cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

ትክክለኛ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ! #Ethiopia #Ethiopianews #Addismereja

Больше
Рекламные посты
3 350
Подписчики
+324 часа
+187 дней
+4230 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
#77ሚልዮንብር ከሰሞኑ የቀድሞ የናይጄርያ ተጫዋቾች እና ፋሽን ሞዴሎች "ሸነን አፍሪካ" በሚል ፕሮግራም ለሶስት ቀናት ኢትዮጵያ ተገኝተው ላደረጉት እንቅስቃሴ (የህዳሴ ግድብ ጉብኝት፣ ኳስ ጨዋታ፣ ኮንፈረንስ መካፈል...ወዘተ) በድምሩ ከመንግስት የወጣው ወጪ 77 ሚልዮን ብር ገደማ ነበር፣ አንዳንድ ወጪዎች በመንግስት ድርጅቶች በአገልግሎት መልክ ባይሸፈኑ ኖሮ ወጪው 110 ሚልዮን ተገምቷል። አንዳንድ ሚድያዎች ሸነን አፍሪካን አህጉር አቀፍ ፕሮግራም እንደሆነ ለማመልከት "በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ግዜ" ቢሉም ፕሮግራሙ መቼም፣ የትም ሌላ ሀገር ከዚህ በፊት ተካሂዶ አያውቅም። የፕሮግራሙ አዘጋጅ የሸነን ኮስሜቲክስ ባለቤት ዮርዳኖስ ሙሴ ናት። Via:EliasMeseret https://t.me/Satenawmedia1
Показать все...
👍 7🤔 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ይቺው ናት ኢትዮጵያ ይህችው ናት አለምህ ብቻዋን የተኛች ከአለም ተደብቃ አኪርዋ ቀዝቅዝዞ ያንቀላፋች ውቢት ያንተው የክት እቃ ልቡዋን አታውልቃት አትጨቅጭቃት በቃ አብረህ አንቀላፋ ወይ አብረሀት ንቃ ነፍስ ይማር ደራሲ፣ ገጣሚ እና ጋዜጠኛ ነብይ መኮንን Via:EliasMeseret https://t.me/Satenawmedia1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
#በአዲስ አበባ ከተማ ዳቦ ከግራም በታች ሲሸጡ የተገኙ 260 ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ‼️ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሚሆነው ዳቦ በሶስት አይነት መንገድ እየቀረበ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል። ለህብረተሰቡ የሚቀርበው ዳቦ  ከ1ሺ በላይ በሚሆኑ በሸገር ዳቦ ማከፋፈያ ፣17 በሚሆኑ በመንግስት የግል ባለሀብቶች ጥምረት የሚቀርቡ እና 1700 በሚሆኑ የግል ዳቦ ቤቶች አማካይነት ለነዋሪዎች እንደሚደርስ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል። በእነዚህ ዳቦ ቤቶች ላይ የሚቀርቡ ዳቦዎች በሸገር ዳቦ 70 ግራሙ 5ብር፣ የመንግስት የግል ባለሀብቶች ጥምረት የሚዘጋጀው በ6 ብር የሚቀርቡ ናቸው። እንዲሁም በግል ዳቦ መጋገሪያ ቤቶች የሚዘጋጁት ከ7 ብር ጀምሮ የሚሸጡ ናቸው። ለህብረተሰቡ የሚቀርቡት ዳቦዎች ዝቅተኛው የግራም መጠናቸው  70 ግራም እንደሆነ እና ከተቀመጠው ግራም በታች መጋገርም ሆነ መሸጥ በየትኛውም መንገድ የሚቀርቡ ዳቦዎች ላይ የተከለከለ ነው ብለዋል። ለህብረተሰቡ የሚቀርቡት ዳቦዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ እና ከግራም በታች ሲጋግሩ የተገኙት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል። በዚህም በዘንድሮው 2016 በጀት አመት ብቻ ከ260 በላይ ከግራም በታች ሲጋግሩ የተገኙ ዳቦ ቤቶች ላይ  እርምጃ ተወስዶባቸዋል። እንዲሁም ዳቦ መሸጫ ሱቆች የዋጋ ዝርዝር ማሳወቂ መለጠፍ ግዴታ እንዳለባቸው አቶ ሰውነት አየለ ጨምረው ተናግረዋል። #ብስራትሬዲዮ 👉ትኩስ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ https://t.me/Satenawmedia1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
