cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

"በተማርከው እና በተረዳኸው ነገር ፀንተ ኑር"

Больше
Рекламные посты
352
Подписчики
+424 часа
+77 дней
+2230 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

1.ከዚህ መተካካት ውጭ ያለ "ክህነት" ትክክለኛ ክህነት አይደለም!!! 2.ከዚህ የክህነት መስመር ውጭ የሚደረግ "ጥምቀት" ውሃ ውስጥ መነከር እንጂ የእግዚአብሔርን ልጅነት የሚያሰጥ ጥምቀት አይደለም!!!3.ከዚህ የክህነት መስመር ውጭ የሚደረግ "የጌታ እራት" (ቅዱስ ቁርባን) እውነተኛ የጌታ ሥጋ እና ደም አይደለም!!! 4.ከዚህ የሐዋርያዊ መተካካት ውጭ ያለ "ትምህርት" የሃሰት ትምህርት፣ የግል መረዳት ፣ አዲስ ወንጌል እና አዲስ ኢየሱስ ነው። ማቴ 28:19 "ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ" ያለው ጌታ በሐዋርያት ከሚተኩት አባቶች ጋርም አብሮ እንደሚሆን ያረጋገጠበት እና የጌታን ቤተክርስቲያን በግለሰብ ከተመሰረቱ ቤተክርስቲያን ነን ባዮች የሚለይ የተስፋ ቃል ነው።     ስብሐት ለእግዚአብሔር አምላከ አበዊነ           ተጻፈ በ ወልደ ማስያስ https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Показать все...
"የጌታ ቤተክርስቲያን" እና "ሃይማኖት" ሲባል ምንድነው ? (በአጭሩ) ሃይማኖት ስንል እኛ ማመን እና መታመንን አንድላይ የያዘ "እምነት" እያልን ነው ። "ሃይማኖት" ቃሉ ግእዝ ነው ትርጉሙ "እምነት" ማለት ነው ስለዚህ አንድ ሰው ሃይማኖት አያድንም ሲል እምነት አያድንም እያለ ነው ። ሃይማኖት የሚለውን ቃል ሲሰማ ድርጅት የተባለ የሚመስለው ሰው ምንም ስለ ሃይማኖት ምንነት የማያውቅ እና ጥራዝ ነጠቅ እውቀት ያለው ሰው ነው ።  ብዙ "እምነት" ነን የሚሉ ብዙ ስብስቦች ቢኖሩም እኛ ግን እረኛውም አንድ መንጋውም አንድ እንደሆነ እናምናለን ከሐዋርያው ጋር አብረን “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤”   ኤፌሶን 4፥5 እንላለን 🙏 ይች ጌታ በደሙ የመሰረታት እምነት ደግሞ በውስጧ ካህናት ፣ ምእመናን ፣ ቅዱሳን መላእክት ፣ ቅዱሳን ሰዎች በስጋም በአጸደ ነፍስም ያሉ እና የሁሉም ራስ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለባት ህብረት ናት ። (ዕብ 12:22-24) ይች ህብረትም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለች እና በታሪካዊ ክርስትና ውስጥም የምትታወቅ አንድ የጌታ ቤተክርስቲያን ናት ማቴዎስ 16 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹³ ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ። ¹⁴ እነርሱም፦ አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት። ¹⁵ እርሱም፦ እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው። ¹⁶ ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ። ¹⁷ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ። ¹⁸ እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። 👆👆 ቤተክርስቲያኔ አለ እንጂ ቤተክርስቲያኖቼ አላለም “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።”   — ሐዋርያት 20፥28 ዮሐንስ 10 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁴-¹⁵ መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ። ¹⁶ ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ። 👉👉 በደሙ የተመሰረተች አንድ ቤተክርስቲያን አለች ሌሎቹም ወደዚች በረት ይመጣሉ ለመዳን እንጂ በያሉበት ሆነው እንደፈለጉ የተለያየ ትምህርት እያስተማሩ እየተማሩ በራሳቸው የፈጠሩትን እምነት እያመኑ ይድናሉ አላለም !!! ለዚህም ማስረጃው ይሄ ነው ሰዎች በስብከት አምነው ክርስትያን ሲሆኑ ሐዋርያት ወደ ሰበሰቧት አንዲት ህብረት እንደተጨመሩ ተጽፏል ። 👉"ተጨመሩ" የሚለው ቃል በጣም ወሳኝ ነው ምክንያቱም ከመጨመራቸው በፊት የነበረ አንድ ህብረት አለ ማለት ነው ። ወደዛ ወደነበረው ህብረት ተጨመሩ እንጂ አዲስ ህብረት አልመሰረቱም!!! እስኪ እንይ የተወሰኑትን👇👇 “ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፥ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤”   — ሐዋርያት 2፥41 “ደግ ሰውና መንፈስ ቅዱስ እምነትም የሞላበት ነበረና። ብዙ ሕዝብም ወደ ጌታ ተጨመሩ።”   — ሐዋርያት 11፥24 ሐዋርያት 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴⁶ በየቀኑም በአንድ ልብ ሆነው በመቅደስ እየተጉ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ፥ በደስታና በጥሩ ልብ ምግባቸውን ይመገቡ ነበር፤ ⁴⁷ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በሕዝብ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው። ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር። 👉"ይሄው ነው ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን " የምንለው ሌላው ደግሞ ቤተክርስቲያን ተቋማዊም ናት ምክንያቱም ይሄንን መንፈሳዊ ዓላማ ለማስፈጸም የአስተዳደር እና የአገልግሎት መዋቅር አላት ይሄም ተቋማዊ ባህርይ ነው ። በተለያየ ሹመት ያሉ አገልጋዮች ያሉባት ሁሉም የየራሱ ሃላፊነት ያለው እና ያንንም የሚያደርግባት ናት ስለዚህ ይሄንንም መካድ አያስፈልግም ። ለዚህም ማቴ 28:19 ፣ የሐዋርያት ሥራ ምእራፍ 6 ሙሉውን ፣ 1 ጢሞ 3 ሙሉ ምእራፉን እና በአጠቃላይ ሙሉ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን እንደ ብፌ እየመረጠ ሳይሆን ሙሉውን የሚቀበል ሰው ብዙ ማስረጃዎች አሉ ። የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ ላይም ጉባኤያተ ቤተክርስቲያንን ጭምር ይሄንን እውነታ ይመሰክራሉ ። እንኳን በአዲስ ኪዳን በብሉይ ኪዳንም የአስተዳደር ሥርዓት ነበር ። ስለዚህ የጌታ ቤተክርስቲያን አንድ ናት እረኛውም አንድ ነው ከዚህ ህብረት ውጭ ያሉ ግን በጌታ እናምናለን የሚሉት ሲጀመር ክርስትያንም አይባሉም ሊሆኑም አይችሉም ። እኛን አንድ የሚያደርገን አንዷ ጥምቀት እና አንዱ የጌታ ሥጋ እና ደም ነው ትምህርቱ ብቻ አይደለም ስለዚህ በዚህ ቁርባናዊ አንድነት ውስጥ ሳይሆኑ አማኝ ነኝ ማለት አይቻልም !!!    ልናውቃቸው የሚገቡን አራት ወሳኝ ነጥቦች 1.ሐዋርያነ አበው(Apostolic fathers) ማለት ከሐዋርያት ቀጥለው በእነሱ እግር የተተኩ እና በቀጥታ ከሐዋርያት የተማሩ እንዲሁም ከሐዋርያት የተማሩት ያስተማሯቸው ክርስትናን ያስቀጠሉ ሐዋርያዊ አባቶች ናቸው። 2.ሐዋርያዊ አስተምህሮ(Apostolic teachings) ማለት ደግሞ በቃል፣በጽሑፍ እና በህይወት ከጌታ ወደ ሐዋርያት ከሐዋርያት ወደ ሐዋርያነ አበው በቅብብሎሽ የመጣ ትምህርት እና መረዳት ነው። እምነታችን የሚመሰረተው በዚ ትምህርት ላይ ነው ምክንያቱም በትክክለኛ ትምህርት ላይ ያልተመሰረተ እምነት አያድንም!!! 3.ሐዋርያዊ ትውፊት(Apostolic tradition/Holy tradition) ማለት ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ማለት ነው። ይሄም በቃል በጽሑፍ እና በህይወት ከጌታ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ አንዱ ለአንዱ እያቀበለ የደረሰውን እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የሚቀጥል የተቋረጠበት ዘመን የሌለ የትምህርት ፣ የሥርዓተ አምልኮ እና የቅዱሳት መጻሕፍት መረዳትን(Understanding) እና ራሳቸው ቅዱሳት መጻሕፍቱን የያዘ ቅብብሎሽ ነው። 4.ሐዋርያዊ መተካካት(Apostolic succession) ማለት ሐዋርያቱ ሌሎች አባቶችን እየተኩ ከስልጣኑ ጋር የሚሰጠውን ሃላፊነትም እየሰጡ የሚሾሙበት፣ እነዛ የተሾሙትም ደግሞ ሌሎችን እየሾሙ እየተተካኩ አገልግሎቱ እንዲቀጥል የሚያረጉበት እና የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከሌሎች የምትለይበትን ነገር የሚያሳይ መሰረታዊ እና መታወቅ ያለበት ነገር ነው። ለምሳሌ:- የእኛ ቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ ክህነታቸውን ወደ ኋላ ስንቆጥር ቅዱስ ማርቆስ ጋር እንደርሳለን ለቅዱስ ማርቆስ ደግሞ ስልጣን የሰጠው ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የሌሎቹም ሐዋርያዊ አብያተክርስቲያናት ልክ እንደ እኛ ወደ ኋላ ሲቆጠር የሚደረስበት ሐዋርያ አለ ለሐዋርያቱ ደግሞ ስልጣን የሰጠው ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
Показать все...
