cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የ ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ዲጅታል ቤተ-መጽሐፍ

ይህ የተለያዩ መንፈሳዊ መጻሕፍት የሚጋሩበት የ ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ዲጅታል ቤተ-መጽሐፍ ነው። ለ መወያየት : ለ ገንቢ ሀሳባት እና ለ መጻሕፍት ጥቆማ @Girmay_AD11 እንዲሁም @YNSel

Больше
Рекламные посты
700
Подписчики
+124 часа
+97 дней
+4130 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

#ጥያቄ
ማንም ኃጢያትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ” 1ኛ ዮሐ. 2፡1
ይሄንን ጥቅስ ይዘን ክርስቶስን አማላጅ ማለት እንችላለን?????? #መልስ👇👇👇 ✅ ጠበቃ፡- ማለት ለተከሳሽ የሚከራከር ተከሳሽን ነፃ በማውጣት ከሳሽን የሚያሳፍር ነው፡፡ ✅ አማላጅ፡- ማለት በአንድ በከበረ ሰው ፊት አሊያም በእግዚአብሔር ፊት አንድን ሰው ወክሎ ይቅርታ የሚጠይቅ ወይም የሚለምን ሲሆን በራሱ ምንም ማድረግ የማይችል ከመሆኑም በተጨማሪ የበዳዩን በደል ማለትም የአጥፊውን ጥፋት በመግለጽ በድሏል እና ይቅር በለው ብሎ የሚለምን(የሚማጸን) ማለት ነው፡፡ 🟢 በአጠቃላይ አማላጅ ኃጢአትን ገልፆ ይቅርታን የሚለምን ነው፡፡ 👉 በዚህ መሰረት የቃሉን ሀሳብ ስንመለከት ቅዱስ ዮሐንስ በመልዕክቱ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቹን ኃጢአት እንዳያደርጉ እንዲህ ሲል ይጽፍላቸዋል ቁጥር 1 ላይ ልጆቼ ሆይ [ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህንን እጽፍላችኋለሁ ] ይልና ቁጥር 2 ላይ ከስጋቸው ድካም የተነሳ ሳያውቁ በስህተት እያወቁ በድፍረት ኃጢአትን ቢያደርጉ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን በማለት የአብ የባህሪ ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቃችን ነው ይላቸዋል፡፡ ☑️ ምክንያቱም ሰው ኃጢአትን በሰራ ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት የሚከስ ከሳሽ አለ እርሱም ሰይጣን ዲያቢሎስ ሰዎችን በእግዚአብሔር ፊት እንደሚከስ ትን.ዘካ.3፡1-5 ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡
ታላቁም ካህን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ ሰይጣን ይከሰው ዘንድ በስተቀኙ ቆሞ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ሰይጣንን  ሰይጣን ሆይ  ኢየሩሳሌምን የመረጠ እግዚአብሔር ይገስጽህ በውኑ ይህ ከእሳት  ትንታግ አይደለም አለው፡፡ ኢያሱም እድፋም ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ ነበር እርሱም መልሶ በፊቱ የቆሙትን እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ አላቸው እርሱንም እነሆ አበሳህን ከአንተ አርቄያለሁ ጥሩ ልብስን አለብስሀለሁ አለው ደግሞ ንጹህ ጥምጥም በራሱ ላይ አድርጉ አለ እነርሱም በራሱ ላይ ንጹህ ጥምጥም አደረጉ ልብስንም አለበሱት የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር፡፡ ]
👉👉👉 በዚህ ታሪክ ላይ እንደተመለከትነው እግዚአብሔር ለኢያሱ አማላጅ ሆነለት ወይስ ጠበቃ ሆነለት ብለን ብንጠይቅ አማላጅ አልሆነለትም ምክንያቱም ኃጢአትን በመግለጽ ሲለምን አልታየምና ነገር ግን ጠበቃ ሆኖለታል፡፡ ምክንያቱም ከሳሹን(ሰይጣንን) አሳፍሮለታልና ነው፡፡ እንዲሁም ዳኛ(ፈራጅ) ሆኖለታል ምክንያቱም የኃጢአት ስርየት ሰጥቶታልና። ✝ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
Показать все...
