cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ሐዊረ ሕይወት

ስለ ስርዓተ ቤተክርስቲያን ፣መንፈሳዊነትና አእምሯዊ አስተሳሰቦች ይለቀቁበታል ።ታድያ እርስዎም ሳይመሽብዎት በዚህ ሊንክ https://t.me/hawire21 ይቀላቀሉ።

Больше
Рекламные посты
388
Подписчики
Нет данных24 часа
-47 дней
-1430 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

“መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡” ምሳ. 31፡29 ክርስቶስን ያከበሩ፤ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ እውነትን የመሰከሩ፤ ስለ ቃሉ የኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ፤ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ታላላቅ የምድር ነገስታትን፤ ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ከነዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ፡፡ ቅድስት ድንግል ሆይ አንቺ እኮ፡- ሰማይ ዙፋኑ ምድር መረገጫው የሆነ፤ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የሰላም አለቃ፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ ከሆነውም አንዳችም እንኳን ያለርሱ ያልሆነ፤ ዓለምን ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የመለሰ፤ መንበሩን የሚሸከሙ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚንቀጠቀጡለት፤ የሁሉ ፈጣሪ፤ የሁሉ አምላክ እናት ነሽ፡፡ በፊትም አሁንም ወደፊትም ካንቺ በቀር ፈጣሪዋን ልጄ ብላ የምትጠራ ሴት አልነበረችም፤ የለችም፤ አትኖርምም ክርስቶስም እናቴ ብሎ የሚጠራት ብቸኛዋ ሴት አንቺ ነሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ እናት ስትሆኝ ድንግል፤ ድንግል ስትሆኝ እናት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ብሎ የሚጠራሽ ብቸኛዋ ሴት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ እግዚአብሔር መርጦና ጠብቆ ያስቀረሽ ዘር በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ ለዓለም ሁሉ ድህነት ምልክት የሆንሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ እናቴ ሆይ እንግዲህ እኔ ምን ልናገር? ሺህ ቃላትን ብደረድር ያንቺን ክብር ልገልፀውስ እንደምን እችላለው?  አዎ አሁንም እላለሁ “መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡” ምሳ. 31፡29 የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር፤ ምልጃ ቃል ኪዳኗ ይጠብቀን፡፡ አሜን!!! @Tenketam!
Показать все...
+ አንገት ተቆርሶ የተከበረ ልደት + በመጽሐፍ ቅዱስ ልደት ያከበሩት የግብፁ ንጉሥ ፈርዖንና የይሁዳው ገዢ ሄሮድስ ናቸው:: እርግጥ ነው ልደትን ማክበር በአሕዛብ ነገሥታት ቢዘወተርም የሚነቀፍ ነገር አይደለም:: ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስም የሚጀምረው የሰማይና የምድርን ልደት በሚተርከው "ኦሪት ዘልደት" ነው:: "እግዚአብሔር አምላክ፥ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ፥ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው" (ዘፍ. 2:4) ትልቅዋ አፈር መሬት በሰባት ዓመት ማረፍዋን አይተን እኛም በሰባት ቀን እንደምናርፍ የምድርን ልደት መተረክ አይተን ልደታችንን ብናከብር ክፋት የለውም:: (Microcosm /ንዑስ ዓለም/ እንዲል ቴዎሎጂ) የመድኃኔዓለምን ልደት ከፍ አድርገን የብዙ ቅዱሳንን ልደት ደግሞ እንዲሁ በቤተ ክርስቲያን ማክበራችን ልደት አንዱ እግዚአብሔርን ማመስገኛ ቀን ስለሆነ ነው:: ከኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት