cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የነገረ መለኮት መድረክ(Theologey Stage)

በዚ የስነ መለኮት መድረክ መጽሐ ቅዱሳዊ ስነመለኮት ያላቸው ጽሁፎች መጣጥፎች ወጉች ፣የጥንት ቤተክርስቲያን አባቶች አባባል ፣ የመጽሐፍ ግምገማ (Book review) ፣አጫጭር ሕይወት ለዋጭ ስብከቶች እና እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆኑ የተለያየ አይነት ይዘት ያላቸው መንፈሳዊ መጽሐፍቶች በቀጣይነት ይለቀቃሉ ። @Theologey_stage @Theologey_stage join and share 🙏

Больше
Рекламные посты
3 726
Подписчики
+3324 часа
+1537 дней
+56730 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
📗የቀዳሚ አንባቢያን አስተያየት📗 " የሮሜ መልዕክት ምዕራፍ ስምንትን መሰረት በማድረግ፣ ስለአማኞች የእግዚአብሐር ልጅነት ምንነት ለመረዳት በማያስቸግር መልኩ ወንድም ቢኒያም ተንትኖታል፡፡ ምዕራፉ በብዙ የልጅነት በረከቶች የታጨቀ በመሆኑ፣ መጽሐፉን የሚያነብ ማንም ተጠቃሚ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡" ደ/ር ተሰማ ፎርሲዶ (የአዲስ ኪዳንና የመጽሐፍ ቅዱስ ግሪክኛ መምህር) @Theologey_stage @Theologey_stage @Theologey_stage
Показать все...
👍 7 2❤‍🔥 1🤩 1🤗 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
📗የቀዳማዊ አንባቢያን አስተያየት📗 "ትልቁ እግዚአብሔር፣ ትልቅ እና የከበረ ዕምቅ መንፈሳዊ ሀብት በውስጡ ያስቀመጠበት ትንሹ ብላቴና ቢኒያም! ልጅ ቢኒያም፣ በሥነ-መለኮት አስተምህሮ ጥናት ውስጥ ደፍሮ በመግባት፤ በሮሜ ምዕራፍ ስምንት ላይ ባለው አስተምህሮ ተመስርቶ፣ የዳኑ አማኞችን “የእግዚአብሔር የማደጎ ልጅነት” አስረግጦ ለማሳየት የሄደበት መንገድ ይደንቀኛል፡፡ በክፍሉ የተቀመጡ አስተምህሮዎችን ከርዕሰ-ጉዳዩ አንፃር በማያያዝ የትምህርቱን ፍሰት/Flow of taught/ ሳያዛንፍ ለማብራራትና ለማስቀመጥ ያሳየው ጥረትም ይበረታታል፡፡ ይህንን መጽሐፍ በማንበቤ፣ ብዙ ተጠቅሜያለሁ፡፡ በመሆኑም በግል ጥናታችን፣በቤተሰብ አምልኮ ጊዜ፣በቡድን ጥናት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ት/ቤቶች..ወዘተ እንድንጠቀመው እመክራለሁ፡፡ ቢኒ! በ21ኛው ክፍለ ዘመን፣ በዘመን እላቂ ለምትገኘው ቤተ ክርስቲያን በረከትና ፈውስ እንድትሆን ምኞቴ ነው። ጌታ ይባርክህ !!" ለማ ፈረጀ መጋቢ እና የስነ መለኮት አስተማሪ @Theologey_stage @Theologey_stage @Theologey_stage
Показать все...
👍 2❤‍🔥 2 2💩 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
"ይህች መጽሐፍ መነሻዋን በሮሜ መልዕክት ላይ ያደረገች ስትሆን ዋና መልዕክትዋ የአማኝ የእግዚአብሔር የማደጎ ልጅነት ውስጥ ለአማኝ ያለው አስደናቂ በረከቶችና ከአባቱ ጋር ያለውን ህብረት ከስነ መለኮት ዕይታ እና ከታሪክ ማህደር ጋር በማያያዝ አስደናቂ ማብራራሪያ ለአንባቢያን በግልጽ መንገድ ዕንካችሁ ብሎናልለ፡፡ ይህችን መጽሐፍ ሁሉም አማኝ አግኝቶ እንዲያነብ አበረታታለሁ፡፡" መጋቢ አበራ ሎጲሶ (በሳውዝ አፍሪካ የኢ/ቃ/ሕ/ቤ/ክ/መጋቢ ኬፕታውን (CapeTown) @Theologey_stage @Theologey_stage @Theologey_stage
Показать все...
