ru
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Открыть в Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

Больше
213
Подписчики
Нет данных24 часа
-17 дноК
-430 дноК
Архив постов
ቀጣይ የሚሆነው አንዱ የትግል ትኩረታችን፤ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በእምነታቸው ሳቢያ ከትምህርት ገበታቸው ስለተባረሩት 2000+ የጉንችሬ ሙስሊም ተማሪዎች መሆን አለበት።
+1
ቀጣይ የሚሆነው አንዱ የትግል ትኩረታችን፤ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በእምነታቸው ሳቢያ ከትምህርት ገበታቸው ስለተባረሩት 2000+ የጉንችሬ ሙስሊም ተማሪዎች መሆን አለበት።

🔰 ሰውን መርዳት ❝ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው❞ ይላሉ‼️ እኔ ግን የምላችሁ ይህንን ነው፤ ሰው ለመርዳት መልካም ልብ፣ ትዕግሥት፣ የሚያስተውል አእምሮና ጥቅመኝነት የሌለበት ፍላጎት ያስፈልጋል። አዎ ሰው መርዳት መልካም ነገር ሆኖ ሳለ፤ ሰውን ለመርዳት ጥንካሬን ይሻል። ይህ ብቻ አደለም መልካም ልብንም ይፈልጋል። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 〽️ አንዳንዴ ሰዎች ረድተናቸው ስናበቃ የሆነ ነገር በተፈጠረ ቁጥር “እንዲህ አርጌልህ፣ እንዲህ ሆኜልህ” እንላለን። ይህ ማለት ፍላጎታችን ጥቅመኝነት እንጂ ሌላ አደለም‼️ 〽️ አንዳንዴ የተወሰኑትን እንረዳና የተወሰኑትን ደግሞ በግል ስሜታችን (ምናልባትም የኛ ወገን አይደሉም ብለን በማሰባችን) ምክንያት አንረዳቸውም። ይህ ማለት በዘረኝነት ሱስ ተለክፈናል እንጂ ሌላ አደለም‼️ 〽️ አንዳንዴ ደግሞ ነገር ቶሎ የሚገባቸውን እንረዳና ቶሎ መረዳት የማይችሉትን ወይም በኛ አስተሳሰብ *ጅል* የመሰሉንን ልንረዳቸው ፍቃደኛ አንሆንም። ይህ ማለት አንድም ሰውን የመርዳት ፍላጎት ሳይሆን የራስን ጥቅም የማስጠበቅ ሱስ ነው ያለብን። በሌላ ወገን ደግሞ ትዕግሥት እና መልካም ልብ የለንም ማለት ነው‼️ ይህ ከሆነ ደግሞ እኛ ራሳችን «የሰው ልጅ» የሚለውን ቀመር ውስጥ ልንካተት አንችልም‼️ ◆ ወዳጆቼ! ሰውን ለማገዝና ለሰው እርዳታ ለመለገስ ብዙ መፈላሰፍ ተገቢ አደለም። እራስን የማይሆን ጥያቄ እየጠየቁ ልብንና አዕምሮን ማቆሸሽም አያስፈልግም! በቃ መርዳት ከፈለግን በምትኩ ምንም ጥቅምና ምላሽ ሳንሻ እንርዳ። ሰውን ለማገዝ ብዙ ርቀን መጓዝም አይጠበቅብንም፤ ባለን ነገር ብቻ የአቅማችንን እርዳታ ማድረግ እንችላለን። ሰውን በመርዳት የሚገኘውን እርካታና ደስታ የሚያውቁት ሰውን የሚረዱ ሰዎች ብቻ ናቸው‼️ ➤ ሁላችንም በየ አቅማችን ሰውን ለመርዳት ዝግጁ ብንሆን ኖሮ አለም ላይ *የሚራብ* ሰው ባልኖረ ነበር። ዘረኝነት የሚባለውን ካንሰር ቀብረን ለእውነት ብንኖር ኖሮ አለም ኢፍትሐዊነትን ባላስተናገደች ነበር፣ መገዳደል፣ መቦጫጨቅና እርሰበርስ *መበላላት* ባልተከሰተ ነበር‼️ ነገር ግን መልካምነታችን በክፉነታችን ተውጦ አለምን እያመስን፣ በዘር በጎሳ እየተገዳደልን፣ ምንም የማያውቁ ምስኪኖች እየሞቱና እየተራቡ ይገኛሉ። ➚የዚህ ሁሉ መፍትሄው አዘኔታና ዘረኝነትን *ጠል* መሆን ነበር ነገር ግን ለዚህ አልታደልንም። ➚ታደልለን ቢሆን እኳን ልባችን ላይ ያለችን ትንሽዬ መልካምነት በዘረኝነት ሰበብ ትወድማለች። ➚ባለማስተዋላችን ምክንያት እኛም እንፋጃለን ሰዎችንም እናፋጃለን። ➚ጥቅምና ጉዳቱን ባለማመዛዘናችን ምክንያት በሰዎች በደል ከማብዛታችን የተነሳ እነሱ ደስታና ሀዘንን መለየት ያቅታቸዋል። ችግርና ምቾትን ለይቶ ማወቅ ይሳናቸዋል። ምናልባትም መጠላላትና የዘረኝነትን ድስኩር ምድር ላይ መዝራት ትክክል መስሎ ይታያቸዋል። ይሄኔ እነሱም የእኛን የጭካኔና የአረመኔነትን ጎራ ይቀላቀላሉ። ▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬ ግን ይህ ሁሉ ሳይከሰት ለማስቆም ማድረግ ያለብን ነገር ቢኖር እኛ *“መልካም አስተሳሰብና ስብዕና አለን የምንል ሰዎችን”* ምንም ቅድመ ሁኔታ ሳናበጅለት ከውስጥ በመነጨ በንፁህ መነሳሳት ሰዎችን መርዳት ግድ ይለናል። ▣ ሰውን ስንረዳ ማየት ያለብን *ፊት ፣ ጎሳ ብሄር፣ ዘር ሀይማኖት ሳይሆን ሰዎች ያሉበትን ችግር ብቻ ማስተዋል ነው። ◉ ይሄኔ ነው የሰዎች መጥፎነት ወደ ጥሩነት፣ ጠላትነታቸው ወደ ወዳጅነት፣ ጥላቻቸው ወደ ሰላምና ፍቅር፣ ከሀዲነት ወደ ታማኝነት፣ ውስጣቸው ለይ ሊበቅል የነበር የዘረኝነት ስሜት ደርቆ ሁሉንም በእኩል በሚያይ የፍቅር ተምሳሌት፣ ንፉግነታቸው ደግሞ ወደ ለጋስነት ሊቀየር የሚችለው። የነሱ መቀየር ለቡዙዎች ስኬት ምክንያት ይሆናል። የብዙዎች ስኬት ደግሞ የሀገር ብሎም የዓለም ሴኬት ይሆናል‼️ Motivation by Reshad t.me/ReshadIbnuMuzemil t.me/InspiresWorld

