኁት የሚባሉት ፭ናቸው።  ✍፭ቱ የመራኁት አገልግሎታቸው የግስ መነሻ፣ የአርእስትና የሠራዊት በር ከፋቶች መሆን ወይም  የቃል መነሻ መሆን ነው ✍አርስት፦ ስንል አለቆች እንደ ማለት ነው።  ቀተለ፣ቀደሰ፣ …የመሳሰሉት።ለግሶች ኹሉ እንደ  አርእስት ኹነው ግሶቹሁሉ በእነዛ አመል ልክ ይገሰሳሉ  ማለት ነው ✍ሰራዊት፦ በቀተለ፣በቀደሰ፣በገብረ ውስጥ ተካተው የሚገኙ ናቸው። ✍ለነዚህ በር ከፋች የሚሆኑ ፭ቱ መራኁት  ናቸው። እነዚህ ፭ መራኁት  በግስ ጊዜ መነሻ እየሆኑ የሚያገለግሉ ናቸው። ፭ቱ መራኁት የሚባሉት 👇 ፩፦ ግዕዝ ፪፦ ራብዕ ፫፦ኃምስ ፬፦ ሳድስ ፭፦ ሳብዕ እነዚህ ፭ቱ መራኁት የግስ መነሻ በመባል  ይታወቃሉ። ግስ ማለት አንቀጽ እንደማለት ነው። ለምሳሌ 🌷ግዕዝ 🌷 ሀ፣ለ፣ሐ፣መ፣ሠ፣ረ፣ እነዚህ የመሳሰሉት ግዕዝን ይወክላሉ። ሀ፦ 👉ግዕዝ ፡ 👉አንደኛ ሁ፦👉ካዕብ  ፥ 👉ኹለተኛ ሂ፦ 👉ሣልስ ፦ 👉ሦስተኛ ሃ፦ 👉ራብዕ ፦ 👉ዐራተኛ ሄ፦👉 ኃምስ  ፦ 👉አምስተኛ ህ፦ 👉ሣድስ ፦ 👉ሥድስተኛ ሆ፦ 👉ሳብዕ ፦ 👉ሰባተኛ ግስ በግዕዝ ሲነሣ 🌷ሀለሐ ፦ወደረ 🌷ሰብሐ፦አመሰገነ 🌷 🌷ለህሐ ፦ጻፈ🌷 🌷ለቅሐ ፦ አበደረ 🌷 እነዚህ መራኁቶች የግዕዝ መነሻነታቸውን ነው የሚፈልጉት። ለምሳሌ ሤመ ብንል ግእዝ አይሆንም ምክንያቱም መነሻ ፊደሉ ኃምስ ስለሆነ ። ወፈረ ተሰማራ፣  ስንል ግን ግዕዝ ነው ከ፭ቱ መራኁት መካከል ግዕዝ ስላለ ወ ግዕዝ ስለሆነ።         🌷፩፦ግዕዝ፦ መጀመሪያ ፊደሉ ግዕዝ ወይም አንደኛ የሆነ  መጨረሻው ግን በግዕዝ የሚጨርስ ማለት ነው  🌷 ለምሳሌ፦ሰብሐ ፦አመሰገነ              ወጠነ ፦ጀመረ              ደነሰ   ፦ ኃጢአት ሠራ              ፈቀደ   ፦ወደደ              እነዚህ ሁሉም ከ፭ቱ መራኁት መካከል በግዕዝ የሚጀምሩ ናቸው። ፪፦🌷ራብዕ ፦መጀመሪያ ፊደሉ  ራብዕ ወይም ዐራተኛ የሆነ  መጨረሻው ግን በግዕዝ የሚጨርስ ማለት ነው  🌷፣  ለምሳሌ ባልሐ ፦አዳነ ሣረረ  ፦ሠራ ዳነየ  ፦ ዳኜ ባረከ  ፦ አመሰገነ ሳቀየ  ፦ስቃይ ዓሳየ እነዚህ ሁሉም ከ፭ቱ መራኁት መካከል በራብዕ የሚጀምሩ ናቸው። ፫፦  🌷ኃምስ  ፦መጀመሪያ ፊደሉ ኃምስ የሆነ ወይም አምስተኛ መጨረሻው ግን በግዕዝ የሚጨርስ ማለት ነው።🌷 ለምሳሌ ሌወወ ፦ጠመጠመ ሌለየ   ፦ ለየ ሴሰየ ፦ መገበ ቄሀ   ፦ ቀላ ሜጠ፦ መለሰ ሤመ ፦ ሾመ ዜነወ ፦ ነገረ እነዚህ ሁሉም ከ፭ቱ መራኁት መካከል በኃምስ የሚጀምሩ ናቸው። ፬፦ 🌷ሣድስ ፦ መጀመሪያ ፊደሉ ሣድስ ወይም ሥድስተኛ የሆነ  መጨረሻው ግን በግዕዝ የሚጨርስ ማለት ነው🌷 ለምሳሌ ስዕነ ፦ደከመ ስህነ ፦ ሞቀ ውዕየ ፦ ተቃጠለ ጥዕየ  ፦ ዳነ ርእየ     ፦ አየ ክህደ   ፦ ካደ ክህለ   ፦ቻለ ንህከ   ፦ አዘነ መሀረ  ፦ አስተማረ ጥህረ   ፦ ጮኸ ፭፦ 🌷ሳብዕ ፦መጀመሪያ ፊደሉ ሳብዕ  ወይም ሰባተኛ የሆነ  መጨረሻው ግን በግዕዝ የሚጨርስ ማለት ነው🌷🌷 ለምሳሌ ጦመረ ፦ ጻፈ ኖመ     ፦ተኛ ሖረ      ፦ሔደ ኖለወ   ፦ ጠበቀ ኦገ      ፦አላገጠ ጾመ   ፦ ጾመ ሎሀ    ፦ ጻፈ  ሞዐ   ፦ አሸነፈ ኖኀ    ፦ ረዘመ ፆረ     ፦ ተሸከመ አንቀጽ  በካዕብና በሣልስ ወይም በኹለተኛ እና በሦስተኛ ፊደል አይነሳም። በግዕዝ፣ በራብዕ ፣በኃምስ፣ በሳድስ፣በሳብዕ፦ ብቻ ነው  የሚነሣው ። ነባር ግን በሰባቱም ፊደላት ይጨርሳል በሰባቱም  ፊደላት ይነሳል።     