cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ተዋሕዶን እንወቅ።

አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ሥረይ ለነ ኩሎ አበሳነ ኢታብአነ ውስተ መንሱት እግዚኦ አድህነነ እምዕለት እኪት ወባልሀነ ውስተ መንሡት። ✝በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ✝ የየእለቱን ስንክሳር፥ ውዳሴ ማርያም፥ ፀሎተ አርጋኖን፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን፥ የጻድቃንና የሰማእታትን ገድል፥ የተለያዩ መንፈሳዊ ጥያቄዎችን፥ የድሮ እና አዳዲስ መዝሙራትን የሚያገኙበት ቻናል ነው። ይቀላቀሉን።

Больше
Рекламные посты
1 007
Подписчики
+824 часа
+357 дней
+18030 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

🕯ዜና እረፍት በአቡነ ዮሴፍ🕯 🌿የሁለት ሴት መነኮሳት እረፍት በታላቁ ገዳም አቡነ ዮሴፍ🌿 🌷ከየት እንደመጡ፣ ምንነታቸው፣ ትውልዳቸው፣ ቤተሰባቸው የሚገልጽ መረጃ የለም።ብቻ ከበርካታ ገዳማት እንደቆዩና በእግራቸው ድካም በረከት እንደሰበሰቡ በያዙት ማስታወሻ ላይ የከተቡት ቀለም ይመሠክራል። 🌹ሁለቱም እናት አንዷ 21 ዓመት አንዷ የ25 ዓመት  የእድሜ ክልል ላይ እንደሚገኙና ስመ-መጠራያቸው ወለተ ትንሳኤና ወለተ አረጋዊ እንደሆነ መታወቂያቸው ይመሰክራል። 🌹ሚያዚያ 30 2012 ዓም የቅዱስ አቡነ ዮሴፍ ፍልፍል የዋሻ ቤተክርስቲያንን ተሳልመዋል። በዚሁ ቀን ከሰዓት ቡሃላ ሱባዔ እንደሚይዙና ወደ ሌላ ቦታ እንደማይሄዱ ፣ የጉዞ መጨረሻቸው እንደሆነ ከዋልዲቢት ገዳም ወደ ቅዱስ አቡነዮሴፍ ይዟቸው ለመጣው ዲያቆን " ከዚህ ቦታ ለቀን ወደ ሌላ ቦታ አንሄድም። ነገር ግን ደግመህ ወደ ዚህ ቦታ ስትመጣ አታገኘነም።" ብለውታል። ከዚህ ዓለም ሊያልፋ? ወይስ ከዛው ሊኖሩ? 🌷ግንቦት 1 2012 ዓም በታላቁ የአቡነዮሴፍ ተራራ ወገብ ላይ ካሉት ቀደምት የመነኩሳት ዋሻ ውስጥ ሱባዔ ገቡ። አንድ ሱባዔ አለፈ። አልወጡም ከበዓቱ። ሁለተኛው ሱባዔ ሞላ። አልወጡም ከባዕቱ ሦስተኛ ሱባዔ ሞላ። 20 ቀናት ሆነ። 🌷አንድ ሰው በጥዋት ፎቶ ግራፍ ሊያነሳ ወደ ተራራው ልቡን አነሳስቶት ሄደ። በድንገት የማይንቀሳቀሱ መነኩሳት ሲመለከት ቀርቦ ሲመለከታቸው ትንፋሽ የለም፣ ሲነካቸው ሰውነታቸው ቀዝቃዛ ነው፣ የደም ዝውውራቸው አቁሟል። የአካላቸው ጅማት በታምር አልደረቀም ፤ የመንፈስ ቅዱስ ስራ ነው። ለመገነዝ ምቹ ሆነ። 🌹 ከዚህ ቀደም ያልታወቀ፣ ያልተለመደ አዲስ ነገር ዋሻቸውን ከሽቶ የበለጠ ልዩ መዓዛ አወደው። ሰውነታቸውም ልዩ መዐዛ ይሸታል። (ጻዲቅ ሲሞት መላእክተ ብርሃን ከገነት ልዩ መዐዛ ያላትን አበባ ቆርጠው አምጥተው ሞቱ ለደረሰው ለጻዲቁ ሰው ያሸቱታል። በዚህ መሳጭ ፣ ጥዑም መዐዛ ነፍስ ከስጋ ትለያለች። መንገደ ሰማይ እና ራእየ ማርያም ያንብቡ።) 