ጁሙዓ ቀን፦ ሰኔ 2/2015 ዓ.ል በአዲስ አበባ ስልጤ ሰፈር በሚገኘው አዒሻ መስጂድ የተላለፈው ኹጥባ ርዕሱና ጭብጡን ላካፍላችሁ። ▬▬▬▬▬▭▭▭▭▬▬▬▬▬ የኹጥባው ርዕስ:- በፊትና ጊዜ መሶበር (ሶብር) ጭብጡ:- 🔰 ፊትና በደረሰብን ጊዜ ያሻንን ከምናደርግና ያሻንን ከምናወራ ሶብር በማድረግና ወደ አላህ በመመለስ የመጣውን በላዕ እንዲያነሳልን ዱዓ ማድረግ። ◉ የሚመራን ሙስሊሙ መሪ ማንም ሆነ ማን፤ ከጎኑ ልንቆም ስህተት ከሰሩም ረጋ ባለ ሁኔታ በአዋቂዎችና በአሊሞች እንዲመከሩ (እንዲታረሙ) ማድረግና የውስጣችንን አይብ አሳልፈን ሙስሊም ጠል ለሆነአካል መስጠት እንደሌለብን ነበር። 👆የኹጥባው ጭብጥ ይህ ነበር‼️ #ረሻድ_ኢብኑ_ሙዘሚል t.me/ReshadIbnuMuzemil