👍 1
🕊                                          🕊 - በሮሜ ንግሥናን የናቀ ፤ - የደገኛው የአባ በብኑዳ ደቀ መዝሙር የሆነ ፤ - ፯፻፺፱ ሙታንን በጸሎቱ ያስነሳ ፤ - በምዕራብ ገዳም ያደረ ፤ - ጌታ ፬ቱ ምርጦቼ ካላቸው ፩ዱ የሆነ ፤ - ስለየዋህነቱ የተመሰከረለት ፤ - ክቡር ኪዳንን ከጌታችን የተቀበለ ፤ - ነደ እሳት የሳመው ፤ - ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በበገና የዘመረለት ፤ - የእግዚአብሔር ሰው ፤ . . . አረጋዊ ክቡር ወጻድቅ አቡነ ኪሮስ ❀ ከኪዳኑ ፡ ከረድኤቱ ፡ ከበረከቱ አይለየን ! " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን":: /የቅዱሳንን ዜና [ ታሪክ ] እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ 💖                      🕊                      💖 https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Показать все...
#ሐምሌ_9 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ዘጠኝ በዚህች እለት #ለአቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ጌታችን ቃልኪዳኑን የሰጠበት ዕለት ነው፣ የአምስቱ አህጉር ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ቴዎድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ #ቅዱስ_ታውድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ መስተጋድል #አባ_ኅልያን አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ሐምሌ ዘጠኝ በዚህች እለት ለአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ጌታችን ቃልኪዳኑን የሰጠበት ዕለት ነው፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናቱ ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡ በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል፡፡ የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል፡፡ በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡ ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት ለአባቶች መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡፡ አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከጾሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል፡፡ ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡ አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡ ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን "ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው" ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል። አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር፡፡ ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ እያጠመቁ፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ጸልየው የምሕረት ቃልኪዳን በዚህች ዕለት ተቀብለዋል፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ "ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ" በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡ ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል "በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ" ብለው ገዝተው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ "አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ" ስትላቸው "እግዚአብሔር ይፍታሽ" ባሏት ጊዜ ጠልቃለች፡፡ ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡ በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ መልክአ መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ ጸሎት አለቻቸው፤ እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ፡፡ ጸሎቷም የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች፡፡ በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ አቡነ ዘበሰማያት ይደግማሉ፡፡ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ጸሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም፡፡ (ይህንን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት የምናገኘው ከገድላቸው ላይ ነው፡፡) ጻድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልው ሚያዝያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ቴዎድሮስ_ሰማዕት (ዘሐምስቱ አሕጉር)  ሐምሌ ዘጠኝ በዚህች ቀን የአምስቱ አህጉር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ቴዎድሮስ በሰማዕትነት አረፈ። ዲዮቅልጥያኖስም በካደና ጣዖትን በአመለከ ጊዜ ምእመናንን ያሠቃዩአቸው ዘንድ መኳንንቱን ወደ ሀገሮች ሁሉ ላከ። ለጣዖትም እንዲሰግዱ ያስገድዷቸው ነበር።  ስሙ ፍላጦስ የሚባል አንድ መኰንንም ወደ አፍራቅያ አገር መጣ። በዚህም ቅዱስ ለክርስቲያን ወገን መምህር እንደ ሆነ ነገር ሠሩበት መኰንኑም ወደርሱ አስቀርቦ ለአማልክት እንዲሠዋ አዘዘው።  ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት ሰማይና ምድርን የፈጠረ አምላክን ትተን ጣዖት ማምለክ አይግባንም። መኰንኑም በውኑ አርጤምስንና አጵሎንን አርዳሚስንም ሌሎች አማልክትንም ያይላቸዋልን ሌላ ነውን አንተ ይምትናገርለት አምላክ ካለ እነዚህስ አማልክት አይደሉምን አለው። ቅዱስ ቴዎድሮስም መልሶ አዎን አማልክት አይደሉም ክብር ይግባውና ከአንድ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አምላክ የለም እርሱም ለፍጥረቶች ሁሉ ፈጣሪያቸው ነው አለው።  መኰንኑም ኃይለ ቃል ስለመመለሱ ተቆጥቶ አርባ ቀን በግርፋትና በስቅላት በእሥራትና በመንኰራኲራት እንዲአሠቃዩት አዘዘ። እርሱ ግን ትእዛዙን አልሰማም ከሥቃዩም የተነሣ አልፈራም። ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ታውድሮስ_ሰማዕት  በዚህችም ቀን ከቆጵሮስ አገር ቅዱስ ታኦድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፡፡ ከእርሱም ጋራ ሦስት ሴቶችና ያሠቃዩት የነበሩ ሁለቱ መኳንንት ሉክያኖስና ድግናንዮስ አረፉ።  ይህም እንዲህ ነው ይህን ቅዱስ ወደእነዚህ መኰንኖች በከሰሱት ጊዜ እርሱ ክርስቲያንና የቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ እንደሆነ ሰምተው ወደ እነርሱ አቀረቡት ስለሃይማኖቱም ጠየቁት። እርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ታመነ በበትሮችም እየደበደቡና እየገረፉ ቀጡት እርሱም እየዳኸ ሒዶ ጣዖቱን ረገጠው ከመንበሩም ላይ ገልብጦ ጣለው። እሊህ ሁለቱ መኳንንትም ተቆጥተው ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ሥጋውንም በማቅ ጨርቅ ጨውና ኮምጣጣ ነክረው ፋቁት እርሱም ጣዖታቱን ይረግም ነበረ። ሁለተኛም ምላሱን ቆረጡት። ያን ጊዜም በዚያ ከነበሩ ሴቶች አንዲቱ ምላሱን አንሥታ ወሰደች።ከዚህም በኋላ ቅዱሱን በአሠሩት ጊዜ ከሴትዮዋ እጅ ምላሱን ተቀብሎ በሆዱ ላይ
Показать все...
09/11/2013                      የዕለቱ የወንጌል ክፍል                          ሉቃስ 13:18-23      እርሱም፦ “የእግዚአብሔር መንግሥት ምን ትመስላለች፥ በምንስ አስመስላታለሁ? ሰው ወስዶ በአትክልቱ የጣላትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤ አደገችም ታላቅ ዛፍም ሆነች፥ የሰማይ ወፎችም በቅርንጫፎችዋ ሰፈሩ፡” አለ። ደግሞም፦ “የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን አስመስላታለሁ? ሴት ወስዳ ሁሉ እስኪቦካ ድረስ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች፡” አለ። ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ከተማዎችንና መንደሮችን እያስተማረ ያልፍ ነበር.... 1 ጢሞቴዎስ 3:1-11 1 ጴጥሮስ 5:1-ፍጻሜ ሐዋ.ሥራ 20:28-31                         ምስባክ                     መዝሙር 83:6 እስመ መምህረ ህግ ይሁብ በረከተ ወየኃውር እምኃይል ውስተ ኃይል ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን                ትርጉም የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Показать все...
