cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو

Wel-come to the official TG channel of ustaz Yasin Nuru. 📹Do you help me with Islamic media and Dewa? 🇵🇸 Free Palestine 🇵🇸 My FB channel is ✅ ☟︎︎︎ https://www.facebook.com/ustazYassinNuru?mibextid=ZbWKwL

Больше
Рекламные посты
4 066
Подписчики
+624 часа
+687 дней
+33530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
👍اللهم تقبّل من الحجيج حجهم، واستجب دعاءهم، وردهم إلى أهلهم سالمين غانمين.. آمييين
Показать все...
👍 20 14
00:36
Видео недоступноПоказать в Telegram
ኢድ ሰሜን ጋዛ
Показать все...
Among_the_rubble,_citizens_in_northern_Gaza_perform_Eid_prayers.mp411.30 MB
16👍 6
🐏 ኡድሒያን የሚመለከቱ ወሳኝ ነጥቦች 🔴 ኡድሒያ ማለት በዐረፋ በዓል ቀን እና ቀጥሎ ባሉ ተከታታይ ሶስት ቀናት ውስጥ ወደ አላህ ለመቃረብ ተብሎ የሚታረድ የቤት እንሥሳ ማለት ነው። "ኡድሒያ" የተባለው የእርዱ ሰዓት የሚጀምረው የዒድ ቀን ረፋድ (ዱሓ) ላይ  ስለሆነ ነው። 🔴 ኡድሒያ ማረድ የዲን አካልና ተወዳጅ ተግባር መሆኑ ላይ ሁሉም ሊቃውንት ይስማማሉ፤ ብዙሃኑ ሊቃውንት ዘንድ ሱንናህ እንጂ ስለት (ነዝር) ለሌለበት ሰው ግዴታ አይደለም። አቡ ሐኒፋን ጨምሮ በርካታ ግዴታ ነው የሚል አቋም ያላቸው ሊቃውንት ስላሉና በዒድ ቀን ማረድ ልዩና ከፍ ያለ ምንዳም ስላለው አቅም ያለው ሰው ኡድሒያ ማረድ ባይተው ይመረጣል፤ 🔴 ከቤት እንስሳት (ከግመል፣ ከከብት ፣ ከበግና ፍየል)  ውጪ ሌላን እንስሳ ለኡድሒያ ማረድ እንደማይቻል የፊቅህ ሊቃውንት በሙሉ (ከሐሰን ኢብኑ ሳሊሕ በስተቀር) ይስማማሉ። 🔴 ለኡድሑያ የሚታረደው እንስሳ ወንድም ይሁን ሴት ለውጥ የለውም፤ ሁለትም ጾታዎች ለኡድሒያ እንደሚሆኑ (እንደ ሚበቁ) የፊቅህ ሊቃውንት ይስማማሉ። 🔴 የዒድ ቀን ከሰላተል-ዒድ በፊትና፣ ከ 14ኛው ቀን የጸሐይ መጥለቅ በኋላ የሚታረድ እርድ ከኡድሒያ አይቆጠርም። 