👍 7💯 2
#ጥያቄ
ማንም ኃጢያትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ” 1ኛ ዮሐ. 2፡1
ይሄንን ጥቅስ ይዘን ክርስቶስን አማላጅ ማለት እንችላለን?????? #መልስ👇👇👇 ✅ ጠበቃ፡- ማለት ለተከሳሽ የሚከራከር ተከሳሽን ነፃ በማውጣት ከሳሽን የሚያሳፍር ነው፡፡ ✅ አማላጅ፡- ማለት በአንድ በከበረ ሰው ፊት አሊያም በእግዚአብሔር ፊት አንድን ሰው ወክሎ ይቅርታ የሚጠይቅ ወይም የሚለምን ሲሆን በራሱ ምንም ማድረግ የማይችል ከመሆኑም በተጨማሪ የበዳዩን በደል ማለትም የአጥፊውን ጥፋት በመግለጽ በድሏል እና ይቅር በለው ብሎ የሚለምን(የሚማጸን) ማለት ነው፡፡ 🟢 በአጠቃላይ አማላጅ ኃጢአትን ገልፆ ይቅርታን የሚለምን ነው፡፡ 👉 በዚህ መሰረት የቃሉን ሀሳብ ስንመለከት ቅዱስ ዮሐንስ በመልዕክቱ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቹን ኃጢአት እንዳያደርጉ እንዲህ ሲል ይጽፍላቸዋል ቁጥር 1 ላይ ልጆቼ ሆይ [ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህንን እጽፍላችኋለሁ ] ይልና ቁጥር 2 ላይ ከስጋቸው ድካም የተነሳ ሳያውቁ በስህተት እያወቁ በድፍረት ኃጢአትን ቢያደርጉ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን በማለት የአብ የባህሪ ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቃችን ነው ይላቸዋል፡፡ ☑️ ምክንያቱም ሰው ኃጢአትን በሰራ ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት የሚከስ ከሳሽ አለ እርሱም ሰይጣን ዲያቢሎስ ሰዎችን በእግዚአብሔር ፊት እንደሚከስ ትን.ዘካ.3፡1-5 ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡
ታላቁም ካህን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ ሰይጣን ይከሰው ዘንድ በስተቀኙ ቆሞ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ሰይጣንን  ሰይጣን ሆይ  ኢየሩሳሌምን የመረጠ እግዚአብሔር ይገስጽህ በውኑ ይህ ከእሳት  ትንታግ አይደለም አለው፡፡ ኢያሱም እድፋም ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ ነበር እርሱም መልሶ በፊቱ የቆሙትን እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ አላቸው እርሱንም እነሆ አበሳህን ከአንተ አርቄያለሁ ጥሩ ልብስን አለብስሀለሁ አለው ደግሞ ንጹህ ጥምጥም በራሱ ላይ አድርጉ አለ እነርሱም በራሱ ላይ ንጹህ ጥምጥም አደረጉ ልብስንም አለበሱት የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር፡፡ ]
👉👉👉 በዚህ ታሪክ ላይ እንደተመለከትነው እግዚአብሔር ለኢያሱ አማላጅ ሆነለት ወይስ ጠበቃ ሆነለት ብለን ብንጠይቅ አማላጅ አልሆነለትም ምክንያቱም ኃጢአትን በመግለጽ ሲለምን አልታየምና ነገር ግን ጠበቃ ሆኖለታል፡፡ ምክንያቱም ከሳሹን(ሰይጣንን) አሳፍሮለታልና ነው፡፡ እንዲሁም ዳኛ(ፈራጅ) ሆኖለታል ምክንያቱም የኃጢአት ስርየት ሰጥቶታልና። ✝ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
Показать все...