አኖራት ወዲያውኑም ምላሱ ተዘርግታ ወደ አፉ ገባች አንዲት ነጭ ርግብም መጥታ በቅዱሱ ላይ ዞረች ሁለተኛም ሶሪት ዎፍ መጥታ በላዩ ተቀመጠች እሊህ ሁለቱ መኳንንትም አይተው አደነቁ። ሉክዮስም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ ያን ጊዜም መኰንኑ ድግናንዮስ ተቆጥቶ ከቅዱስ ታኦድሮስ ኋላ ይከተሉ የነበሩ ሦስት ሴቶችን ገደላቸው።  ከዚህም በኋላ ቅዱስ ታኦድሮስ ነፍሱን በሰጠ ጊዜ ርግቧና ሶሪት ዎፍ በርረው ሔዱ ድግናንዮስም አደነቀ ሉክዮስም የክርስቲያን ሃይማኖት የቀናች እንደሆነች አስረዳው ክብር ይግባውና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ።  ከዚህም በኋላ ሁለቱ መኰንኖች ከቆሮንቶስ አገር በመርከብ እስከ ቆጵሮስ ሔዱ በዚያም ክርስቲያኖችን ሲአሠቃያቸው ሌላውን መኰንን አገኙ ሉክዮስም ከድግናንዮስ ተሠውሮ በመኰንኑ ፊት ቆመ የጣዖታቱንም መንበር ገለበጠ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። ድግናንዮስም ሥጋውን ወስዶ ገንዞ ቀበረው።  ከዚህም በኋላ ድግናንዮስ በመኰንኑ ፊት ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ይህንንም በሰይፍ ራሱን ቆርጠው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አባ_ኅልያን_ገዳማዊ  በዚህችም ቀን መስተጋድል አባ ኅልያን አረፈ። የዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ዲስጣ የእናቱ ስም ካልሞና ነው የአገሩም ስም ዐይነ ፀሐይ ይባላል። እርሱም ቀድሞ በወጣትነቱ ጊዜ የወርቅና የብር አንጥረኛ ነበር በሥራውም የተመሰገነ ነው።  በአንዲት ቀንም ከዐረብ አገልጋዮች አንዲት ሴት መጥታ ለጆሮዎቿ ጉትቻ እንዲሠራላት ለመነችው ከሠራላትም በኋላ የሠራበትን ዋጋ ከእርሷ ፈለገ። በፊቱም ራሷን ዘንበል አድርጋ ወንዶች ከሴቶች የሚሹትን ብትሻ እነሆኝ አለሁ ሌላ ገንዘብ ግን የለኝም አለችው። ይህንም በሰማ ጊዜም አንቺ የጨለማው አበጋዝ ልጅ ከእኔ ራቂ ፊትሽንም አታሳይኝ አላት።  ከዚህም በኋላ ሞትና ፍርድ መኖሩን ለነፍሱ እያሳሰባት በማደሪያው ውስጥ ጥቂት ቆየ። ተነሥቶም ለድኆችና ለችግረኞች ገንዘቡን መጸወተ ከገንዘቡም ከፍሎ ለእናቱ ሰጥቷት ተሰናበታት። ለሦስት ቀን የሚበቃውንም ስንቅ ይዞ ወደ ገዳም ሔደ እግዚአብሔርም የልቡናውን ንጽሕና ስለ አየ መራው የራቀውን ቦታ ወደ እርሱ አቀረበለት ወደ ኤርትራ ባሕር ዳርቻም በአንዲት ቀን ደረሰ።  ቆሞ ሳለም ነጭ ልብስ የለበሱና እንደ ፀሐይ የሚያበራ መስቀልን የተመረኰዙ ሦስት ሰዎች ተገለጡለት አነቁትና ከእሳቸው ጋራ ወሰዱት ወደ አትክልት ቦታም በደረሱ ጊዜ በትርና የዕንቁ መስቀል ሰጡት። በዚያም በአንድነት ጸለዩና ሰገዱ ከሰገደበትም ራሱን ቀና ባደረገ ጊዜ ከእርሳቸው ያገኘው አልነበረም በመለየቱም አዘነ አለቀሰም።  ከዚህም በኋላ ከአትክልቱ ቦታ ቅጠል እየበላ ውኃም ከርሷ እየጠጣ ኑሮውን በብሕትውና አደረገ። ወደ ቦታዎችና ወደ ዋሻዎች ለመሔድ የፈለገ እንደሆነም በትረ መስቀሉ ታበራለት ነበር። የረዘመውንም መንገድ ትጠቀልልለት ነበር ልብሱም ከእነዚያ ዛፎች ቅጠል ነበር።  የተረገመ ሰይጣንም ተጋድሎውን በአየ ጊዜ ሰው ተመስሎ ወደ ክፉዎች ሰዎች ሔደ እንዲህም ብሎ ነገራቸው በእገሌ በረሀ የተሠወረ ገንዘብ አለ የሚጠብቀውን ከያዛችሁት ታገኛላችሁ ወደዚያ ወንዝ ማዶም መርቶ አደረሳቸው በደረሱም ጊዜ መሻገሪያ መንገድ አጡ። እጅግም ተጠምተው ነበርና ውኃውን እያዩ ወደ ውኃው መድረስ ተሳናቸው።  ሁለተኛም በሚያስፈራ ዘንዶ ተመስሎ ቅዱስ ኅልያንን ውኃ ሲጠማቸው አንተ ለባልንጀሮችህ እንዴት አትራራም እንዴትስ ውኃ አታጠጣቸውም አለው በዚህ የሚይዙት መስሎት ነበርና። ለቅዱስ ኅልያንም በአውሬ አንደበት እግዚአብሔር የዘለፈው መስሎት ውኃ ቀዳላቸው ያጠጣቸውም ዘንድ ተሻገረ። እነርሱም ድኃነቱን አይተው ራሩለት ልብስ ሊሰጡትም ወደዱ እርሱ ግን አልተቀበላቸውም ወደ በዓቱም ተመለሰ።  ሰይጣንም ተንኰሉ በከሸፈበት ጊዜ በደጋጎች መነኰሳት ተመሰለ ሊአስቱትም ወደርሱ ሔዱ በመስቀል ምልክትም በማተበ ጊዜ አፍረው ተበተኑ ። የዕረፍቱም ሰዓት በቀረበ ጊዜ ቀድሞ ተገልጸውለት የነበሩ እነዚያ ሦስት ሰዎች መጥተው ገድሉን ጻፉ ባረፈ ጊዜም ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ) https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Показать все...