🌹ዓይን ሳይፈዝ በወጣትነት። በጸሎት ላይ እንዳሉ ፤ በጉልበታቸው እንደተበረከኩ ፣ ሁለት እጆቻቸውን ወደ ላይ እንደ ዘረጉ፣ ዓይኖቻቸው ወደ ሰማይ እንዳ ቀና የዚህን ዓለም አድካሚውን ኑሮ ተሰናብተው ወደ ላይኛው ዓለም ግንቦት 19 ቀን በቅዱስ አቡነ ዮሴፍ እረፍተ በዓል ቀን 2012 በቅዱስ ገብርኤል እለት ተሰናበቱ ። 🌷ሻንጣቸው ተፈተሸ። የተለያየ የስንቅ ዓይነት የለም። ልብስም የለም። ብርም የለም።ትንሽ የማያሰነብት ሽንብራ አለ። ነገር ግን መንፈሳቸውን ለመመገብ አብዝተው በርካታ የጸሎት መጸሐፍት፣ በርካታ ገድላት....ይዘዋል። በአንዲት ብጫቂ ወረቀት፤ " ዳዊቱን ከዚህ ቦታ ላመጣን ዲያቆን... ይሰጠው ተብሎ አድራሻ ተጽፏል" 🕯በቅዱሱ ስፍራ በቅዱስ አቡነዮሴፍ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በታላቅ ክብርና በሊቃውንት ታጅበው ለአምላክ ብለው መከራ የተቀበሉለት ቅዱስ በድነ ስጋቸው በክብር አረፈ። // የአሁኑ ኢትዮጵያውያን መልካሙን ታሪክ የመጻፍ ልምዳችንን ውሀ በልቶታል // Credit :©ኢያሱ ዘአቡነ ዮሴፍ
Показать все...
👍 5
🥰 7
የአሥርቱ ትዕዛዛት አከፋፈል   የክርስቲያን ሕግ የፍቅር ሕግ ነው። ቅዱስ ጴጥሮስ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታል ካለ በኋላ ከአሥርቱ ትዕዛዛት የተወሰኑትን በመጥቀስ ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍጻሜ መሆኑን በግልጽ ይናገራል። /ሮሜ 13÷8-10/   እንዲሁም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን ፍቅር በሁለት ይከፈላል። /ማቴ 22÷34-41/ 1, ፍቅረ እግዚአብሔር (እግዚአብሔርን መውደድ) 2, ፍቅረ ቢጽ (ወንድምን መውደድ) - በተጨማሪም ጌታችን ሕግም ነቢያትም በነዚህ በሁለቱ ትዕዛዛት ተጠቃለዋል ብሎ ስለተናገረ በዚህ መነሻነት አሥርቱን ትዕዛዛት በሁለት እንከፍላቸዋለን። 1, #ፍቅረ_እግዚአብሔር ፦ ከ1ኛው ትዕዛዝ አስከ 3ተኛው ትዕዛዝ ድረስ ያሉት። - ከኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁንልህ - የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ - የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ 2, #ፍቅረ_ቢጽ ፦ ከ4ተኛው ትዕዛዝ እሰከ 10ኛው ትዕዛዝ ያሉት። - አባትና እናትህን አክብር  - አትግደል - አታመንዝር - አትስረቅ - በሐሰት አትመስክር - የባልንጀራህን ቤት አትመኝ - ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ JOIN @Applied_CHRISTIANITY
Показать все...
🙏 6👍 1
#የመጽሐፍ_ቅዱስ_ንባብ_ክፍል_1 📖 መዝሙረ ዳዊት መዝ 1-2 የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍለ ንባቡን በሚመች መልኩ በጽሑፍና በድምጽ በአንድነት አቅርበነዋል ⚡INSTANT VIEW የሚለውን በመጫን ይመልከቱ ! #ለሌሎች_አጋሩ
Показать все...