"ጥላቻ፣ ጦርነት፣ ጠብ፣ ክርክር፣ ሞኝ መሆኑን፡ እያወቅን እዚያ ላይ እንንከባለላለን። የሰው ልጅ ህልውናውን ለመጠበቅ ሰላምን መምረጥና መከተል ይኖርበታል። የሰላምን እጦት ያመጣነው ራሳችን ነን። ማንም አምጥቶ አልጫነብንም።ሰላም ከሌለ መንፈሳዊም ሆነ ዓለማዊ ተቋማት ምንም መሰራት እንደማይችሉ አውቀን ለሰላም በአንድነት መቆምና ሰላምን መከተል ይኖርብናል። ለዚህም ሁላችንም ከቀደመው እየተማርን መጪውን ሰላማዊ ለማድረግ መጣር ይኖርብናል። የሔድንበት መንገድ ጎድቶናል።ስለሆነም ወደ ሰላም፡ እንመለስ ብለን መወሰን አለብን።ለዚህም ሁላችንም ወደ አእምሮችን ተመልሰን ሰላምን እንከተላት።" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወክጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት *** "የሃይማኖት ተቋሞቻችን ለዘላቂ ሰላማችን"በሚል ርእስ በሸራተን አዲስ ዛሬ በተካሔደው መድረክ ላይ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ። #አዩ 👉ትኩስ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ https://t.me/Satenawmedia1
Показать все...
3🥰 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ከመጭው መስከረም ጀምሮ ከዚህ በፊት የተሰጠው የሆቴሎች የኮከብ ደረጃ ስራ ላይ አይውልም ተብሏል። የሆቴሎች የኮኮብ ደረጃ ምደባ በአዲስ መልክ ሊሰራ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዳግም ደረጃ ምደባ ዙሪያ ከሆቴል ባለንብረቶችና ስራ አስፈጻሚዎች ፣ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ምክክር አድርጓል። የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የደረጃ ምደባ ደንብ ሆቴሎች በየሶስት አመቱ በዳግም የደረጃ ምደባ ሂደት ማለፍ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ በዚህም መሰረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ እና በክልሎች የሚገኙ ሆቴሎችን የደረጃ ምዘና ለማድረግ ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል። ሆቴሎች ከዚህ ቀደም የተሰጣቸው የኮከብ ደረጃ በህጉ መሰረት የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ በመሆኑ የኮከብ ደረጃው እንደሚሰረዝ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ አሳውቀዋል። ይህ ዳግም ምደባ በዋናነት ሆቴሎች የሚሰጡትን አገልግሎት ማሻሻል እና የሀገሪቱን የቱሪዝም አገልግሎት ተወዳዳሪነት ማሳደግ ላይ ትኩሩቱን ያደረገ መሆኑንም ኢዜአ በዘገባው አመልክቷል:: ቤተሰብ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ https://t.me/Satenawmedia1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
#በሕንድ ሃይማኖታዊ ፌስቲቫል ላይ ከ110 በላይ ሰዎች ተረጋግጠው ሞቱ! በሰሜናዊ ሕንድ በሃይማኖታዊ ፌስቲቫል ላይ ቢያንስ 116 ሰዎች ተረጋግጠው መሞታቸውን ፖሊስ አስታወቀ።አደጋው ያጋጠመው አትራ ፕራዴሽ ግዛት ሳትሳንግ በተባለ የሂንዱ እምነት ተከታዮች ሃይማኖታዊ ፌስቲቫል ላይ መሆኑን የፖሊስ ኃላፊ ሻላብህ ማቱር ተናግረዋል።ከሟቾቹ መካከል ሴቶች እና ሕጻናት እንደሚገኙበት ተገልጿል። እስካሁን ድረስ የመረጋገጥ አደጋው እንዴት ሊከሰት እንደቻለ ግልጽ ባይሆንም የዓይን እማኞች ፌስቲቫሉ የተካሄደበት ስፍራ መውጫ በጣም ጠባብ መሆኑን እና አቧራማ አውሎ ንፋስ ግራ መጋባት እና ድንጋጤ ፈጥሮ ሰዎች መሯሯጥ መጀመራቸውን ተናግረዋል።ከአንደጋው የተረፈ አንድ ግልሰብ ለቢቢሲ ሲናገር፤ “ሁሉም ነገር በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነበር። ድንገት ጩኅት ሰማሁ። መሯሯጥ እና መረጋገጥ ተፈጠረ” ብሏል። ሌላ የፌስቲቫሉ ተሳታፊ ደግሞ የነበረውን ሁኔታ ስትናገር፤ “ስነ-ስርዓቱ እንዳበቃ ሰዎች በፍጥነት ለመውጣት ሲሞክሩ መገፈታተር እና መረጋገጥ ተፈጠረ። በጣም ብዙ ሰዎች ቱቦ ውስጥ ወድቀው ሕይወታቸው አልፏል” ስትል ተናግራለች።እስካሁን የሟቾች ቁጥር 116 ነው የተባለ ቢሆንም በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የአትራ ፕራዴሽ ግዛት የፖሊስ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ዘጋቢ ተናግረዋል።
ቤተሰብ