.             መንፈሳዊነት ምንድነው ? ➯እውነተኛ መንፈሳዊ ሰው ማለት ከልቡ ጋር እና ከሕሊናው ጋር የሚኖር ነው። ➯መንፈሳዊነት ማለት ማንን እየመሰልኩ ነው ብሎ ማሰብ ነው ➯መምሰል ያለብንም ቅዱሳንን  ከፍ ሲል  ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስን ነው ➯የመንፈሳዊነት መጀመሪያም እግዚአብሔርን መፍራት ነው ➯ክፉውን እዳትሰራ እግዚአብሔርን ፍራው ➯በጎውን እድትሰራም እግዚአብሔርን ፍራው ➯መልካም ነገር ላለማድሰግህም እግዚአብሔርን አስበው ➯እግዚአብሔር ግን ይሄን አድርጎልኛል :-      እየሰጠኝ እቀማዋለሁ : እያቀረበኝ እርቀዋለሁ : እየተከተለኝ እሸሸዋለሁ : እየወደደኝ እጠላዋለሁ :  እኔ እንደዚህ ነኝ እግዚአብሔር ግን ይወደኛል ብሎ  ማሰብ ይገባል ። ➯ሰው ይኸንን ማሰብ ሲጀምር ነፍሱ ሕሊናውን መግዛት ትጀምራለች ሕሊናው ስጋውን መግዛት ይችላል ሕሊናው ስጋውን ሲገዛለት  በመንፈስ መመላለስ ይጀምራል ተስፋውም ሰማያዊ ይሆናል። ርእሰ ሊቃውንት  አባ ገብረ ኪዳን☦🤍 https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Показать все...
📌ወደ ላይ እይ            ሌባው ከአንድ ግቢ ይገባል ጊዜው ጨለማ ነው የግቢው ባለቤት ግቢው ከሚገኘው ዛፍ ላይ ወጥቶ ሌባውን ይመለከታል። ሌባው እሮጦ መጥቶ ዛፉ ሥር ቆመ። አሁን ባለቤት ከላይ ሌባ ከታች ሆነዋል። ሌባው አያይም ባለቤት ግን ሌባውን ያየዋል ሌባው ዛፉ ሥር እንደቆመ ቅኝት ይጀምራል ወደ ፊት፣ ወደ ኋላ ወደ ቀኝና ወደ ግራ እየተዟዟረ ዐየ.......ይሄኔ የቤቱ ባለቤት ዛፍ ላይ ሆኖ አንዲት የዛፍ ፍሬ ወደ ታች ለቀቀበትና ፍሬዋም የሌባውን አናት ዳብሳ ወደቀች። ይሄኔ ሌባው ቀና ብሎ ወደ ላይ ዐየ። ከቤቱ ባለቤት ጋርም ተፋጠጠ ......የቤቱ ባለቤትም "ሁሌ ልትሰርቅ ባሰብክ ጊዜ "ወደ ቀኝና ወደ ግራ ብቻ ሳይሆን ወደ ላይም ማየት እንዳለብህ ላስታውስህ ፈልጌ ነው" አለው ይባላል። 📌👇 #ሰው አያውቅብንምና ዐያየንም ብለን የምን ሠራውን መጥፎ ሥራ ሁሉ እግዚአብሔር ያውቅብናል ብለን ልንተወው ይገባል። ክርስቲያን በሁሉ ቦታ ታማኝ ነው። ዐይነ ስጋችንንም ሆነ ዐይነ ልቡናችንን ሁልጊዜ ወደ ላይ ወደ እግዚአብሔር ልዕልናና ክብር ሊያይ ይገባል። https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Показать все...