👍 6 6👏 1💩 1🤗 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
📗የቀዳማሚ አንባቢያን አስተያየት📗 "ቢኒያም “ሂዮቴሲያ” በሚለው በዚህ የትንታኔ መጽሐፉ፣ በሮሜ ምዕራፍ ስምንት በመመርኮዝ፣ የአማኝ የእግዚአብሔር ልጅነትን ለአንባቢያን በግልጽ ቋንቋ አብራርቷል። የአማኞችን የእግዚአብሔር ልጅነትን፣ ከባህላዊው የጉዲፈቻ ልጅነት ከሚያስገኘው መብት አንጻር ከአገራችን ምሳሌ በመጠቀም፣ በግልጽ አብራርቷል። ሐዋርያው ጳውሎስ በምዕራፉ ውስጥ የተጠቀማቸውን አምቅ ሀይል ያላቸውን ቃላቶች፣ በአዕምሮአችን ውስጥ ምስል ከሳች በሆኑ ቃላቶች በድንቅ ሁኔታ ፍቺ ሰጥቶ አስረድቶናል። የሮሜ ምዕራፍ ስምንት ጥልቀትን፣ በትንታኔው አሳይቶናል። ቢኒያም እንደ ጀማሪ ጸሐፊ ሳይሆን፣ ብዙ ልምድ እንዳላቸው ደራሲያን ሀሳቦችን በጥልቀት አሳይቷል ። መጽሐፉን በማንበብ ከበረከቱ እንድንቋደስ አበረታታለሁ ። እግዚአብሔር ይባርክህ፤ ያሳድግህ።" መምህር ክፍሌ ዋጄቦ ( በወቅቱ የሆ/ዕ/ቃ/ሕ/ቤ/ክ መሪ ሽማግሌ) @Theologey_stage @Theologey_stage @Theologey_stage
Показать все...
7🥰 1💩 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
"የሮሜ መጽሐፍ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ዋና ሐሳብ የያዘ በመሆኑ፣ ሰውን ሁሉ ያለልዩነት ይሞግታል። ሮሜን መነሻ በማድረግ የተቃኘው ይህ መጥሐፍ፣ በክርስቶስ የሚኖር አማኝ በአሁኑና በሚመጣው አለም ያለውን አስደናቂ ሕይወትና ስፍራ ይተነትናል። በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ሁሉ፣ ከአብ ዘንድ ስለ ተገለጠላቸው፣ ወደር የለሽ ጽድቅና በረከትም ይዘረዝራል። መጽሐፉ ከዋናው ሐሳብ ጀምሮ፣ በግሪክ የተዋዛ አቀራርብ ያለው ሲሆን፣ የአንባቢያንን ቀልብ ሊስብ በሚችል አገላለጥ ቀርቦአል። በክርስቶስ ምክንያት፣ አለም በሙሉ በሁለት የተከፈለ ነው፤ የዳነና ያልዳነ በመሆን። ውድ አንባቢ ሆይ፣ በክርስቶስ ከሆኑ ታድለዋል፤ ካልሆኑ ግን ይህን መጥሐፍ በማንበብ ራስዎን በጥንቃቄ ይፈትሹ ዘንድ ይበረታታሉ። በአጠቃላይ ወንድማችን ብንያም ያቀረበልን ይህ መጽሐፍ፣ ሰውን ሁሉ የሚሞግትና የሚያነቃቃ በመሆኑ፤ ሁሉም አንባቢያን ይታንጹበታል ብዬ አምናለሁ።" ዶ/ር ሽፈራው ፈለቀ (ቄስ) (ከቺካጎ ) @Theologey_stage @Theologey_stage @Theologey_stage
Показать все...
9👎 2👍 1 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
📗የቀዳሚ አንባቢያን አስተያየት 📗 "በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ ሮሜ 8 የጳውሎስ መልዕክቶች መልህቅ ነው! ይህንን ቢኒያም ዓለሙ "ሂዮቴስያ; የአማኝ የእግዚአብሔር ልጅነት" በሚለው መጽሐፊ ውስጥ "የሮሜ መጽሐፍ ስምንት ስነመለኮትና አስተንትኖት" በሚለው ንዑስ ርዕስ የእግዚአብሔር ልጅነት ገጽታና አንድምታውን፣ ለሁሉም አማኝ አንባቢዎች ግልጽ በሆነ ቋንቋ ስላብራራልን "ቱ ቱ እደግ ተመንደግ” ልለው እወዳለሁ፡ስለዚህ ይህ መጽሐፍ በቃሉ አገልጋዮችና ምዕመናን ዘንድ ከቤት መጽሐፍታቸው እንዳይለይ በአንክሮት አሳስባለሁ።" መጋቢ አበራ አዋኖ (በኢ/ቃ/ሕ/ቤ/ክ/ት/ስ/ክ/ሀ) @Theologey_stage @Theologey_stage @Theologey_stage
Показать все...
