918
Подписчики
+124 часа
+27 дней
+930 дней
Архив постов
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓረብኛ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰዱ ነጥቦች፦
• የተቅዋ (የፈሪሃ አላህ)፣ የጸሎት እና የመቻቻል የሆነው የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ ለመላው ሙስሊም ማኅበረሰብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
• ኢትዮጵያ የሁለቱ ስደቶች (ሒጅራ) ምድር እንደሆነች እና ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) "ማንም የማይበደልባት የእውነት ምድር ናት" ሲሉ የመሰከሩላት ስለመሆኗ ገልጸዋል።
• የመጀመሪያውን የአንድነት ድምፅ (አዛን) ለዓለም ያሰማውን ታላቁን ኢትዮጵያዊ ቢላል ቢን ረባህን ያፈራች ምድር መሆኗንም አስታውሰዋል።
• ዓባይ ሁሉም በእኩልነት እና በፍትሕ ሊጠቀምበት የሚገባ መለኮታዊ ስጦታ መሆኑን እና ለትብብር ድልድይ እንጂ ለግጭት አውድማ መሆን እንደሌለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልዕክታቸው አብራርተዋል።
• ኢትዮጵያ የሌሎችን ድንበር የመጋፋት ፍላጎት እንደሌላት፣ የጎረቤቶቿ የደኅንነት ስጋት እንዳልሆነች እና የማንንም የውኃ ድርሻ ለመቀነስ አቅዳ እንደማትሠራ አረጋግጠዋል።
• የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት በሰላማዊ እና ተፈጥሮዓዊ የሕዝብ ቁጥር መጨመር ምክንያት አስገዳጅ የሆነ የሕልውና ጉዳይ መሆኑ፣ እንዲሁም የጎረቤቶችን ሉዓላዊነት የማይነካ የትብብር ጥሪ መሆኑን ገልጸዋል።
• የሰላም ንግግር የጦርነት ነጋሪትን የሚተካበት ጊዜ አሁን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሀብታችን ከመሣሪያ ማምረት ወደ ልማት፣ ሰውን ከመግደል ወደ ማከም እና ማስተማር እንዲቀየር ጥሪ አቅርበዋል።
• ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቁሳዊ ግንባታ ብቻ ሳይሆን በመቻቻል መንፈስ እና በጋራ መኖር መርሆዎች ላይ የተመሠረተ የሞራል እና የሰብዓዊ እሴት ሕዳሴ እንደሆነ በመልዕክታቸው አስምረውበታል።
የካቲት 08/2018 ዓ/ም
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!!
ለ7ተኛው ዙር ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የመወዳደርያ ምልክት የሆነውን" የስንዴ ነዶ" የማስተዋወቅ መርሃ ግብር ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የወረዳ አስተባባሪ ኮሚቴ የፓርቲያችን የምርጫ መወዳደርያ ምልክት አስተዋወቀ።
"የስንዴ ነዶ" የመደመር ፣የአንድነት እና የትብብር ተምሳሌት መሆኑ ተገልጿል።
የሳምንቱ አበይት ዜናዎች
የካቲት 08/2018 ዓ.ም
🎤 በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የወረዳ የፖሊስ አመራሮችና አባላት ማጥራትና ሂስ ግለ ሂስ ግምገማ መድረክ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 ከረዥም ጊዜ በኋላ የንፁህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚ በመሆናቸው ደስተኛ እንደሆኑ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የጅማ ወለኔ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በትምህርት ዘርፋ ያጋጠመንን የውጤት ስብራት በተቀናጀና በተባበረ መንገድ መጠገን ይገባል ተባለ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 ከሼሽት ማዴ- አመቶ መንገድ የዳገት ቆረጣ እና የአፈር ስራዎች ያሉበት ደረጃ የመስክ ምልከታ አካሄዱ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ብልፅግና ህብረቶች "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ሀሳብ የአባላት ኮንፈረንስ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መድረክ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በሀደሮ ቀበሌ በበጋ መስኖ የለማ ኩታገጠም የድንች ማሳ በከፊሉ
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨
🎤 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲደረግ የቆየው የ2018 በጀት ዓመት የ6ወር የፓርቲ እና የመንግሰት ስራዎች ግምገማና የአመራር ምዘና መድረክ ተጠናቀቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2018 በጀት አመት የ6 ወራት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች ግምገማና የጠቅላላ አመራር የምዘና መድረክ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የካቲት 07/2018 ዓ/ም
