cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

ግጥም '''ስሜቶች ከተደበቁበት ወረቀት ላይ ሰፍረዉ እልፍ ትዝታዎች ከተበተኑበት ተሰብስበዉ የሚቀመጡበት የጸሃፊያን ሀሳብ ማረፊያ የአንባቢያን መጽናኛ ነች''። በዚ ቻናል @betagitim ግጥሞች🔥💌 ደብዳቤዎች✍️💌 ያገኛሉ። ሃሳብ እና አስተያየቶን በዚ 👇👇👇 ያናግሩን @dawit_wegayew

Больше
Рекламные посты
1 089
Подписчики
+724 часа
+337 дней
+7630 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

እሷን መልሱልኝ እግዜር ከሰዉ ለይቶ እንደሰራት እንደ ማህተብ ከልቤ ያነጻት በፍቅር ደቂቃ ሰኮንዶች የሆነችኝ ሀሁ በላ ፍቅርን ያስቆጠረችኝ ሀገር ምድሩ የመረቃት ከእኔም ልብ ዘመናት ያቆያት ጠፊ ሁና የዉሃ ሽታ ሁለመነዋ ሊቀር በትዝታ ልቤ ሳይደፈን ሳይዘጋ ማንም ላይገባበት እሷን መልሱልኝ የልቤን ነገር ዳግም ታስብበት ✍️ዳዊት ============================ @betagitim @betagitim
Показать все...
3
00:36
Видео недоступноПоказать в Telegram
2.08 MB
👍 4 1
ሀገሩን በሙሉ ፥ ጨለማ ሲወርሰው እድሜ ላንቺ ከንፈር መብራት ጠፋ ብዬ ፥ አልጮህም እንደሰው አንዴ ስትስሚኝ ፣ ብርሀን ያፈልቃል ፣ ነዝሮት ሰውነቴ አለም ይታየኛል ፣ እንኳን ጠባብ ቤቴ😂 ። (በላይ በቀለ ወያ) @betagitim @betagitim
Показать все...
2
Фото недоступноПоказать в Telegram
5👏 3
#አንክሮ °°°°°°°° ውዴ በፈጠረሽ ሐረጎቼን ቆጥረሽ ግጥሞቼን ደርድረሽ ስንኞቼን መዘሽ ' ይህ ግጥም ለኔ ነው? ደሞስ እውነት አለው? ' አጠይቂኝ ብለሽ አታድክሚኝ ደክመሽ እኔ በግጥሜ ላይ ካንቺ ውጪ ሰማይ ካንቺስ ውጪ ፀሐይ እንደማይወጣልኝ ከውነት ስንኝ ውጪ እንደማይገጥምልኝ ሐቄን እያወቅሽው ምነው ባታደክሚኝ እየደጋገምሽው ሐረጋትን መዞ እስከዛሬ ድረስ ጣቴ ካሰፈረው ለመሐላ እንዲሆን አንድ እውነት ያልያዘው ከግጥሜ መካከል ይህኛው ብቻ ነው ሌላው ግን አለሜ እውነት ያሰከረው እውነት የተረፈው እምልልሻለው አማን በአማን ነው። @betagitim @betagitim
Показать все...
3
እኔና አንቺማ   አመላችን ገጥሞ ባያዉቅም   ተራርቀን እንኳን ባንነፋፈቅም የተሳብንበት ቀለም ሁለታችንን የሚያፈካ የወደድነዉ መጠጥ ሁለታችንን የሚያረካ   አለ..የከነፍንለት ህልም              ለሌላዉ ቅጀት የሆነ የምንድክመልት ህይወት     ፍሬ አፍርቶ ትዉልድን ያዳነ አለ...ያ'ካፋ ለት ጉም ወርሶት ሰማዩን    እኔና አንቺ እንጠርጋለን ላይ ላዩን ጥሪት ተርፎት ሁሉ ሰዉ ምድሩን ሲያስዉበዉ እኔና አንቺ ግን ሰማዩን ነበር ምናስበዉ ምድር ሁሌ እንድትርስ     እንድታፈራ ዘላለም ብሩክ ትሁን እያልን     ምድረ ለምለም ይህ ሁሉ ቢሆንም እኔ እና አንቺ ግን አልተገናኛንም። ✍️ዳዊት @betagitim @betagitim
Показать все...
1
ተስፋ ና አንድ ቀን በጊዜ በትር ጅራፍ እለት ከእለት መ'ገረፍ መጓዝ     ከባህሩ በትዝታ መንሳፈፍ ርቆ ሲያስተክዝ ገዝፎ ተስፋዉ ሲደበዝዝ ቀን በቆለፈዉ ጊዜ በዘጋዉ በር ሰዉ አይከፍተዉም ቢችል እንኳን መስበር መቆም ታክቶን ጉዞዉ አንድ ቀን   በቁም ገደለን። ✍️ዳዊት @betagitim @betagitim
Показать все...
3👍 1
ማመን እና ማወቅ (በላይ በቀለ ወያ) . . ከቀጠርሽኝ ቦታ ፣ ቀርተሻል አውቃለሁ ያወኩትን እውነት ... ማመን ቢቸግረኝ ፣ "ትመጣለች " እያልኩ ፣ እጠብቅሻለሁ፡፡ "አትመጣም" እያለ... ለሚነግረኝ ሁሉ ፣ መቅረትሽን አውቆ "የቀረበት እንጂ ... የመጣለትማ ፣ አያውቅም ጠብቆ" ስል እመለሳለሁ በቃ ትመጫለሽ ፣ ቀርተሻል አውቃለሁ!!! @betagitim @betagitim
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram