cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ስነፅሁፍ በወንጌል - Gospel Literature

◉ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች በዚህ ቻናል ላይ ፦ ➫ #አጭር_እና_ረጅም_ልብወለዶች ➫ #መንፈሳዊ_ተውኔት ➫ #መንፈሳዊ_ትረካዎች ➫ #መንፈሳዊ_ፅሁፎች ➫ #መንፈሳዊ_መነባነቦች ➫ #መንፈሳዊ_ድርሰቶች_ያገኛሉ። ለአስተያየት ጥያቄ 👉 @wunu_pa አጋር ቻናል 👉 @zema_sink 👉 @wunuye_picture Since Thursday 11-9-2014-

Больше
Рекламные посты
10 295
Подписчики
+3424 часа
+1287 дней
+67130 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

እውነተኛ የክርስቲያኖች ቻናል እነዝህ ብቻ ናቸው እናንተም ተቀላቀሉ
Показать все...
1
🇪🇹 JOIN 🇪🇹
ሰላም ቅዱሳን በTELEGRAM ቻናል ተወዳጅ የሆኑትን በደረጃ አስቀምጠናል እናንተም JOIN በማለት በተሰብ ይሆኑ 🙏 ለማስታወቅያ ስራ👉@skat_kal
Показать все...
YIKIRTYE
YE MEZMUR MAIKEL
KINE TUBE
MEZMUR CLUB
MERCY IN BERUA
SINETSUF BE WANGEL
WUNU PICTURE
JOIN US
.        🤔ጥያቄዬ🤔 📘ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ📘           #ክፍል30 ......መሞከር ጀመርኩ  በጭራሽ ስልኩ አይሰራም እንዳፈጠጥኩ ነጋልኝ ስልኩ አሁንም ዝግ ነው ወዲያው አማን ደወለልኝ አሙ ስልኩ ለሊቱን ሙሉ ዝግ ነው አሁንም እንደዚያው አልኩት ሰላምታም ሳልሰጠው አትጨናነቂ እፁ ምንም አይሆንም እኔ እቤት እሄድና ደውልልሻለሁ አለኝ የእርሱን ስልክ እየጠበኩ እዛው እንቅልፍ ወሰደኝ ። የተኛሁበት ክፍል በር ተከፈተ ተዐምር አትረብሺኝ ለሊቱን አልተኛሁም አልኩኝ በደከመ ድምፅ ምላሽ አልሰጠችኝም የእግሯ ኮቴ ቀረበኝ አጠገቤ ስትቆም ምን ፈልገሽ ነው ብዬ ብርድ ልብሱን ከፊቴ ላይ ሳነሳው ማሂ ነበረች በየሱስም አንቺ ምን ትሰሪያለሽ አልኩኝ አፍሽን ዝጊ ብላ አፈጠጠች የያዘችውን ትልቅ ሹል ቢለዋ እያሳየችኝ ። ማሂ ምን እያደረግሽ ነው እኔ እኮ ጓደኛሽ ነኝ አልኳት ከት ብላ ስቃ ጓደኛ እኮ አንቺ የኔ ጓደኛ የማይሆነውን ህይወቴን እንዳመሰቃቀልሽው ለዘላለሙ ናኦድን ወደማታዪበት አሰናብትሻለሁ ብላ ቢለዋውን ወደ ላይ አነሳችው ና ወደ ሆዴ ቁልቁል ሰደደችው ማሂ ብዬ ጮኹኩ ምንድነው በኢየሱስ ስም ተዐምርና ማሚ ነበሩ ምን አይተሽ ነው ። በርግጌ ስነሳ ምንም ነገር የለም ምን አይተሽ ነው አሉኝ ሰውነቴ በላብ ተጠምቋል እንጃ ማሚ ቅዠት አይሉት ህልም ብቻ መጥፎ ነገር ነው ያየሁት ናዲ ትናንት ከሸኘኝ ጀምሮ ስልኩ አይሰራም አማንም ደውላለሁ ብሎ ዝም አለ ብዬ በፍጥነት ፒጃማዬንም ሳልቀይር ክፍት ጫማ እንዳደረኩ ወደ እነ ናዲ ቤት  ሄድኩ የጊቢው በር  እስኪከፈት ነብሴ ተጨነቀች በሀይል ነበር የምደበድበው ታናሽ እህቱ በፍጥነት መጥታ ከፈተችልኝ እርሷም ከውጪ በጉጉት ምትጠብቀው ነገር አለ መሠል እኔ መሆኔን ስታይ ኤጭ ብላ ወደ ኋላ ተመለሰች ተከትለዋት