cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

REVEAL JESUS

We have to reveal jesus

Больше
Рекламные посты
4 615
Подписчики
+124 часа
-197 дней
+13330 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ሁለት እህቶች ከሴቴኛ አዳሪነት መዉጣት ችለዋለል ከዝህ በፊት ለማሳወቅ እንደሞከርነዉ በእግዝአብሔር ጸጋ ና በናንተ ርብርብ ከዝህ አስከፊ ህይወት ከወጡ ሳምንታትን አስቆጥርሬዋል በመልካም ሕይወት ላይ ይገኛሉ ክትትልም በቅርሬበትም እያደርግንላቸዉ እንገኛለን ለዝህ ሁሉ ክብሩን ጌታ ይዉሰድ የአገልግሎቱን ስፋት ተመልክተን በተለይም በሀዋሳ ከተማ በ ተወሰኑ ቦታዎች የነበርዉ በመንገድ ዳር የምቆሙ እህቶች ቁጥር እጅግ እየጨመር ይገኛል በተለይም ሀዋሳ ላይ አይጋ ( በርሙዳ), አሮገዉ መናሪያ ,አድሱ መናርያ , እንድሁም 05 ሰፈር ልክ ስመሽ ልክ ሰዉ ስራዉን ልሰራ እንደምወጣ ያህል በምያስፈራ ሁኔታ ለዝሁ ተግባር ተግተዉ ይቆማሉ እነሱ እንደምሉት ስራ ከተገኘ ይሰራሉ ያለበለዝያ ደግሞ እንድሁ በብርድ ዉጭ ያነጋሉ # አስቡት እንግድህ የክርስትያን ከተማ በምትባለዋ ሀዋሳ እዝችሁ በቅርብ ርቀት ቸርቾች በሞላባት እንድሁም የወንጌል አገልጋዮች በሞላንበት ከተማ ብዙ እህቶቻችንን በዝህ አስከፊ ህይወት እያጣን እንገኛለን ወዳጆቼ አላየንም ማለት እየሆነ አይደለም ማለት አይደለም አይተንም ባለየ አለፊን ማለት ይቆማል ማለት አደለም በጥቅቱም ከነሱ ጋር ባሳለፈኩት እንድሁም ባጠናሁት መሰርት እኛ ለነሱ እንዳለን አመለካከት አይደለም ሕይወታቸዉ በብዙ አይነት መንገ መንገድ ወደዝህ ህይወት ይገባሉ ከገብም በኋላ ለመቆቆም ሱስ የጠቀማሉ ለጥቅት ቀን ችግር ብለዉ የገብበት ሕይወት ጠላት ምክንያት እየፈለገ ያዘልቃቸዋል በርግጥም ተመችቶቸዉ እዝህ ለቅጦት የምሰሩ እህቶች ከመቶ እህቶች አንድ ብቻ ነዉ የምትሆነዉ ስለ ነሱ በሰፊዉ ሌላ ጊዜ የምናቀርብ ስሆን እዝህ ስራ ላይ ከስዳማ አካባቢ እንደ ባህል ነዉረም አንደ ክርስትናም አስጸያፊ የምወሰደዉ ይህ ተግባር በአሁኑ ሰአት በብዛት የምታዩት ሀዋሳ ላይ ለማየት እንደሞከርኩት ከፈተኛዉን ስፊራ ይዘዉ ይገኛሉ ስንጠይቃቸዉም የምመልሱልን መልስ ስራ ማጣት የአሁኑ የኑሮ ሁኔታ የመሳሰሉ ምክንያቶችም ያነሱልናል ምንም ግን ቢፈጠር እንደ ገንዘብ ማግኛ አማራጭ ልወሰድ በጭራሽ የለበትም ብዬ አምናለሁ ለዝሁ ደግሞ ቤተክርስቲያንም መንግስትም ነገ ዛሬ ሳንል ይሄን ነገ ቤተክርስትያንንም ሀገርንም ምርከብ ትዉልድ ማዳን ይጠበቅብናል እላለሁ እንደ reveal jesus እኛ በተቻለን መጠን በነዝህ ሴቴኛ አዳሪዎች ላይ በመስራት ላይ ስሆን ለነሱ ወንጌል ነግሮ መሸኘት ደግሞም ገንዘብ ሰቶ መተዉ የተሟላ ለውጥን ስለማያመጣ እንሱን የምንርዳበት ማዕከል አስፈልጎናለል ና ሁላችንም እንርባርብ እንላለን እርዳታችሁ ያሻናል call us , 0980404779 " አንተም ደግሞ በሥራዬ አብረህ የተጠመድህ እውነተኛ ሆይ፥ እንድታግዛቸው እለምንሃለሁ፤ " (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:3) ተባርኩ @revealjesus
Показать все...