አንዳንዶቹ ደግሞ የልደቴ ቀን ብለው የሚያከብሩት ለዳግም ልደት ክርስትና የተነሡበትን ቀን ነው:: በዛሬው ዕለት ሔሮድስ ያከበረው ልደት ግን እጅግ የተረገመው ልደት ነበር:: ተጋባዦቹ የንጹሕን ሰው ደም የጠጡበት ልደት ሔሮድያዳ እንደ ታላቂቱ ባቢሎን "በሰማዕቱ ደም ሰክራ" የዋለችበት የልደት ግብዣ ቀን ነበር:: በዚህ ልደት የተቆረሰው ኬክ አይደለም:: በዚህ ልደት እፍ ተብሎ የጠፋው ሻማ አይደለም:: በሰይፍ ተቆርሶ በሰሃን የቀረበው ከሴት ከተወለዱት ሁሉ የሚመስለው የሌለ ቅዱስ ሰው አንገት ነበር:: በሻማ ፈንታ የጠፋው ክርስቶስ "እርሱ የሚያበራ መብራት ነበር እናንተም ጥቂት ዘመን በብርሃኑ ደስ ሊላችሁ ወደዳችሁ" ብሎ የተናገረለት መብራት ቅዱስ ዮሐንስ ነበር:: እርግጥ ነው በልደት ሰበብ ብዙ ኃጢአት ይሠራል:: በሔሮድስ ልደት ግን የተሠራው ግፍ ዓለምን የሚያንቀጠቅጥ ግፍ ነው:: ሔሮድስ የገደለው ማንን ነው? ነቢይን ነውን? እውነት እላችኁዋለሁ ከነቢይ የሚበልጠውን ነው:: ከሴት ከተወለዱት ሁሉ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ያለ አልተነሣም:: አንድን ሰው ብቻ የገደለ መስሎታል:: እርሱ የገደለው ዓሥር ሰው ነው:: ከነቢያት የመጨረሻውን ነቢይ ከሐዋርያት የመጀመሪያውን ሐዋርያ ገደለ:: ለብዙዎች የንስሓ ሰባኪያቸውን ለብዙዎች አጥማቂያቸውን ገደለ:: መለኮትን ያጠመቀውን ወደር ያልተገኘለትን አጥማቂ ገደለ:: አንገቱ ተቀልቶ ለሚያይ ወንጀለኛ ይመስለዋል እርሱ ግን ብቻውን በበረሓ የኖረ ባሕታዊ ነበረ:: ጮማ ያቆረጠ ጠጅ ባፉ ያልዞረ በልብስ ያላጌጠ ሰውነቱን በኃጢአት ያላሳደፈው መናኝ በዚያች በተረገመች የልደት ቀን አንገቱ በሰሐን ቀረበ:: የሐዲስ ኪዳኑ ናቡቴ ሕገ እግዚአብሔርን ርስት አድርጎ በኤልዛቤዋ ሔሮድያዳ ምክር በሔሮድስ ትእዛዝ ተገደለ:: የሐዲስ ኪዳኑ ኦርዮ የሔሮድስን አመንዝራነት ለመደበቅ በግፍ ተገደለ:: ዳዊት ኦርዮን ባስገደለ ጊዜ በእጅ አዙር አደረገው እንጂ በፊት ለፊት አላደረገውም:: በኁዋላም ዕድሜውን ሙሉ አልቅሶአል:: ሔሮድስ ግን ኀዘኑ የለበጣ ነበረ:: ቅዱስ ያሬድ “ቢበላው ይሻላል” ባለለት መሐላው አሳብቦ ታላቁን ነቢይ አንገቱን ቀላው:: ቅዱስ ኤፍሬም "አዳምን በጎኑ አጥንት በሔዋን ድል የነሣው ሰይጣን ሔሮድስን በጎኑ አጥንት በሔሮድያዳ ድል አደረገውና ቅዱሱን ዮሐንስ ገደለው" ይላል:: በቤተ መንግሥቱ መካከል የዮሐንስ አንገት እንደ ምግብ በሳሕን ይዘሽ ለእናትሽ ያቀበልሽ አንቺ ሴት ምንኛ ብትረገሚ ይሆን:: በምድረ በዳ የጮኸ አፉን ክፉ ያላዩ ዓይኖቹን ምላጭ ያልነካው ጠጉሩን በሳሕን ላይ ይዘሽ ስትሔጂ ምን ተሰምቶሽ ይሆን? መጥምቁን በመግደል ኃጢአትን መሸፈን አይቻልም:: ቅዱስ ኤፍሬም "የዮሐንስ ራስ የገዳዮቹን ኃጢአት አጉልቶ የሚያጋልጥ መብራት ነበረ:: ዮሐንስ በቃሉ ከተናገረው በላይ በሞቱ ኃጢአታቸውን ከፍ አድርጎ አሳየ" ይላል:: ክፋታቸውን ለመደበቅ እንደ ሔሮድስ ንጹሐንን የሚያስሩ : የልባቸውን ሠርተው በሞተ ጊዜ የውሸት የኀዘን መግለጫ የሚሠጡ ሁሉ መጨረሻቸው ዕብደት ነው:: ከማንም በላይ የሟች ደም የሚጮኸው በገዳይ ሕሊና ውስጥ ነው:: ሔሮድስ ዮሐንስ ገድሎ ተረበሸ:: አይሁድ ጌታ ለመነሣቱ ብዙ ምስክር ቀርቦላቸው ያላመኑትን እርሱ ግን ያለ ማስረጃ "መጥምቁ ዮሐንስ ተነሥቶአል" ብሎ መዘላበድ ጀመረ:: ዮሐንስን በሰይፍ መቅላትና ስብከቱን ዝም ማስባል የሚቻል መስሎት ነበር:: ዮሐንስ ግን ሰማዕት ሲሆን በገዳዩ ሔሮድስ ልብ ውስጥ ስብከት ጀመረ:: እኛ ቆመን ስንለፈልፍ አንሰማም ዮሐንስ ግን ሞቶ ገዳዩን አስጨነቀ:: ነቢዩ ኤርምያስን ጉድጉዋድ የጣለው ንጉሥ ጳስኮርን :- ከእንግዲህ ስምህ ማጎርሚሳቢብ ነው ለራስህና ለወዳጆችህ ፍርሃት አደርግሃለሁ እንዳለው የመጥምቁ ገዳዮች ገድለን አረፍን ሲሉ ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው ፍርሃት ሆኑ:: ንጹሐንን መግደልና በሞታቸው መሳቅ ይቻላል:: የደማቸውን ድምፅ ግን ከራስ ከሕሊና ማጥፋት አይቻልም:: አሁንም እንላለን ከሟች በላይ ገዳይ ያሳዝናል:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መስከረም 2 2013 ዓ ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Показать все...
+• ሰበር ዜና የለንም •+ የዛሬ ዘጠና ሦስት ዓመት የተከሰተ፥ ከዚያ በፊት ተከስቶ የማያውቅ፥ ምናልባትም ከዚህ በኋላም የመከሰት እድል የማይኖረው አንድ ነገር ልንገራችሁ። ይህ የሆነው በእንግሊዝ ሀገር ሲሆን የተከሰተውም ኤፕሪል 18 1930 ዓ.ም ነው። የታዋቂው የእንግሊዙ የዜና ማሰራጫ ቢቢሲ የስቱዲዮ ሰራተኞች የዜና ሰዓቱን ይጠባበቃሉ። ዕለቱም ስቅለት ነበር። የዜና አንባቢው ሰዓቱን ጠብቆ ወደ ስቱዲዮ ገባና፤ የዓለማችን አጭሩ ዜና እወጃ ሆኖ የተመዘገበውን ዜና እንዲህ በማለት አነበበ፦ “እንደምን አመሻችሁ። ዛሬ ስቅለት ነው። ለእለቱ ምንም ዜና የለንም።” ከዚያ በፊትም ሆነ በኋላ ‘ዛሬ ዜና የለም’ የሚል እወጃን በዜና ማሰራጫዎች የሰማ ሰው የለም። በእለቱ የቢቢሲ ኤዲቶሪያል ያሉትን የዓለም ጉዳዮች ዳስሶ “ዜና ለመሆን የሚበቃ ነገር የለም” በማለት ውሳኔውን ስላሳለፈ፤ ጋዜጠኛውም ለሕዝቡ ይሄንን አወጀ። ሁሉ ነገር ዜና - አልፎም ደግሞ “ሰበር ዜና” - ለሆነብን ለእኛ ትልቅ ትምህርትን የሚሰጥ ነው። ይህ ግን ከግርምት አልፎ ለእኛ ለክርስቲያኖች ጥልቅ መልእክት አለው። በነገራችን ላይ ዜና ማለት ወሬ ማለት ነው። ሁሉ ነገር ዜና (ወሬ) ተብሎ ለሕዝብ አይታወጅም። የቱ ቢነገር እንደሚጠቅም፥ የቱ ቢነገር እንደማይጠቅም መመዘን አለበት። በክርስትና የዜናዎች ሁሉ ዜና፤ የሰበር ዜናዎች ሁሉ ሰበር ዜና አንድ ጊዜ ታውጇል። ከዚህ በኋላ እኛ ክርስቲያኖች ልንሰማውና ልንደነቅበት የምንችል ሰበር ዜና የለንም። እኛ ማወጅ ካለብን ለሕዝቡ ሁሉ መልካሙን ዜና ወንጌልን እናውጅለት። የዘመናት የተስፋ ጥበቃ አልፎ ጌታችን ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን እናውጅ። ቃል ሥጋ መሆኑን እናውጅ። ንጉሥ እንደመሆኑ በቤተመንግሥት ሳይሆን በግርግም መወለዱን እናውጅ። በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ መጠመቁን እናውጅ። በአንዴ ልደግ ሳይል በጥቂቱ በጥቂቱ ማደጉን እናውጅ። ሁሉን የሚቀይር ትምህርትን ማስተማሩን እናውጅ። በራሱ ደቀመዝሙር ተላልፎ መሰጠቱን እናውጅ። አንድም በደል ሳይኖርበት እንደተፈረደበት እናውጅ። ለእኛ ሲል አጥንቶቹ እስኪቆጠሩ መገረፉን እናውጅ። ለእኛ ሲል በቀራንዮ በመስቀል ላይ መሰቀሉን እናውጅ። ስለ ኃጢአት ስርየት ብሎ መሞቱን እናውጅ። ከሁሉ በላይ ደግሞ ሞትን ድል አድርጎ መነሳቱን እናውጅ! እንዲህ አይነቱን መልካም ዜና ማወጅ ካልቻልን "ዛሬ ዜና የለም" ማለቱ የተሻለ ነው:: ሌላው ቢቀር የሰሚውን ጊዜ በማይጠቅሙ ወሬዎች ከማባከን እንድናለንና:: 🖋 Fresenbet G.Y Adhanom
Показать все...