🔴 በመሰረቱ የኡድሑያ እንስሳ መግዣ ገንዘቡን ሰደቃ ከመስጠት ይልቅ ኡድሒያ ማረዱ በአጅር ይበልጣል። ይህም የሆነው ኡድሒያ በዕለቱ ተወዳጅና ከዒድ ሰላት ጋር የተያያዘ ዒባዳህ ስለሆነ ነው። (ኢብኑልቀይም) ነገር ግን ገንዘቡን መስጠቱ ለተቸገረ ሰው ይበልጥ የሚጠቅምበት ሁኔታዎች ላይ በላጩ ገንዘብ መስጠቱ ይሆናል። (ኢብኑ ዑሠይሚን) 🔴 ብዙሃኑ የፊቅህ ሊቃውንት ዘንድ ለኡድሒያ እርድ በላጭና ተመራጩ እንስሳ በቅደም ተከተል ግመል፣ ከዛም ከብት፣ ከዛ በግ ወይም ፍየል ነው። ይህ የሚባለው ግን ግመል ወይም ከብት አንድ አባወራ ለብቻው የሚያርድ ከሆነ ነው። ለጋራ ወይም በቅርጫ ከሆነ ግን የሚያርደው ከግመልና ከከብት ይልቅ በግ ወይም ፍየል ይሻላል። ኢማሙ ማሊክ በሁሉም ሁኔታ ላይ  በላጩ በግና ፍየል፣ ከዛም ከብት፣ ከዛ ግመል ነው የሚል አቋም አላቸው። ይህ በላጩና ይበልጥ ተወዳጁን ከመግለጽ አንጻር ነው እንጂ ከ4ቱ የቤት እንስሳት ውስጥ ማንኛውንም ቢያርዱ ትክክል ይሆናል። 🔴 ለኡድሒያ የሚታረድ ማንኛውም እንስሳ ቁመናና መልኩ የሚያምረው፣ ስጋው ይበልጥ ጣፋጭና ንጹህ ይሆናል የሚባለውና በዋጋም ውድ የሆነው ከዚህ ተቃራኒ ከሁኑ እንስሳት ይልቅ ለኡድሑያ ተወዳጅ እንደሚሆን ሊቃውንት ይስማማሉ። (አን'ነወዊይ) ይህም ኡድሒያ የሚታረደው ለአላህ ተብሎ ስለሆነና ለርሱ የሚደረግ ነገር በሙሉ ንጹሁ፣ ትልቅና የሚያምር መሆን ስለሚገባው ነው። 🔴 ለኡድሒያ የሚታረድ እንስሳ እድሜው በግ ከሆነ 6 ወርና ከዛ በላይ፣ ፍየል ከሆነ 1አመትና ከዛ በላይ፣ ከብት ከሆነ 2 አመትና ከዛ በላይ፣ ግመል ከሆነ 5አመትና ከዛ በላይ መሆን አለበት። ዕድሜው እዚህ ከተጠቀሰው በታች የሆነ እንስሳ ለኡድሒያ በቂ አይሆንም። 🔴 በተፈጥሮ ምንም ቀንድ የሌለው ወይም ቀንዱ በጣም ትንሽ የሆነ፣ ጭራ ወይም ላት የሌለው፣ የተኮላሸ፣ ጆሮው የተሰነጠቀና ከግማሽ በታች የሚሆነው ብቻ የተቆረጠ እንስሳን ለኡድሒያ ማረድ ችግር የለውም። በላጩ ግን ቀንድ ያለውና አካላቱ ሙሉ የሆኑትን ማረዱ ነው። 🔴 ግልጽ የሆነና እንደልቡ ተንቀሳቅሶ እንዳይበላ የሚያደርግ ሸፋፋነት ያለበት፣ አንድ ወይም ሁለቱም አይኑ የማያይ፣ በጣም ከመክሳቱ የተነሳ ቅልጥም፣ ጮማና ሞራው ያለቀ/የሌለው፣ ግልጽ የሆነ በሽታ ወይም የበሽታ ምልክት ያለበት ማንኛውም እንስሳ ለኡድሒያ አይሆንም። ከላይ ከተጠቀሱት እንከኖች ጋር ተመሳሳይና የባሰ እንከን ያለበትንም ማረድ አይቻልም። ነገር ግን ከእነዚህ እንከኖች መካከል ቀላልና ግልጽ ያልሆነ ያለበትን ማረድ አማራጭ ካጡ እንደሚቻል ሊቃውንት ይስማማሉ።ጤነኛና ከእንከን ንጹህ ሆኖ የገዙት እንስሳ ያለጥንቃቄ ጉድለት ከላይ የተጠቀሱ እንከኖች ቢገጥሙት ማረድ ይቻላል፤ አቅም ያለው ሰው ሌላ ቢቀይር ግን ይመረጣል። 🔴 አንድ በግ ወይም ፍየል ለአንድ አባወራ እስከ ቤተሰቦቹ፣ አንድ ከበት ወይም ግመል ለ7 እና ከዛ በታች ለሆኑ አባወራዎች ( ቤተሰቦች) ይበቃል። አንድ ሰው ኡድሒያው ላይ ማንኛውንም (በህይወት ያለም ይሁን የሞተን) ሰው በምንዳው ማጋራትና ማካተት ይችላል። ለአንድ አብሮ ለሚኖር ቤተ ሰብ አንድ ኡድሒያ የሚበቃ ከመሆኑም ጋር አቅም ያለው በሙሉ በስሙ ኡድሒያ ቢያርድ መልካም ይሆናል። 