❤‍🔥 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
እግዚአብሔር ባሪያዬን እዮብን አይተሃል አለ እዮብ እግዚአብሔርን ያመነ እግዚአብሔርም በእዮብ የተማመነ ነበር እዮብ ወደ እግዚአብሔር ለምን ተውከኝ እያለ ከፈተናው የተነሳ ይፀልያል እንጂ እግዚአብሔርን በምንም አይቀይርም እግዚአብሔርም ከነፍሱ ውጪ እንደፈለገ እንዲያደርገው አሳልፎ ቢሰጠውም እዮብ እንደማይክደው ያውቅ ነበር
እግዚአብሔር ይታመንብን❕❗
" እግዚአብሔርም ሰይጣንን። በውኑ ባሪያዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም አለው። " (መጽሐፈ ኢዮብ 1:8) @MARKENGETA
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
“The Gospel is the only gun which brings a dead man back to life when shot.” - Reinhard Bonnke @revealjesus
Показать все...
❤‍🔥 1
🐬 ሰላም  እህቶቼ እንደምን አላቹ? እስኪ ካደመጥኳቸው ተረቶች ውስጥ እጅግ የሚገርመኝን የአንድ ዓሣ አጥማጅ ታሪክ ልንገራቹ።፡ ይህ ዓሣ አጥማጅ ገና ሳይነጋ በጠዋቱ ወደ ባህር ዳርቻ ሄደ ነገር ግን ይህ ሰው የደረሰበት ሰዓት ጨለማ ነበር በወቅቱም ለሥራው ስላልተመቸው እስኪነጋ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ጀመረ ከባህር ዳርቻውም አጠገብ በድንጋይ ጠጠሮች የተሞላ ጆንያ አጋጠመው፡፡ ዓሣ አጥማጁም ከጆንያው ውስጥ ያለውን አንድ ጠጠር አውጥቶ ወደባህሩ ሲወረውረው እንቦጭ የሚል ድምፅ ሰማ፡፡ ይህም ድምፅ ስላስደሰተው ወድያውኑ ሌሎች ጠጠሮችን በየተራ እየወረወረ እንቦጭ እንቦጭ እያደረገ እየተደሰተ መወርወሩን ቀጠለ... ይህ ዓሣ አጥማጅ በጆንያ ውስጥ የነበሩትን ጠጠሮች ወርውሮ አንዲት ጠጠር ብቻ በቀረው ሰዓት የብርሃን ወገግታ መምጣቱን አስተዋለ፡፡ አጥማጁም የያዘውን ጠጠር ለመወርወር ከመቀመጫው ብድግ ሲል በእጁ የያዘውን ጠጠር በደንብ አገላብጦ ተመለከተ በድንጋጤም ሲያስተውለው ጠጠር ሳይሆን አልማዝ መሆኑን ተረዳ፡፡💎 ዓሣ አጥማጁም በንዴት ሲቃ ተናነቀው ምከንያቱም እስኪነጋ ድረስ ሲወረውር የነበረው በጆንያ ሙሉ ጠጠር ሳይሆን አልማዝ መሆኑን አስተዋለ፡፡ ብዙ ሰዎች በህይወታቸው እንዲሁ ናቸው፡፡ በእጃቸው ያለው ጊዜ አልማዝ መሆኑን ሳይረዱ እንቦጭ እንቦጭ የሚል ድምጽ ለመሰማት ሲሉ ጊዜያቸውን በእንቅልፍ፣ በምንም፣ በፊልም፣ በማህበራዊ ድህረ-ገጽ፣ በወሬ፣ በጥል፣ በክርክር እና