#ዝክረ_ቅዱሳን_ሰኔ_9/፱ (ስንክሳር) እንኳን ለታላቁ #ለነቢይ_ሳሙኤል ለዕረፍቱ መታሰቢያ፣ እንዲሁም #ለቅዱስ_ሉክያኖስ ከሌሎች አራት ሰማዕታት ጋራ ሰማዕት ለሆነበት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን። "በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።" #ነቢዩ_ቅዱስ_ሳሙኤል ➯ሰኔ ዘጠኝ በዚህች ዕለት የታላቁ ነቢይ ሳሙኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። የዚህ ቅዱስ አባቱ ሕልቃና ይባላል የእናቱም ስሟ ሐና ነው። እነርሱም ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ወገን ናቸው። ሐናም መካን ነበረች ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር እያለቀሰች አዘውትራ ስለ ማለደች ይህን የተባረከ ልጅ ሰጣት በቤቷም ሦስት ዓመት አሳደገችው። ➯ከዚህም በኋላ ገና ስትፀንሰው እንደተሳለች ወደ እግዚአብሔር መቅደስ አቀረበችው ካህኑ ኤሊንም በመላላክ የሚያገለግለው ሆነ። የካህኑ የኤሊ ልጆች ግን ክፉዎች ነበሩ እግዚአብሔርንም አይፈሩም ነበር በቅዱስ መሥዋዕቱም ላይ በደሉ። ይህ ሕፃን ሳሙኤል ግን በኤሊ ፊት ለእግዚአብሔር ሲያገለግል ኖረ በነዚያ ወራቶችም ቃለ እግዚአብሔር ውድ ነበር የሚታይ ራእይም አልነበረም። ➯ከዚህም በኋላ በአንዲት ሌሊት እንዲህ ሆነ ኤሊ በመኝታው ተኝቶ ሳለ ዐይኖቹም መፍዘዝ ጀምረው ነበር ማየትም አይችልም ነበር። የእግዚአብሔርንም መብራት አብርቶ ለማሳደር ገና አላዘጋጁም ነበር ሳሙኤል ግን በቤተ መቅደስ በእግዚአብሔር ማደሪያ ታቦት አጠገብ ተኝቶ ነበር።  ➯እግዚአብሔርም ሳሙኤልን ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው እነሆ እኔ አለሁ አለ። ወደ ኤሊም ፈጥኖ ሔደ ስለጠራኸኝ እነሆ እኔ መጣሁ አለው ኤሊም አልጠራሁህም ተመልሰኽ ተኛ አለው ሔዶም ተኛ። ➯እግዚአብሔርም ዳግመኛ ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ ኤሊ ሔደ ስለጠራኸኝ እነሆ መጣሁ አለው። ኤሊም አልጠራሁህም ተመልሰህ ተኛ አለው። ሳሙኤልም ከዚህ አስቀድሞ እግዚአብሔርን በራእይ ገና አላወቀውም ነበር ቃለ እግዚአብሔርም አልተገለጠለትም ነበር።  ➯ዳግመኛም እግዚአብሔር ሳሙኤልን ሦስተኛ ጊዜ ጠራው ተነሥቶም ወደ ኤሊ ሔደ ስለጠራኸኝ እንሆ መጣሁ አለው ኤሊም ያንን ልጅ እግዚአብሔር እንደጠራው አሰበ። ልጄ ተመልሰህ ተኛ የሚጠራህ ካለ እኔ ባርያህ እሰማለሁና ጌታዬ ተናገር በለው አለው ሳሙኤልም ሒዶ በመኝታው ተኛ። ➯እግዚአብሔርም መጥቶ እንደ መጀመሪያው በፊቱ ቁሞ ጠራው። ሳሙኤልም እኔ ባሪያህ እሰማሃለሁና ጌታዬ በል ተናገር አለው እግዚአብሔርም ሳሙኤልን የሰማው ሁሉ ሁለቱን ጆሮዎቹን ይይዝ ዘንድ እነሆ እኔ በእስራኤል ላይ የተናገርሁት ቃሌን አደርጋለሁ።  ➯በዚያችም ቀን በኤሊና በወገኑ ላይ የተናገርኹትን ሁሉ አጸናለሁ እጀምራለሁ እፈጽማለሁም። ልጆቹ የእግዚአብሔርን ቃል አቃልለዋልና እርሱም አልገሠጻቸውምና በልጆቹ ኃጢአት እኔ ወገኑን ለዘላለም እንደምበቀለው ነገርሁት። ስለዚህም ነገር በዕጣንም ቢሆን በመሥዋዕትም ቢሆን የኤሊ የወገኑ ኃጢአት እስከ ዘላለሙ ድረስ እንዳይሠረይ ራሴ እንዲህ ብዬ ማልሁ። በኤሊ ወገኖችና ልጆች ላይ እግዚአብሔር የተናገረው ሁሉ ተፈጸመ።  ➯ከዚህም በኋላ የቂስ ልጅ ሳኦልን ቀብቶ ለእስራኤል ልጆች ያነግሠው ዘንድ እግዚአብሔር ሳሙኤልን አዘዘው እንዲአነግሥላቸው ለምነዋልና። ሳኦልም የልዑልን ትእዛዝ በተላለፈ ጊዜ ዳግመኛ ለእስራኤል ንጉሥ ሊሆን የዕሴይ ልጅ ዳዊትን ይቀባው ዘንድ ይህን ነቢይ ሳሙኤልን ዳግመኛ አዘዘው። ይህም ነቢይ ሳሙኤል በሕይወት በኖረበት ዘመን ሁሉ እስራኤልን አስተዳደራቸው። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ።#ቅዱስ_ሉክያኖስ (ስንክሳር) ➯በዚህችም ዕለት ቅዱስ ሉክያኖስ ከሌሎች አራት ሰማዕታት ጋራ ሰማዕት ሆነ። ይህም ቅዱስ አስቀድሞ የጣዖት ካህን ነበረ የሰማዕታትንም መከራቸውን በእሳት ሲአቃጥሏቸውና ሕዋሳታቸውን ሲቆራርጧቸው ሲሰቅሏቸው ከእሳት ምድጃ ውስጥም ሲጥሏቸው ምንም ምን ጉዳት እንዳልደረሰባቸው በአየ ጊዜ ከዚህ ሥራ የተነሣ አደነቀ ክብር ይግባውና በጌታችን አመነ ያገለግላቸው የነበሩ ጣዖታት ከእሳት ቢጥሏቸው ፈጥነው ይቃጠላሉ እንጂ ይህን ሥራ ሊሠሩ እንደማይችሉ ተረድቷልና።  ➯ዳግመኛም እንዲህ አለ ይህን ድንቅ ሥራ የሚሠራ አምላክስ በእውነት እርሱ አምላክ ነው። ከዚህ በኋላም በንጉሥ ፊት እኔ ክርስቲያን ነኝ ክብር ይግባውና በክርስቶስ አምናለሁ ብሎ በግልጥ ጮኾ ተናገረ። ንጉሡም ወደርሱ አቅርቦ ጣዖት ማምለክን እንዳይተው መከረው ወደ አምልኮ ጣዖት ይመለስ እንደሆነ ብሎ ብዙ ቃል ኪዳኖችን ገባላት። ➯እርሱ ግን አልሰማውም ሥቃዩንም አልፈራም ከዚህም በኋላ ንጉሡ ጽኑዕ ሥቃይን ሊአሠቃየው ጀመረ ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት መንጋጋውንም በደንጊያ እንዲሰብሩት ታላቅ ግርፋትንም እንዲገርፉት አዘዘ።  ➯ከዚህ በኋላም አራት ክርስቲያን እሥረኞች ቀረቡና ከእርሱ ጋራ አቆሟቸው ንጉሡም ለአማልክት ዕጣን ዕጠኑ ይህ ካልሆነ ግን ታላቅ ሥቃይን አሠቃያችኋለሁ አላቸው። እነርሱም ለስሕተቱ አልታዘዙለትም በላያቸውም ተቆጥቶ በእሳት ምድጃ ውስጥ ጨመራቸው ያንጊዜ ዝናብ ዘነበ እሳቱንም አጠፋው።  ➯ቅዱስ ሉክዮስን ግን እንደ አምላክህ እሰቅልሃለሁ ብሎ በዕንጨት መስቀል ላይ እንዲሰቅሉት አዘዘ በረጃጅም ችንካሮችም ሥጋውን ሁሉ ቸነከሩት ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። እነዚያን አራቱን ሰዎችም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ➯ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። #ስንክሳር ሰኔ 9 ቀን https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Показать все...
                         †                           [      🕊  ፍኖተ ቅዱሳን   🕊      ] [ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  ተርእዮን [ መታየትን ] አለመውደድና ለታይታ ብሎ ምንም ነገር አለማድረግ !  ] 🕊 "  ራሱን የሚያዋርድ ከፍ ይላል .... !  " ........ አባ ዮሐንስ ሐፂር እንዲህ አለ ፦ "ብቻውን የሚኖር አንድ መንፈሳዊ ሽማግሌ ነበር፡፡ በከተማው ሕዝብ ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ ይከበር ነበር፡፡ ሌላ አረጋዊ ሊያርፍ ሲል ከዚህ ዓለም ከመውጣቱ በፊት ወደ እርሱ እንዲመጣና ዓይን ለዓይን ተያይተው ይሰናበተው ዘንድ ወደዚህ ሽማግሌ ላከበት፡፡ በዚህ ጊዜ እንዲህ ሲል አሰበ ፦ "በቀን ብሄድ ሰዎች ከእኔ በኋላ ይመጡና ብዙ ክብር እናክብርህ ይሉኛል፣ ይህ ደግሞ ሰላም አይሰጠኝም። ስለዚህ ማንም ሰው እንዳያየኝ ሌሊት በጨለማው እሄዳለሁ፡፡" ሌሊት ተነሥቶ በጨለማ ሊሄድ ሲልም ሁለት መላእክት ያበሩለት ዘንድ መብራቶችን ይዘው ከእግዚኣብሔር ዘንድ ተላኩ። መላእክት እያበሩለት ሲሄድ የከተማው ሰው በሙሉ ወጣና የዚህን አረጋዊ ክብር ተመለከተ፡፡ ከክብር ለመሸሽ አብዝቶ ባሰበ መጠን የበለጠ ከበረ "ራሱን የሚያዋርድ ከፍ ይላል" እንደ ተባለ። [ሉቃ.፲፬፥፲፩] የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡ †                       †                         † 💖                    🕊                     💖 https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.