ሙሉ ቤተሰቡና አማንም በረንዳውን ሞልተውት ነበር ። ናዲስ አልኩኝ ሁሉም አፍጠውብኛል ዝም አሉ ንገሩኝ እንጂ ናዲስ አልኩኝ አሁንም ዝም አማን ናዲስ ብዬ ጮኹኩኝ እናትየው አንቺን እንጠይቅሽ እንጂ ትናንት አንቺን ሊያገኝ ወጣ ከተባለበት መቼ ተመለሶ አሉኝ እንባ ባደከመው ድምፅ አማን ናዲ እዚህ የለም አልኩኝ አቅሜ ሲከዳኝ ይታወቀኛል እንባዎቼ እየረገፉ አዎን በለኝ ወይም ናዲን አሳየኝ አልኩት እፁ ተረጋጊ ነይ እስቲ ወደዚህ አረፍ በይ አለኝ ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ እያኋቸው ሰዎቹ ብዥዥዥ ይሉብኝ ጀመር ። ከዚያ ራሴን ያገኘሁት የፈረደበት ሆስፒታል ነበር አጠገቤ ተዐምር ነበረች ግሉኮሱን ልነቅለው ስል ነርሶቹን ጠራቻቸው መሠለኝ ትንሽ ነው ይሄ ብቻ ይለቅ ብለው ከለከሉኝ ሆስፒታሉን በአንድ እግር አቆምኩት  ለእኔ አይታወቀኝም የናዲ ነገር ብቻ ነው የሚያሳስበኝ ለ4ሆነው ከአቅማቸው በላይ ስሆን መርፌ አምጥተው ወጉኝ በድጋሚ ስነቃ ጎረቤቶቻችን ነበሩ ግሉኮሱ ተነቅሎ ነበረ በፍጥነት ብድግ አልኩ ትንሽ እንደማዞር ሲያደርገኝ  አልጋው ላይ ቁጭ አልኩና ራሴን አረጋግቼ ተነስቼ ወጣሁ እፁ ተረጋጊ የት ነው የምትሄጂው አሁንም ትወድቂያለሽ እያለች ተዐምር ትከተለኛለች  እርምጃዬ ከአልጋ የተነሳ ሰው አልመስልም እልህ ና ንዴቴ ህመሜን አስረሱኝ ተዐምር አልቆም ስላት ከፊት ለፊቴ በሩጫ አልፋኝ ቆመች ዞር በይልኝ ብዬ ገፈተርኳት አሁንም ትከተለኝ ጀመር ጎረቤቶቻችን ለማሚ ደወሉላት መሠለኝ ደወለች ስልኬ ተዐምር ጋር ነበር ይኸው ማሚ ሰማችልሽ መሠለኝ እፁብ ቁሚ እያለከለከች ትለምነኛለች የሆስፒታሉ ርዝመት ከሀገር ሀገር ስደት ጉዞ መሠለኝ እንደወጣን ታክሲ ውስጥ ገባሁና ብር እንደያዘ ሰው ወደነ ማሂ ሱፐርማርኬት  እንዲነዳው ነገርኩትና ሄድን ተዐምር ብር ይዛ ነበር እንደወረድኩ ወደ ሱፐር ማርኬቱ በቀጥታ ገባሁ ተቀምጣ ስልኳ ላይ አፍጣ ነበር ብቻ በሁለት እጄ እንቅ አደረኳት ናዲን የት አደረስሽው አንቺ ክፉ የእስከዛሬው አንሶሽ ትንፋሽ አትሯት እንዴት ትተንፈስ የሱፐር ማርኬቱ ሰራተኞች እንደምንም አስለቀቁኝ ጥበቃ ኸረ የህግ ያለ እያለ አንዱ ሲንጣጣ ተው ብላ በእጇ ምልክት አሳየችው  እያሳለች መናገር ፈልጋለች ግን ደም ስሯ ተገታትሯል ከሞት አፋፍ ሳትመለስ አልቀረችም ። ተዐምር አንቺ እፁ አብደሻል እንዴ ሌላው ቢቀር ክርስትናሽን ረሳሽው አለችኝ ገላመጥኳት ና አንቺ ሰይጣን ናዲ የት ነው ያለው አልኩኝ መከረኛ እንባዬ እየረገፈ....... ............ይቀጥላል ........... @Gospel_literature @Gospel_literature ✍written by Aksan Adane
Показать все...
😱 14👍 7😭 1
ሰላም ቅዱሳን በTELEGRAM ቻናል ተወዳጅ የሆኑትን በደረጃ አስቀምጠናል እናንተም JOIN በማለት በተሰብ ይሆኑ 🙏 ለማስታወቅያ ስራ👉@skat_kal
Показать все...
👍 2
YIKIRTYE
YE MEZMUR MAIKEL
KINE TUBE
MEZMUR CLUB
MERCY IN BERUA
SINETSUF BE WANGEL
WUNU PICTURE
JOIN US
የዛሬው አጠር ስላለ 2 ክፍል ፖስቻለው enjoy it😊
Показать все...