ወጣቶች በበጎ ፍቃድና በስፖርት ዘርፍ በማሳተፍ፣መዝናኛ ማእከላት በማብቃት ተጠቃሚነታቸው ማረጋገጥ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
መምሪያው የ2018 የግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የወጣቶች መዝናኛ ማእከላት ለማብቃት የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።
የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ረሻድ እንዳሉት የወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በበጎ ፍቃድ፣በስፖርት ዘርፉ ላይ ማሳተፍና መዝናኛ ማእከላት ማብቃት ያስፈልጋል።
በዞኑ ያሉ የስብእና ማእከላት በግብአትና በኢኮኖሚ በመደገፍ ከማዘውተሪያነት ወደ ስብእና ማበልጸጊያነት ማሸጋገር ይገባል ያሉት አቶ ሙራድ ሁሉም መዋቅሮች ቢያንስ አንድ ሞዴል ማእከል መፍጠር ግዴታ ነው ብለዋል።
የወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከኢንተርፕራይዝ እና ከስራ እድል ፈጠራ ጽ/ቤት ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል።
የዞናችን የስፖርት አቅምና ጸጋ በመለየት ፣በሁሉም የስፖርት አይነቶች በመሳተፍ እና የስፖርት ሀብት በተገቢው በመሰብሰብ የዞኑ የስፖርት ውጤታችንን ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በበጎ ፍቃድ የተጀመሩ ቤቶች በአፋጣኝ ማጠናቀቅ እንደሚገባና መጤ ባህሎች የሚያሰቀር ግብረ ሀይል እንዲቋቋም መክረዋል።
የመምሪያው ምክትልና የወጣት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሸምሱ ሸሀቡ በበኩላቸው በግማሽ ዓመቱ ከ434 ሺ በላይ ወጣቶች በማሳተፍ 856 ሺ 475 ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተናግረዋል።
በዚህም ከ470 ሚሊየን 787 ሺ ብር በላይ ከመንግስትና ከህዝቡ ይወጣ የነበረ ገንዘብ ማዳን ተችሏል ያሉት አቶ ሸምሱ የወጣቶች ማእከላት ከበጎ አድራጊ ድርጅቶች ጋር ተቀናጅቶ እንዲሰራ አሳስበዋል።
የመምሪያው ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አደም ሽኩር፦የስፖርት አደረጃጀቶችና ማዘውተሪያ ስፍራዎች ማጠናከር እንዲሁም ታዳጊ ስፖርተኞች ማፍራት ላይ በአጽንኦት እንዲሲራበት ተናግረዋል።
ስፖርቱ ህዝባዊ መሰረት ለማሰያዝ በሀብት አሰባሰቡ ላይ በአግባቡ መስራት ወሳኝ ተግባር ነው ያሉት አቶ አደም በቅርቡ በሚካሄደው የክልሉ ስፖርት ውድድር የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
የውስጥ ለውስጥ ውድድሮች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የገለጹት ኃላፊው የዞኑ ህዝብ የሚገልጽ ስቴዲየም እንዲገነባ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አቶ አደም አስታውቀዋል።
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የሴቶችና ወጣቶች ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ጥሩነሽ ምኑታ እንዳሉት የወጣቱ ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መቀናጀት፣በቁርጠኝነትና በኃላፊነት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ አካላት እንዳሉት በየአካባቢው ያሉ የወጣቶች ስብእና ማእከላት አገልግሎት አሰጣጣቸው ሰፊ ክፍተት የነበረባቸው ሲሆን በቀጣይ ግን በቂ ገንዘብ መመደብ እና የግንዛቤ ስራዎች ላይ ሰፊ ስራ መስራት ይጠይቃል።
በ16ቱ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ህብረተሰቡ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች እየሰራን ነው ያሉት ሀሳብ ሰጪዎቹ ስራ አጥ ወጣቶች በመለየት ስራ እንዲያገኙ ተሰርቷል።
በሁሉም የስፖርት አይነቶች ተሳታፊ በመሆን ከክልል እስከ ሀገር ውጤት ለማምጣት የበለጠ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸው የስፖርት ሀብት ገቢን አሟጦ መሰብስብ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
ቀጣይ ወልቂጤ ከተማ ላይ በሚካሄደው ክልል አቀፍ ውድድር በሁሉም ስፖርት አይነቶች ተሳትፎ በማሳደግ የተሻለ ውጤት ለማምጣት በትኩረት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
ወደ ባሕር አስተማማኝ ተደራሽነት!!
