917
Подписчики
Нет данных24 часа
+17 дней
+730 дней
Архив постов
የካቲት 20/2018 ዓ.ም
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ለባለድርሻ አካላት የ2018 የ2ኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ሪፖርት በዛሬው እለት አቅርቧል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በመድረኩ የ2ኛ ሩብ አመት የተቋም ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
ሪፖርቱን ያቀረቡት የተቋሙ ኃላፊ አቶ ሄኖክ ጉልላት እንደገለፁት በግማሽ አመቱ በርካታ ተግባራት ለመፈፀም እንቅስቃሴ የተደረገ ሲሆን ለአብነትም የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት እና ለማስተዋወቅ ከሀገርህን እወቅ ጉብኝት ከማድረግ ጀምሮ ያሉንን ፀጋዎች በተለያዩ አማራጮች የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ኃላፊው አክለውም ባህል የአንድ ማህበረሰብ መገለጫ እሴቱ እንደመሆኑ መጠን ጠብቆ ለማቆየት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋም ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በመድረኩ የተሳተፉ አስተያየት ሰጪዎች በተቋሙ እያደጉ የመጡ ለውጦች የሚበረታቱ መሆናቸውና በቀጣይም በወረዳችን ውስጥ ያሉ ሀብቶቻችንን በደንብ ማስጠዋወቅ እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል።
መድረኩን የመሩት የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሄኖክ በቀጣይ ቀሪ ወራቶች ቀሪ ተግባራቶችን ለመፈፀም ርብርብ እንደሚደረግ በማጠቃለያቸው ገልፀዋል።
በመድረኩ የህዝብ ክንፍ የዜጎች ቻርተር እንዲሁም የተቋማት የልማት እቅድ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
የካቲት 20/2018 ዓ/ም
የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር በጉረጌ ዞን መካሄድ ጀመረ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የጉራጌ ዞን የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር መካሄድ ጀምሯል።
"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የብልጽግና ፓርቲ የ7ኛው ሀገራዊ የምርጫ ምልክት ''የስንዴ ነዶ'' ሲሆን ምልክቱ የመደመር፣ አንድነት እና ትብብር መገለጫዎችን የያዘ መሆኑን ተገልጿል።
በመርሃ ግብሩ የጉራጌ ዋና አስተዳዳሪና የእለቱ የክብር እንግዳ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ፣የጉራጌ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል ጨምሮ የዞን፣የወረዳና የከተማ ከፍተኛ የመንግስትና ፓርቲ አመራሮች፣ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የካቲት 19/2018 ዓ/ም
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት 30 ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ወገኖች የረመዳን ጾም አስመልክቶ ድጋፍ አደረገ፡፡
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ጽ/ቤቱ የ1447ኛውን የረመዳን ጾም ምክንያት በማድረግ በወረዳው ለሚገኙ 30 ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ወገኖች ከ54 ሺህ በላይ በሆነ ወጪ የአስቤዛና አልባሳት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ለአቅመ ደካሞች በረመዳን ወር ደራሽ መሆን ወገኖቻችንን ከማስደሰት ባለፈ በፈጣሪ ዘንድ ምንዳ የምናገኝበት እንዲሀሁም አቅመ ደካሞችንና የተቸገሩ ወገኖችን መርዳትና መደገፍ የመኖር ተስፋቸዉ እንዲለመልም የማድረግ ሰው ተኮር በጎ ተግባር እንደሆነም ተመላክቷል።
የካቲት 19/2018 ዓ/ም
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ት/ቤቶች ፅህፈት ለመምህራን ስልጠና እየሰጠ መሆኑ አስታወቀ ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ መምህራን ለሁለት ተከታታይ ቀናት የአቅም ማጎልበቻ የሚሰጥ ስልጠና ነው ከ650 በላይ መምህራን እና ርዕሳነ መምህራን በ6 የስልጠና ማዕከል ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ።
ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን!!!
የካቲት 19/2018 ዓ/ም
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ት/ቤቶች ፅህፈት ለመምህራን ስልጠና እየሰጠ መሆኑ አስታወቀ ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ መምህራን ለሁለት ተከታታይ ቀናት የአቅም ማጎልበቻ የሚሰጥ ስልጠና ነው ከ650 በላይ መምህራን እና ርዕሳነ መምህራን በ6 የስልጠና ማዕከል ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ።
ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን!!!
የካቲት 18/2018 ዓ.ም
እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!!!
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን "ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ"አማካኝነት
የተገነባው የመሃል አምባ ከተማ ጥልቅ የንጹህ መጠጥ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በማስመልከት ለመላው የወረዳችን ህዝቦች በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን መንግስት የባለሃብቱን፣ የህብረተሰቡን እና ረጂ ድርጅቶችን አቅም በመጠቀም የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋኑን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ ባለው ስራ አበረታች ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል።
"ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ" ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 1 ባለ 100 ሜትር ኪዮብ እና 1ባለ 50 ሜትር ኪዮብ ተገጣጣሚ ታንከር ስራ፣ 12 ቦኖ ግንባታን ጨምሮ ከ12 ኪሎ ሜትር መስመር ዝርጋታ እንዲሁም 3 ባለ መቶ KB እና ባለ 50 KB
የትራንስፎርመር ተከላ በማካሄድ በዛሬው በተሳካ መልኩ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጸዋል።
በመጨረሻም አቶ ሚፍታ ሁሴን ባስተላለፉት መልዕክት ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከወረዳው አስተዳደር ጋር በመሆን የህዝባችንን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ እያደረገ ያለው ብርቱ ጥረት ተደናቂ መሆኑን በማንሳት በወረዳው መንግስትና ህዝብ ስም ላቀ ያላ ምስጋናቸውን አቅርበው በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!!!
የካቲት 18/2018 ዓ/ም
"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር"
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )በተገኙበት ለ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት የማስተዋወቂያ መርሐ ግብር በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" ! በሚል መሪ ሀሳብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት የማስተዋወቂያ መርሐ ግብር በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው
በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር )በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ማኒፌስቶ እያቀረቡ ነው።