ነባር በሰባቱ ፊደላት ሲነሣ ለምሳሌ 🌷በግዕዝ ሲነሣ🌷 መሰንቆ    ፦ መሰንቆ መልበስ  ፦ ልብስ ነምር      ፦ ነብር አንበሳ    ፦ አንበሳ ከሀሊ     ፦ ቻይ መዋዒ   ፦አሸናፊ ሰባሒ   ፦አመስጋኝ ሰኮና     ፦ ተረከዝ መራሒ  ፦ መሪ 🌷በካዕብ ሲነሣ 🌷 ኁባሬ ፦ አንድነት ኑባሬ  ፦ መቀ ኩለሄ  ፦ ዘወትር ሙራድ  ፦ መውረጃ ሙባእ ፦ መግቢያ 🌷በሣልስ ሲነሣ🌷 ሚካኤል ሲራክ ሢመት፦ ሹመት ኢየሱስ  ፦መድኃኒት ኪዳን ሚጠት ፦መመለስ ሊቀ ካህን ቂርቆስ ዲያቆን ፦አገልጋይ 🌷በራብዕ 🌷 ናብሊስ ፦አታሞ ዳንኤል ማስያስ ማርያም ማትያስ ማርቆስ ታቦት ናሁ ፦አኹን 🌷በኃምስ🌷 ጌልጌላ ፦ሰማይ ሜላት ፦ሐር(ግምጃ) ሴሰየ ፦መገበ ሴት፦ምትክ ዜናዊ ፦ወረኛ፣አብሳሪ 🌷በሳድሥ🌷 ርእስ ፦እራስ ስእርት  ፦ ጸጉር ኅብስት  ፦ዳቦ ጽፍር  ፦ጥፍር ቅዳሴ፦ምስጋና እዝን ፦ጆሮ ስን ፦ጥርስ ልገት ፦ጎጆ 🌷በሳብዕ🌷 ዮሴፍ ዶርሆ፦ ዶሮ ዮም  ፦ ዛሬ ዮሐንስ ቶማስ ✍ስለዚህ በነባር ጊዜ በሰባቱም ፊደላት ይነገራል። በካዕብና በሣልስ የማይጀምረው በአንቀጽ ጊዜ ሲኾን  ብቻ ነው። ከዚህ ቀጥለን በነባር ወይም በሰዋሰው ጊዜ በሰባቱም ፊደላት ሲጨርሱ እናያለን ። በአንቀጽ ጊዜ ግን በግዕዝ ብቻ  ነው የሚጨርሱት 🌷በግዕዝ ሲጨርሱ ጥቀ ፦ፈጽሞ ንሕነ ፦እኛ በይነ ፦ስለ እንከ ፦እንግዲህ 🌷በካዕብ ሲጨርሱ🌷 አንትሙ ፦እናንተ ውእቱ  ፦  እርሱ ከረዙ ፦መስቀል 🌷በሳልስ የሚጨርሱ🌷 መናሒ፦ጤፍ ተዳሒ፦ ስመ አምላክ ሱሲ ፦መጠምጠሚያ ሜፌቲ፦ ሞኝ 🌷በራብዕ የሚጨርሱ🌷 ትሕትና  ፦ትትና ልቦና  ፦ ዕውቀት መና ፦እንጀራ ላሊበላ 🌷በኃምስ የሚጨርሱ🌷 ሠርዌ፦ አለቃ ትንባሌ፦ ልመና ቅዳሴ ፦ምስጋና ሥላሴ ቡራኬ   ቡራኬ ትንባሌ  ልመና አይቴ     የት ማዕዜ     መቼ ህላዌ       ኑሮ 🌷በሳድስ የሚጨርሱ🌷 ዓይን   ዐይን ከናፍር   ከንፈር መክሊት  ሳንቲም ምንት    ምን ጸጉር   ጠጉር አንፍ   አፍጫ ማርቆስ 🌷በሳብዕ የሚጨርሱ🌷 መርኆ፦ ቁልፍ ከበሎ ፦ ቀለበት መሰንቆ ፣ መሰንቆ ሞ፣ ብርሌ ግእዝን ለመማር  የሚያስፈልጉ ፬ ነገሮች፦ ፩🌷፦እውቀቱን እንዲገልጽልን   እግዚአብሔርን በጸሎት  መጠየቅ  ። ፪🌷፦ በትጋት መከታተል። ፫🌷፦ መመራመር። ፬🌷፦ በቀን ፫ ፫(ለተቻለው ከዚያም በላይ) የግስ  ቃላትን (አንቀጽ/ግስ)  መያዝ ቃለ ሕይወት ያስምዕ ለነ መምህርነ ጥቀ ንሴብሐከ እግዚአብሔር የሀብ ለነ ። የቃላት ግድፈት ካላ እያረማችኹ አንብቡት የቀረውን ከሪከርዱ አዳምጡት
Показать все...
