cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Sheger Press️️

Official channel of sheger press If you want to give a suggestion or comment, contact us 👉 @birukepromo

Больше
Рекламные посты
40 064
Подписчики
+924 часа
-527 дней
-25230 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

በሕወሃት አመራር ውስጥ የርስበርስ መገዳደል ሊሰፍንና ይህም በትግራይ ሕዝብ ላይ አደጋ ሊደቅን ይችላል በማለት ዶይቸቨለ የዜና ማሠራጫ ጣቢያ ባለፈው ዕሁድ "ሐሰተኛ" እና "አሳሳች" መረጃ አሠራጭቷል ሲል ሕወሃት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከሷል። ሕወሃት፣ የጣቢያው ዘገባ በክልሉ ሽብር እና ጥርጣሬ እንዲነግስ የሚያደርግ እና ምናልባትም ያልታወቀ ስውር ሴራ መኖሩን የሚያሳይ ሊኾን ይችላል ብሏል። ሕወሃት፣ የጣቢያው አስተዳደር በዘገባው ላይ ምርመራ በማድረግ ለዘገባው ተጠያቂ በኾኑ ግለሰቦች ላይ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስድና ይቅርታ እንዲጠይቅም ጠይቋል። @sheger_press
Показать все...
👍 9🥴 2🥰 1
በደቡብ ኢትዮጵያ እና የኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ዳግም በተነሣ ግጭት ሦስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ‼️ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ እና በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ሱሮ ባርጉዳ እና ገላና ወረዳዎች አዋሳኝ አካባቢዎች፣ በታጠቁ ሰዎች መካከል ውጊያ እየተካሔደ መኾኑን ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡ በምዕራብ ጉጂ ዞን የገላና ወረዳ አስተዳደር ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢያሱ ጂኦ፣ ግጭቱ ትላንት ማክሰኞ መቀስቀሱንና አንድ አርብቶ አደር ሲገደል ሌላ አንድ መቁሰሉን አረጋግጠዋል፡፡ የኮሬ ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንዶራ በበኩላቸው፣ ከጃሎ እና ከሻፉለ ቀበሌዎች፣ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ አንድ ሰው መቁሰሉን ተናግረዋል፡፡ በርካታ ሰብልም በገጀራ ቆራርጠው አበላሽተዋል ሲል አንድ የአዩዘሀበሻ ቤተሰብ ከላይ ያለውን ምስል አያይዞ ገልጿል።
Показать все...
👍 13 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
በርካታ ባለጠጎች የሚገኙባችው 10 የአፍሪካ ሀገራት በአፍሪካ 21 ቢሊየነሮችና ከ135 ሺህ በላይ ሚሊየነሮች እንደሚገኙ የአፍሪካ ዌልዝ የ2024 ሪፖርት ያሳያል። ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ ሃብት ያስመዘገቡ ሚሊየነሮች (ሴንቲ ሚሊየነሮች) ቁጥርም 342 መድረሱን የሚያነሳው ሪፖርቱ፥ የአህጉሪቱ 90 በመቶ ቢሊየነሮችና 56 በመቶ ሚሊየነሮች በአምስት ሀገራት እንደሚኖሩ ያመላክታል።ዝርዝሩን ይመልከቱ 😮👆 Alain
Показать все...