ʏɪʟɪᴋᴀʟ ᴏʀᴛʜᴏᴅᴏx

የኢኦተቤ/ክርስቲያን አባቶች እና መምህራን ያስተማሩት ትምህርቶች የሚተላለፍበት፤ በተጨማሪም የምትፈልጉትን የ ኦርቶዶክስ መዝሙሮችን የምታገኙበት ይቀላቀሉን @YilikalOrthodox ፈልጋችሁ ያጣችሁትን መዝሙር ለመጠየቅ @YilikalOrtho ላይ የመዝሙሩን ርዕስ ወይም የዘማሪውን ስም ብቻ ይጻፉ፡፡

✝✝✝ ግንቦት 26 ✝✝✝       🔶 አቡነ ሀብተማርያም የተወለዱበት ቀን ⚡️⚡️⚡️አቡነ ሀብተማርያም የተወለዱት በመንዝ አውራጃ ልዩ ስሙ የራዊ በተባለ ቦታ ሲሆን የአባታቸው ስም ፍሬ ብሩክ የእናታቸው ስም ዮስቴና ይባላል፡፡  ሁለቱም በሕግ ጋብቻ ጸንተው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው ምግባር ቱሩፋት ሰርተው በንጽህና በቅድስና ይኖሩ ነበር፡፡ ሆኖም ልጅ አልነበራቸውም፡፡ በዚህ ሁኔታ ያዘኑ ቅድስት ዮስቴና ማለትም እናታቸው መንነው በአካባቢያቸው ከሚገኝ ጫካ ውስጥ ዋሻ ፈልገው ገብተው ዘጉ፡፡ ✨✨✨በዚያም አንድ መናኝ መነኩሴ አግኝተዋቸው እግዚአብሔር በቅድስቲቱ ያለው ድብቅ ነገር ስለገለጠላቸው አንቺ ለምንኩስና የተፈቀደልሽ አይደለሽም ወደ ቤትሽ ግቢ ጸሎቱ ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ሰው ሁሉ የሚማጸነው ስሙ፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የሚነገርለት ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ አሏቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ድንቅ ተዓምር የሰሙ ቅድስት ዮስቴናም እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቤቸው ተመለሱ፡፡ የተናገረውን የማያስቀር አምላክ በቸርነቱ ጎበኛቸውና አባታችን ነሐሴ 26 ቀን ተጸነሱና ግንቦት 26 ቀንም ደም ግባታቸው እንደ ንጋት ኮከብ ያማሩ ሃብተማርያም ተወለዱ፡፡ 🙏🙏🙏 ✨✨✨እግዚአብሔር ለቅድስና ሥራ ስለመረጣቸው በእናተቸው ጀርባ ታዝለው ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው በሕጻን አንደበታቸው ከቀዳሹ ካህን ጋር “እግዚኦ ማሐረነ ክርስቶስ” በማለት ይጸልዩ ነበር፡፡ ባደጉም ጊዜ ይህን ጸሎት ደጋግመው ይጸልዩ ነበር፡፡ ➡ላባቸውም እስኪንጠባጠብ ድረስ በመስገድ ይጋደሉ ነበር፡፡ ⚡️⚡️⚡️ጊዜ እረፍታቸው በደረሰ ጊዜ ጌታ ተገልጦላቸው ስለ ተጋድሎአቸውና ስለንጽህናቸው ሰባት አክሊል እንደሚቀበሉ ነግሯቸዋል፡፡በ490 ዓ.ም ህዳር 26 ቀን ዐርፈው በደብረሊባኖስ ገዳም መካነ ቅዱሳን ቀበሯቸው።                                        
         🕊✝✝✝ ቃልኪዳን