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

ንባቡን በድምጽ ለማድመጥ ከስር ያለውን video በመክፈት ይጠቀሙ ! "በበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !" መዝሙረ ዳዊት መዝ 1 ¹ ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። ² ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። ³ እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። ⁴ ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፥ ነገር ግን ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ ናቸው። ⁵ ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ፥ ኃጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር አይቆሙም። ⁶ እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች። ______________________________ መዝሙረ ዳዊት መዝ 2 ¹ አሕዛብ ለምን…

👍 5
ተግባራዊ ክርስትና: አሥርቱ ትዕዛዛት በምን ላይ ተሰጡ ? አሥርቱ ትዕዛዛት በሙሴ በተሰጡ ጊዜ በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ተጽፈው ነበር። /ዘጸ 31÷18 ፣ 34÷1-28/ #ታቦት እና #ጽላት - አስቀድሞ በኦሪት ዘመን #ታቦት ማለት ማደሪያ መገለጫ ማለት ሲሆን ማደሪያነቱም ስለ ሁለት ነገር ነው። 1, ለእግዚአብሔር ክብር 2, ለጽላቱ - የጽላት ማደሪያ እንዲሆን ታቦት ከግራር እንጨት እንዲሠሩ ታዘዋል /ዘጸ 25÷10-22/ #ጽላት ማለት ደግሞ በቁሙ ሲፈታ ሰሌዳ ማለት ነው። ሰሌዳነቱም ለእግዚአብሔር ትዕዛዛት ነው። የሚሰራውም ከድንጋይ ነው /ዘጸ 10÷1/ ◦ በቤተክርስቲያናችን ዛሬም ታቦትና ጽላት እንደ ብሉይ ኪዳን በመለያየት ሳይሆን በአንድነት ለመስዋዕትነት እንዲመች ተደርጎ ይቀረጻል። ይህን ስላደረገች አንዳንድ ያልተረዲ ሰዎች ቤተክርስቲያን ጣኦት ታመልካለች ለድንጋይ ታሰግዳለች ይላሉ። ነገር ግን ይህን ማለታቸው አግዚአብሔርን መቃወማቸው መሆኑን ሊያውቁ ይገባቸዋል። ምክንያቱም የጽላቱም ሆነ የታቦቱ ሰጪ ወይም መስራች እግዚአብሔር ነው። በሐዲስ ኪዳንም ቤተክርስቲያናችን እንደ ኦሪት የእንስሳት ደም ሳይሆን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም እየፈተተት (እየሰዋችበት) ለምዕመናን የእግዚአብሔር ልጅነትን የዘለዓለም ሕይወትን ታድልበታለች። /ዮሐ 6÷53/ #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ JOIN @Applied_CHRISTIANITY
Показать все...
🥰 3👍 2💔 1
በመልካም ሥነ ምግባር ውጤታማ ለመሆን ከፈለግን መልካም ምግባራትን በታማኝነት ማድረግና ለምን እንደምናደርገው ጠንቅቀን ማወቅ ይጠበቅብናለ።  ያንንም ስናደርግም በስሜታዊነት ማደረግ አይገባም ሌሎች ሲያደርጉ አይቶ ማድረግ አይገባም የሆነ ጥቅም ለማገኝት ተብሎ ማድረግ አይገባም......  እንደዚህ ከሆነ ዘለቄታዊነት አይኖረውም ትክክለኛው የሥነ ምግባር መገለጫ ነው ማለትም አንችልም። - አምላካችን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንድንሆን የሚፈልገው ለጊዜያዊ ሳይሆን በምድራዊውም ኑሮ በሰማያዊውም ኑሮ ጭምር ነው። #ለአዳም_የተሰጠው_ትዕዛዝ /ዘ ፍጥ 2÷18-19/ "እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።"  ◦ በገነት ካለው የዛፍ ፍሬ መብላትና አለመብላት የመጀመሪያው የሥነ ምግባር ህግ ነው። የመኖርና ያለመኖር ማሳያ ነው። ◦ አዳም ትዕዛዙን መጠበቅ ባለመቻሉ ለእርሱ ብቻ ሳይሆን በእርሱ መስመር ለተወለዱት በሙሉ በኃጢያት መውደቅ ምክንያት ሆኗል። #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ JOIN @Applied_CHRISTIANITY
Показать все...
🙏 7👍 2🥰 2
የክርስትና ህይወትን ስንጀምር የመጀመሪያው ሥራችን ለእግዚአብሔር ቃል መገዛት መሆን አለበት። “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። /ዮሐ 14፥15/ #የዐሥርቱ_ትእዛዛት_ዓላማ 1, ከግብጽ ባርነት ስላወጣቸው ውለታውን እንዳይረሱ። 2, ወደፊት በአረማውያን (በማያምኑ) መካከል ሲመላለሱ ከኃጢያት እንዲጠበቁ። 3, አካሄዳቸው ምን ምን አቅጣጫ መያዝ እንዳለበት ለማመልከት ነው።ዛሬም እግዚአብሔር ከኃጢያት ነፃ አውጥቶናል ይኸውም በበግ ደም ሳይሆን በልጁ ደም ስለሆነ ውለታውን ልናስብ ይገባል።ኃጢያት በሚሰሩ አለማውያን መካከል ስንኋዝ ዐሥርቱ ትዕዛዛትን በማስተዋል እንጠብቅ። ◦ ትዕዛዛቱን ከጠበቅን መንፈሳዊ አካሄዳችን መልካሙን አቅጣጫ የተከተለ ይሆናል። #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ JOIN @Applied_CHRISTIANITY
Показать все...