record.ogg8.86 MB
record.ogg20.43 MB
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ትምህርተ ልሳነ ግዕዝ  ክፍል ፯  [ሰባት] 🌷ተአምኆ ወይም ሰላምታ አሰጣጥ🌷     እፎ 👉እንዴት ወዐልከ 👉ዋልኽ ✍እፎ ወዐልከ 👉እንዴት ዋልኽ አንድ ሰው መጥቶ (እፎ ወዐልከ)  እንዴት ዋልኽ ቢለን   የኛ መልስ እግዚአብሔር ይሰባሕ (እግዚአብሔር ይመስገን) ይኾናል።🌷 ✍ከላይ   እንዴት ዋልኽ ለማለት ስንፈልግ  እፎ  ወዐልከ  ብለን አይተናል ።  አሁን ደግሞ እንደምን ዋልኽ  የሚለውን እናያለን። ከመ  👉እንደ እፎ     👉እንዴት ወዐልከ👉ዋልኽ አይ       👉ምን ✍ እፎ ወዐልከ      👉እንዴት ዋልኽ ✍ከመ እፎ ወዐልከ 👉እንደምን ዋልኽ ✍ከመ አይ ወዐልከ  👉እንደምን ዋልኽ ከመ እፎ  ብንልም ከመ አይ ብንልም ትክክል ነው በኹለቱም ያስኬዳል። እፎ እና አይ ምን የሚል ትርጉም ስለሚሰጡን ነው። ለዚህም መልሱ 👇 እግዚአብሔር  ይሰባሕ እግዚአብሔር ይትቀደስ እግዚአብሔር ይትአኮት እግዚአብሔር ይትባረክ ብሎ መመለሾ ይችላል። እነዚህ ኹሉ እግዚአብሔር ይመስገን የሚለውን ይተካሉ ።ወይም ከላይ የዘረዝርናቸው ወደ አማረኛ ሲተረጎም እግዚአብሔር ይመስገን ማለት ነው። ✍የሆነ ሩቅ ሰው ወይም የታመመ፣እንግዳ ሰው ሊኾን ይችላል፣የታማሚውን ዘመድ አግኝተን   ያልጅ እንደት ኹኖ ዋለ  ለማለት ብንፈልግ ✍እፎ ወዐለ        👉እንዴት ዋለ ✍ከመ እፎ ወዐለ👉እንደምን ዋለ ✍ከመ አይ ወዐለ  👉እንደምን ዋለ ብለን መጠየቅ እንችላለን። ለዚህም መልሱ ከላይ የተዘረዘሩት ናቸው።እግዚአብሔር ይሰባሕ፣ይትባረክ፣ይትቀደስ፣ይትአኮት። ✍ሴቷን  እንዴት ዋልሽ፣ እንደምን ዋልሽ ለማለት ስንፈልግ👇 ✍እፎ ወዐልኪ       👉እንዴት ዋልሽ ✍ከመ አይ ወዐልኪ👉እንደምን ዋልሽ ✍ከመ እፎ ወዐልኪ 👉እንደምን ዋልሽ መልሱ እግዚአብሔር  ይሰባሕ፣ ይትባረክ፣ይትአኮት፣ይትቀደስ፣) በዳኅና  ሀሎኩ ማለትም ይቻላል። ✍ሩቅ ወንዶችን እንደት ዋሉ ማለት ስንፈልግ ፣ ✍እፎ ወዐሉ       👉እንዴት ዋሉ ✍ከመ እፎ ወዐሉ 👉እንደምን ዋሉ ✍ከመ አይ ወዐሉ  👉እንደምን ዋሉ እግዚአብሔር ይሰባሕ በዳኅና ወዐሉ ፣(እግዚአብሔር ይመስገን  በደኅና  ውለዋል፣ሠናያን እሙንቱ  መልካሞች ናቸው ምንም አይሉም ፣ጥሩዎች ናቸው ብሎ ሊገልጽልን ይችላል። ✍ለቅርብ ወንዶች  ሰላምታ ለመስጠት ስንፈልግ፣ ✍እፎ ወዐልክሙ       👉እንዴት ዋላችኹ ✍ከመ እፎ ወዐልክሙ👉እንደምን ዋላችኹ ✍ከመ አይ ወዐልክሙ 👉እንደምን  ዋላችኹ መልሱ ከላይ  እንዳየነው  ነው። ✍እንደምን ዋለች  ለማለት ስንፈለግ ፣ ✍እፎ ወዐለት         👉እንዴት ዋለች ✍ከመ አይ ወዐለት  👉እንደምን ዋለች ✍ከመ እፎ ወዐለት  👉እንደምን ዋለች ✍እንደት ዋልሽ ለማለት ስንፈልግ 👇 ✍እፎ ወዐልኪ        👉እንዴት ዋልሽ ✍ከመ እፎ ወዐልኪ 👉እንደምን ዋልሽ ✍ከመ አይ ወዐልኪ  👉እንደምን ዋልሽ ✍ለቅርብ  ሴቶች ሰላምታ ለመስጠት ስንፈልግ👇 ✍እፎ ወዐልክን         👉እንዴት ዋላችኹ ✍ከመ እፎ ወዐልክን  👉እንደምን ዋላችኹ ✍ከመ አይ ወዐልክን   👉እንደምን ዋላችኹ ✍ከመ እፎ ጸናሕክን  👉 እንደምን ቆያችኹ ✍ከመ እፎ ሀለውክን 👉እንደምን አላችኹ ✍ሩቅ  ሴቶችን  እንዴት ዋሉ ብለን ከሌላ ሰው ለመጠየቅ ስንፈልግ👇 ✍እፎ ወዐላ          👉እንዴት  