🔴 አንድ እንስሳ ቤት ውስጥ ተወልዶ ያደገ (የረባ)ም ይሁን፣ እራሱ ወይም ገንዘቡ በስጦታ መልኩ የተገኘም ይሁን በማንኛውም ህጋዊ በሆነ መንገድ የራስ የተደረገ ከሆነ ለኡድሒያ ነይቶ ካረዱት በቂ ይሆናል። የግድ በጊዜው ለኡድሒያ ተብሎ በራስ ገንዘብ የተገዛ ካልሆነ አይባልም። 🔴 አንድን እንስሳ ለኡድሒያ ከወሰኑት በኋላ ሀሳብ ቀይሮ ማረዱን መተው፣ መሸጥ ወይም ለሌላ ሰው ስጦታ መስጠት አይቻልም።ግዴታ ላልሆነ ኡድሒያ የተዘጋጀ እንስሳ ያለጥንቃቄ ጉድለት ቢጠፋ ሌላ መተካት ግዴታ አይሆንም። 🔴 ለኡድሑያ የታረደን እንስሳ ቆዳውንም ይሁን ምኑንም መሸጥ፣ ለአራጅ ክፍያ ይሆን ዘንድ ብሎ ምንም ነገር መስጠት አይቻልም።በምንም መልኩ ክፍያው ላይ ተጽዕኖ ሳይኖረው ለአራጅ እንደተጨማሪ ስጦታ ወይም ሰደቃ መስጠት ግን ይቻላል።
Показать все...
👍 10
ፍራሽ አልባው ምቾት‼ ================ ✍ ጀበለ ረሕማንና መስጂደ ነሚራን ጨምሮ በዐረፋህ ሜዳ ላይ ጌታቸውን ሲማፀኑ የዋሉ የአላህ ባሮች፤ ልክ ጸሐይዋ ስትጠልቅ ከፊሉ በባስ፣ ከፊሉ በእግሩ ወደ ሙዝደሊፋ ያመራል። ሙዝደሊፋ እንደደረሱ መጝሪብና ዒሻእን ሰግደው ባሉበት ለሽሽ ብለው ይተኛሉ። በቤታቸው ያለው ከምርጥም ምርጥ ተመርጦ የሚተኙበት ውብና ዘመናዊ ፍራሽ እንደ ሙዝደሊፋ አፈር አይመችም። የሙዝደሊፋ አፈር መኝታ እዛው ሂዶ ተኝቶበት ከቀመሰው ውጭ አፈር ከፍራሽ የበለጠ ይመቻል ቢባል ማን ያምናል! ከላይ መጠለያ የለም፣ አውሬ መጥቶ ይበላን ይሆን? ዝናብ ቢጥልብንስ…? ሰው እንደት ያለ አንዳች ስጋት ለመጀመሪያ ጊዜ ባየውና ልምዱ በሌለው ቦታ ላይ ነፍሱ ከፍርሃት ጸድታ በዛ ደረጃ በተረጋጋ መንፈስ ምንም የለብኝም ብሎ ለሽሽሽ ብሎ ይተኛል? ግን ሙዝደሊፋ ላይ እንደዛ ነው። አላህ ይቀበላቸው፣ እኛንም አላህ ይወፍቀን። || t.me/MuradTadesse
Показать все...
👍 11🤷‍♂ 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
🤝 7👍 5 3
_____ | __| | |__ | __ID | |__ |_____| |'''''"\_/'''''"| | |\_/| UBARAK foryou & your Family &Friend Allah Forgiveness stiqama and we give A key to Babarayan class in jenah 🌙🌟عيد مبارك🌴🌴🌴تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمل🌴🌴🌴🌙🌟 🌟🌙Eid Mubarak🌟🌙
Показать все...