አል-ሐምዱ ሊላህ‼ በአንዋር መስጅድ ህዝበ ሙስሊሙ የጁሙዓህ ሶላቱን በሰላም ሰግዶ አጠናቋል። ከሰላም እንጂ ከግጭት ትርፍ አይገኝም። እኛ ሙስሊሞች የአላህን ጥበቃ እንጂ ሰላማችንን ለማስጠበቅ ከማንም
+7
አል-ሐምዱ ሊላህ‼ በአንዋር መስጅድ ህዝበ ሙስሊሙ የጁሙዓህ ሶላቱን በሰላም ሰግዶ አጠናቋል። ከሰላም እንጂ ከግጭት ትርፍ አይገኝም። እኛ ሙስሊሞች የአላህን ጥበቃ እንጂ ሰላማችንን ለማስጠበቅ ከማንም የማንከጅል፣ ከራሳችን አልፎ ለሌሎች ተምሳሌት የምንሆን የሰላም አምባሳደሮች ነን። || t.me/ReshadIbnuMuzemil

🔰 እኛም እኮ ምተናል የሰው ቁስል ስናክም የኛው አመርቅዞ ሞታችን *አረዱን* - በወረቀት ተዪዞ መቋቋም ሲያቅተን - የህይወትን ጠለል የማይድን ስናክም - የማይሞት ገድለናል በጥቅመኝነት ካንሰር -
🔰 እኛም እኮ ምተናል የሰው ቁስል ስናክም የኛው አመርቅዞ ሞታችን *አረዱን* - በወረቀት ተዪዞ መቋቋም ሲያቅተን - የህይወትን ጠለል የማይድን ስናክም - የማይሞት ገድለናል በጥቅመኝነት ካንሰር - ሀኪም ቤት ገብተናል ሞታችንም አውቀን - ቀናችን ቆጥረናል ይሀው ሟቹ በዛ - እኛም እኮ ሞተናል። በረሻድ ሙዘሚል t.me/ReshadIbnuMuzemil

🔴 ወጣቶች ሆይ... ወቅታዊ ተከታታይ መልዕክት                  ክ/1 🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም 🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸 🌐https://telegram.me/ahmedadem 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ

«በፊትና ጊዜ መደረግ ካለበት ነገር አንዱ መረጋጋት ነው።» ©️ ኡስታዝ አሕመድ ኣደም ዲናዊ ምክሮችንና ትምህርቶችን ከፈለጋችሁ የዚህን ኡስታዝ የቴሌግራም ቻነል ተቀላቀሉ። 〽️〽️〽️〽️〽️〽️〽️ t.me/AhmedAdem

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ  የተሰጠ መግለጫ ሰኔ /1/2015 t.me/ReshadIbnuMuzemil

ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ በዛሬው መግለጫ ላይ የተናገረው‼ || t.me/ReshadIbnuMuzemil