“ዮሐንስ በእናቱ ሆድ ውስጥ ሆኖ የድንግል ማርያምን ድምፅ ሲሰማ የተሰማውን ደስታ መናገር ባይችልም ፣ ‘የተባረክሽ ነሽ’ ብሎ ለማመስገን ባይታደልም እናቱ ኤልሳቤጥ ግን ልጅዋን ወክላ ‘በደስታ ዘለለ’ ብላ ተናገረችለት፡፡ እርሱ ቃል አውጥቶ ማመስገን ባይችልም እናቱ የጌታን እናት አመስግና የልቡን አደረሰችለት፡፡ እርሱ በመዝለልና በመስገድ እናቱ ደግሞ በታላቅ ድምፅ በማመስገን ድንግል ማርያምን ተቀበሏት፡፡  በእናቱ ሆድ ውስጥ ያለ ሕፃን ‘ኖር’ ብሎ እጅ ነሥቶ የሚቀበላት ክብርት እንግዳ ከድንግል ማርያም በቀር ወዴት አለች? ገና ያልተወለደ ልጅ ድምፅዋን ሰምቶ ከእናቱ ሆድ ለመውጣት ከጓጓላት ማርያም ስም በቀርስ ሴት ልጅ ምጥ ላይ በሆነች ጊዜ ልጁን ልውጣ ልውጣ ለማሰኘት  ሊጠራ የሚገባው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስም ምን አለ?    ዮሐንስ በእናቱ ሆድ ሳለ የድንግል ማርያምን ድምፅ ስለሰማ ከተወለደ በኋላ የዓለምን ድምፅ መስማት አስጠልቶት ወደ በረሃ ሸሸ፡፡ አረጋዊው ስምዖን ‘ዓይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ’ እንዳለ ዮሐንስም ‘ጆሮዎቼ የእናትህን ድምፅ ሰምተዋልና ባሪያህን አሰናብተኝ’ ብሎ ለዓለም የሞተ ሆኖ በበረሃ ኖረ፡፡ ድንግሊቱን የሰሙ ሰዎች ልባቸው ወደ ምናኔ ሕይወት ያዘነብላል፡፡ ወደ ምድረ በዳ ሔደው ድንጋይ ተንተርሰው ሲተኙ ደግሞ እንደ ያዕቆብ እግዚአብሔር በላይዋ የተቀመጠባትን መሰላል ያያሉ፡፡     በማሕፀን የነበረውን ዮሐንስን በትኩረት ሳስበው በቤተ ክርስቲያን ያሉ የዋሀን ምእመናንን ይመስለኛል፡፡ በድንግል ማርያም ፍቅር ልባቸው እየነደደ ስምዋን ሲሰሙ ፣ ምስጋናዋን ሲያዩ የሚናገሩት የሚጠፋቸው ፣ እመብርሃንን እየወደዷት ቃላት አሳክተው ስለ እርስዋ ለመናገር ግን አንደበት የሚያጥራቸው ምእመናን ይታዩኛል፡፡ በቅኔ ማኅሌቱ ዳር ቆመው ማኅሌት ሲቆም ለጌታና ለእናቱ ምስጋና ሲቀርብ እንደ ዮሐንስ የሚይዙት የሚጨብጡትን አጥተው በደስታ የሚዘልሉ ፣ አንድም ቃል ከአፋቸው ሳይወጣ በሐሴት የሚሰግዱ ብዙ የዋሃን ምእመናን ትዝ ይሉኛል፡፡  ወዳጄ አንተም ድንግሊቱን ለማመስገን እንደ ዮሐንስ መናገር ካቃተህ ብዙ አትጨነቅ፡፡ መንፈስ ቅዱስን የተመላች እናትህ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከኤልሳቤጥ በላይ ለድንግሊቱ የሚሆን ብዙ ምስጋና      አላትና ለንግግርህ ሳትጨነቅ በደስታ እየዘለልህ አጅባት፡፡ በእናትህ ቤተ ክርስቲያን ሆድ ውስጥ እንደ ያዕቆብና ኤሳው ለብኵርና እየተጣላህ ሆድዋን መርገጥህን ትተህ እንደ ዮሐንስ ለምስጋናና ስግደት ከተጋህ ቤተ ክርስቲያን ፍቅርህን አይታ ምስጋናን ታስተምርህና እርስዋ ‘የጌታዬ እናት እንዴት ወደ እኔ ትመጣለች’ እንዳለች አንተም ነፍስ ስታውቅ እንደ ዮሐንስ ‘ጌታ ሆይ አንተ እንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ?’ ብለህ ለመናገር ትበቃለህ” የብርሃን እናት ገጽ 304-307
Показать все...