🙏 5🥰 2
ስድስቱ ሕግጋተ ወንጌል 1, በወንድምህ ላይ በከንቱ አትቆጣ 2, ወደ ሴት አትመልከት በልብህ አታመንዝር 3, ሚስትህን ያለ ዝሙት ምክንያት በሌላ ነውር አትፍታ 4, ፈጽመህ አትማል 5, ክፋን በክፋ አትመልስ 6, ጠላትህን ውደደ #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ JOIN @Applied_CHRISTIANITY
Показать все...
🙏 7👍 3
የክርስቲያናዊ ሥነ ምግባራት መለኪያ ◦ ሕግ ሕግ የሚለው ቃል ደነገገ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን በቁሙ ሰፈታ ውሳኔ ሥርዓት ደንብ አጥር ማለት ነው። ህይም ደግሞ ለማድረግ የሚታያዝ ከማድረግ የሚከለክል በአጭሩ አድርጉ ወይም አታድርጉ የሚል ተብሎ ይተረጎማል። - ማንኛውም ክርስቲያን በእግዚአብሔር ዘንድ ቅድስናን አግኝቶ ይኖር ዘንድ የሥነ ምግባር ሕጎች የትኞቹ እንደሆኑ ግብራቸውንና ስልታቸውን ለይቶ ማወቅ ይኖርበታል። ሕገ ልቦና ሰው በተባለ ላይ ሁሉ በልቦናው ሰሌዳነት ተጽፎ የሚገኝና እያንዳንዱ ሰው ማንም ሳያስተምረው ክፉውንና ደጉን ሳይነግረው የሚፈጽም የሚያውቀው ነው። ስለዚህ ህገ ተፈጥሯዊ ወይም ህገ ጠባያዊ ይባላል። ◦ ሕገ ኦሪት - ኦሪት ማለት ሕግ ማለት ነው  ከአዳም እስከ ሙሴ ድረስ የነበርው የሰው ዘር መጻሕፍት ሳይጻፍለት በሕገ ልቦና ይመራ ነበር። በሙሴ ዘመን ግን መጻሕፍ ተጽፈውለት ሕግጋት ተደንግገውለታል፡፡ - በቅድመ ኦሪት እንደተገለጸው እግዚአብሔር ሙሴን ሕግ የምሠራ ነኝና ወደ ደብረ ሲና ወጣ ብሎታል፡፤ /ኦ.ዘጻ 24፡12 / “እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ በዚያም ሁን፤ እነርሱን ታስተምር ዘንድ እኔ የጻፍሁትን ሕግና ትእዛዝ የድንጋይም ጽላት እሰጥሃለሁ አለው።" -  ይሀ ህገ ኦሪት (ዐሥርቱ ትዕዛዛት) የተሰጡት እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በሶስተኛ ወር ፋሲካን ባከበሩ በ3ተኛ ቀን በደብረ ሲና ሳሉ ነበር። አስርቲ ትዕዛዛት ዘጠኙ ትዕዛዛት ከ1-9 በኦ ዘጸ 20 ከ ቁጥር 1 - 17 ባለው ላይ ይገኛሉ። የቀረው አሥረኛው ትዕዛዝ ደሞ በኦ ዘሌ 19÷18 ላይ ይገኛል። 1, ከኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁንልህ 2, የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ 3, የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ  4, አባትና እናትህን አክብር  5, አትግደል 6, አታመንዝር 7, አትስረቅ 8, በሐሰት አትመስክር 9, የባልንጀራህን ቤት አትመኝ 10, ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ JOIN @Applied_CHRISTIANITY
Показать все...
👍 9🥰 1
የክርስቲያናዊ ሥነ - ምግባር ትምህርት ዓላማ ምንድነው? 1, በሃይማኖታችን ላይ መልካም ፍሬና ምግባርን ለማፍራት። /ማቴ 3÷10/ “እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።” ፣ /ያዕ 2÷10/ “ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ፥ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል” 2, ሕጉን ፣ ሥርዓቱን ፣ አምልኮቱን እንድናውቅ። /መዝ 34÷11/ “ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።” 3, እኛ ተለውጠን ኖረንበት ሌሎችን ለመለወጥ። /ማቴ 5÷16/ “መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።" 4, ሰው ከተፈጠረበት አላማ ውጪ። እንዳይወጣ ያግዛል። ምክንያቱም ሰውና መላዕክት የተፈጠሩት ለምስጋና ነው። ◦ ክርስቲያን ፦የሚለው ቃል በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኙ የሚጠሩበት ስም ነው። /ሐዋ 11÷26/ ◦ ሥነ ምግባር ፦ የሚለው ቃል ሠነየ እና ገብረ ከሚባሉ ከሁለት የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መልካም ሥራ ፣ የተስማማ ተግባር ፣ ደስ የሚያሰኝ ሥራ ማለት ነው። #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ! JOIN @Applied_CHRISTIANITY
Показать все...
🥰 6👍 2🙏 1