«ስምምነት የተደረሰባቸውን የመፍትሄ አቅጣጫዎች ለማስፈጸም ሁላችንም ተግተን እንስራ! —————————  በሸገር ሲቲ የመስጊዶች ፈረሳ የፈጠረውን ቀውስ ለመቆጣጠር በእስልምና ጉዳዮች መሪነት ብዙ ጥረት ሲደረግ የቆየ ሲሆን ከክልል መንግስቱ እና ከሌሎችም የመንግስት ኃላፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በተደረገው ውይይት በፈረሳውና አስከትሎ በተፈጠረው የተቃውሞ ሂደት በሙስሊሙ ላይ የደረሰው በደል በስፋት ተዘርዝሮ የቀረበ ሲሆን በመንግስት ኃላፊዎች በኩልም የተፈጸመው ተግባር ስህተት መሆኑ ታምኖበት ችግሩን ለመፍታት የታሰቡ እርምጃዎች በውይይቱ ሂደት ወደፊት ወጥተዋል። በዚህም የመስጊድ ፈረሳው በአስቸኳይ እንደሚቆምና ከፕላን ውጭ ያሉ መስጊዶች ጉዳይ ከመጅሊሱ ጋር በመሆን እንደሚታይ፣ የፊታችን ሀምሌ በሚጸድቀው የከተማዋ ፕላን ላይ መጅሊሱን በማማከር ደረጃቸውን የጠበቁ መስጊዶች እንደሚሠሩ፣ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲና ግዙፍ ማዕከላዊ መስጊድን ጨምሮ መንፈሳዊ ማዕከላት እንደሚኖሩ፣ ነዋሪ ባለባቸው አካባቢዎችም ጊዜያዊ የመስገጃ ቦታዎች እንደሚዘጋጁ ከመንግስት በኩል ቃል ተገብቷል። በተቃውሞው ሂደት የታሰሩ ሰዎች ጉዳይም ከዛሬ ጀምሮ ከጸጥታ አካላት ጋር በሚደረጉ ቀጣይ ውይይቶች እንደሚታይ ስምምነት ላይ ተደርሷል። (ከመንግስት ኃላፊዎች ጋር ስምምነት ላይ የተደረሰባቸውን የመፍትሄ አማራጮች በዝርዝር በመጅሊሱ መግለጫ ማግኘት ይቻላል።) በሂደቱ የተፈጠረው ቀውስ ሙስሊሙን ለበርካታ ህመም የዳረገ እንደመሆኑ ለጉዳዩ አስቸኳይ እልባት ለማግኘት መንቀሳቀስ የግድ ነበር። ህዝበ ሙስሊሙም የተባበረ ድምጹን በማሰማት በሸሂዶቹ ደም የከፈለው መስዋዕትነት ቀላል አይደለም። አሁን ላይ ደግሞ ሁላችንም ወደመፍትሄው አፈጻጸም በማተኮር የሸሂድና የተጎጂ ቤተሰቦችን መንከባከብ፣ በእስር ላይ ያሉ ወንድም እህቶቻችንን ማስፈታት እና በመንግስት በኩል ቃል የተገቡትን ነጥቦች ተከታትሎ ማስፈጸሙ ላይ ልንረባረብ እንደሚገባን ለማሳሰብ እንወዳለን። ህዝበ ሙስሊሙ በዘወትር ጨዋነቱ ይህንን የመፍትሄ ክትትል ሂደት ከሚያስተጓጉሉ አካሄዶች ተቆጥቦ ነገሮች ወደነበሩበት መረጋጋት ይመለሱ ዘንድ ጁሙዓን የመሳሰሉ የስብስብ አጋጣሚዎቻችን መሪ ድርጅታችን ባስቀመጠው አቅጣጫ ብቻ እንዲካሄዱ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን። በግልም ሆነ በቡድን በማኅበራዊ ሚዲያም ሆነ በሌሎች የመገናኛ መንገዶች የሚኖሩን ሂደቶች በተቻለ መጠን መፍትሄውን ተከታትሎ የማስፈጸም መንፈስ ላይ ያተኮሩ እንዲሆኑ እና ሙስሊሙን ወዳልሆነ አቅጣጫ መምራት ለሚፈልጉ አካላት በር የማይከፍት አካሄድ እንድንከተል ጥሪ እናደርጋለን። የመሪ ተቋማችንን ትእዛዝ እና የትግበራ አቅጣጫ መከተል በዚህ መሰል የቀውስ ወቅቶች እጅግ አንገብጋቢ እና ብቸኛ አማራጭ መሆኑንም ለማስታወስ እንወዳለን። በሌላ በኩል በመንግስት ኃላፊዎች በኩል ቃል የተገቡትን የመፍትሄ ሀሳቦች ከዳር ማድረስ ችግሩ ይፈታ ዘንድ ቁልፍ ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን የመንግስት የጸጥታ ኃላፊዎች ይህንኑ ያገናዘበ አካሄድ ሊሄዱ ይገባል። የሰላም ቀንዲል በሆነው የህዝበ ሙስሊሙ መስጊዶች ከእንግዲህ ወዲህ አንድም ጠብታ ደም ሊፈስ አይገባምና ህዝበ ሙስሊሙ ላይ ጉዳት ከሚያደርስ አካሄድ ፈጽመው እንዲቆጠቡ በጥብቅ ልናሳስብ እንወዳለን። ለመስጊድ ክብር ሲሉ ደማቸውን ላፈሰሱት ሸሂዶቻችን መታወሻ በሸገር ሲቲ በሚገነባው "የሸሂዶች መስጊድ" ስያሜ ሁሌም በዱዓ እንድናስታውሳቸው ያበቃን ዘንድ አላህን እንለምናለን! በቀጣይ ወቅቶች ሁላችንም ከሸሂድና ተጎጂ ቤተሰቦች ጎን በመቆም ጉዳታቸው ይጠግግ ዘንድ እስልምና ጉዳዮች ይፋ ባደረጋቸው የባንክ ሂሳቦች እርዳታ በማሰባሰብ እና በመንከባከብ በኩል እንበራታ! አላህ ለዲኑ የተከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ ይቀበል! አገራችንንም ሰላም ያድርግልን! አሚን ያረበል ዓለሚን!» ©: ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ

በመጅሊስ የመግለጫ ታሪክ ይህን ያክል ብዛት ያለው ሚዲያ መግለጫውን ለመዘገብ አልተገኘም። በዛሬው መግለጫ ከአልጀዚራ እስከ DW በርካታ የግልና የመንግስት ሚዲያዎች ተገኝተዋል፤ ከአንድ ቲቪ በስተቀር
+2
በመጅሊስ የመግለጫ ታሪክ ይህን ያክል ብዛት ያለው ሚዲያ መግለጫውን ለመዘገብ አልተገኘም። በዛሬው መግለጫ ከአልጀዚራ እስከ DW በርካታ የግልና የመንግስት ሚዲያዎች ተገኝተዋል፤ ከአንድ ቲቪ በስተቀር። እርሱም ካሜራውንና ማይኩን ይዞ ጡል ጡል ሲል በውዱእ ማድረጊያ የመጅሊስ ጡሌ ቅንድቡን ተብሎ ከበር እንዲመለስ ተደርጓል። እርሱም ባለፈ ቆርጦ ቆራርጦ የተሳሳተ ይዘት ያለው መልዕክት በማስተላለፍ የሚዲያ ስነ ምግባርን ያላሟላው፣ መጅሊሱ ያቋቋመውን ኮሚቴ ከህዝበ ሙስሊሙ ለመነጠል የሠራው አዲስ ሚዲያ ኔተወርክ (አዲስ ቲቪ) ነው። ይገባቸዋል! እንዳውም በህግ ቢጠየቁ ሁላ ደስ ይለኛል። || Murad Tadesse t.me/ReshadIbnuMuzemil

ነገ ተቃውሞ የለም‼ ============== ✍ በሸገር ሲቲ የመስጅድ ፈረሳ ሳቢያ በተለይም በአዲስ አበባ አንዋርና በኒ መስጅዶች የሚደረግ ተቃውሞ ቢቀጥልና እየተፈጸመብን ያለው መከራ ባይቆም የሚመኙ ብዙ ነበሩ። ምክንያቱም ይህ አጋጣሚ መጅሊሱን ከህዝበ ሙስሊሙ ለመነጠልና በጎድን ደግሞ መጅሊሱን ከመንግስት ጋር አጋጭቶ ሲናፍቁት የነበረውን የመጅሊስ ስልጣን ዳግሞ ለመቆናጠጥና አሁን ስልጣን ላይ ያሉትን ለማሳጣት ምቹ አጋጣሚ ተፈጥሮላቸው ነበር። አልፎ አልፎም ተጠቅመውበታል፤ ዘላቂነት ባይኖረውም ውጤታማም ነበሩ። በተለይም አሕባሾችና ዘመዶቻቸው! በሌላ በኩል የህዝበ ሙስሊሙን ትግል መረማመጃ ለማድረግ በቋሚ ጠላትነታቸው እንደማናውቃቸው ሁሉ ከወትሮው በተለዬ መልኩ የሚዲያ ሽፋን ከመስጠት ጀምሮ ወዳጅ መስለው ከፊት ሊማግዱን የቋመጡ አሐዳዊያን ኃይሎች ነበሩ። የሁሉም ህልም በአላህ ፈቃድ ዛሬ መክኗል። ይበልጥ ህልማቸው የሚመክነው ደግሞ ዛሬ በመግለጫው ላይ የተነሱት ነጥቦች መሬት ላይ ወርደው ተፈጻሚ ሲደረጉ ነውና ለዚያ እንበርታ። ከዚያ ውጭ ግን በነገው ዕለትም ሆነ ከዚያ በኋላ በየትኛውም የሃገራችን ክፍል ምንም አይነት ተቃውሞ የለም፤ መግለጫውም ላይ ተወስቷል። እኩይ ህልማችሁ በዚህ ሳቢያ ብዙ ሳትራመዱ ለተኮላሸባችሁ ወይዘሪት አሕባሽና ወይዘሮ አሐዳዊያን የተሰማኝን የደስታ ሐዘን እየገለጽኩ፤ አላህ ለኛ መጨረሻችንን እንዲያሳምርልንና በጠላቶቻችን ላይ ሁሌም ድል እንዲያቀዳጀን እለምነዋለሁ። የተጎጂ ቤተሰቦች! አብሽር! ከዚህ በኋላ በዚህ ጉዳይ ከሚኖር በጎ ድል ጀርባ ሁሉ የልጆቻችሁ መስዋዕትነት እንዳለ እንዳትዘነጉት። በዚህ ደግሞ ልትኮሩ እንጂ ልታዝኑና ልትጸጸቱ አይገባም። || MuradTadesse t.me/ReshadIbnuMuzemil