በብስጭት ወደ ማይመልሰው ባህር ይወረውሩታል ጥቂቶች እንደ ዓሣ አጥማጁ በመጨረሻ ሰዓት ጊዜያቸው አልማዝ እንደሆነ ሲረዱ አብዛኞቹ ግን ጊዜ ምንም እንዳልሆነ ሳያውቁ በዚያው ያበቃል፡፡ የሰው ልጅ በምድር ላይ የተሰጠው ጊዜ ውስን መሆኑ ለማንም ግልፅ ነው፡፡ ይህንንም ውስን ጊዜ በወቅቱና በሰዓቱ ካልተጠቀመበት እድሉ ላይመለስ ይወሰድበታል፡፡ ማንም ምንም ቢለፋ ቢያለቅስ ቢፀፀት ተመልሶ አያገኘውም፡፡ ይልቁንም በጊዜው የዘራውን መልካም ይሁን ክፉ በጊዜው ያጭዳል፡፡ ስለዚህ ማድረግ  የሚገባሽን ነገር ሁሉ በጊዜው አድርጊ።😊                         @revealjesus                
Показать все...
🤔 1
አመለካከቴን የቀየረው ክስተት አንድ እሁድ ጠዋት እንደተለመደው ወደ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ጌታን ለማምለክ ሄድኩኝ ፤ ያው ሁላቹም እንደምታውቁት የቃል ጊዜ ሲደርስ የእግዚአብሔር  ቃል ይሰበካል በእዛም ቀን አንዲት አገልጋይ ወደ መድረኩ ወጥታ ጌታን ፀንቶ ስለመጠበቅ መስበክ ጀመረች፤ በጊዜው መድረኩ ላይ ምን የሚታይ መስቀል አልነበር   እኔ ግን ድንገት አይኖቼ ተከፍተው ቃል እየሰበከች ካለችው ሴት ጀርባ ኢየሱስን መስቀል ላይ ተሰቅሎ አየሁት በሰዓቱ በጣም ስለደነገጥኩ  ጎንበስ አልኩኝ በድጋሚም ነገሩ እውነት ስላልመሰለኝ ቀና ለማለት ሞከርኩ ነገር ግን አሁንም ያ ያየሁት ኢየሱስ መስቀል ላይ ተንጠልጥሎ ፊቱ ከበፊቱ ይልቅ ጎልቶ አየሁእኔ  ምንም እንቅስቃሴ ላለማድረግና ድምፅ ላለማሰማት  አንደምንም ብዬ ራሴን ተቆጣጠርኩት ከዛም አንዲ የሚል ድምፅ ሰማሁ.... " በመስቀሉ ስራ ነው እንዲህ የተሰባሰባቹት " የሚል ድምፅ ሰማው 😭  ከዛም ቀን በኃል ስለ ቤተ ክርስቲያን ያለኝ አመለካከት በሙሉ ተቀየር ለካስ ልማድ ስለሆነብን አይደለም  ቸርች የምሄደው የእውነት ለካስ የመስቀሉ ስራ ነው ከዚም ከዛም አሰባስቦን አንድ ላይ ንጉሱን እንድናመልክ ያደረገን.... ወዳጆቼ  በዚያ ቀን የሚያገለግሉን አገልጋዮች ምንም ሊሆኑ ይችላሉ የምናመልክበትም ቤት ብዙ ምቾት ላይሰጠን ይችላል ነገር ግን በእዛ ስፍራ ዋጋ ከፍሎ ያዳነን ጌታ ይገኛል ቸርች ለመሄድ ደግሞ ከዚህ በላይ ምክንያት አያስፈልግንም ኢየሱስ መኖሩ ብቻ በቂ ነው... ቸርች የሰዎች መሰብሰቢያ ስፍራ ብቻ ሳይሆን የሰማይ መላእክት ማምለኪያም ስፍራ ጭምር  ነውየመሰባሰባችን ዋና ርዕስ ደግሞ የታረደው በግ ነው ይህን እውነት ነው ልንረዳው የሚገባን። Adonai 🔥@revealjesus🔥
Показать все...