👏 8👍 3👎 1 1🫡 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
📗የቀዳሚ አንባቢያን አስተያየት 📗 "ልጅነት፤ በመስቀሉ ስራ የተገኘ ልጅነት ነው። ልጅነት፤ የማደጉ ልጅነት፤ የመንፈስ ልጅነት ነው። የርስቱ ወራሽነት፥ የዘላለም ህይወት ዋስትና፥ አባ አባት ብሎ የመጥራት መብት የተገኘበት ልጅነት ነው ይለናል ወንድማችን ቢኒ። የክርስትና ዋና ዶክትሪን ስለሆነው ነገረ ድነት በስፋት ይተነትናል። የድህነት ብቸኛ መንገድና በሩ ክርስቶስ ነው ይለናል። ድነናል፥ እየዳንን ነው፥ ደግሞም እንድናለን ይለናል። እንዲሁም በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ የሌሎች ሰዎች እይታ በማቅረብ ቅዱስ ቃሉን በክፍሉ እየተረጎመ ይሞግታቸዋል። ቢኒ፥ በመፅሐፉ፥ በሮሜ ምዕራፍ 8 ውሰጥ የሚገኙትን መልዕክቶችንና ሌሎችንም፥ ያኔ እዚያ(በሮም ባህልና አውድ) የነበርን እሰኪመስለን ድረስ፣ ከታሪካዊ ዳራ ጋር በማስተዋወቅ አሁን ወዳለንበት ቦታና ጊዜ(አሁን እዚህ) በመመለስ ሂወት ተኮር መርሆችን ይዘረዝራል፥ የተለያዩ ግላዊና ቡድናዊ አቋማችንንም ቻሌንጅ ያደርጋል። ደግሞም ሁሉም ሰው በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ ከህይወቱ ጋር እንዲያዛምድ ሀሳቡን ይጠቁማል፥ ያበረታታል። ስለዚህ መፅሐፉን አንብቡት፥ በብዙ ትጠቀማላችሁ። " ወንድም ጫኮሮ ታምሬ(ጫካኮ) (ETC,BTh.በኢትዮጵያ ምረቃ የነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ተማሪ) @Theologey_stage @Theologey_stage @Theologey_stage
Показать все...
👍 7 2👎 1👏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
📗የቀዳሚ አንባቢያን አስተያየት 📗 "ልጅነት፤ በመስቀሉ ስራ የተገኘ ልጅነት ነው። ልጅነት፤ የማደጉ ልጅነት፤ የመንፈስ ልጅነት ነው። የርስቱ ወራሽነት፥ የዘላለም ህይወት ዋስትና፥ አባ አባት ብሎ የመጥራት መብት የተገኘበት ልጅነት ነው ይለናል ወንድማችን ቢኒ። የክርስትና ዋና ዶክትሪን ስለሆነው ነገረ ድነት በስፋት ይተነትናል። የድህነት ብቸኛ መንገድና በሩ ክርስቶስ ነው ይለናል። ድነናል፥ እየዳንን ነው፥ ደግሞም እንድናለን ይለናል። እንዲሁም በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ የሌሎች ሰዎች እይታ በማቅረብ ቅዱስ ቃሉን በክፍሉ እየተረጎመ ይሞግታቸዋል። ቢኒ፥ በመፅሐፉ፥ በሮሜ ምዕራፍ 8 ውሰጥ የሚገኙትን መልዕክቶችንና ሌሎችንም፥ ያኔ እዚያ(በሮም ባህልና አውድ) የነበርን እሰኪመስለን ድረስ፣ ከታሪካዊ ዳራ ጋር በማስተዋወቅ አሁን ወዳለንበት ቦታና ጊዜ(አሁን እዚህ) በመመለስ ሂወት ተኮር መርሆችን ይዘረዝራል፥ የተለያዩ ግላዊና ቡድናዊ አቋማችንንም ቻሌንጅ ያደርጋል። ደግሞም ሁሉም ሰው በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ ከህይወቱ ጋር እንዲያዛምድ ሀሳቡን ይጠቁማል፥ ያበረታታል። ስለዚህ መፅሐፉን አንብቡት፥ በብዙ ትጠቀማላችሁ። " ወንድም ጫኮሮ ታምሬ(ጫካኮ) (ETC,BTh.በኢትዮጵያ ምረቃ የነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ተማሪ)