በመግለጫው ላይ የተነሱት ነጥቦችና የተደረሰባቸው ስምምነቶች መሬት ላይ ወርደው ተፈጻሚ እስኪሆኑ ድረስ ተቋሙ በሚሰጠን አቅጣጫ በንቃት ከተከታተልን፤ ሁሉም ነጥቦች ጥሩ የሚባሉ ናቸው። አል-ሐምዱ ሊላህ ዓላ ኩሊ ሐል! Murade t.me/ReshadIbnuMuzemil

ከፌደራል ፖሊስ እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮች ጋር «መስጅዴን አታፍርሱብኝ» በማለት በመጠየቃቸው ከመስጅድ ዙሪያና ቤት ለቤት ታፍሰው በታሰሩ ሙስሊሞች ጉዳይ ከከሰዓት ውይይት የሚደረግ ይሆናል። ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በግፍ የታሰሩና ታፍነው የተወሰዱ በአላህ ፈቃድ ይፈታሉ።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ ሰኔ /1/2015 || t.me/ReshadIbnuMuzemil
+2
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ  የተሰጠ መግለጫ ሰኔ /1/2015 || t.me/ReshadIbnuMuzemil

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🔰 በማንረዳው ነገር ላይ፣ በማይገባን ጉዳይ ላይ ያሻንን መናገርና መሰዳደብ አግባብ ነውን⁉️ ▭▭▬▬▭▭▬▬▬▬▭▭⁉️ #በብዙ ሚዲያዎች ብዙ ነገር ይባላል፣  ብዙ ነገር ይወራል፤ ለዚህ ለሚወራው ነገር ሁላችንም ማለት በሚቻል ሁኔታ የምንሰጠው áˆ€áˆłá‰Ľ ወይም አፀፋዊ-መልስ የግል ስሜታችንና የግል ስሜታችን ብቻ ነው። #እኛ ያመረ እስልምና አለን፤ ረጋ ሰከን እንድንልም ታዘናል። ራሳችንን ሙስሊም ብለን እየጠራን ነገር ግን *እልም* ያሉ ወገኝተኞች፣ በስሜት የሚነዱ ሰዎች፣ ተሳዳቢዎች ወጥቶናል። 💬 አማርኛ እኳን በአግባቡ መፃፍ የማንችል ለመሳደብ ሲሆን ግን ሰይጣን ያግዘናል መሰለኝ የምንሰባብራቸው ፊደሎች ልሹ አይኖሩም። ያው በመጥፎ ነገር ሰይጧን ከጎናችን አደል!? ◉ ምናልባትም በኛ ወንጀል የተነሳ ይሆናል ሙስሊሙ ኡማ እየተጨቆነ ያለው ብለን ዱዓ ማድረግና ወደ አላህ መመለሾ ሲገባን መሰዳደቡን፣ መነቋቆሩን፣ ለሆነ አካል መወገኑን፣ ዘረኝነቱን አጧጡፈን ተያይዘነዋል። ◉ እየሆነ ያለው ነገር ከገባን በሸሪዓዊ እይታ ነገሩን መዳኘት ሲገባን እኛ ግን የግል ስሜታችንን እናፀባርቃለን። የሆነ አካል የሆነ ነገር በተናገረ ወይም ባደረገ ቁጥር የግል ስሜታችንን ባሻን የግል ስሜትና እኛ በፈለግነው የንግግር ዘይቤ ሀሳባችንን እንገልፃለን (እንሳደባለን ብለው የተሻለ ይሆናል)‼️ ➤ እውነት ግን እኛ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እናስባለን? ➤ እውነት ግን እኛ ከልባችን በሙስሊሙ ማህበረሰብ እየተፈፀመ ያለው አስነዋሪ ጭቆና አስቆጥቶናል!? አስከፍቶናል!? ውስጣችን ደምቷል ቆስሎዋል!? 