💌ይድረስ ለውድ የግቢ ጉባኤ 2015 ዓ.ም ተመራቂዎች ! 🎓🎓🎓Baga gammaddan🎓🎓🎓 እንግዲህ ታላቅ በእናንተ የሆነው ደስታ እየተሰማኝ የአደራ መልእክቴን ለመፃፍ ብዕሬን አነሳው፡፡ መቼ፤ እንዴት፤ ከየትኛው ፊደል በየትኛው ቃል እንደምጀመር  ባላውቅም በጣቶቼ የተጨበጠው ብዕር ከአዕምሮዬ የመጣውን የወንድማዊ ፍቅር መልዕክት ሀሳብ ሊያንጠባጥብ ወደደ፡፡ በአገልግሎት የተዛመደ ፍቅሩና ወዳጅነቱ እጅግ የከበረና የጠነከረ ነው፡፡ እንዴት ነው ቢሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለማገልገል የሚደረገው ውጣ ውረድ፤ መውደቅ መነሳት የአገልግሎቱን ጡዘት(መድመቅ) ስለሚያጎላው በዛው ልክ  የእርስ በእርስ የአገልግሎት ትስስር ይበልጥ እንዲጠነክር ስለሚያደርገው ነው፡፡ መቼስ አያንዳንዳችሁ እንጀራን ለማብሰል የሚሆነውን የቀለም ማገዶ ለመሰብሰብ ከአራቱም(4) የሀጉሪቱ አቅጣጫ  ማለትም ከሰሜን ከምስራቅ . . . ከደቡብ ከምዕራብ ለአንድ አላማ መሰባሰባችን እውን ሲሆን ከዚህ በዘለለ ፊታችንን ወደ ቤቱ መልሶ በሁለተኛው ጎናችን ሊስለን(በሁለት ወገን የተሳላችሁ ሰይፍ ሁኑ እንዲል) በፍቅሩ ወደ ግቢ ጉባኤው የበረከት ደጃፍ በእህቶችና በወንድሞች ላይ አድሮ አቀረበን....እኛም ቀረብን....መቅረብም ብቻ አይደል ቀመስናት፤ በአንደበት ቢነገር፤ በጣቶችም ቢፃፍ እንኳ የውስጣችንን ስሜት በሙሉ የማያስረዳልንን ማራኪ መንፈሳዊ ህብረት የሚታይበትን የግቢ ጉባኤ ህይወት ተዋሀድነው . . .ለመድነው . . .ኖርነው . . .ተማርነው፤ ዘወትር ብርሃን ጨልማ እስክትበራ በርታም እስክትጨልም ሙሉ ግዜያችንን ብንችል ሰጥተን ብናገለግል የማንሰለቸው የግቢ ህይወት በግዜ ቆይታችን መገደቡን ስናስብ ለሁላችንም የናፍቆት ስብራትን ማስከተሉ በተለይ ለኖረበት ኖሮም ለተጠቀመበት ሰው አይቀሬ ነው፡፡ ምክኒያቱም ይህን የመሰለ የፍቅር አገልግሎት በግዜ ቆይታ ሲገታ የእውነት ሆድ ያስብሳል ብንል ውሸት አይሆንብንም፡፡ ባለ 3 ዓመቱ በ3 . . . ባለ 4ቱ በአራት . . .ባለ 5 እና ከዚያ በላይም ቢሆን ግዜው መቼ ሄደ ሳይባል ይሄ ምርቃት መጥቶ ይደቀንና የናፍቆታችንን ሸምቀቆ ሲያጠብቀው ምንው ቆይታዬን ባራዘመውና ከግቢ ጉባኤው ጋር እንዲሁ በፍቅር በደመቀ አገልግሎት ተመስጬ ጌታን ባገለገለኩ ያሰኛል!!! ያም ሆነ ይህ ግን አቋምና ብርታትን፤ ጥንካሬና ጽናትን በግቢ ጉባኤው ቆይታ ገንዘብ ላደረገ ሰው ፈታኝ ይሆናል የሚል ምልከታ በዉስጤ የለም፡፡ ለዚህም ለወደፊቱ የስራው ህይወት እንዲዘነጋ የማልሻውን ምክር በአደራ ቋጠሮ ጠቅልዬ ላስረክባችሁ የወደድኩት፡፡ እንግዲህ ውድ የግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች የዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁን እናንተ ባሰባችሁት ሳይሆን ጌታ በመራችሁ  የአሸናፊነት መንገድ ለዚህ ታላቅ ክብር ምርቃት በቅታችኋል.......