ዋሉ ✍ከመ እፎ ወዐላ  👉እንደምን ዋሉ ✍ከመ አይ ወዐላ  👉እንደምን ዋሉ ብለን እንጠይቃለን። መላሹ  ከላይ እግዚአብሔር ይሰባሕ(እግዚአብሔር ይመስገን) ፣(ሠናያት እማንቱ)(ጥሩ ናቸው) ፣በኂሩቱ ለእግዚአብሔር  ሀለዋ እስከ ይእዜ በሠናይ፣(በእግዚአብሔር ቸርነት እስከ  አሁን በጥሩ  አሉ ።) ኹል ጊዜ  ፪ወይም ከዛ በላይ ለሆኑ ሴቶች አንቀጽ ስንሰጥ የአንቀጹን  መጨረሻ ፊደል  ወደ አራተኛ  ወይም ወደ ራብዕ ፊደል መቀየር ነው። ለምሳሌ፦ ወዐለ ፣ዋለ ፣ወዐላ ፣ዋሉ              ነበረ ፣ተቀመጠ ፣ነበራ ፣ተቀመጡ ፈቀደ ፣ወደደ ፣ፈቀዳ፣ ወደዱ ጌሠ ፣ገሠገሠ ፣ጌሣ፣ገሠገሡ ሰብሐ፣አመሰገነ፣ሰብሓ ፣አመሰገኑ ✝✝✝✝✝✝✝ ✍ግእዝን ለመማር  የሚያስፈልጉ ፬ ነገሮች፦ ፩🌷፦እውቀቱን እንዲገልጽልን   እግዚአብሔርን በጸሎት  መጠየቅ  ። ፪🌷፦ በትጋት መከታተል። ፫🌷፦ መመራመር። ፬🌷፦ በቀን ፫ ፫(ለተቻለው ከዚያም በላይ) የግስ  ቃላትን (አንቀጽ/ግስ)  መያዝ ቃለ ሕይወት ያስምዕ ለነ መምህርነ ጥቀ ንሴብሐከ እግዚአብሔር የሀብ ለነ ። የቃላት ግድፈት ካላ እያረማችኹ አንብቡት የቀረውን ከሪከርዱ አዳምጡት።
Показать все...
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ትምህርተ ልሳነግዕዝ ክፍል ፭🌷 ✍ከአኹን በፊት ዐራት ክፍሎችን አይተናል። ዛሬ ፭ተኛ  ክፍል እናያለን። በባለፈው የ እና ተ የኹለቱን አስራውን አይተናል ። ዛሬ ደግሞ አ  እና ነ እናያለን። ✍አ በአንድ መራሒ በ፫ አንቀጾች ይነገራል ማለት ነው።በካልዓይ ፣በዘንድ በትእዛዝ ይነገራል። 🌷ሰከበ ፦ተኛ🌷 አነ  ሰከብኩ፦እኔ ተኛኹ አነ እሰክብ ፦ እኔ እተኛለኹ አነ እስክብ ፦ እኔ  እተኛ ዘንድ አነ እስክብ ፦  እኔ ልተኛ 🌷ዘበጠ፦ መታ🌷 አነ ዘበጥኩ፦ እኔ መታኹ አነ እዘብጥ ፦እኔ እመታለኹ አነ እዝብጥ ፦እኔ እመታ ዘንድ አነ እዝብጥ  ፦እኔ ልምታ 🌷ደቀሰ ፦ተኛ🌷 አነ ደቀስኩ ፦ እኔ ተኛኹ አነ እደቅስ ፦ እኔ እተኛለኹ አነ እድቅስ ፦ እኔ እተኛ ዘንድ አነ እድቅስ  ፦ እኔ ልተኛ 🌷መተረ፣ ቆረጠ 🌷 አነ መተርኩ  ፣እኔ ቆረጥኹ አነ  እመትር ፣እኔ እቆርጣለኹ አነ  እምትር   ፣ እኔ እቆርጥ ዘንድ አነ  እምትር   ፣ እኔ እቆርጣለኹ ✍ነ  በአንድ መራሒ በ፫ አንቀጽ ይገኛል። ነ፣በንሕነ  መራሒ ይነገራል።በካልዓይ ፣በዘንድ እና በትዛዝ ይነገራል 🌷 ገደፈ ፦ጣለ🌷 ንሕነ ገደፍነ ፦ እኛ ጣልን ንሕነ ንገድፍ፦ እኛ እንጥላለን ንሕነ ንግድፍ፦ እኛ እንጥል  ዘንድ ንሕነ ንግድፍ፦ እኛ እንጣል 🌷መለከ፣ገዛ🌷 ንሕነ መለክነ  ፣ እኛ ገዛን ንሕነ ንመልክ ፣እኛ እንገዛለን ንሕነ ንምልክ ፣ እኛ እንገዛ ዘንድ ንሕነ  ንምልክ ፣እኛ እንግዛ 🌷መተረ ፣ቆረጠ🌷 ንሕነ መተርነ ፣ እኛ ቆረጥን ንሕነ ንመትር ፣ እኛ እንቆርጣለን ንሕነ ንምትር  ፣እኛ እንቆርጥ ዘንድ ንሕነ  ንምትር  ፣ እኛ እንቁረጥ ነ፣እና አ፣ በአንድ አንድ መርሕያን በ፫ በ፫ አናቅጽ ይነገራሉ። ግእዝን ለመማር  የሚያስፈልጉ ፬ ነገሮች፦ ፩🌷፦እውቀትን እንድገልጽልን  በጸሎት እግዚአብሔር መጠየቅ  ። ፪🌷፦ በትጋት መከታተል። ፫🌷፦ መመራመር። ፬🌷፦ ቃላትን  መያዝ ቃለ ሕይወት ያስምዕ ለነ መምህርነ ጥቀ ንሴብሐከ እግዚአብሔር የሀብ ለነ ። የቃላት ግድፈት ካላ እያረማችኹ አንብቡት የቀረውን ከሪከርዱ አዳምጡት
Показать все...