〽️ መልሳችን አዎ ከሆነ፤ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚጨነቅ አካል ጊዜውን በመሰዳደብ ያሳልፋል ወይስ ሙስሊሙን የሚጠቅም ነገር ለማድረግ ጥረት ያደርጋል!? ▬ እኛ እያደርግን ያለነው እኮ እርሰበርስ በመበላላትና በመጠላላት እንዲሁም ሙስሊሙን የሚከፋፍሉ ወሬዎችን ምድር ላይ በመዝራት መንግስት የፈለገውን አላማ እያሳካንለት ነው። እነሱ እኮ የፈለጉት ይህንን ነው። እኛ በራሳችን ሀጃ ተውጠን በምንቦጫጨቅ ሰዓት እሱ (መንግስትና የመንግስት ባለስልጣኖች) ደግሞ ሙስሊሙን ገድለውናና መሲጂዶቻችንን አፍርሰው የሚፈልጉት ዓላማ ላይ ይደርሳሉ። ▣ ለምንድነው ረጋ የማንለው!?፤ ለምንድነው ሰከን የማንለው⁉️። ➤ ለምንድነው እየሆነ ያለው ነገር እስከ ሚገባን ድረስ፤ ማን ከሙስሊሙ ጎን ነው ማን ደግሞ ከሙስሊሙ ጎን አይደለም ሚለውን አበጥረን እስክናውቅ ድረስ ጉንዮሽ ጉዳዮችን ተወት አድርገን ሙስሊሙን ማህበረሰብ ሊረዳ የሚችል ነገር የማንሰራው⁉️ ⬛️ ለምሳሌ፦ በተለያዩ ሀገራት ያሉ ሙስሊም ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ሰዎች በትዊተር አካውንታቸው ላይ በአስታየት ቋት (በ Reply) እየገባን ሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን በደል በአጭር የፅሑፍ መልእክት በምስልና በቪድዮ በማስደገፍ መላክ‼️ ✔️ ሁሉም በየ አቅሙ የሚችለውን ቢያደርግ አላህም ለዲኑ ያለን ቦታ አይቶ ነስሩን ያመጣልናል ኢንሻአላህ‼️ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፤ እባካችሁን በማይረብ *ለሙስሊሙ ጥቅም ሊያስገኙ በማይችሉ* ጉዳዮች ላይ ጊዜያችንን አንፍጅ፤ ጊዜውም ይታዘበናል!! ▬ የኛ መቦጫጨቅ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ድልን ሳይሆን ውርደትን ነው ይዞ የሚመጣው። ▬ የኛ መከፋፈል ለዲኑ ሳይሆን ዲኑን ለማጥፋት ቆርጦና ወስኖ ለተነሳው አካል ነው የሚጠቅመው። ▬ የኛ እዚህ ግባ በማይባል አጀንዳ ራሳችንን መዝፈቅ መንግስትና የመንግስት አካላት ልካችንን በማወቅ የልብ-ልብ ተሰምቷቸው ካሁን በኋላም ባሉት ጊዜያቶች ብዙ ሙስሊሞች እንዲገደሉና ብዙ መስጂዶች እንዲፈርሱ ምክንያት ይሆናል። ስለዚህ *«እኔ ሙስሊም ነኝ»* የምንል ሁሉ ነቃ ልንልና ሰከን ብለን ሙስሊሙን በሚጠቅሙ ጉዳዮች ብቻ ትግል ልናደርግና የቻልነውን ሁሉ መስዋዕትነት ልንከፍል ግድ ይለናል‼️ የናተው መልካም ፈላጊ ወንድማችሁ፦ ረሻድ ሙዘሚል ቀን:- ግንቦት 30/2015 E.C [June 7/2023 G.C] t.me/ReshadIbnuMuzemil t.me/InspiresWorld

በአዲስ አበባ በተለይም እንደ መርካቶ ባሉ ሙስሊም በዝ ሰፈሮች ከፍተኛ አፈሳና ከወትሮው ለየት ያለ ፍተሻ ስላለ ጥንቃቄ አድርጉ፣ መታወቂያ ያዙ።