🥰 30👏 10👍 8 5
.      🤔ጥያቄዬ🤔 📘ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ📘          #ክፍል_29 ........ድንግጥ ብሎ ቀረ ። ወዲያው ለማስቀየስ ማለት አለኝ ናዲ ብቻህን ለመጨነቅ እየሞከርክ ነው እኔ እድሌ ጠማማ ነው ባክህ ስንት ነገር አለፈ በቃ እፎይ ብዬ ሳላበቃ ሌላ ጣጣ ትናንት እህትህና እናትህ ሲጨቃጨቁ ሰምቼአቸዋለሁ አልኩትና በረጅሙ ተነፈስኩ በጣም ደነገጠ ፊቱ ልውጥውጥ አለ ምን እንደሚለኝ እንኳን ያጣ መሠለኝ ከእነርሱ ሀሳብ በላይ የእኔ መስማት አስጨነቀው ። አንዴ አፉን ይይዛል አንዴ ጭንቅላቱን ይይዛል ጭንቅንቅ ሲል  አሳዘነኝ ናዲ የኔ መስማት ከሆነ ያስጨነቀህ እሱ አያሳስብህ ። ከቤተሰቦችህ ጋር በእኔ ምክኒያት ባትጋጭ ደስ ይለኝ ነበር ግን ምን ማድረግ ይቻላል የኔ መዘዝ ሁሌም ላንተ እንደተረፈ ነው አልኩት ። ብስጭት ብሎ በሚያስፈራ አስተያየት አየኝ እኔና አንቺ መሀል የኔ ያንቺ ሚባል ነገር አለ እንደሱ እንዴት ታስቢያለሽ ደግሞ  እግዚአብሔርን አምነዋለሁ ቤተክርስቲያን እንኳን ምታውቀውን አይደለም ቤተ ክርስቲያን ራሱ ጌታ የሚያውቀውን የኔ ቤተሰቦች ቢሆኑ ብሩክ ቢሆን ማሂ ብትሆን ልፉ ሲላቸው ነው እድሌ ምናምን እያልሽ ይብሱን አታበሳጪኝ እግዚአብሔር ለእኔና ለአንቺ ስንት ነገር አላደረገልንም እንኳን ይህቺን ልጁን ሰጥቶን የለ ምን አስጨነቀሽ ለእርሱ እንተውለታለን በራሱ መንገድ ያሰማምረዋል አለኝ ተፅናናው ደግሞ አባቢ ራሱ እንዴት የተባረከች አስተዋይ ልጅ ነች ሲልሽ ነበር በጣም ነበር ደስ ያለኝ ማሚ መጥታ ደስታዬን አቀዘቀዘችው እንጂ ሁሉንም  ለምን እንዳደረገ ራሱ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ዝም ማለት ነው እሺ እፁዬ አለኝ ። አብረን እያለን ቴክስት ደረሰው መሠለኝ ይህቺ ልጅ ወሬ ከየት ነው ምታመጣው ጌታ ሆይ አለ የእኔም ስልክ የአዲስ የመልዕክት ድምፅ አሰማኝ ። ሳየው ብሩክ ነበር ስሚ አማች ይሆኑኛል ያልሻቸው ሰዎች አይኗን ላፈር አሉ ተባለ እና ምን ይሻልሻል መቼም ናኦድሽ በአንድ እናቱ እንደማይደራደር የታወቀ ነው ስሰማ እኔን ይመርጣል ብለሽ እንዳትሳሳቺ ይላል ። ይሄ ሰይጣን ብዬ ስልኩን ጠረጴዛው  ላይ ስወረውረው ምንድነው አለኝና ስልኩን አንስቶ አነበበው እኔም የእርሱን ስቀበለው ማሂ ነበረች ቤተሰቦችህ ያቺን መዘዘኛ ለቤቱ ክብር አትመጥንም አሉአ ገና ምን አይተህ የእኔ ግፍ 😂😂  ይላል እነዚህ አጋንኝቶች ምን አድርጉ ነው የሚሉን አሁንስ አበዙት ቆይ ባልሰራላቸው እንስሶች አልኩኝ ሳግና ንዴት እየተናነቀኝ እንዴ እፁ ስሜታዊ እየሆንሽ ነው የኔ እናት እንዴት ብትናደጂ ነው ከአንደበትሽ ክፉ ወጥቶ የማያውቅ መፅሀፍ ለሰነፍ እንደ ስንፍናው አትመልስለት ነው የሚለው እነርሱም የዘሩትን በሚያጭዱበት ጊዜ እኛም የዘራነውን መልካም እናጭዳለን እናቴ አትናደጂ በቃ ንቀሽ ተያቸው ስናወራ ስናወራ ሰአቱ ነጎደ እረ መሸ እኮ ተነሺ ብሎ እስከ እቤት አድርሶኝ ተመለሰ ። ከነማሚ ጋር ተጨዋውተን የተዐምርን ቡና ጠጥቼ ወደ ጓዳ ገባሁና አምላኬን አውርቼው ነገሬን አደራ ሰጥቼው መፅሀፍ ቅዱሴን አነሳሁ አንብቤ ስጨርስ ናዲ ሌላ ቀን በግዜ ነው የሚደውልልኝ ስደውልለት ስልኩ አይሰራም ለፀሎት ዘግቶት ነው የሚሆነው ብዬ ከአንድ ሰአት በኋላ ደወልኩለት አይሰራም ጌታ ሆይ ፍርሃት ፍርሃት አለኝ ለአማን ደወልኩና ከተኛበት ተነስቶ በደከመ ድምፅ አወራኝ አትጨናነቂ እኔ እደውልለታለሁ አለኝ ጠበኩ 30ደቂቃ አልደወለም አገኘኸው ብዬ ቴክስት አደረኩለት እፁ ይቅርታ ያልደወልኩት አስጨንቅሻለው ብዬ ነው ጠዋት እንሞክርለታለን ያው እሱ ረጅም ሰአት አይደል የሚፀልየው የተለመደ ነው ተኚና ጠዋት እንደውላለን አለኝ ። እኔ በየት በኩል እንቅልፍ ይውሰደኝ ደጋግሜ መሞከር ጀመርኩ...... ..........ይቀጥላል ........ @Gospel_literature @Gospel_literature ✍written by Aksan Adane
Показать все...
👍 15🔥 2🥰 2😱 2
.     🤔ጥያቄዬ🤔 📘ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ📘          #ክፍል_28 .... ሸኙኝ ማሚና ተዐምር ከሱቅ አልገቡም ነበር መሄጃ የለኝ ጌታዬ ላይ ተነፋረኩኛ ጌታ ሆይ በእኔ ምክኒያት ይሄ ቤተሰብ ሰላም ማጣት የለበትም ናዲን ከተናገሩት በጣም ይጣላቸዋል እርግጠኛ ነኝ ከቤተሰቡ እንዲቂያቂያም አልፈልግም ያውም በእኔ ምክንያት ። መንፈስ ቅዱስ ከፋኝ አልኩት የተሰማኝን እየለፈለፍኩ ልክ ስሞታ እንደሚናገር ህፃን እርሱም ደግሞ አፅናናኝ ጭንቀቱን ረሳሁና ራሱን አየሁት ከቆይታ በኋላ ለናዲ ደወልኩለት አያነሳም በቃ ለጌታ ሰጥቼ ተኛሁ ከረጅም ደቂቃዎች በኋላ ደወለልኝ ። እፁዬ ይቅርታ የሆነ ጉዳይ ይዤ ነበር አለኝ በቃ ሲጨቀጭቁት ነበረ ብዬ ገባኝ ድምፁ ተረብሾ እንደሆነ ያሳብቃል ምን እንደሆነ መጠየቅ ሁሉ አስጠላኝ ገብቶኝ ለምን እንዳልገባው ሆናለሁ ብዙም አላወራንም ስልኩ ተዘጋ ። ማሚ  እንደመጣች ፊቴን ነው የምታየው ግንባሬን ነው የምትስመው ምንድነው ፊትሽ ምን ተፈጠረ አለችኝ እንደገና ተነፋረኩባታ ብዙ መከረችኝ አትፍሪ ጌታ ከእናንተ ጋር ከሆነ አይደለም ቤተሰቡ ሙሉ የአለም ህዝብ ቢያድምባቹ ምንም አይፈጠርም ለበጎ ነው የኔ ቆንጆ ልጅ አለችኝ ። በጠዋቱ ተነስቼ እቤት መስራት ያለብኝን ሁሉ ሰራሁና ናዲን አገኘሁት በጣም ተረብሾ ተጨናንቋል ምን እንደሆነ ብጠይቀው አልጋገር አለ ነው በድብብቆሽ  ነው ቸምንቀጥለው ስለው ትንሽ ከቤት ተጋጭቼ ነው አለኝ በምን አልኩት ሊያለቅስ ደረሰ አንቺ አታውቂውም የቤተሰብ ጉዳይ ነው አለኝ እየከፋው በእኔ ምክንያት ነዋ አልኩት ድንግጥ ብሎ ቀረ...... ...........ይቀጥላል ........ @Gospel_literature @Gospel_literature ✍written by Aksan Adane
Показать все...
👍 18
.        🤔ጥያቄዬ🤔 📘ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ📘           #ክፍል_27 እሁድ እቤታቸው ተጋብዣለሁ  ቀናቶች አልሄድ ብለውኝ ስጓጓ ከርሜ አይደርስ የለ ቀኑ ደረሰና ያስደስታቸዋል ብዬ ያሰብኩትን አለባበስ ለብሼ ሄድኩኝ ናዲና አማን ነበር ይዘውኝ የሄዱት እቤታቸው ተውቧል እነርሱ አምረውና ደምቀው ነበር የጠበቁን የምግቡ ና የቡናው መዐዛ ቤቱን ድግስ ቤት ድግስ ቤት አሰኝቶታል እነዚህ ሰዎች በዚሁ ሊያስቀሩኝ አስበው ነው እንዴ ናዲ አልኩት ፈገግ አለና እኔም አልገባኝም እስቲ እንጠይቃቸዋለን አለኝ ሁሉንም በየተራ ሰላም አልኩ ሁለት እህትና ሶስት ወንድም አሉት አንዷ ታላቁ ስትሆን አንዷ ታናሹ ነች አንዱ ታላቁ ሲሆን ሁለቱ ታናናሾቹ ናቸው ። አባትየው ፈገግታቸው በቂ ነው እንደ በረዶ የነጣው ፀጉራቸው ና ፂማቸው ልዩ ውበትን ችሮአቸዋል አባትህ ደስ ሲሉ እኮ ውበታቸው ከፊት ይልቅ ጨምሯል እውይ ፀጉራቸው ገፅታቸው ሲያምር አልኩት እኔም በእርሱ እኮ ነው የወጣሁት አለኝ ጉረኛ የሳቸውን ያክል እንኳን አታምርም አልኩት አማን ቀስ ብሎ እናንተ ምን ትንሾካሾካላችሁ በጋራ ከቤተሰቡ ጋር