ከመ እፎ ወዐልኪ
Показать все...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ገብርሄር መንፈሳዊ ጭውውት ትዕይንት አንድ ✝አንድ ንጉሥ ፦ ገብርሄር ገብርሔር ገብርሔር #ባለ አምስት መክሊት ፦ተነሱ ጓዶች ንጉሥ ይጠሩናል ዛሬ ወደ ሆነ ቦታ ይሄዱ  ይመስለኛል ። #ባለአንድ ምክሊት ፦ኦኦኦ ምን ዓይነት ጣጣ ነው አሁን ብተኛበት እስኪ ምን አለበት  ቆይ እኔ የምለው በእኛ እግር አይሄዱም ምንድን ነው በትንሽ በትልቁ ጥሪ ባያበዙ ምን አለበት ። #ባለሦስት መክሊት ፦ ተው እንጂ ወዳጄ ሲጠሩን አቤት ሲሊኩን ወዴት ማለት የግድ ነው  ይልቁኑ ተነስ እንሂድ እንቅልፉ ይደረሳል። #ንጉሥ ፦በሉ ልጆቼ እኔ አሁን የጠራዋችሁ እሩቅ ሀገር ልሄድ ሰለሆነ መክሊት ልሰጣችሁ ነው ና እንደ የአቅማችሁ ታዲያ  እስክመለስ ድረስ አትርፋችሁ ቆዩኝ #ባለአምስት መክሊት ፦ እሺ ጌታዬ ሰላም ይመልሶት እኛንም ፈጣሪ ታማኝኞች ያድርገን በተሰጠን ላይ እንድንገኝ አትርፈን በሀሳባችን ሁሉ እሱ ይከተለን። #ባለሦስት መክሊት ፦ቻው ጓደኞቼ ደህና ሁኑ እንሰነባበት ከዛሬ ጀምረን ለሰል እንፈጠን ባለአደራዎች ባለብዙ መክሊት እንገናኛለን ሲመለሹ ንጉሥ ። #ባለአንድ መክሊት ፦ወይ እዳ ደግሞ ምን አመጡበኝ ጭራሽ ይባስ ብለው እዳ ጦስ ጣሉብኝ ደግሞ ንቃታቸው ለሌሎቹ ብዙ ለኔ ደግሞ አንድ ብቻ ሰጡኝ ቆይ ባልሰራሎት  አሁን ይጠብቁ መክሊቴን ቀብሬ ባልመልስሎት ሲመጡ። ትዕይንት ሁለት #አንዲት ከመድረክ ጀርባ ሆና እንዲህ ትላለች ፦ ሁሉም በየፊናው ወቶ ተሰማራ የተረከበውን አጥብቆ በመያዝ መንገዱን አቀና ቀናት ተለውጦ ጊዜው ደረሰና  እናከየአሉበት መጡ ሁሉም ተጠሩና ንጉስ ተቀምጦ ሆኖ በዙፉኑ የመረካከቢያ ደረሰና ቀኑ እንዲህም አሏቸው አይናቸውን እያዩ ፦ #ንጉሱም ፦ያስረከብኳችሁን በሉ መልሱልኝ ያተረፉችሁትን ይዛችሁ ቅረቡ ልክፈላችሁ የድካማቸሁን የላባችሁን ዋጋ #ባለአምስት መክሊት ፦ይሄው ጌታዬ ሆይ አመሰግናለሁ በአምስቱ ፋንታ ስልሳ አትርፌበታለሁ በፊቶት ሞገስን ለማግኘት ችያለሁ ነገር ግን ይሄ ሁሉ ሊሆን የቻለው ሀሳቤን አቅንቶ አምላክ ስለረዳኝ ነው ። #ባለሦስት መክሊት ፦ሺህ ዓመት ይንገሥ በእውነት ሁለት በእጥፍ አድርጌ ያቆየዋት ለእኔ ለደካማው የሰጡኝ አሁን ከእኔ ትርፌን ተረከቡኝ በመልካም ጎዳና ሰላሰማሩኝ ልቤን አነሳስቶ ለቤት ያሳኩልኝ ለፍጥረታታ ግዢ ለእርሱ ይሁን ። #ባለአንድ መክሊት ፦ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንክበት የምትሰበስብ ጨካኝ ንጉሥ መሆንህን አውቃለሁ ፈራሁ ሄጄም መክሊትህን በምድር ላይ ቀበርኩት እንሆ ይረከቡኝ አትርፍ ባይ አጉዳይ እንዳይሆን ነገሩ በጥንቃቄ ጠብቄ ቆየውትን ይውሰዱት አሁን ሳልቀንስ ሳለውጥ እራሱንም እንኩ ። #ንጉሡም ፦እናንተ በጥቂቱ ታምናችኃል በቡዙ ሾማችኃለሁ። አንተ ግን ክፉ እና ሀሰተኛ ባርያ ከእግዚአብሔር በተሰጠህ መክሊት ብታመሰግን ይጨመርልሃል ግን በተሰጠህ ስላልታመንክ የተሰጠህም ይወስድብሃል @መጋረጃው ከተዘጋ በኃላ አንዲት ሴት እንዲህ ትላለች ፦ የስጦታ ጥጌት የአምላክ ክፋቱ አይባልም አሉ ባገኙት ማመስገን ይላልና ቃሉ ለቅጣት መቿኮል አምላክን ማታለል ህግን መተላለፍ  አስፈላጊም አይደል በዙም ሆነ ትንሽ አያያዝ ያሻዋል የድካምን ዋጋ አትርፎ ይሰጣል ትሁን ልብ ላለው አምላክ ይረዳዋል በንቀት በተንኮል የሚጓዝ ከሆነ ይፈረድበታል ለዚህ ነው ጌታችን ገብርሄር በማለት ሰለ ታዛዥነት የሚያስተማረን ይሄው በዚች ዕለት ። ተፈፀመ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር ይቆየን ። በማርያም ከወደዱ ሟር link ያድርጉ @menfesawigetem @menfesawigetem @menfesawigetem
Показать все...
