cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ፍኖተ ሎዛ ሰ/ት/ቤት

ይህ መንፈሳዊ ገፅ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በጂማ ፈለገ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የፍኖተ - ሎዛ ሰ/ት/ቤት ህጋዊ የቴሌግራም ገጽ ነው ። ®

Больше
Рекламные посты
385
Подписчики
+124 часа
+27 дней
+3130 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ለነገ ተዘጋጁ
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንኳን ለቅድስት ሥላሴ በዓል አደረሳችሁ ! አብርሃም ይስሐቅን ለመሰዋት ወደተራራ ወስዶት ነበር። እግዚአብሔር ግን በይስሐቅ ፈንታ በግን በዕፀ ሳቤቅ አወረደለት። ያ በግ ከሦስቱ አካላት የአንዱ የወልድ ምሳሌ ነው። ለጊዜው ይስሐቅ ከሞት የዳነው በዚያ በግዕ ቤዛነት ነው። የሰው ልጅ ሁሉ ከሞት የዳነበት ሕያው በግዕ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ዕፀ ሳቤቅ የድንግል ማርያም ምሳሌ ነው። ክርስቶስ ለእኛ ቤዛ ሆኖ በመስቀል ተሰቅሎ አዳነን። "አብርሃም ወሰዶ ለይስሐቅ ወልዱ ከመ ይሡዖ። አውረደ ሎቱ ቤዛሁ በግዐ"። መልካም በዓል !
Показать все...
🙏 2🥰 1
Repost from N/a
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንኳን ለቅድስት ሥላሴ በዓል አደረሳችሁ ! አብርሃም ይስሐቅን ለመሰዋት ወደተራራ ወስዶት ነበር። እግዚአብሔር ግን በይስሐቅ ፈንታ በግን በዕፀ ሳቤቅ አወረደለት። ያ በግ ከሦስቱ አካላት የአንዱ የወልድ ምሳሌ ነው። ለጊዜው ይስሐቅ ከሞት የዳነው በዚያ በግዕ ቤዛነት ነው። የሰው ልጅ ሁሉ ከሞት የዳነበት ሕያው በግዕ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ዕፀ ሳቤቅ የድንግል ማርያም ምሳሌ ነው። ክርስቶስ ለእኛ ቤዛ ሆኖ በመስቀል ተሰቅሎ አዳነን። "አብርሃም ወሰዶ ለይስሐቅ ወልዱ ከመ ይሡዖ። አውረደ ሎቱ ቤዛሁ በግዐ"። መልካም በዓል !
Показать все...
የእውነት አክብራችሁ ፣ በረከት እናገኝበታለን ብላችሁ የመጣችሁ አምላከ ቅዱስ ገብርኤል ይቀበልላችሁ ፥ በስራም በፈተና ያልተገኛችሁ በቀጣይ በጋራ የምንሰራ ይሆናልና ተዘጋጁ 🙏
Показать все...
🙏 4🥰 3
ሰላም እንደምን አላችሁ 🙏 ነገ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ የበረከት ስራ ስላለ ሁላችንም እንገኝ ። የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን 🙏
Показать все...
🙏 3👏 1
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ ‹‹ተማሕለሉ ወሰአሉ ኃበ አቡክሙ ሰማያዊ እስመ አብ ይሁበክሙ ኵሎ ዘሰአልክሙ…አባታችሁ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋልና ወደ ሰማይ አባታችሁ ለምኑ፣ ምሕላንም አውጁ›› ኢዩኤል 1፤14 ቅዱስ ያሬድ በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን፣ምሕላን በማወጅ ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው አምላካችን አግዚአብሔር ምልጃን ማቅረብ የሚያስፈልግ መሆኑን ከሀገራችን ሊቃውንት መካከል የመጀመሪያ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ከሰማያውያን ዐውደ ማህሌት ሰምቶ በቀሰመው ጣዕመ ዜማ አበክሮ ይነግረናል፡፡ በመሆኑም ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷልና በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በሁሉም የሀገራችን ክፍልና በሌሎችም አህጉራተ ዓለም የምትገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብላችሁ የምሕላ ጸሎት እንድታደርሱ፣ በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀር እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንድትይዙ፣ ቋሚ ሲኖዶስ በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ከአደራ ጋር ያሳስባል፡፡ ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ›› ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. አዲስ አበባ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኢኦተቤ ቴቪ ገጽ አገኘነው።
Показать все...
👍 1🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንኳን አደረሰን! ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አባቶቻችን ሐዋርያትን ሰማዕትነት በተቀበሉበት ቀናት በዓላት ሰይማ ታከብራቸዋለች፡፡ እንዲሁም በስማቸው የተሰየመውን ጾም በመጾም አሠረ ፍኖታቸውን ይከተሉ ዘንድ ምእመናንን ታሳስባለች፡፡ በሐምሌ ፭ ቀን ደግሞ የደጋጎቹን ሐዋርያት የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስን በዓል ታደርጋለች፡፡ የእነዚህ ቅዱሳን አባቶቻችን በዓል መደረጉ በአንድ ቀን ሰማዕትነት በመቀበላቸው ነው፡፡ ሁለቱም ቅዱሳን ሐዋርያት በሮማው ቄሳር ኔሮን ዘመን ፷፯ ዓ.ም. ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ቁልቁል ተሰቅሎ ሰማዕትነት የተቀበለ ሲሆን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ አንገቱን ተቀልቶ ሰማዕትነትን ተቀብሏል፡፡ በረከታቸው ይደርብን፤ አሜን!
Показать все...
🙏 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
የፊታችን እሁድ ከቅዳሴ በኋላ ማረሚያ ቤት የምንሄድ ወጣት አባላት ዝርዝር
Показать все...
👍 1
ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁ ! ምህረት ቸርነቱ ከእኛ ጋር የሆነ የቅዱሳን አምላክ የኛም አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን ። እንደሚታወቀው የእግዚአብሔር አምላክ ፈቃድ ሆኖ የደብራችን የልማት ስራዎችን በጋራ ስናከናውን ቆይተናል ፣ የፊታችን ቅዳሜ ከቅዳሴ በኃላ ትልቅ የበረከት የልማት ሥራ አለና ልክ እንደዚ ቀደሙ በንቃት እንድንሳተፍ ከወዲሁ እራሳችሁን አዘጋጁ ፣ የፊታችን በታላቅ ድምቀት የምናከብረውን ክብረ በዓላችንን ያማረ ይሆን ዘንድ ይሄን የበረከት ስራ በጋራ ማጠናቀቅ ስላለብን ፣እንዲሁም እኛ የመላኩ የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች በቤቱ ለምናገለግል ለኛ ትልቅ በረከት እና ረድኤት ይዞልን ይመጣልና ተቀሳቅሰን የበረከት ስራን የምንሰራ ይሁን ። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን 🙏
Показать все...
🙏 4👍 1👏 1
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.