🔶 በዚያም በዓት አጽንተው ሲጸልዩ ጌታችን ቅዱስ ገብርኤልንና ቅዱስ ሚካኤልን በቀኝና በግራ አስከትሎ ተገለጠላቸውና ‹‹ወዳጄ ሀብተ ማርያም ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን›› አላቸው፡፡ ያን ጊዜ አባታችን ከፈጣሪአቸው ግርማ የተነሳ ደንግጠው ከመሬት ወድቀው እንደ በድን ሆኑ፡፡ ✝ ጌታችንም አንስቶ ክቡራን በሆኑ እጆቹ አጸናቸውና ‹‹የመጣሁት ላጸናህ ነው ሰውነትህንም እንደ ንስር ላድሳት ነው እንጂ ላጠፋህ አይደለም፡፡ ድካምህና ገድልህ ሁሉ ለዘለዓለም መታሰቢያ ሊሆን በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ተጽፎልሃል ብዬ በእውነት እነግርሃለሁ፡፡ ለአንተ ለወደድኩህና ለመረጥኩህና ወዳጄ የማቴዎስንና የማርቆስን ወንጌል ባነበብክ ጊዜ ተጭነህ ወደምትሄድበት ቦታ የሚያደርስህ የብርሃን ሰረገላ ሰጥቼሃለሁ፡፡  እንደ አንተም ካሉ በዋሻ በመሬት ፍርኩታ ከሚኖሩ ከመረጥኳቸው ቅዱሳን ጋር ትገናኝ ዘንድ ወደ አራቱም አቅጣጫ ትበር ዘንድ የብርሃን ሠረገላ ሰጥቼሃልሁ፡፡ ዳግመኛም የሉቃስንና የዮሐንስን ወንጌል ባነበብክ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ትሄድ ዘንድ የእሳት ሠረገላ ሰጥቼሃለሁ›› አላቸው፡፡ 🔶🔶🔶ዳግመኛም ‹‹በጸሎትህ አምኖ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ፣ ስምህን የጠራውን ዝክርህን ያዘከረውን ሁሉ የሀብተ ማርያም አምላክ ሆይ ከጠላት እጅ አድነኝ ያለኝን በኅሊና ያሰበውን በልቡናው የወሰነውን እፈጽምለታለሁ፡፡ አንተን ገድልህንና ቃል ኪዳንህን የናቀውን ያቃለለውን ሁሉ ፍጹም መበቀልን እበቀለዋለሁ፡፡ እንደ ወዳጄ እንደ ፊቅጦርም በእናቴ በማርያም ድንግል አተምኩህ›› ካላቸው በኋላ ቅዱስ ሚካኤል ከእርሳቸው እንዳይለይ የዘወትር ጠባቂ አድርጎ ሰጣቸውና በታላቅ ግርማ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡        ወስብሐት ለእግዚአብሔር  
Показать все...
14👏 1
Source : Janderebaw media https://t.me/janderebaw_media . . . . . የክርስቶስ መዐዛውን ዕጣኑን ፣ የወርቅ ማዕጠንት የተባለች እመቤታችንን የምናጣጥምበት መልካም የቅዳሴ እና የክርስቲያን ሰንበትን ተመኘን🙏🙏🙏
Показать все...
5
Source : From Janderebaw Media https://t.me/janderebaw_media . . . . . የክርስቶስ መዐዛውን ዕጣኑን እንዲሁም ፣ የወርቅ ማዕጠንት የተባለች እመቤታችንን የምናጣጥምበት መልካም የክርስቲያን ሰንበት ፣ የቅዳሴ ሰንበት እንዲሆን ተመኘን🙏🙏🙏
Показать все...