‹‹. . . ስለማይነገረው ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን››!! አሜን፡፡ግን ተወዳጆች ሆይ ስለእውነት ከዚህ ስትወጡ ህይወታችሁ ምን ይመስል ይሆን???? ያ . . . ያ . . .ያኛው  ብርቱ የአገልግሎት ፍቅራችሁ  ጠንካራው የአስፈጻሚነት ወኔያችሁ ሚማርከው የተልዕኮ ፅናታችሁ  አብሯችሁ  ይጓዝ ይሆን?ሰራው፤ ትዳሩ፤ የአለም ውጣ ውረድ በግቢ ቆይታችሁ  ያተረፋችዋቸውን  መክሊቶች እንዳያስጥላችሁ ከበፊት ይልቅ አሁን በመንፈስ ልትበረቱ፤ ልትጠነክሩ  ይገባል!!!ገንዘብ ሲመጣ፤ የተደላደለ የመሰለው ኑሮ ከፊት ብልጭ ሲል ጠንካራው የመንፈሳዊነት ወኔያችሁ  እንደ ጽልመት እንዳይጨለም ከአሁኑ መንፈሳችሁን ለዚያ ተጋድሎ እንድታሰናዱት  አደራ አልኩኝ!! እናም ተወዳጆቼ! መቼስ ለመካሪነት የበቃው ሆኜ ሳይሆን ምክርን ያልጠገብኩ ወጠጤ መሆኔን በማመን ፊደላትን በሚያኮላትፉ ጣቶቼ ወንድማዊ/መንፈሳዊ/ ስንቅ እንደ አቅሜ ባስቋጥር በሚል የዋህነት ነው፡፡መቼስ እንደተረዳችሁኝ ባለ ጎዶሎ እምነት ነኝ አልልም!!! ምክኒያቱም ይህች ትንሽ ቋጠሮ ከማትዘነጓቸው የግቢ ጉባኤው የትዉስታ መዝገብ(አገልግል) ውስጥ በጥንቃቄ እንደምታኖሩት በማመን ነው፡፡ የምወዳችሁ የግቢ ጉባኤ ፍሬዎች  ሆይ በግቢ ጉባኤው ያደረጋችሁትን መልካም ቆይታችሁን የማይዘነጋው የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀሪውንም ዘመን/የስራውን መስክ ቆይታ/ በፍቅሩ እንዲባርክላችሁ እየተመኘው፤ በውስጣችሁ ያለውን የመልካምነት የሀይማኖት ፍሬ ከልባችሁ ነቅሎ በማስተፋት ሊለቅመው በዙሪያችሁ  ከሚያንዣብበው አድፍጦም ከሚጠብቃችሁ የጨለማው ገዥ ጥንተ ጠላት ዲያቢሎስ ጠብቆ እንዲያቆያችሁ በመመኘት መልካሙ ሁሉ እንዲገጥማችሁ ወደ ፈጣሪ እየተማፀንኩ በቅዱስ ጳውሎስ መልእክት የምክር ስንቅ የአደራ ቋጠሮዬን አስሬ ልሰናበታችሁ…… ‹‹እምነታችሁ አጅግ ስለሚያድግ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በእርሳችሁ ስለሚበዛ፤ ሁልግዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤ ስለዚህ በምትታገሱት በስደታችሁም(የአለም ኑሮ ስደት ነው!!) በመከራችሁ ሁሉ ከመጽናታችሁና  ከእምነታችሁ የተነሳ በእግዚአብሔር አብያተ ቤተክርስቲያናት ስለ እናንተ እራሳችን እንመካለን . . . . .  ስለዚህም ደግሞ እንደ አምላካችን እንደ ጌታም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ፤የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእናንተ ዘንድ ሊከብር እናንተም በእርሱ ዘንድ ልትከብሩ፤ አምላካካችን ለመጠራቱ የምትበቁ አድርጎ ይቆጥራችሁ ዘንድ፤ የበጎነት ፈቃድ ሁሉ የእምነትም ሥራ በኃይል ይፈፀም ዘንድ ስለ እናንተ ሁልጊዜ እንፀልያለን››          2ኛ ተሰ 1፡3-12፡፡ 🌻🌹እንኳን ደስ አላችሁ🌹🌹!      Congratulations!/Baga gammaddan ! 👉መልካም የሥራና የአገልግሎት ዘመን ይሁንላችሁ! ከወንድማችሁ ዲ/ን መኳንንት መላኩ ተፃፈ
Показать все...