"በሰላማዊ ትብብር ወደ ባሕር አስተማማኝ ተደራሽነት ማግኘት ለኢኮኖሚያዊ የወደፊት ህይወታችን እና በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ መረጋጋትና ብልጽግና መሰረታዊ ነው።"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ
#AbiyAhmed #AfricanUnion #Ethiopia #አቢይአሕመድ #አፍሪካህብረት
የካቲት 06/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የወረዳ የፖሊስ አመራሮችና አባላት ማጥራትና ሂስ ግለ ሂስ ግምገማ መድረክ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በመድረኩ የክልሉ፤ የዞኑ እና የወረዳው ነባራዊ ሁኔታ የያዘው የግምገማ ሰነድ የቀረበ ሲሆን በሰነዱ ዙሪያ ከአባላት ጋር ውይይትና የግምገማ መድረክ ተካሄዷል።
የፖሊስ ተቋምን በማዘመን፣ አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት እና የወረዳውን ሠላም ለማስከበር የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ለቀጣይ ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት የሚያዘጋጅ የግምገማ መድረክ እንደነበር ተመላክቷል።
በመድረኩ የወረዳው ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሰማ በድሩ፣የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ጀማል አስፍር እዲሁም የወረዳው ፖሊስ አባላት ተሳትፈዋል።
የካቲት 06/2018 ዓ/ም
ከረዥም ጊዜ በኋላ የንፁህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚ በመሆናቸው ደስተኛ እንደሆኑ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የጅማ ወለኔ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የጅማ ወለኔ ከተማ በጀነሬተር የሚሰራ የጥልቅ ጉድጓድ የንጹህ መጠጥ ውሃ ከ7.5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 4.1 ኪ.ሜ መብራት ዝርጋታ እና ትራንስፎርመር በመአጸምና በመትከል ወደ መበራት የመቀየር ስራ መስራቱን የከተማው ማዘጋጃ ቤት አስታወቋል።
ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በወረዳው የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋንን ለማሳደግ የመንግስትና የተራድኦ ድርጅቶች እንዲሁም የማህበረሰቡና የባለሀብቱን አቅም በመጠቀም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
አቶ ሚፍታ አክለውም የጅማ ወለኔ ከተማ ነዋሪዎች የረዥም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የነበረው የንጽህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት የወረዳው መንግስት ከከተማው ማዘጋጃ ቤት ጋር በመሆን ከ7.5 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ የህዝቡን የልማት ጥያቄ መመለስ እንደተቻለ ጠቅሰው በዛሬው እለት የንጽህ መጠጥ ወሃ በመብራት ተቀይሩ መሞከሩንና ስኬታማ
መሆኑን አስተውቀዋል።
የጅማ ወለኔ ስራ አስኪያጅ አቶ ሱልጣን ተማም በበኩላቸው ለከተማው ማህበረሰብ የንፁህ መጠጥ ውሀ ተደራሽ ለማድረግ የክልሉ ውሃ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ ጥልቅ የጉድጓድ ውሃ ተቆፍሮ ነበር ያሉት ስራ አስኪያጁ የጀነሬተሩ የነዳጅ ፍጆታ ከፍተኛ በመሆኑ ህዝቡን ማስጠቀም እንዳልተቻለ አመላክተዋል።
ችግሩን ለመፍታት ማዘጋጃ ቤቱ ከወረዳው መንግስት በጋራ በመሆን ከ7.5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ
የትራንስፎርመር ግዢ በመፈጸምና በመትከል እንዲሁም
4.1 ኪ.ሜ መብራት ዝርጋታ በመካሄድ ወደ መብራት የመቀየር ስራ መስራቱን አቶ ሱለደጣን ተማም ገልጸው ለከተማው ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላቹ ብለዋል።
አቶ ደንበል መሀመድ እና ወ/ሮ ጎሃለም አበራ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የጅማ ወለኔ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ የከተማው ማህበረሰብ በንፁህ መጠጥ ውሀ እጦት እየተቸገረ መሆኑን አንስተው ከእንስሳት ጋር ከአንድ የምንጭ ውሀ ይጠቀሙ እንደነበር ጠቅሰው በዛሬው እለት ምስጋና ለወረዳው አስተዳደርና ለከተማችን ማዘጋጃ ቤት ይገባውና ንጽህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ መሆን ችለናል በማለት በቀጣይም መንግስት በሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች ከጎን በመሆን ለማገዝ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