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ ዐሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
#አንብቡት 🔶በአንድ ወቅት አንድ አባት ከነበሩበት ቦታ ወደ በረሃ መሰደድ ግድ ሆነባቸው። ከቅዱስ መጽሐፋቸው ሌላ ሦስት ነገሮች ነበሯቸው። 🔶እነሱም፦ ቅዱስ መጽሐፉን በጨለማ ወቅት ለማንበብ የሚጠቅማቸው ኩራዝ ፣ጎህ ከመቅደዱ በፊት ከእንቅልፍ የሚቀሰቅሳቸው አንድ አውራ ዶሮ እና ለመጓጓዣነት የሚገለገሉበት አንድ አህያ ነበሩ። 🔶አንድ ቀን ምሽት ከጉዞ የተነሣ በጣም ስለ ደከሙ እኚህ አባት ወደ አንድ መንደር ቀርበው ማደሪያ ቢጠይቁም መንደርተኛው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማንም አላሳደራቸውም። ስለዚህም ከመንደሩ አቅራቢያ አንድ ጉድጓድ ያገኙና በዚያ ውስጥ ገብቶ ለማደር በመወሰን ገብተው አደሩ። እንደ ወትሮው ቅዱስ መጽሐፋቸውን ለማንበብ ኩራዛቸውን ቢለኩሱትም የነበረው ብርቱ ነፋስ አጠፋባቸው። 🔶ስለዚህም ለመተኛት ጋደም እንዳሉ ተኩላ መጥቶ አውራ ዶሮዋቸውን፣ አንበሳም አህያቸውን በሉባቸው። የተደራረበ ጉዳት ስለደረሰባቸው ሽማግሌው እርዳታን በመሻት ወደዚያ መንደር ቢመለሱ ዘራፊ ሽፍታዎች የመንደሩን ነዋሪዎች በሙሉ ገድለው ንብረት ዘርፈው ዖና መንደር ሆኖ አገኙት። 🔶ሽማግሌው ይህን ሁሉ ባጤኑ ጊዜ እግዚአብሔር ምን ያህል መልካም ነገርን እንዳደረገላቸው አስተዋሉ። በዚያች ምሽት በመንደርተኞቹ በአንዱ ቤት ቢያድሩ ኖሮ የዘራፊዎች ሰለባ ሆነው ሊገደሉ በቻሉ ነበር። ቀንዲላቸውንም ነፋስ ባያጠፋው የብርሃኑ ወጋገን እዚህ ጋር ሰው አለ በማለት ለሽፍታዎቹ ያሳብቅ ነበር። አውራ ዶሮአቸውና አህያቸውም ባይበሉ ኖሮ ከሽፍታዎቹ ተደብቀው ማደር ባልቻሉ ነበር።” እግዚአብሔር ከክፉ ነገሮች ውስጥ መልካም ነገር ማውጣት የሚችል አምላክ ነው።" 🔶ስለዚህ እንዲህ በሉ፦ "የሚደርስብኝ ፤ የሚገጥመኝ ፈተናና መከራ ሁሉ አምላኬ ሆይ ለበጎ ታደርግልኛለህና አመሰግንሃለሁ" አሜን #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አንዘንጋ🙏🙏🙏
Показать все...
23
✝✝✝ አንድ አረጋዊ መነኩሴ ከበኣቱ ወጥቶ ሳለ "የሰው ልጆችን ሥራ አሳይኽ ዘንድ ና" የሚል ድምፅ ሰማ፤ ርሱም ከበኣቱ ወጥቶ የጠራውን ድምፅ ተከትሎ ተጓዘ። ✝✝✝ ያ ድምፅ ወደ አንድ ቦታ አደረሰውና አንድ ኢትዮጵያዊ እንጨት እየፈለጠ ሲከምር አሳየው፤  ያ እንጨት የሚፈልጠው ሰው፣ ሊሸከመው ሞከረና አቃተው፤ ይኹን እንጂ በመቀነስ ፈንታ አኹንም እየቆረጠ መከመር ቀጠለ። ✝✝✝ ጥቂት አለፍ ብሎ ደግሞ፦ አንድ ሰው በሐይቅ አጠገብ ቆሞ፣  በተሰበረ ማሰሮ ውሃ ሲቀዳ ተመለከተ፤  ማሰሮው የተሰበረ በመኾኑ ውሃው እንደገና ወደ ሐይቁ ይመለስ ነበር። ✝✝✝ በሌላ ሥፍራ ደግሞ፦  ኹለት ሰዎች ጎን ለጎን ኾነው መጡ፤  በትከሻቸውም በትራቸዉን(ዱላቸዉን) ጫፍ እና ጫፍ ላይ አጋድመው ይዘውት ነበር፤ በመቅደስ በሩ ወደ ውስጥ ሊያልፉ ቢፈልጉም፣  በትራቸውን አግድም ስለያዙት ያግዳቸው ነበር፤ አንዳቸውም ከሌላኛው ኋላ በመኾን በትሩን ፊትና ኋላ አድርገው ሊገቡ አልፈለጉም፤ ስለዚኽ በፉክክር ከውጪ ቀሩ። 