💌ይድረስ ለውድ የግቢ ጉባኤ ተመራቂዎች ወንድሞቸ እና አህቶቸ ! " እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገልን ደስም አለን "!!! ከሁሉም አስቀድሜ ከዚህ እንድትደርሱ የረዳችሁን የሰራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር ን በምልጃዋ የረዳቻችሁን የቃልኪዳኗ አመቤት ቅድስት ድንግል ማርያምን በክንፎቹ ጥላ ከመከራ የጠበቃችሁን  ገናናዉ መላእክ ቅዱስ ገብርኤልን እያመሰገንኩ ከአዕምሮዬ የመጣውን የወንድማዊ ፍቅር መልዕክት በትንሹ ጫርጫር ላደርግ ወደድኩ። በአገልግሎት የተዛመደ ፍቅሩና ወዳጅነቱ እጅግ የከበረና የጠነከረ ነው፡፡  የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለማገልገል የሚደረገው ውጣ ውረድ፤  በዛው ልክ  የእርስ በእርስ የአገልግሎት ትስስር ይበልጥ እንዲጠነክር ስለሚያደርገው ነው፡፡   መሰባሰባችን እውን ሲሆን ከዚህ በዘለለ ፊታችንን ወደ ቤቱ መልሶ  በፍቅሩ ወደ ግቢ ጉባኤው የበረከት ደጃፍ በእህቶችና በወንድሞች ላይ አድሮ አቀረበን።   መንፈሳዊ ህብረት የሚታይበትን የግቢ ጉባኤ ህይወት ለመድነው ሙሉ ግዜያችንን  ሰጥተን ብናገለግል የማንሰለቸው የግቢ ህይወት በግዜ ቆይታችን መገደቡን ስናስብ ለሁላችንም የናፍቆት ስብራትን ማስከተሉ በተለይ ለኖረበት ኖሮም ለተጠቀመበት ሰው አይቀሬ ነው፡፡ግቢ ጉባኤን ባሰብናት ጊዜም ማንባታችን በትዝታ መመለሳችንም የማይቀር   ነዉ። ዉድ የግቢ ጉባኤ ፍሬዎች  ወንድሞቸ እና እህቶቸ በግቢ ጉባኤው ያደረጋችሁትን መልካም ቆይታችሁን የማይዘነጋው የሰራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር ቀሪውን ዘመናችሁን እንዲባርክላችሁ ልባዊ ምኞቴ ነዉ። በውስጣችሁ ያለውን የሀይማኖት ፍሬ ከልባችሁ ለማዉጣት  አድፍጦም ከሚጠብቃችሁ  ጥንተ ጠላት ዲያቢሎስ ጠብቆ እንዲያቆያችሁ በመመኘት  ልሰናበታችሁ ...😭 🌻🌹እንኳን ደስ አላችሁ🌹 መልካም የሥራና የአገልግሎት ዘመን ይሁንላችሁ!
Показать все...
📕#ተአምር_ዘአቡነ_ዘርዓ_ብሩክ🌹 📘☞•••ወር በገባ በ13 ታስበው የሚውሉ አባታችን ዘርዐ ቡሩክ ያደረገው ታአምር ይህ ነው ስሟ ፋሲካዊት በምትባል ሴትዮ ቤት እግዚአብሔር ዳግመኛ ታላላቅ ተአምራት አደረገ፡፡ ያቺም መልካም ሴት ሁል ጊዜ የዘርዐ ብሩክ መታሰቢያውን ታደረግ ነበር አሱንም ከመውደዷ የተነሳ ተገዛችለት ለቃሉም ታዙችለት፡፡ ☞በአንድ ወር ለመታሰቢያው የሚሆን የማኀበሯ ተራ በደረሰ ጊዜ ትደክም ጀመር ብዙ ቀን ሰትጥር ስትግር ሰይጣን ቀንቶባት የመታሰቢያውን የወይን ጠጅ አጠፋባት፡፡ ☞ይህ ሁሉ የደረሰብኝ ሰለ ኃጢአቴና ሰለ በደሌ ነው ብላ ብዙ ምሾ እያወጣቸ ፈጽማ አለቀሰች፡፡ ☞እግዚአብሔርም የለቅሶዋን ጽናትና ኅዘኗን አይቶ በሰይጣን ቅናት የጠፋባትን ያን ወይን ጠጅ የቃናን ውሃ ለውጦ የጣመ እንዳደረገው ያን ቦዶ እንስራ ወደ ወይን ለወጠው ፈጽሞም ጣፈጠ፡፡ ☞በዚያ በጻድቁ አባቷ ዘርዐ ብሩክ ጸሎት ያ የወይን ጠጅ ተለውጦ እንዳ ጣፈጠ ያቺ ሴት አይታ እግዚአብሔርን አመሰገነች፡፡ እናቱ ድንግል ማርያምንም አመሰገነች በጸሎቱና በአማላጅነቱ ተአምራትን መንክራትን ያየረገላት ቅዱስና ብፁዕ የሚሆን አባታችን ዘርዐ ቡሩክ እጅግ ወደደችው፡፡ ☞የጣፈጠው ያ የወይን ጠጅም በክቡር የሚካኤል በዓል ቀን ዳግመኛ አለቀባት የነበሩ ብዙ ማኀበርተኞችም እጅግ አዘኑ የወይን ጠጅ ትበደራቸው ዘንድ በየሀገሩ ዞረች የምትሰጣቸው የወይን ጠጅ ባጣች ጊዜ ከዚያ ከሚጣፍጠው የወይን ጠጅ የቀረ(የተረፈ)አንድ ማድጋ ቅራሪ አመጣችላቸው በቀዱት ጊዜ አተላ ሆነ፡፡ ☞ያዚ ሴትም እጅግ አዘነች ማኀበርተኞችም ሁሉ እንደ አርሷ አዘኑ ዳግመኛ ቀዱት ንጹህና ጣፈጭ ሆነው አገኙት እጅግ ተደነቀች ማኀበርተኞችም እንደ እርሷ አደነቁ፡፡ ☞ይህ ሁሉ ተአምር የተደረገ በጻዱቁ አባታችን ዘርዐ ብሩክ ጸሎትና ልመና ነው፡፡ ☞መታሰቢያውን ለምናደርግ ስሙን ለምንጠራ እንደ እርሷ ተአምራትን ያድርግልን ለዘለአለሙ አሜን፡፡ ☞(ገድለ ዘርዐ ቡሩክ) ☞https://t.me/hawire21
Показать все...