የምንወደው ጸሎት "የአባታችን ሆይ" አድምታ ትርጓሜ ስንቶቻችን እናውቀዋለን . ሐዋሪያት ወደ ጌታችን ቀርበው የምንጸልየውን ጸሎት አስተምረን አሉት። ጌታችንም " እናንተስ ስትጸልዩ የሰማይ አባታችን በሉኝ " በማለት ማንም ቢሆን ሲቆምና ሲቀመጥ ሲተኛና ሲነሣ ዘወትር ሊጸልየው የሚችለውን አጭር ጸሎት አስተማረ። ማቴዎስ 6÷9-14 ይኽም ጸሎት እንደ አባቶቻችን አስተምህሮ አድምታ ትርጓሜው አጠር ባለ መልኩ እንደሚከተለው ቀርቧል። #አባታችን_ሆይ :- ጌታችን ከግብርናተ ዲያብሎስ / ከዲያብሎስ ባርነት / ነፃ እንዳወጣን: አጥተነው የነበረውን ልጅነት እንዳገኘን ሲያጠይቅ አቡነ / አባታችን / በሉኝ አለ። ጌታ ሎሌውን መምህር ደቀመዝሙሩን ምን ቢወደው ያበላዋል ያጠጣዋል የልቡናውን ምስጢር ያጫውተዋል እንጂ ርስቱን አያወርሰውም። ርስቱን የሚያወርሰው ለልጁ ነው። እርሱ ግን ጌታችን እና አምላካችን ሲሆን የማታልፍ ርስት መንግሥተ ሰማያትን የሚያወርሰን ስለሆነ 'አቡነ' በሉኝ አለ። አባት ለወለደው ልጁ እዲራራ የሚራራልን ስለሆነ አቡነ በሉኝ አለ። #በሰማያት_የምትኖር :- እንዲህ ማለቱ ራሱን ከምድራዊ አባት ሲለይ ነው። ምድራዊ አባት ሲወልድ በግዙፍ ሲያሳድግ በግዙፍ ነው። ኋላም ሓላፊ ርስቱን ያወርሳል። እርሱ ግን ሲወልደን በረቂቅ ሲያሳድገን በረቂቅ ነው። ኋላም የማታልፍ ርስቱን መንግሥተ ሰማይን ያወርሰናል። በተጨማሪም ጌታ በሁሉ ምሉዕ ሲሆን ስለ ልዕልናው በሰማይ የምትኖር ይባላል። 1ኛጴጥ.1÷8-10 ራዕይ 21÷2-6። #ስምህ_ይቀደስ :- ይኽም " ስሜ መሐሪና ይቅር ባይ ነው። " ያልኸው ይጽናልን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለው ስምህን አመስግነው ቅድስናህን ተሳትፈው እንዲኖሩ እኛም ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለን አመሰገንህ ቅድስናህን ተሳትፈን እንድንኖር አድርገን በሉ ሲለን ነው። ኢሳያስ 6÷3 ራዕይ 4÷8። #መንግሥትህ_ትምጣ :- መንግሥተ ሰማየት ትምጣልን ልጅነትን ትሰጠን በሉ ሲል ነው። እንዲህም ማለቱ መንግሥተ ሰማይ ከወዲያ ወዲህ የምትመጣ ከወዲህም ወዲያ የምትሄድ ሆና ሳይሆን ትገለጽልን በሉ ማለቱ ነው። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፈሪሳውያን ቀርበው " የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች? " ብለው በጠየቁ ጊዜ " የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም ከዚህ አለች ከዚያ የለችም አትባልም የእግዚአብሔር መንግሥት እንሆ በመካከላችሁ ናት" ብሏቸዋል። ሉቃስ 10÷20-21። #ፈቃድህ_በሰማይ_እንደሆነ_እንዲሁ_በምድር_ትሁን :- መላእክት ከሰማይ ሲያመሰግኑህ ፈቃድህ እንደ ሆነ እኛም በምድር ያለን ደቂቅ አዳም እናመስግንህ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን። ኋላ ሞተን ተነሥተን እናመስግንህ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን በሉ ሲል ነው። እንዲሁም አቤቱ ፈቃደ መዓትህን ትተህ ፈቃደ ምሕረትህን አድርግልን ብላችሁ ብትለምኑኝ አደርግላችኃለሁ ሲልም ነው። #የዕለት_እንጀራችንን_ስጠን_ዛሬ :- በዚህ ዓለም ሳለን ለዕለት የሚሆነንን ምግብ ስጠን በሉ ሲል ነው። በሰማይ ያሉ መላእክት ስብሐተ እግዚአብሔር ተመግበው / በሰማይ አመስግነውህ ያው ምስጋናቸው ምግብ ሆኗቸው/ እንዲኖሩ እኛም በምድር እህል ምግባችንን አትንሣን ብላችሁ ብትለምኑኝ አልነሣችሁም ሲል ነው። #በደላችንን_ይቅር_በለን_የበደሉንን_ይቅር_እንደምንል :- ማረን ይቅር በለን ኀጢአታችንን አስተስርይልን በደላችንን ደምስስልን መተላለፋችንን ሁሉ ይቅር በለን