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው ይከታተሉ https://t.me/Satenawmedia1
Показать все...
ራያ‼️ በ #ራያ #አላማጣ ከተማ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ላይ ሰፍረው የነበሩት የትግራይ ታጣቂዎች ትናንት ጀምረው አካባቢው ለቀው እየወጡ መሆኑን የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልፀዋል። የትግራይ ታጣቂዎች ከሁለት ወር በፊት ወደ ራያ አላማጣ ወረዳ በመግባት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሰፍረው እንደነበር ይታወሳል። በዚህ የተነሳ ህዝቡ ታጣቂዎቹ በደል እያደረሱብን ስለሆነ እንዲወጡ በሰላማዊ ሰልፍ ሲጠይቅ እንደነበር ይታወቃል። 👉ትኩስ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ https://t.me/Satenawmedia1
Показать все...
ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

ትክክለኛ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ! #Ethiopia #Ethiopianews #Addismereja

Фото недоступноПоказать в Telegram
#Update መሪጌታ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ከእስር ተፈቱ። የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ  መሪጌታ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ከእስር መለቀቃቸውን የማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል። ዋና ሥራ አስኪያጁ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ነበር ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ለእስር የተዳረጉት። ከሁለት ወራት በኋላ ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2016  ዓ.ም  ከእስር  መለቀቃቸውን  ከቤተሰቦቻቸው ማረጋገጥ ተችሏል https://t.me/Satenawmedia1
Показать все...
🙏 4🔥 3
ማክሰኞ ሰኔ 25/2016 ዓ፣ም ዕለታዊ ዜናዎች ‼️
1
፤ በቱርክ አደራዳሪነት ትናንት አንካራ ውስጥ የተነጋገሩት ኢትዮጵያና ሱማሊያ ነሃሴ 27 በድጋሚ ለመነጋገር መስማማታቸውን የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሐካን ፊዳን ትናንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫም፣ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ታዬ አጽቀሥላሴ እና የሱማሊያው አቻቸው አሕመድ ፊቂ በኹለቱ አገሮች ልዩነት ዙሪያ በተናጥል ግልጽነት የተሞላበት ውይይት እንዳደረጉና ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ በንግግር ለመፍታት እንደተስማሙ ገልጧል። የኹለቱን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ንግግር የመሩት፣ የቱርኩ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሐካን ፊዳን ናቸው።
2
፤ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከአንዳንድ ቀበሌዎች ነዋሪዎች የታጣቂዎችን ጥቃት በመሸሽ ከቀያቸው እየለቀቁ እንደኾነ ቪኦኤ ዘግቧል። በወረዳው ታጣቂዎች በሚያደርሱት ጥቃት፣ ሰላማዊ ሰዎች እየተገደሉ መኾኑን ነዋሪዎች መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። የዞኑ አስተዳደር፣ በደራ ወረዳ እና በአጎራባቾቹ ወረዳዎች ለቀጠለው ጥቃት፣ የፋኖ እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርጓል ተብሏል። ባካባቢው የመንግሥት ኀይሎች ከኹለቱም ቡድኖች ጋራ ግጭት ላይ እንደኾኑ አስተዳደሩ መግለጡንም ዜና ምንጩ ጠቅሷል።
3