8👍 1
1445ሒ_የጁሙዓ_ኹጥባ_በኡስታዝ_ያሲን_ኑሩ_በነጃሺ_ኢንተርናሽናል_መስጅድ_አፍሪካ_ህብረት.m4a9.11 MB
👍 21 3
26:06
Видео недоступноПоказать в Telegram
543.30 MB
👍 13 2
መጅሊሱንና ፕሬዝዳንቱን አድንቁልኝ‼ ========================= («መብታችንን ተቀማን ብለን እንደወትሮው አንገታችንን ደፍተን አንቀመጥም!» ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ) || ✍ የፌዴራሉ መጅሊስ የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽነጀ ሙስሊሙን አግልሎ እየሄደበት ያለውን መንገድ ቀድሞ ነቅቶበታል። መንቃት ብቻ ሳይሆን እንዲያስተካክል ወትውቷል። በግል በማናገር ካደረገው ጥረት ባሻገር በይፋዊ ደብዳቤም ባለፈ አሳውቋል። እነሆ ዛሬም የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ከሃሩን ሚዲያ ጋር የነበራቸው ቆይታ ሃሩን ሚዲያ በዚህ ጽሑፍ አቅርቦታል። «ሀገራዊ ምክክሩን በተመለከተ  የኢትዮጵያ  እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሀጅ ኢብራሂም መልእክት  አስተላለፉ። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የዘመናት የታሪክ ጠባሳ አለባቸው በዚሁ የተነሳ የሀገራዊ ምክክር ሲነሳ ቀድሞ የተደሰተው ሙስሊም ማህበረሰብ መሆኑን እንደተቋም ኮሚሽኑ በአዋጅ ሲቋቋም ቢሯቸው በመገኘት "የእንኳን ደስ አላችሁ" መልዕክት ያስተላለፈው በቀዳሚነት መጅሊሱ መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ተናግረዋል።የሀገራዊ ምክክር ሂደት ከተጀመረበት ባለፉት ሁለት አመታት ሙስሊምን ማህበረሰብ  በተመለከተ እንደ ተቋም ከኮሚሹኑ ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች ማድረጋቸውን አንስተዋል። ... የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ለምክክር ሒደት የሚቀርቡ የሀገሪቱን ሙስሊሞች አጀንዳዎች በተመለከተ ታላላቅ ምሁራንን ፤ኡለማኦች፣ የታሪክ ባለሙያዎች፣ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰውችና ሌሎች አካላት በማካተት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች በ9 አጀንዳዎች ተካተው፣በ47 ጥያቄ ቀርቦ የካቲት ወር ላይ ለኮሚሽኑ ማቅረቡን ሼኽ ሀጂ ለሀሩን ሚዲያ ገልፀዋል።የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታ በሚያደርግበት ወቅት ሙስሊሙ በሚመጥን ልክ አለማካተቱን በፌዴራል መጅሊሱ ስር ካሉት የክልል እና ከተማ አስተዳደር መጅሊሶች ካቀረቡት ቅሬታ መረዳታቸውን አያይዘው ገልፀው ነገር ግን ቁጥሩን በትክክል የሚያስቀምጥ መረጃ እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል። ... የሙስሊሙን አጀንዳዎች እና የተሳታፊ ልየታ ሂደቱን በተመለከተ መጅሊሱ ፕሬዚደንቱ የሚመራ የመጅሊሱን ስራ አስኪያጅ እና የህግ ክፍሉን ያካተተ ልዑክ ከኮሚሽኑ አመራሮች ጋር ከሰሞኑ የፊትለፊት ውይይት ማድረጋቸውን አንስተው ተፈፃሚነቱን እየጠበቁ መሆኑን ተናግረዋል።ለመሆኑ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የሙስሊሙን ቅሬታ ጆሮዳባ ብሎ የሚቀጥል ከሆነስ የመጅሊሱ አቋም ምን ይሆናል?በሚል ከሀሩን ሚዲያ ጋዜጠኛ ከማል ኑርዬ ለተነሳላቸው ጥያቄ "እንደዛ ይሆናል ብለን አናምንም ነገር ግን እኛ እንደትላንቱ መብታችንን ተቀማን ብለን አንገታችንን ደፍተን ዝም አንልም በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ትግላችንን እንቀጥላለን ብለዋል።ሙስሊሙ ማህበረሰብ በያለበት በሰላማዊ  መንገድ ንቁ ተሳታፊ በመሆን ሀገሩን እንድገነባ አንድነቱን እንድጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል። ... ¤ሀሩን ሚዲያ ከፌዴራል መጅሊስ ፕሬዚዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ጋር ያደረገውን ቆይታ በነገው ዕለት ወደናንተ ያደርሳል!» ... ©ሀሩን ሚዲያ
Показать все...
👍 9
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.