👉👉👉እንጨት የሚቆርጠው ሰው በኀጢአት ላይ ኀጢአት የሚጨምር ሰውን ይመስላል፤  ንስሓ ከመግባት ይልቅ ሌሎች ኀጢኣቶችን እንደገናን ይጨምራል። 👉👉👉 ውሃ የሚቀዳውም ሰው፣   መልካም ሥራን የሚሠራ ሰውን ይመስላል፤ ነገር ግን መልካም ሥራው ከክፉ ሥራው ጋር የተቀላቀለ በመኾኑ ጥቂቱ መልካሙ ሥራው ይበላሽበታል። 👉👉👉 ባለ በትሮቹ ሰዎች የጽድቅን ቀንበር በትዕቢት ተሸክመውታል፤  ራሳቸዉን ዝቅ ዝቅ አላደረጉም፤  ራሳቸዉን ለማረምና በክርስቶስ የትሕትና ጉዞ ለመጓዝ አልፈለጉም፤  ስለዚኽ ከመንግሥተ ሰማያት በአፍኣ/በውጪ/ ይቀራሉ። 👉 ✝✝✝ ስለ ኾነም እያንዳንዱ ለሚሠራው ነገር ሊጠነቀቅ እና በከንቱ እንዳይደክም ሊያስብበት ይገባል" አለው።
Показать все...
14👍 2
ቅዱስ ጴጥሮስ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” የሚለውን የትንሣኤውን ጌታ ድምጽ ከሰማ ፣ የተጠራጠረው ቶማስ እጁን በጎኖቹ አግብቶ “ጌታዬ አምላኬ” ብሎ ሲያምን ከተመለከተ በኋላ “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” ብሎ ሲናገር እናገኘዋለን።(ዮሐ 21፥3) ክርስቶስ ተላልፎ በተሰጠበት በሐሙስ ምሽት ከእሳት ዳር ተቀምጦ ያደረገውን ሊረሳውና ራሱን ይቅር ሊል ስላልቻለ፣ ጌታው ቀድሞ የሰጠውን የወንጌል መረብ ተወና የዓሣውን መረብ ጨብጦ ወደ ገሊላ ባሕር ሮጠ።(ማቴ 4፥19) በኃጢአት ምክንያት የተሰማው ኃፍረትና መሸማቀቅ ሐዋርያነቱን ትቶ በድሮ ማንነቱ ውስጥ ራሱን እንዲደብቅ አደረገው። የካደን ማን ለምስክርነት ይፈልገዋል በሚል ዓይነት ስሜት ለወንድሞቹ  “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” አላቸው። ደስ የሚለው ነገር ግን ይህን አስቀድሞ የሚያውቅ ይቅር ባይ አምላኩ ጴጥሮስን “በገሊላ ቀድሞት ነበር”። በበደሉ ተሸማቆ የተወውን ሐዋርያነት ሥልጣን በፍቅሩ መማለጃነት መልሶ ሊሰጠው፣ አይገባኝም ብሎ ያስቀመጠውን የወንጌል መረብ ዳግመኛ ሊያሲዘው በገሊላ ባሕር ዳር ቀደመው። እኛም አንድ ኃጢአት ይኖረናል። መርሳት ያልቻልነው፣ ንስሐ እንኳን ብንገባበት ራሳችንን ይቅር ለማለት የተቸገርንበት፣ “ከዚህ በኋላማ...” እያሰኘ የድሮ መረብ አስይዞ ወደ ገሊላ የሚመልስ አንድ በደል ይኖረናል። ነገር ግን ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዳደረገው ለእኛም እንዲሁ ያደርጋል። ከባሕሩ ዳር ይጠብቀናል፣ “ትወደኛለህ” ብሎ ይጠይቀናል፣ ከዚያ በማይለወጥ ፍቅሩ ወልውሎ ሰንግሎ አፍረን ወደ ሸሸነው መንፈሳዊነት ይመልሰናል። +++ ጌታችን በገሊላ ይቀድመናል! +++ ዲያቆን አቤል ካሳሁን
Показать все...