አታወሩም እንዴ አለን ፋዘርን ካየኋቸው ቆየሁ ለዛ እኮ ነው አልኩት ። ለዛ ያለው ጨዋታ እየተጨዋወትን ቆየን ናዲማ የማላውቀው ናዲ ጨዋ ሆኖ አረፈው በጣም ነው የሚያከብራቸው ከጌታ ቀጥሎ  ለቤተሰቡ ባለው ክብር አይደራደርም ። ሴቶቹ  እየተንጎዳጎዱ ያስተናግዱናል  ። እናትየው በየመሀሉ እየተነሱ ይመለሳሉ ምን ጎደለ ብሉ ጠጡ ይሉናል ። መፀዳጃ ቤት መሄድ ፈለኩ ና አንዷን እህቱን ስጠይቅ ወደ ውስጥ እለፊ አለችኝ ። በግምት እየሄድኩ ጆሮዬ ውስጥ ሚሰቀጥጥ ወሬ ዘለቀ እርምጃዬን ገታ አድርጌ ቆምኩ አሁን የኔ ልጅ ሴት አጥቶ ነው እናቱ ነበሩ እማዬ ዝም በይ በጥልቀት ስለማታውቂያት ሴት እንዴት እንዲ ታወሪያለሽ ። አፍሽን ዝጊ ገና በ12ኛ ክፍል አልነበር እንዴ ልታገባ የነበረው የአሜሪካ ዳይስፖራ አስጠልቶት የተዋትን የኔ ልጅ በምን እዳው ነው? ገና ያለ እድሜዋ አይደል እንዴ መቅበጥ የጀመረችው እኔ  ስንት ነገር ቸርች ውስጥስ እንደተወራ አታውቂም እኔ በህይወት እያለው ልጄ እሷን አያገባም እንዴት እስከዛሬ አትነግሩኝም ወይኔ ዘውዲቱ እናትና ልጅ ይጨቃጨቃሉ እዛው አዙሮ ሊጥለኝ መከረኛ እንባዬ እርግፍ እርግፍ አለ  ከኋላዬ የእግር ኮቴ ሲሰማኝ ቶሎ እንባዬን ጠራረኩና ወደ ኋላ ተመለስኩ እፁዬ ግቢ አለችኝ ታናሹ ሊዲያ ነበረች ተመልሼ ተቀመጥኩ ። የሚያወሩትን ሁሉ አልሰማም ድንዝዝ ብዬ እነዚያን ቃላቶች በድግግሞሽ ያቃጭሉብኝ ጀመር አይደል እንዴ የኔ ልጅ አሉ አባቱ ህህህ ብዬ ከሄድኩበት የሀሳብ ማዕበል ተመለስኩ ልክ አይደለሁ ወይ አሉኝ ኸረ ልክ ኖት አልኩኝ ምን እንዳሉም ሳልሰማ እናትየው ተመልሰው መጥተው ተቀመጡ ሳያቸው አልቅሽ አልቅሽ አለኝ ሰው እንዴት በቀድሞ ማንነቱ ይለካል  ለነገሩ ጥሩ ስራ መልካም ነገር በህይወቴ ሆኖ ቢያልፍ ማንም አያስታውሰውም ነበር ሳልፈልገው በህይወቴ ለተፈጠረ ያውም እኔን ጎድቶ እኔን ሰብሮ ላለፈ ጉዳይ በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ ያሰቃቸኛል ። ምን ሆነሻል ልክ አይደለሽም አለኝ ናዲ ደህና ነኝ አልኩ ሊወርድ ጥቂት የቀረውን ዕንባ ዋጥ ለማድረግ ከውስጤ ጋር ትንቅንቅ ገጥሜ ኸረ እፁብ አትዋረጂ ዋጪው ዋጪው ራሴን አበረታው ዘንድ ሞከርኩ  እንዴ አመመሽ እንዴ አለኝ ኸረ በጭራሽ ዝም ብዬ ነው አልኩት ። ወጥተሽ ጥፊ ጥፊ አሰኘኝ መከረኛዋ እናቴ እቅፍ ውስጥ መሆን አጓጓኝ ከመች መች ደረሰ ብዬ የጠበኩትን ቀን በምን ቀን እዚ ቤት መጣሁ ለማለት አበቃኝ እየመሸም ስለነበር አባትየው ከመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል አካፈሉን ። የፈራኸው አይወርስህም በሚል ርዕስ አሁን ይሄ መልዕክት ለእናትየው ነው ለእኔ ነው ግራ ግብት ብሎኝ አሜን አንኳ እንዴት ልበል ተሳሰርኩ እናትየው አሜን አይወርሰኝም ቤቴ አይገባም እያሉ ይቀበሉ ነበር ግራ ግብት እንዳለን ፀልየውልን ናዲና አማን ሸኙኝ....... ........ይቀጥላል .......... @Gospel_literature @Gospel_literature ✍written by Aksan Adane
Показать все...