፤ የምግብ ዘይት አምራቾች ማኅበር፣ መንግሥት በቅርቡ የከለሰውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ደንብ እንደገና እንዲያጤነው መጠየቁን ካፒታል ዘግቧል። ማኅበሩ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማሻሻያው በአገሪቱ የሚታየውን የዋጋ ንረት ያባብሰዋል በማለት ማስጠንቀቁን ዘገባው አመልክቷል። መንግሥት ባደረገው ማሻሻያ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የነበሩት የምግብ ዘይትና የቅባት እህሎች ምርቶች በተጨማሪ እሴት ታክሱ ተካተዋል። የምግብ ዘይት፣ የቅባት እህሎች ውጤቶችና የእንስሳት መኖ ከእሴት ታክስ ነጻ አለመደረጋቸው፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ አምራቾችና ታክሱን በማይከፍሉ ነጋዴዎች መካከል ፍትሃዊ ያልኾነ ውድድር ይፈጥራል ሲል ማኅበሩ ለገንዘብ ሚንስቴር ቅሬታውን አቅርቧል ተብሏል።
4
፤ መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ፣ ትናንት ሳዐዲ ዓረቢያ ውስጥ ባስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 195 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን መመለሱን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ከተመላሾቹ መካከል፣ 76ቱ ሴቶች፣ 15ቱ ጨቅላ ሕጻናት እንደኾኑና እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የኾኑ 43 ታዳጊዎችም እንደሚገኙበት ሚንስቴሩ ገልጧል። ኮሚቴው ከሚያዚያ 4 ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ ከ54 ሺህ በላይ ፍልሰተኞችን መልሷል።
5
፤ በኬንያ ከግብር አዋጅ ጋር በተያያዘ በተቀሰቀሰው አገር ዓቀፍ ተቃውሞ በኹለት ሳምንት ውስጥ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 39 መድረሱን የአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተቋጣጣሪ ኮሚሽን አስታውቋል። በተቃውሞው ሌሎች 361 ሰዎች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ኮሚሽኑ ገልጧል። መንግሥት ከተቃውሞ ጋር በተያያዘ የተገደሉት ሰዎች 19 ብቻ እንደኾኑ ዕኹድ'ለት አስታውቆ ነበር። መንግሥት ተቃውሞውን ተከትሎ አዲሱን የግብር አዋጅ ባለፈው ሳምንት ቢያነሳም፣ ተቃዋሚ ወጣቶች ግን ዛሬ በድጋሚ ወደ አደባባይ እንደሚወጡ መግለጣቸውን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። https://t.me/Satenawmedia1
Показать все...
ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

ትክክለኛ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ! #Ethiopia #Ethiopianews #Addismereja

Фото недоступноПоказать в Telegram
Update‼️ በቱርክ አደራዳሪነት ትናንት አንካራ ውስጥ የተነጋገሩት ኢትዮጵያና ሱማሊያ ነሃሴ 27 በድጋሚ ለመነጋገር መስማማታቸውን የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሐካን ፊዳን ትናንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫም፣ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ታዬ አጽቀሥላሴ እና የሱማሊያው አቻቸው አሕመድ ፊቂ በኹለቱ አገሮች ልዩነት ዙሪያ በተናጥል ግልጽነት የተሞላበት ውይይት እንዳደረጉና ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ በንግግር ለመፍታት እንደተስማሙ ገልጧል። የኹለቱን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ንግግር የመሩት፣ የቱርኩ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሐካን ፊዳን ናቸው። ሁለቱ ሚኒስቴሮች በቀጣይ በነሀሴ ወር መጨረሻ በድጋሚ ተገናኝተው እንደሚመክሩ ታውቋል። ===========≠========== 👉ትኩስ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ https://t.me/Satenawmedia1
Показать все...
👍 3
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.