8👍 2
✟✟✟ግንቦት 21✟✟✟                    ደብረ ምጥማቅ 💫ግብጽ በምትገኘው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም የተሠራች ቤተክርስቲያን ናት ✨በ ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ ድንግል ማርያም ከግንቦት ፳፩(21) ጀምሮ እስከ ፳፭ (25)ቀናት በተከታታይ ትገለጣለች ✨እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ምድረ ግብጽና ኢትዮጵያ በተሰደደች ጊዜ በአሁኑ ጊዜ ደብረ ምጥማቅ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ ዐርፈው ነበር:: ጌታችንም ቦታውን ባርኮ የእርሷ መገለጫ እንዲሆን ቃል ኪዳን ገብቶላት ስለነበር ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት በዓት ሆነ:: 💫በደብረ ምጥማቅም እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም ብርሃን ተጎናጽፋና በሠራዊት መላእክት ታጅባ ተገልጣለች፤ በዚያን ጊዜም ሱራፌል ማዕጠንታቸውን ይዘው ሰገዱላት፤ እንዲህ እያሉም አመሰገኗት፤ ‹‹አብ በሰማይ አይቶ እንዳንቺ ያለ አላገኘም፤ ባንቺም ሰው ሆነ፡፡›› (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፰) ✨አባ ጽጌ ድንግልም በደብረ ምጥማቅ በታላቅ ክብር ለምእመናን የታየችው የአምላክ እናት የድንግል ማርያምን መገለጥ በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ እንዲህ በማለት ገልጾታል፤  ➖‹‹አመ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኀምሰ ዕለታተ፣ ትእምርተ ገጽኪ ይርአይ እስከ ይትነሣእ ዘሞተ፣ሚ መጠነ ማርያም ታሥተፌሥሒ ትፍሥሕተ፣ ኅድጊሰ ጽጌ ፍቅርኪ በጊዜ ንቃሁ መዓልተ፣ ብፁዕ ዘርእየኪ በሕልሙ ሌሊተ፤ የፊትሽን መልክ ያይ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሣ ድረስ በደብረ ምጥማቅ ለአምስት ቀናት ያህል በተገለጽሽ ጊዜ ማርያም ምን ያህል ደስ ታሰኚ ኖሯል! በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና ሌሊት በሕልሙ ያየሽ ምስጉን ነው፡፡›› (ማኅሌተ ጽጌ) ✨በደብረ ምጥማቅ ከተሰበሰቡት ሕዝብ መካከል ➖እናትና አባታቸው፣ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ባልንጀሮቻቸው የሞቱባቸው ሰዎች ቅድስት ድንግል ማርያም እንድታሳያቸው በለመኗት ጊዜ እንደ ቀደመ መልካቸው አድርጋ ታሳያቸው ነበር፡፡ 💫የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች እመቤታችን ድንግል ማርያምን ያዩባቸው ቀናት አረማውያኑ ያመኑበት፣ የበደሉት በምልጃዋ ቸርነትን ምሕረትን ያገኙበት፣ ያመኑት ደግሞ የተባረኩበት ዕለታት ነበሩ፡፡ ሕዝቡ እርሷን ተመኝተው ያጡት ወይንም ጠይቀው ያልተፈጸመላቸው ምንም ነገር አልነበረም::
Показать все...
2