😢 26👍 10 2😁 2
.      🤔ጥያቄዬ🤔 📘ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ📘            #ክፍል_26 .....እኮ እንዴት አልኩት በጣም በረጅሙ ተነፈሰና ጓደኞችሽ ደወሉልኝና በጣም መታመምሽን ነገሩኝ  የእውነት በራሴ በጣም ነበር የተናደድኩት እውነት ቢሆን ኖሮ እንኳን በቃ ስላልቻልኩ ልደውልልሽ ነበር ልክ ልደውል አልደውል ስታነሳ ምን ብዬ ልጀምር ይቅርታ አድርጌልሻለው ልበላት ወይስ እስክትደውል ጠብቄ ኮስተር ብዬ ላውራት እያልኩ ከራሴ ስሟገት አቤል ደወለልኝ በቃ ደስ አለኝ እንደሌላ ቀኑ በሰው ስልክ ደውላ ነው ብዬ አነሳሁት ሲነግረኝ እየቀለደም መስሎኝ ነበር ጭራሽ ራሷን ስታ አልነቃ ብላለች ሲለኝ ምሆነውን አጣሁ።   ደስ እያለኝ በፈገግታ ተመስጬ ስሰማው  ንግግሩን አቆመና ኸረ አትመሰጪ በቃ አላወራም አለኝ እሰይ ተጋደልናታ ብዬ ስኮሳተር ስቀልድ ነው ከዚያ የእግዚአብሔር ነገር ዝም ብዬ ብቻ ተነስቼ ልመጣ ስል አማን ደወለልኝ የት ን ደብሮኛል አለኝ ነገርኩት ደስ አለው በጣም እኔ ተናደድኩ ታማለች እያልኩህ ምን ሆነሀል ብዬ ስጣላው አይ ደስ ያለኝ ሰላም ሊወርድ በመሆኑ ነው ስጠብቀው ነበር አለኝ እኚህ ሰዎች አውቀው ነው እንዴ አልኩና ከሆነም ይሁን ብዬ ስነሳ በቃ አብረን እንሂዳ አለኝ መጣን የእውነት ባላይሽ ይሻለኝ ነበር በቃ ራሴን ይቅር አልለውም ነበር አለኝ ። ወሬ አታብዛ ወደዛ የፊልም አክተር አክተር አትጫወት አልኩት ጉዱ መች አለቀና አለኝ የምኑ ስለው አቤል ለአንቺ ሲል የማሂን የሶሻል ሚዲያዎች ሰርች አድርጎ ማውራት ከጀመሩ ሰነባብተዋል ለእኔ እንዳለኝ የድሮ ማንነቴን ተጠቅሜ ሙሉ እምነቷን ስትጥልብኝ ምንም አትደብቀኝም ብሎ የተፃፃፉትን አሳየኝ የእኔና የአንቺ አብሮ መሆን ሰላም እንደሚነሳት ከብሩክ ጋርም አብረው እንደሚያሴሩ ነገረችው ። ራሴን ጠላሁት ከአንቺ ይልቅ እነሱን አመንኳቸው ለስቃይና በሽታ ዳረኩሽ ክፉ ነኝ አይደል  እውነት ቢሆን እንኳን የስንት ቀን መልካምነትሽን በአንድ ጊዜ ስህተት ቀየርኩት እንዴት እንዳስቻለኝ ራሱ ይገርመኛል ጨካኝ ነኛ ?አለኝ ሳላስበው ለካ እየተነፋረኩ ነው  ቁስሌን አስታወሰኝ  ግን አሁን በዚያ ከመከፋት ይልቅ በጊዜው በሆነው መልካም ነገር ማመስገን ይሻላል ብዬ እምባዬን ጠራረኩኝ እፁ ይቅርታ የምልበት አቅም ራሱ የለኝም ምን እንደምልሽ ራሱ ሲል እንግዲ አታሽቃብጥ በቃ ያለፈው አልፏል በራሴው ታሪክ እንደ አሰለቃሽ ፊልም ልታስለቅሰኝ ነው እንዴ ብዬ ፈገግ አልኩ ። ከዚህች ከማሂ ጋር ግን ብዙ ማወራው ጉዳይ አለኝ በቁጭት ነው የሚያወራው እንግዲ አታናደኝ በቃ ንቆ መተው ነው አይሻልም ሰላም ለምን እናጣለን አማን በሩን ከፍቶ ገባ እናንተ ልጅቷ ማረፍ ሲኖርባት አፍጣቹ የሆድ የሆዳችሁን ታወራላችሁ ብሎ ተቀመጠ በል ሂድ አረፍ በል እኔ እጠብቃታለሁ አለው በስልኬ ሰአት ሳይ 10ሰአት  አዎ ሂድ አልኩት ግደሉኝ ከዚህ አልሄድም አለ ከደረቀ ስለማይሰማ ተውነው  ስለ እግዚአብሔር መልካምነት በሚገርም አገላለፅ ይሰብከን ጀመር አማንም በተራው ሲያወራ እንዳፈጠጥን ነጋ  እነ ሊዩም መጡ  ህክምናዬን ጨርሼ እንድወጣ ተፈቀደልኝ ። ጌታን አያመሠገንን ወጣን አቤሎና ሊየን አመሠገንኳቸው የራስ ሰው አይመሠገንም አለች ሂዩ ። እነ ናዲም ያን ቀን ሆቴል አርፈው ስራ ስለሚስተጓጎልባቸው ተመለሱ ። ቀኖች እየገፉ አመቶች እየተተካኩ ልመረቅ ደረስኩ በየእረፍቱ እነ ማሚ ጋር እየተመላለስኩ የብሩክ ዛቻና ጭቅጭቅ ሳይቆም የማሂም ሴራ ሳይቆም እግዚአብሔር እየረዳን