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የተወደዳችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች፣ እንኳን ደስ ያላችሁ!👐 ያለፉትን ሶስት ሳምንታት ከመጽሐፍ ሕትመት ጋር በተገናኘ ላቀረብንላችሁ ጥያቄ በደስታ አጋር በመሆን፤ መጽሐፉን በቅድመ ክፍያ በመግዛትና ምክረ ሀሳቦችን በመለገስ፤ ልጥፎቸን በማጋራት፤ በማበረታታት፤ ከጉናችን የነበራችሁ ሁሉ፣ ብሩካን ናችሁ። መጽሐፏ በዚህ ሰአት ማተሚያ ቤት የገባች ስትሆን፣ በጥቂት ቀናቶች ውስጥ ሕትመትዋን ጨርሳ ትወጣለች። ቀጣይ የመጽሐፉን ምረቃ ፕሮግራም ሂደት በአዲስ አበባ፣ በሆሳዕና እና በሌሎች ክልል ከተሞች ላይ የምናደርግ ሲሆን ቀናቶቹን በቀጣይ የምናሳውቃችሁ ይሆናል። በቅድመ ክፍያ መጽሐፉን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለገዛችሁ በያላችሁበት መጽሐፉ ከእጃችሁ የሚደርስበትን አቅጣጫ ዘርግተናል። መጽሐፏ ሕትመትዋን ጨርሳ እንደወጣች ስርጭታችንን የምንጀምር ይሆናል ። አሁንም መጽሐፉን በቅድመ ክፍያ በመግዛት ከጉናችን መሆን ለምትፈልጉ ሁሉ የመጀመሪያው ዕትም አንድ ሺህ (1000) ኮፒ ብቻ በመሆኑ አሁንም ፈጥነው ይመዝገቡ😍🙏 ቢኒያም አለሙ ኤርቲሮ; @Biniyam_Alemu7 ለበለጠ መረጃ 0986190733 ስለምታደርጉልን ትብብር ከልብ እናመሰግናለን ብሩካን ናችሁ🙏🙏 "የእግዚአብሔር ወንጌል፣ ሁሌም ሕያው ነው" ! @Theologey_stage @Theologey_stage @Theologey_stage
Показать все...
5👎 1🔥 1🥰 1👏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
እያደረጋችሁልን ስላለው ትብብር ከልብ እናመሰግናለን🙏🙏 የመጀመሪያው እትም 1000 ኮፒ ብቻ በመሆኑ ከአሁኑ ፈጥናችሁ የዚህ ታሪካዊ ስራ አካል እንድትሆኑ አሁንም አበረታታችሁአለው🙏 🙏 📚 "ሂዮቴሲያ; የአማኝ የእግዚአብሔር ልጅነት ;የሮሜ መጽሐፍ ምዕራፍ ስምንት ስነመለኮት እና አስተንትኖት" 📎ይህ መጽሐፍ በአሁን ሰአት ማተሚያ ቤት የገባ ሲሆን ሕትመቱን ጨርሶ ለእናንተ እና ለቅዱሳን ሁሉ በረከት ይሆን ዘንድ የእናንተን ደጋግ እና ለጋስ እጅ ይፈልጋል ስለሆነም ከዚህ የወንጌል አገልግሎት ጉን መሆን የምትፈልጉ ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ሁለት አማራጭ አቅርበናል፦ 📌የመጀመሪያው 1000 ሰዎች 100 ብር ብንለግስ መጽሐፉን በቀላሉ ቶሎ ታትሞ እንዲወጣ ማድረግ እንችላለን፤ 📌ሁለተኛው መጽሐፉን በቅድመ ክፍያ በመውሰድ መደገፍ የምትፈልጉ በአዲስ አበባና በክፍላገር ያላቹ ውድ ቤተሰቦቻችን መጽሐፉ ከማተሚያ ቤት በሚወጣበት ወቅት እስከያላችሁበት ድረስ ለማሰራጨት ዝግጅታችንን የጨረስን ስለሆነ ሶስት መቶ ብር ብቻ(300 ብቻ) የመጽሐፉን ዋጋ ከታች ባሉት ቁጥሮች ቅድመ ክፍያ በማድረግ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ልናበስርላችሁ እንወዳለን!🙏 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:1000628469761 አቢሲኒያ ባንክ Account no ;96195834 አዋሽ ባንክ ;Account no;01320742143000 ቅድመ ክፍያም( 300 ብር) ሆነ ስጦታ (100) የፈጸማችሁትን screenshots በማድረግ በነዚህ አድራሻ እንድታሳውቁን። @Biniyam_Alemu7 ቢኒያም አለሙ ኤርቲሮ; @Biniyam_Alemu7 ለበለጠ መረጃ 0986190733 ስለምታደርጉልን ትብብር ከልብ እናመሰግናለን ብሩካን ናችሁ🙏🙏 "የእግዚአብሔር ወንጌል ሁሌም ሕያው ነው" ! @Theologey_stage @Theologey_stage @Theologey_stage
Показать все...
👍 10 2👏 2 1🙏 1
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.