👍 23🤔 2
በሰሜን ሸዋ ዞን በሁለት ወረዳዎች በተመሳሳይ ቀን በደረሰ የድሮን ጥቃት የበርካታ ሰላማዊ ሠዎች ሕይወት አለፈ!! በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ ጉሎ በተባለ ትምህርት ቤት እና ሞላሌ ወረዳ እሁድ ግንቦት 4፤ 2016 ዓ.ም. በደረሰ የድሮን ጥቃት ከአስር በላይ ሠላማዊ ሰዎች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ተገለጸ። ከቀወት ወረዳ ዋና መቀመጫ ሸዋሮቢት በግምት 20 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው የጉሎ (ጎጥ) አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከቀኑ 7፡30 ገደማ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት አራት ሠዎች ሲገደሉ አምስት ሠዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የዐይን እማኞችና የተጎጂ ቤተሰቦችን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል። ዶይቼ ቬለ የዜና ወኪል በቀዎት ወረዳ እና ሞላሌ ወረዳዎች በዕለቱ ተፈጸመ በተባለ የሰውአልባ ድሮን ጥቃት 14 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን ዘግቧል። በትምህርት ቤቱ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት መምህራንና የአካባቢው ማሕበረሰብ የወላጅ መምህራን ህብረት (ወመህ) ስብሰባ ላይ በነበሩበት ቅጽበት መሆኑን ለቢቢሲ የተናገሩ አንድ የስብሰባው ተካፋይ፤ በጥቃቱ እሳቸውም ጭንቅላታቸው ላይ እንደቆሰሉ ገልጸዋል። ከሟቾቹ ውስጥ ሁለቱ የስብሰባው ተሳታፊዎች ሲሆኑ፤ ሁለቱ ደግሞ የት/ቤቱ ዙሪያ ላይ የነበሩ ሠላማዊ ሠዎች እንደሆኑ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሌላ የአይን እማኝ ተናግረዋል። የፍንዳታ ድምጽ ሰምተው ወደ አካባቢው በፍጥነት እንዳመሩ የተናገሩ አንድ የዐይን እማኝ እንደደረሱ አስከሬን ማየታቸውን ጠቅሰው፤ የአራት ሠዎች ሕይወት ማለፉንና በርካታ ሠዎች መቁሰላቸውን ተናግረዋል። ተመሳሳይ ዞን በሞላሌ ወረዳ መዘዞ ተብላ በምትጠራው ከተማ አጠገብ በተጣለ ሌላው የድሮን ጥቃት ሶስት የፋኖ አባላት እና በመጠጥ ሽያጭ ላይ የተሰማራች አንድ ሴት ጨምሮ አራት ያልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ዶይቸ ቼለ ዘግቧል። @sheger_press @sheger_press
Показать все...
👍 21 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ሰዉ ሰራሽ የነዳጅ እጥረት እንዲፈጠር በሚያደርጉ ነዳጅ ማደያዎች ላይ ከማሸግ የዘለለ እርምጃ መዉሰድ የሚያስችለውን አዋጅ ማዘጋጀቱ ተነገረ ባለስልጣኑ ባዘጋጀው በዚህ አዋጅ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት በሚፈጥሩ ሕገ ወጦች ላይ እስራትና የገንዘብ ቅጣት እርምጃ መውሰድ የሚያስችሉ አንቀጾች መካተታቸውን ተጠቁመዋል። አዋጁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን ተከትሎ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ስራ እንደሚገባ የተነገረ ሲሆን በነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ እያለ እንደሌለ ማስመሰል፣ የነዳጅ ግብይትን በጥሬ ገንዘብ መሸጥ፣ ነዳጅን በተለያዩ ስፍራዎች ደብቆ ማስቀመጥና የመሳሰሉትን ህገወጥ አሰራሮችን ሊያስቀር እንደሚችል ካፒታል ዘግቧል።
Показать все...
👍 11👎 2
መንግሥት የመንግሥት ሠራተኞች ቅጥርና ምደባ የአገሪቱን ብሄረሰቦች ብዝኀነትና የጾታና የአካል ጉዳተኞችን ተዋጽዖ የጠበቀ እንዲኾን የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል። ምክር ቤቱ፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ ትናንት ተወያይቷል። ረቂቅ አዋጁ፣ በመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ ጭማሪ፣ ደሞዝ እርከን፣ ክፍያና ጥቅማጥቅሞች ላይ ማሻሻያ እንዳደረገም ተገልጧል። የአነሳ ብሄረሰቦችና የማኅበረሰብ ክፍሎች በመንግሥት መስሪያ ቤቶች በቅጥር፣ ምደባ፣ ዝውውር፣ በሥራ ደረጃ እድገት፣ በትምህርትና ሥልጠና ረገድ ተጨማሪ መንግሥታዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ረቂቅ አዋጁ ይደነግጋል። ምክር ቤቱ፣ ረቂቅ አዋጁን ጉዳዩ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል።
Показать все...
👍 31👎 6🤔 1
ማስታወቂያ Old telegram groups መሸጥ ለምትፈልጉ‼️ Old telegram ግሩፖች ያላችሁ (በ2022 እና ከዛ በታች ባለው አመተ ምህረት የተከፈቱ ግሩፓች)  የGroup ሜምበር ብዛት አያስፈልግም የGroup ሜምበር 1 ሰው ቢሆንም በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዛን ነው።  ግን የተከፈተበት አመተ ምህረቱን ነው የምፈልገው  ቢያንስ አንድ አመት የቆየ መሆን አለበት። ቢያንስ አንድ አመት የቆየ እና ትንሽ ሜምበር ያለው ግሩፕ (ከ1 ሜምበር ጀምሮም ይቻላል) ያላችሁ ሰዎች እና መሸጥ የምትፈልጉ 👍በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዛን እንገኛለን። 📌የተከፈተበት አመተ ምህረት ከጨመረ ጥሩ ተጠቃሚ ይሆነሉ ማንም መሸጥ የሚፈልጉ የዋጋ ዝርዝር 👇 2018 = 500 birr 2019 = 400 birr 2020 = 300 birr 2021 = 250 birr 2022 = 200 birr ለመሸጥ ምትፈልጉ @sorithefirst ወይም በ 0928232227 መደወል ይችላሉ For more information join https://t.me/old_group_buyerchannel
Показать все...
