ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

Открыть в Telegram
925
Подписчики
+224 часа
+27 дней
+830 дней
Архив постов
የሳምንቱ አበይት ዜናዎች ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ደሳ ቀበሌ የመስኖ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመደብ የተዘጋጃ የጎሮ አትክልት በምስል፦ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎"ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለሀገር ሉዓላዊነትና የተሟላ ክብር'' በሚል መሪ ሀሳብ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ አንበልታ ቀበሌ ከ3 ሄክታር መሬት ላይ የመኸር የጤፍ ዘር ተዘርቷል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የክልሉን የገቢ አቅም በማሳደግ ሁለንተናዊ ልማት ዕውን ለማድረግና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የክልሉ መንግስት የላቀ ቁርጠኝነትና ዝግጅት አለው፦ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ዘመናዊ አሰራርን በመዘርጋት ሌብነትን ለመቀነስ እየተሰራ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎“ብዙ መንግሥታት ካልደፈሩት እና የመደመር ትውልድ ደፍሮ ካነሣቸው ሐሳቦች አንዱ የመካከለኛው ምሥራቅ እና የቀይ ባሕር ጉዳይ ነው” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #EBC 👉🏼‎ፖለቲካ በጥላቻና ስሜት ሳይሆን በሃሳብ የበላይነት መመራት አለበት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ" እያከናወናቸው ያሉ የንፁህ መጠጥ ውሃ ስራዎች 95 በመቶ መድረሳቸው ተገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ ለማህበረሰባችን እሴት ግንባታ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው የክረምት በጎ ፍቃድ በዘሬ ቀበሌ ለወ/ሮ ሎሚናት ሽኩሬ የወረዳው አብይ ኮሚቴ 40 ቆርቆሮ፣ 2 ፓኬት የግድግዳ ሚስማርና 1 ፓኬት የቆርቆሮ ሚስማር በዛሬው እለት ድጋፍ በማድረግ የቤት ግንባታውን አስጀምሯል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ቦኔ ቀበሌ የመስኖ ቅድመ ዝግጅት የተለያዩ የጎሮ አትክልቶች በመደብ የተዘጋጀ ቀይ ሽንኩርት፣ ቃሪያ ፣ ጎመን በምስል፦ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ልማት ፅህፈት ቤት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የጉራጌ ዞን አስተዳደር  ልዩ ልዩ ሹመቶች ሰጥቷል። የጉራጌ ዞን አስተዳደር በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥቷል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2018 ዓ.ም መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ ተማሪዎች ምዝገባ ስራ በሁሉም ትምህርት ቤቶች በዛሬው ዕለት ተጀመረ። ፨፨፨፨///፨፨፨፨

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ስለ ኩርሙክ የወርቅ ፋብሪካ የተናገሩት… ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘውን የኩርሙክ ዘመናዊ የወርቅ ፋብሪካ የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጉብኝታቸው በኋላ ስለ ፋብሪካው የተናገሩት… 👉 በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የወርቅ ፋብሪካ ይሆናል 👉 ከሚቀጥለው ዓመት አጋማሽ በኋላ ወደ ምርት እንደሚገባ ይጠበቃል 👉 በዚህ አካባቢ የሚመረተው ወርቅ በዓመት እስከ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ያስገኛል 👉 ከ20 ኪሎ ሜትር ራዲየስ በላይ ቦታ ይዟል 👉 ሦስት ግድቦች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚኖሩበት የመኖሪያ ካምፕ የያዘ ነው 👉 በዘርፉ ለኢትዮጵያ የእውቀት ሽግግር ያመጣ ፋብሪካ ነው 👉 ፋብሪካው የተገነባው ያለንን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም ባለን ፍላጎት መሰረት ነው 👉 በሁሉም ዘርፎች የተሟላ ልማት ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥል ስራ ነው (ኤፍ ኤም ሲ)

ነሐሴ 17/2017 ዓ.ም ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በዞንና በልዩ ወረዳ ደረጃ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! በሚል መሪ ቃል ያለፉት ዓመታት ጉዞዎች እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የሚወያይ የአመራር መድረክ መካሄድ ጀመረ። Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau

ነሐሴ 17/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ደሳ ቀበሌ የመስኖ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመደብ የተዘጋጃ የጎሮ አትክልት በምስል፦

ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለፀው በወረዳው ነዋሪ ለሆኑ አራት አቅመ ደካማ ወገኖች አዲስ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ዛሬ በተካሄደበት ወቅት ነው። ድጋፉም በገንዘብ ሲተመን ከ121 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ስለመሆኑም ተመላክቷል። በዛሬው ዕለት ድጋፍ ከተደረገላቸዉ ቤተሠቦች መካከል የደነብ፣ጊ/ዲምቱ፣ ቦኔ እና ቤደር ቀበሌ ነዋሪ ለሆኑት ወ/ሮ መህቡባ ከማል፣ አቶ አለዚብ አህመድ፣ ቦኔ ቀበሌ የዘማች ቤተሠብ ለሆኑት ወ/ሮ እልፍነሽ ሳኒ እና ምስኪን እናት ለሆኑት ወ/ሮ ፍጡማ ደንበል ለእያንዳንዳቸው ባለ 45 እና ባለ 40 ቆርቆሮ አዲስ መኖሪያ ቤት ግንባታ ስራ ድጋፍ በዛሬው ዕለት ተከናውኗል። በድጋፉ ላይ የተገኙት የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንደገለፁት መንግስት የመንግስት አቅምን በመጠቀም ከፍተኛ በጀት በመመደብ፣ ወጣቶችንና መላውን ህብረተሰብ በማስተባበር ልዩ ትኩረት ሠጥቶ ተግባራዊ እያደረጋቸው ከሚገኙ መስኮች መካከል አንዱና ዋነኛው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሆኑን ጠቅሰዋል። በበጀት ዓመቱ እየተደናወኑ ባሉት የበጎ ስራዎች በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማስጠቀም የተቻለበት ሂደት መኖሩን ያወሱት ዋና አስተዳዳሪው በዛሬው ዕለት የተደረገው ድጋፍ ላብነት ማሳያ መሆኑን በማንሳት ወጣቶችና መላው ህብረተሰብ የመደጋገፍና የመረዳት ባህሉን በማስቀጠል የበጎ ስራዎችን በተጀመረው ግለት ልክ ተሳትፎውን አጠናክሮ በማስቀጠል ባጠረ ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት በማብቃት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል። የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚፍታ አረቦ በበኩላቸው የብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር በመሆኑ መሠረታዊ ችግር ያለባቸውን ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ችግር ለመፍታት አፅንኦት ሠጥቶ በመስራት የበርካታ ዜጎችን ህይወት እየታደገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።  አክለውም በህብረተሰቡ መካከል ለበጎ ፈቃድ ስራዎች መሳካት በህብረተሰቡ ዘንድ የተመለከቱት ተነሳሽነት የሚደነቅ ስለመሆኑ ጠቅሰው የብልፅግና መንግስት ወጣቶችንና በየደረጃዉ ያሉ አካላትን በማስተባበር ድጋፍ የሚያሻቸው ወገኖችን የማስጠቀሙ ርብርብ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በማንሳት የተጀመሩ ስራዎችን ከዳር ማድረስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የወረዳዉ ወጣቶችና ስፖርት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም ፅህፈት ቤታቸው በዘንድሮ በጀት አመት በ15 የስምሪት መስኮች ላይ ዕቅድ በማቀድ በተከናወኑ የበጎ ፈቃድ ተግባራት የበርካታ ማህበረሰብ መሠረታዊ ችግሮች መቅረፍ መቻሉን ገልፀዋል። በዛሬዉ ዕለት ብቻ ግምቱ ከ121 ሺህ 750 ብር በላይ የሚገመት 125 ቆርቆሮ እና 10 ፓኬት ሚስማር በጠቅላላዉ 121 ሺህ 750 ብር የሚገመት የቁሳቁስ እገዛ መደረጉን አስታውቀዋል። ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች በሠጡት አስተያየት ቀደም ሲል በመኖሪያ ቤት ችግር ምክንያት ለዝናብና ፀሃይ በመዳረግ ለተለያዩ በሽታዎች ሲዳረጉ መቆየታቸውን ጠቅሰው አሁን ላይ ምስጋና ለመንግስትና በየደረጃው ለሚገኙ አካላት ይግባና ችግራቸው እንደሚቀረፍ ፅኑ ተስፋ እንዳላቸው በማንሳት ምስጋናቸውን በደስታ ጭምር ገልፀዋል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።

"ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለሀገር ሉዓላዊነትና የተሟላ ክብር'' በሚል መሪ ሀሳብ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ አንበልታ ቀበሌ ከ3 ሄክታር መሬት ላይ የመኸር የጤፍ ዘር ተዘርቷል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት እራስን በራስ ለማቋቋም በተለያዩ ቀበሌዎች ስንዴና ጤፍ እየለማ ይገኛል።