ብዙ ቀናቶች አለፉ ሊዩና አቤሎም የሶስታችንም ጓደኝነት እንደተጠበቀ ሆነ እግዚአብሔር ከረዳቸው መጪ አመት የመጋባት እቅድ አላቸው ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ እያሉ ያስቁኛል ቆይ በምን ልትኖሩ እያልኩ ሳናድዳቸው ከቤተሰቦቼ ጋር እሰራለሁ እሷ ምን በወጣት ደግሞ ተመርቀንስ ስራ የለ ማለት የሁሌ ንግግሩ  ነው አቤሎ ለቤተሰቡ በቸኛና የሀብታም ልጅ ነው ። የማይደርስ የለ እግዚአብሔርም ጤናችንን ጠብቆ ሰላማችንን ጠብቆ በድካማችን አግዞን ተመረቅን ማሚና ናዲ ተዐምር አማን መጥተው አስመረቁኝ የአቤሎና የሊዩ ቤተሰቦችንም በደንብ ተዋውቀናል ቤተሰቦቻችንም እርስ በእርስ ተዋውቀው አዳማ ላይ ደስ የሚል ግዜ አሳለፍን ከሊዩና አቤሎ ተለይቶ መኖርን ደግሞ ልጀምር ነው አሰንደእነርሱ መልካም ጓደኛ በዘመኔ ገጥሞኝ አያውቅም ። እንደዋወላለን ረጅም ሰአት አወራቸዋለው በቃ ቢከፋኝም ተላቅሰን ከተለያየን ቀን ጀምሮ እየኖርኩት ነው ያለ እነርሱ ። እንግዲ ተመርቆ ወዲያው ስራ የለ ከማሚ ጋር ንግዱን አጧጥፈው ጀመር ጀግናዋ እናቴ ከትንሹ ተነስታ ትልቅ ወደ ትልቅ ሱቅ አሳድጋዋለች ። በጅምላ ብቻ እቃዎችን ታስረክባለች ። ብሩክ ተብዬው አሁን ድር ይደውላል አላነሳም እርሱም ተስፋ አይቆርጥም ማሂ ስታየኝ እንኳን መንገድ ትቀይራለች ። የናዲ እህትና ወንድሞች ስለእኛ ቢያውቁም እናትና አባቱን እንድተዋወቅ እሁድ እቤታቸው ተጋብዣለሁ ........ ..........ይቀጥላል........... @Gospel_literature @Gospel_literature ✍written by Aksan Adane
Показать все...
🥰 28👍 16
.          🤔ጥያቄዬ🤔 📘ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ📘           #ክፍል_25 ......ከዚያ በኋላ የሆነውን አላስታውስም ራሴን ያገኘሁት ከሌላ ቀኑ በተለየ አልጋ ላይ ነበር ነጭ ኮርኒስና የመብራቱ ብርሀን በብዥታ ታየኝ ። እንዴ ነቃች መሠለኝ የአቤል ድምፅ ነበር እጄን የግሉኮስ ካኖላው ህመም ተሰማኝ  ከደቂቃ በኋላ አይኔ በጥራት አሳየኝ አንገቴን አዙሬ ሳይ ህልምም መሠለኝ አሁንም አልነቃሁም ብዬ አሰብኩ ናዲ ወንበር ላይ ተቀምጧል እንዳየሁት ከተቀመጠበት ብድግ አለ እየቃዠው አይደለማ ብዬ ለመነሳት ስሞክር ሰውነቴ አልታዘዝ አለኝ አቃሰትኩ ። አትነሺ ያምሻል አለኝ  የእውነት የራሱ ድምፅ ነው ጌታ ሆይ ምን ይሳንሀል አልኩ በውስጤ አይኖቼ ሱስ ይመስል የለመዱት አይቅርብኝ ይመስል እንባዬን ይዘረግፉት ጀመር ለምን ታለቅሺያለሽ አሁን እኮ መጥቻለሁ አለኝ እንባዬን እየጠረገ ሊዩና አቤል ግርግዳ ተደግፈው ቆመዋል ሳያቸው ፈገግ አሉልኝ ሳያቸው ደስ አለኝ ጤንነት ተሰማኝ ከእኔ ጋር በምን እዳቸው ነው የሚንከራተቱት የእኔ ምርጥ ጓደኞች አልኩ በሆዴ እፁ እድለኛ ነሽ ሳይደግስ አይጣላም አይደል የሚባለው ጓደኞችሽ በጣም መልካም ናቸው አለኝ ። ከዚያም በላይ ናቸው አልኩት ዶክተሩ መጣ ከኋላውም አንድ ሰው ጁስ ይዞ ገባ ማየው ደግሞ እያልኩ ናዲ ከተቀመጠበት ተነሳ እፁብ እንዴት ነሽ አለኝ ደህና ነኝ አልኩት  በደንብ ረፍት ካደረግሽና ከዚህ በኋላ ምግብ በአግባቡ ከተመገብሽ ይበልጥ ደህና ትሆኚያለሽ ይህንን ጨርሺና ግሉኮሱም ይበቃሻል ብዙ አታስወሯት ረፍት ታድርግ ብሏቸው ወጣ እፁብ እንዴት ነሽ ፀጉረ ልውጡ ደህና ነኝ አልኩት ፊቴ ላይ ማነው የሚለው ጥያቄዬ ተነበበለት መሠለኝ ኦው አማን ነኝ ስላየሁሽ ደስ ብሎኛል አለኝ  ድምፅህ አልጠፋኝም ነበር በስልክም ቢሆን ግን እንዴት መጣችሁ አልኩት እሱ ምን ይሰራልሻል ዋና መምጣታችን አይደል አለኝ ናዲ ።