ይቅርታን እናገኝ ዘንድ እኛም የበደሉንን ሁሉ ይቅር እንላለን ሲል ነው። ለዚህም ነው ጌታ "ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ የሰማይ አባታችሁ ደግሞ ይቅር ይላችኋል ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም" ብሏል። ማቴዎስ 6÷13-15። እንዲሁም "አበሳ" የዓመት ነው: " ጌጋዬ " / በደል / የዕለት ነው። አበሳ የዓመት ያለውም ነፍስ መግደል ቋንጃ መቁረጥ ቤት መስበርና ይኸንን የመሳሰለው ሁሉ ነው። ይኸን ያደረገም ጠላቱን ሲርበው ቢያበላ ሲጠማው ቢያጠጣው ሲታረዝ ቢያለብሰው በደለኛ ሲክሰው ዋስ ጠበቃ ቢሆነው ንስሐ ቢገባ ስለክፉ ሥራው ቢያዝን ቢጸጸት ቢያለቅስ ይድናል እንጂ ያለዚያስ አይድንም። ፊያታዊ ዘየማን ሲድን ፊያታዊ ዘጸጋም አለመዳኑ ንስሐ ባለመግባቱ ነው። ጌጋየ ዕለት ያለው ደግሞ ሰው ሆኖ በተለያየ ምክንያት መጣላት መጋጨት አይቀርምና ቂም በቀል ሳይዙ ዕለቱን ስለ እግዚአብሔር ይቅር መባባል ነው። ለዚህም ነው ሐዋርያው "በቁጣችሁ ፀሐይ አይግባ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት" ያለው። ኤፌሶን 4÷27 #አቤቱ_ወደ_ፈተና_አታግባን :- ከክፉ አድነን ወደ ኀጢአት ወደ ክህደት ወደ መከራ ወደ ገሃነም አታግባን ከዚህ ሁሉ አድነን እንጂ በሉኝ ሲል ነው። #መንግሥትህ_ያንተ_ናትና :- መንግሥተ ሰማያት ያንተ ገንዘብ ናትና በሉኝ ሲል ነው። #ኃይል_ምስጋናም_ለዘላለሙ :- ከሃሊነት ጌትነት ለዘላለሙ ገንዘብህ ናትና አሜን በእውነት በሉኝ ሲል ነው። የእግዚአብሔር ኃይል የባሕርይ በመሆኑም ነው ጻድቁ ኢዮብ "ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደሆንህ አሳብህም ይከለከል ዘንድ እንደማይችል አወቅሁ" በማለት የገለጸው ኢዮብ 42÷2 #ማጠቃለያ ፡- በዚህ የጸሎት ክፍል ውስጥ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱስ መጽሐፍት የተገኙ ቁም ነገሮችን አስተምሯል እነሱም :- -ተስፋ-ፍቅር-ትህትና-ጸሎት ናቸው @menfesawigetem
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
#እንባችንን_እግዚአብሔር_ይመለከታል። 🔸 🔸 🔸 🔸 🔸 🔸 🔸 🔸 🔸 🔸 ▪ በዚያን ወራት ሕዝቅያስ እስከ ሞት ድረስ ታመመ። ነብዩ የአሞፅ ልጅ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል አለው። ▪ፊቱንም ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ▪ አቤቱ በፊትህ በእውነትና በፍፁም ልብ እንደ ሄድሁ ፥ የሚያሰኘህንም እንዳደረግሁ ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ ። ሕዝቅያስም እጅግ አድርጎ አለቀሰ። ▪ ኢሳይያስም ወደ መካከለኛው ከተማ አደባባይ ሳይደርስ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት። ▪ ተመልሰህ የሕዝቤን አለቃ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው። የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ። ጸሎትህን ሰምቻለሁ  ፧ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ እፈውስሃለሁ... ▪ በዕድሜህም ላይ አሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ። "ኢሳይያስም ፥የበለስ ጥፍጥፍ አምጡልኝ አለ ፤ አምጥተውም በእባጩ  ላይ አድርጉለት ፥ እርሱም ተፈወሰ (2ኛ. ነገስት 20 ፥ 1- 7)። https://t.me/beteabagiworgiszegascha
Показать все...