ሐዊረ ሕይወት

ስለ ስርዓተ ቤተክርስቲያን ፣መንፈሳዊነትና አእምሯዊ አስተሳሰቦች ይለቀቁበታል ።ታድያ እርስዎም ሳይመሽብዎት በዚህ ሊንክ

https://t.me/hawire21

ይቀላቀሉ።

እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ።  💠#በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ። 💠በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው። 💠ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ  በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን! #ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገኪዳን
Показать все...
“እኔ ክርስቲያን ነኝ፡፡ ለሚጠይቁት እንደዚህ ብሎ የሚመልስ ሰው በአንድ ጊዜ በኹሉም ነገሮቹ ላይ ማወጁ ነው፡፡ ሀገሩ የት እንደ ኾነ፣ ሥራው ምን እንደ ኾነ፣ ቤተሰቡ እነማን እንደ ኾኑ መመስከሩ ነው፡፡ ክርስቲያን የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ነዋሪ እንጂ በምድር ላይ ካሉት ከተሞች የአንዲቱም አይደለምና፡፡” ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Показать все...
🎭 ሁለቱ ወንበዴዎች 🎭 ሁለቱ ወንበዴወች አብረው ሲዘርፉ የነበሩ ጓደኛሞች ነበሩ።... ...እነዚህ ወንበዴዎች እኩል ቢበድሉም እኩል ግን አልተጸጸቱም።💠ለስጋቸው አብረው ኖረው ለነብሳቸው ሲሆን ተለያዩ።✏️ዛሬ ቢካፈሉት ለሁለታቸውም የሚበቃ የህይወት እንጀራን አግኝተው ነበር። አንዱ ሲበላው ሌላኛው ግን ረግጦት አለፈ። ጌታችን የተሰቀለው ከሁለቱም በእኩል የቅርብ ርቀት ነበር፤ ሁለቱም የመስቀሉን ተአምራት አይተዋል፤ የተመለሱት ግን ሁለቱም አይደሉም። 🔶 እንደ ሸክላና ሰም ሆኑ ፤ ሁለቱም ወደ ፀሐይ ክርስቶስ ቀረቡ፤ አንደኛው እንደ ሸክላ በፀሐይ ምክንያት ሲጠነክር አንደኛው ግን ቀልጦ ቀረ። በዚህ ምክንያት "ሦስት መስቀሎችን በቀራንዮ ስናይም ሦስት ነገሮችን እናስታውሳለን፦ ❶ የመካከለኛውን ቅዱስ መስቀል ✝️ ስናይ ያለሀጢአት ለቤዛነት የመሞት ምልክት ሆኖ ይታየናል፤ ❷ የቀኙን መስቀል ➕ ስናይ ንስሃ ገብቶ የመሞት ምሳሌ ሆኖ ይታየናል፤ ❸ የግራውን ➕ ስናይ ግን ከሃጢአት ጋር የመሞት ምልክት ይሆንብናል። 🧶{ሕማማት ገጽ 153 በ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ} https://t.me/hawire21
Показать все...
ሐዊረ ሕይወት

ስለ ስርዓተ ቤተክርስቲያን ፣መንፈሳዊነትና አእምሯዊ አስተሳሰቦች ይለቀቁበታል ።ታድያ እርስዎም ሳይመሽብዎት በዚህ ሊንክ

https://t.me/hawire21

ይቀላቀሉ።

Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.