❤‍🔥 3
ቲቪያቹን 📺  አስተካክሉት Frequency :  ፀሎት Symbol Rate : የእግዚአብሔር ቃል Polarization : ጉልበቶቻቹን በ 90 ዲግሪ በኩል ብታንበረክኩት ታገኙታላቹ ቆይ ግን የምር የቤታቹ Tv ምስል አጥፍቶ ድምፅ ቢያቆራርጥባቹ ቁጭ ብሎ ለማየት ትዕግስት ይኖራቿል ? በእርግጠኝነት ሁላቹም ተነስታቹ ለማስተካከል ትሞክራላቹ ታዲያ በመንፈሳዊ አለምም እኮ ይሄ ብልሽት አለ... አሁን ለምን ተነስታቹ  ህልማቹን... ራዕያቹን... ከጌታ ጋር ያላቹን ህብረት ለምን አታስተካክሉትም፤ ከጌታ የሆነን ህልም አለማለምን ራዕይ አለማየት የጌታን ድምፅ አለመስማትማ Normal አታድርጉት አሁን ተነሱና ምርኳቹን አስመልሱ Jehovah 🔥@revealjesua
Показать все...
❤‍🔥 4👍 1
ንቀነው እንጂ ንቆን የተለየነው የዓለም ደስታም ክብርም የለንም! 👏
Показать все...
👍 2❤‍🔥 1🥰 1
እንግዲህ በእኛ ውስጥ እንደሚሠራው እንደ ኀይሉ መጠን፣ ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ በላይ እጅግ አብልጦ ማድረግ ለሚቻለው፣ በቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በክርስቶስ ኢየሱስ፣ በዘመናት ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ክብር ይሁን፤ አሜን። ኤፌሶን 3:20-21 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙት የእግዚአብሔር ስሞች ሁሉ፣ ይህንን እወደዋለሁ፦ "እጅግ አብልጦ ማድረግ ለሚቻለው... ለእርሱ" ቀይ ባህርን የከፈለው እና 5000 ሰዎችን በአምስት እንጀራ የመገበው እግዚአብሔር የእኛም እግዚአብሔር ነው። ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ በላይ ሊያደርግልን ይፈልጋል! ሆኖም ጥልቀት በሌለው ጸሎቶቻችን እና በደካማ ሕልሞቻችን እንዲሠራ ዕድል አልሰጠነውም። ለእግዚአብሔር ስንል ትልልቅ ሕልሞችን እናልም። ከዚያም ከምናስበው በላይ ሲያደርግ እንመልከተው። @revealJesus
Показать все...
1
01:35
Видео недоступноПоказать в Telegram
ሰላም ለእናንተ ይሁን አስቸኳይ መልዕክት ይዘን መጥተናል ደቡብ ኦሞ ከሐምሌ 5_15/2016 የወንጌል ዘመቻ ጂንካ እና ደቡብ ኦሞ መዘጋጀቱ ይታወቃል። ገንዘቡ የሚገባው ንግድ ባንክ በ3 ሰው አዋሽ በሁለት ሰው ተደርጎ የሚንቀሳቀስ ነው። CBE 1000 590 723 618 Tseganeh D.$ MIhiret E.$Genene G. Awash bank 013201330525200 Tseganeh D & tesfaye G screenshot ከታች ባሉ ስልክ ይላኩ 0911807101 0916623103 +251943196205 ኢትዮጵያን ለኢየሱስ  channel @e4jsong  https://t.me/e4jsong Group. @e4jesus https://www.facebook.com/e4j.ethiopea?mibextid=ZbWKwL    ኢትዮጵያን ለኢየሱስ (E4J)
Показать все...
IMG_1670.MOV18.87 MB
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.