«በዛሬው ዕለት በየኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም የተመራ ልዑክ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የኦሮሚ ክልል የሥራ ኃላፊዎች
«በዛሬው ዕለት በየኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም የተመራ ልዑክ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የኦሮሚ ክልል የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሸገር ከተማ ስለፈረሱት መስጂዶች ጉዳይ ከቀኑ 9:00 እስክ ምሽት 2:00 ሰዓት ድረስ አምስት ሰዓታት የፈጀ ሰፊ ዉይይት አድርገናል። በዉይይቱ ማጠቃለያ ላይ በተደረሰባቸው ነጥቦች ላይ በነገው እለት ጠዋት 4:00 ሰዓት ላይ በፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫውን ለመዘገብ ሁሉም ሚዲያዎች በስፍራው እንድትገኙ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።» ©: አሕመዲን ጀበል

ወደ ትራካችን እንመለስ‼ ================== ✍ በፌዴራል መጅሊሱ የጠቅላላ ጉባዔ ወቅት ከተቋቋሙት 9 ኮሚቴዎች መካከል አንዱ የሆነው ሱፍያን ዑሥማንና ሌላ አንድ ሰው በተናገሩት ንግግርና
ወደ ትራካችን እንመለስ‼ ================== ✍ በፌዴራል መጅሊሱ የጠቅላላ ጉባዔ ወቅት ከተቋቋሙት 9 ኮሚቴዎች መካከል አንዱ የሆነው ሱፍያን ዑሥማንና ሌላ አንድ ሰው በተናገሩት ንግግርና አዲስ ቲቪ ቆራርጦ ባቀረበው ዘገባ ትናንትና ዛሬ ትንሽ ወቀሳዎች ነበሩ። ድንበር ከዘለሉት ወቀሳዎችና «ከትክክሌ ስህተትዎ ይበልጣል!» አይነት ሰዎች ጭፍን ድጋፍ ውጭ የተሰነዘሩት ሚዛናዊ ትችቶች ተገቢ ናቸው። እነዚህን ሃሳቦች ታሳቢ በማድረግ በዛሬው መድረጅ ላይ ሱፍያን ዑሥማን ማብራሪያ ሰጥቷል። ኡማው በኮሚቴው ላይና አለፍ ሲልም ኮሚቴውን ባቋቋመው መጅሊሱ ላይ ያለው አመኔታ እንዳይበጣጠስ ጉዳዩን ሳይንቁ ታሳቢ አድርጎ ተገቢውን ማብራሪያና ብዥታ ማጥሪያ መሰጠቱ የሚበረታታና ለወደፊቱም ተመሳሳይ ነገሮች ካጋጠሙ ሊለመድ የሚገባው ነው። ሱፍያን እንደተናገረው ከሆነ እንኳን ሊሽለጠለጡ ያቀረቡላቸውን ውሃ እንኳ አንፈልግም ብለው እንዳስወጡ ተናግሯል። በተጨማሪም «እኛ ቪዲዮና ቴሌቪዥን የለንም። እነሱ እንደሚመቻቸው አድርገው አቅርበውታል። መንግስትን ሙሉ ውይይቱን ለህዝብ እንዲለቀቅ ጠይቀናል። እነሱ የማይለቁት ከሆነ እኛ እንለቀዋለን። በውይታችን ላይ ሙስሊሙን የሚያስጠቃ እና የሚያስቆጣ ንግግር ተናግሬ ከሆነ ህዝቡን አውፍታ ጠይቄ የያዝኩትን ቦታ እለቃለሁ።» ብሏል። ንግግሩን ማዳመጥ ከፈለጋችሁ፦ https://t.me/MuradTadesse/29977 የሚበረታታ ነው። በሉ! አውፍ እንባባል። ለወደፊቱም መሰል መጅሊሱን ከህዝበ ሙስሊሙ የሚነጥሉ ሴራዎች ከተፈጸሙ፤ ወደ ውሳኔ ከመሄዳችን በፊት ቀድመን እናጣራ፤ ማብራሪያ እንጠይቅና ብዥታችንን እናስወግድ። አሁንም የትግላችንን ቀስት ወደርስበርሳችን ሳይሆን በአንድ ወደ አጥፊዎች ይሁን። አላህም ያግዘናል! ቸር ያሰማን‼ || t.me/MuradTadesse