ይቀጥል 🈸#ማብራሪያ ንጉሥ  ሕዝቅያስ ታመመ ፤ ሁሉ ተሟልቶለት ሳለ ጤና አጣ። ሕመሙም ለሞት የሚያደርሰው ሆነ። ነቢዩ ኢሳይያስ ከእግዚአብሔረ ተላከና ፦ ትሞታለህ እንጂ አትተርፍም ብሎ አረዳው ። ትሞታለህ የተባለው ሰው ምንም ነገር ያልጎደለው ፣ ሁሉ ያለው ንጉሥ ነበር። ገንዘብ ቢኖረውም ሕይወቱን ግን ማትረፍ አልቻለም። ትሞታለህ የተባለው ንጉሥ ሕዝቅያስ በዘመኑ ከነበሩት ይልቅ መልካም ሥራን የሠራና በሕይወት ቢኖርም ብዙ ሊሠራ ይችላል የሚባልለት ዓይነት ንጉሥ ነበር። በይሁዳ የነበሩትን ብዙ የጣዖት አምልኮ ስፍራዎችን ያፈረሰም ነበር። ለሕዝቅያስ አትድንም ያለው ባለ መድኃኒቱ (ሐኪም) ቢሆን ኖሮ፦ የለም እግዚአብሔር ያድነኛል ብሎ እንዳይሞት  ተስፋ ያደርግ ነበር። ትሞታለህ ያለው ግን እግዚአብሔር በመሆኑ መሞቱ እርግጥ ሆነ። ብትታመሙና ሐኪሞ በቃ አትድኑም ቢላችሁ ምን እንደሚሰማችሁ አስቡት? ሕዝቅያስ ደግሞ እንዲህ ያለው ከማኅፀን  ያወጣውና የፈጠረው አምላኩ በመሆኑ ሊድን እንደማይችል በማመን እጅግ አድርጎ አለቀሰ። ንጉሥ ምን ጎሎት ያነባል ? ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ? ማንስ ምን የማይጎድለው አለ? ያነገሠው አምላክ ፦ ትሞታለህ ሥላለው መቀበል ነበረበትና ማንባቱን ቀጠለ? ለማንስ ቢሆን የማያነባበት ነገር ይጠፋና ነው? አያነባም ቢሆን ወደ አምላኩ ጸለየ። አምላኩ ግን አልዘገየም፤ ትሞታለህ ባለው ነብይ መልሶ አትሞትም ፤ እኔ እፈውስሃለሁ ፤ ደግሞም እንባህን አይቻለው በማለት ለጸሎቱ መልስ ሰጠው። እዚህ ላይ በጣም የሚገርመው እግዚአብሔር የሕዝቅያስን ጸሎት የሰማው ነቢዩ ኢሳይያስ ገና ከቤተ መንግሥቱ ሴይርቅ ነው። ትሞታለህ ብለህ ንገረው የተባለው ነቢዩ ኢሳይያስ መልደህ ሂድና ለሕዝቅያስ አትሞትም በለው ሲለው ለነቢዩ ኢሳይያስ ሳይቀር አግራሞትን የሚፈጥር ነው። ሕስቅያስ ትሞታለህ እንደ ተባለ መጸለይ ጀመረ ፤ ጸልዮ ሲጨርስ በዚህ ቅጽበት ለኢሳይያስ ተመለስና አትሞትም በለው ተባለ። እግዚአብሔር ፈጥኖ ጸሎትን እንደሚሰማ ተመልከቱ። ያነባው ሕዝቅያስ አንብቶ አልቀረም ፤ እንባውን የተመለከው አምላክ የሻተውን ዕድሜ ጨመረለት ። ንጉሥ ሆኖ አንድ ዓመት ልሹ መኖርና መሞት ትልቅ ነገር ነው። ንጉሥ እንደ ሆነ 15 ዓመት ተመርቆለት በጤና መኖር ደግሞ የበለጠ ደስ ያሰኛል። እንኳን ወዳጅ ጠላት (የሚጠላን ለማለት ነው) ሲያለቅስ ስናይ ልባችን የሚያዝንለት ጊዜ አለ። የሰው ልጅ ያሰበውን ማድረግ ሲያቅተው ያለቅሳል ። በዚህ ሰዓት አለሁልህ የሚለው ሲገኝ ያስደስታል። ለሕዝቅያስ ፦ እንባህን አይቻለሁ ያለ አምላክ የእኛንም እንባ ይመለከታል። በሆነ ምክንያት ስናነባ ፦ ደግሞ ታለቅሳለህ ? ይህን እንባህን እንዳይ አልፈልግም የሚል ክፉ አባት  አይደለም። ከዓይናችን የወረዱትን የእንባ ዘለላ አንዳቸውም ሳይቀሩ ያውቃቸዋል። እንድናይበት  የፈጠረልን ዓይናችን እንባን ሲያፈልቅ ሲያይ ቸል የሚለን አምላክ አይደለም። እርሱ ደረቅ እንባንም ይመለከታል። እንባ ስለማይወጣን በጉንጫችን ባይወርድም ያንን ደረቅ እንባ ዝም ብሎ አይተወዉም ። ልዑል ከማደሪያው ሰማይ ሆኖ በተለያየ ምክንያት የወረደውን እንባችንን ያይያል ። ለእንባችንም መልስ የሚሰጥ አምላክ ነው። አልቅሶ እንዳልቀረው ሕዝቅያስ እኛም አልቅሰንና እንባችን ፈሶ አይቀርም ። እንባችንን ያብስልናል። የለመንነውንም ይሰጠናል።     ወስብሐት ለእግዚአብሔር። አሜን! 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿⛪️🌿⛪️ https://t.me/beteabagiworgiszegascha 🌿🌿🌿🌿🌿🌿❤️❤️❤️❤️❤️
Показать все...

Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.