አንተ ዝም በል አንተን ያናገረህ የለም አልኩት አቤል ኸረ እፁ ልፋታችንንማ ገደል አትከቺውም ካላሁት ብለሽ በሞትና በህይወት መካከል አልሆንሽም አለ ሁሉም ሳቁ ያኔ ነበራ አሁን ከፈለገ ተመልሶ መሄድ ይችላል አይሞቀኝ አይበርደኝ አልኩት ። እንደማላደርገው አውቀሽ ነዋ አለኝ አንተ እንድታወራ አልተፈቀደልህም አልኩት ። እሺ ብሎ ዝም አለ አንጀቴ ተንሰፈሰፈ ገፅታው ሲያሳዝን ከልቤ መስሎት ድንግጥ ነው ያለው  ልክ እንዳልናፈኩት ሳስመስል ለራሴም ገረመኝ ሲያወሩ ሲስቁ ሰአቱ ነጎደ  ። አይ እግዚአብሔር ትገርመኛለህ እኮ ባልጠበቁህ መንገድ ትመጣለህ አሁን ምን ቢሉት ነው የመጣው ታማለች ብለውት ነው የመጣው ወይስ እውነቱን አውቆ ለነገሩ እራሳቸው ይነግሩኝ የለ ሆነም ቀረም ግን ስለሆነውም ስላልሆነውም ስምህ ይባረክ አልኩኝ ። እፁ ምነው የት ሄድሽ አለችኝ ሊዩ ኸረ የት እሄዳለሁ  እናቴ ደውላ አታውቅም አልኳቸው ደውላ ነበር በፌሎ ምሽግ ገብታለች አልኩኝ ጌታ ይቅር ይበለኝና ስትወጣ እኛ ራሳችን አንደውላለን ብዬአቸው ነበር ደውይላቸው አለችኝ ስንት ቀን ሆነኝ አልኳት 4ቀን የስኳርና ግሉኮስ መጠንሽ በጣም ወርዶ ነበር እና በዚህ እድሜ ለአቅመ ትልቁ ጨጓራ ደርሰሻል እንኳን ደስ ያለሽ አለኝ አቤል ቀውስ ብዬ ሳኩ ለማሚ ደወልኩላት በቃ ስፍስፍ አለች የሆነ ነገርማ ታውቋታል እኔ እኮ ቢጨንቀኝ ልመጣ ነበር ፀሎት ሲሉ አልዋጥ ብሎኝ ኡፍፍፍፍፍፍ ጌታ ይባረክ ሰይጣን ስንቱን አሳሰበኝ መሠለሽ አለችኝ አይዞሽ እናቴ ደህና ነኝ አትጨናነቂ ብዬ አረጋጋኋት ደስ አላት ሌላም ሌላም ነገር ስትነግረኝ ቆይተን ስልኩ ተዘጋ ። የናዲ ስልክ ደጋግሞ ይጠራል አያነሳም  ለምን አታነሳውም አልኩት አላስፈላጊ ስልክ ነው አለኝ ወዲያው የጓደኛው ስልክ ጠራ ኸረ ጀለስ ወደ እኔ ዞረች አለው አላየሁትም በላት እንደ አመሏ በውሸትና ክፋቷ ልትሞላኝ ነው አለ በስጭትጭት እያለ ማሂ ናት አልኩኝ ካቀረቀረበት ቀና አለ ። ለምን አታነሳላትም አልኩት ድጋሚ ህይወቴን ትበጥብጠው አለኝ ወደህና ፈቅደህላት መስሎኝ የበጠበጠችህ አልኩት ። ኸረ እፁ እንደሱ አይደለም አለኝ እየተስለመለመ እውይ ሊያስለቅሰኝ ነው እንዴ እፁብ አታደርጊውም አትጃጃዪ አልኩኝ ለራሴ ኮስተር ብየረ አልፈታ አልኩት እፁዬ እንደዚህ ስትሆኚ ታስፈሪያለሽ ከጥፋቴ አንፃር ባይገባኝም እስቲ እን ደበፊቱ ሁኚልኝ አለኝ ዝም አልኩት አቤሎና ሊዩ እየመሸም ስለሆነ በጠዋት እንመጣለን ብለው ወደ ጊቢ ሄዱ ነገ ጠዋት እኛም ልንወጣ እንችላለን ግን እስቲ ኑ አላቸው እስከ ምሽቱ 5ሰአት ምናምን አማን ሲለፈለፍ እንቅልፍ ወሰደኝ የሆነ  ሰአት ላይ ሰነቃ አማኑ የለም ናዲ አንዷ ወንበር ላይ ጥቅልልል ብሎአል አሳዘነኝ እንደምንም ባለኝ በሌለኝ ሀይል ተነሳሁና ብርድ ልብሱን አለበስኩት እኔ አንሶላውን እና ፎጣ ነበረ እሱን ለብሼ ገና ደቂቃ ሳይሆን ነቃ አይኑን እያሻሸ ለምን ተነሳሽ አለኝ ብርዱስ አልኩት የምን ብርድ የለም እኮ አለኝ አማንስ አልኩት መኪና ውስጥ አረፍ በል ብዬው ገብቷል ይመጣል አለኝ ። ብርድ ልብሱን መልሶልኝ ፎጣውን ደርቦ ተቀመጠ ቆይ እንዴት መጣህ አልኩት ፈገግ አለና እግዚአብሔር ነዋ በራሱ መንገድ አርጎ አለኝ እኮ እንዴት አልኩት....... ..........ይቀጥላል ........... @Gospel_literature @Gospel_literature ✍written by Aksan Adane
Показать все...
👍 34🥰 5 4🔥 3