👍 11 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
NewsUpdate‼️ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ ወቅታዊ የጸጥታና ፖለቲካዊ ኹኔታ ዙሪያ ከኦነግ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ እና ከኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ጋር ትናንት አሜሪካ ኢምባሲ ውስጥ ተወያይተዋል። ኦነግ፣ ሐመር እና ዳውድ "ሰፋ ያለ ውይይት" ማድረጋቸውንና ዳውድ ኦነግ ለዓመታት ያለፈባቸውን አስቸጋሪ የፖለቲካ ኹኔታዎች ለሐመር እንዳብራሩላቸው ገልጧል። ዳውድ የአገሪቱን ችግሮች ለመቅረፍ፣ ለዓመታት ከሕግ ውጭ የታሠሩ የኦነግ አመራሮችን "ባስቸኳይና ያለምንም ቅድመ ኹኔታ" መፍታት፣ “የተዘጉ የኦነግ ጽሕፈት ቤቶች መክፈት" እና "በመላው አገሪቱ ታስረው የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞችን ኹሉ መፍታት" እንደሚያስፈልግ ሃሳብ ማቅረባቸውን ግንባሩ ጠውሷል። ሐመር በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ አሜሪካ ጥረት እንደምታደርግ ለዳውድ ነግረዋቸዋል ተብሏል። [ዋዜማ]
Показать все...
👍 31🥴 5 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ🙆‼️ በሀድያ ዞን ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ ለአንድ የዩኒቨርስቲው የፋይናንስ ቡድን መሪ የ790 ቀን አበል እንዲሁም ለሌላኛው የፋይናንስ የቡድን መሪ ደግሞ በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ የ1,469 ቀን (1,056,854 ብር) አበል እንደተከፈላቸው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሰነድ ማስረጃዎችን፣ጥቆማዎችን እና መመሪያዎችን በማጣቀስ ምርመራ አድርጎ ውጤቱን ይፋ አድርጓል። ሌላም የዩኒቨርስቲው ፋይናንስ ሳያውቅ 1.4 ቢሊዮን ብር ለኦክስጅን ማምረቻ በሚል በህገወጥ መንገድ መንቀሳቀሱን እና ፍቃድ የሌለው የኮንስትራክሽን ድርጅት ግንባታውን እንዲሰራ ያለ ጨረታ እንደተሰጠው በምርመራ ውጤቱ ተገልጿል። በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተመሳሳይ ምርመራ ቢደረግ ከዚህም በላይ የሙስና ወንጀል እንደሚገኝ እሙን ነው። @sheger_press @sheger_press
Показать все...
👍 38🤔 10🥴 5 3😍 1
በትምህርት ተቋማት በሚቀጠለው 2017 ዓ.ም ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደማይኖሩ ተገለጸ‼️ በሚቀጠለው ዓመት 2017 ዓ.ም ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደማይኖሩ የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ አስታወቁ። ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን ያስታወቁት የትምህርት ሚኒስቴርና የ22 ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 በጀት ዕቅዳቸው በተገመገመበት ወቅት ነው። የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሚኒስቴሩ ሁለት ተጠሪ ተቀማት፣ የ8 የምርምርና የ14 የአፕላይድ ዩኒቨርስቲዎች የ2017 በጀት እቅድ በገንዘብ ሚኒስቴር በተካሄደ የበጀት ስሚ መርሀ ግብር ተገምግሟል። የበጀት ስሚ መርሀ ግብሩን የመሩት የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት የበጀት ዝግጅቱ ዋና ትኩረት የሀገሪቱን ሀብትና የመንግስትን በጀት በእቅድ ለተያዘለት አላማ ብቻ በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም መሁኑን ጠቁመው አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችና የስራ ሀላፊዎችም በጀትን በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ የበጀት እቅዳቸውን በተቀመጠላቸው የበጀት ጣሪያ መሰረት አስተካክለው በጠቂት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ መጠየቃቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።(አዲስ ሰታንዳርድ)
Показать все...
👍 12👎 3 2