917
Подписчики
+124 часа
+17 дней
+730 дней
Архив постов
መጋቢት 04/2018 ዓ/ም
በጉራጌ ዞን የመሀል አምባ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የ 6ወር አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ የ6 ወር ዕቅድ አተገባበር ዙርያ የቦርድ አባላት ውይይት አካሄዱ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የኮሌጁ ዲን ወ/ሪት ሰላማዊት ኡርባኖስ አማካኝነት የተቋሙን የ6ወር አፈፃፀም አቅርበው ውይይት ተደርጎበት ሃሳብ አስተያየት ተሰጥቶበት ግምገማ መድረክ ተካሄዷል።
ባለፉት 6 ወራት የተሰሩ ስራዎች በማስቀጠል ቀሪ ስራዎች ላይ በቅንጅት እና በመናበብ የተቋም ተልዕኮ ግብ ማድረስ እንደሚገባ እና የተጀማመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው እና የውስጥ ገቢ ከማዳበር የፈጠራ ስራዎች ከመስራት በቴክኖሎጂ ማህበረሰቡ ከማስጠቀም አንፃር የተጀመሩ ስራዎች ፈጥኖ በማውጣት ለማህበረሰቡ ማሸጋገር እና ሀብት ማፍራት ይኖርበታል በማለት እና ዞኑ ከተቋሙ አቅም በላይ የሆነ የውስጥ ለውስጥ የመብራት ዝርጋት እና የተቋሙ ደረጃ ማሻሻል ጉዳይ የፖሊ ቴክኒክ ጥያቄ ፈጥኖ ከሚመለከተዉ አካል ጋር በመናበብ ምላሽ ሊያገኝ እንደሚገባ የቦርድ አባላት አስተያየት ሰጥተዋል።
መድረኩን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪና የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሚፋታ ሁሴን ፣ የጉራጌ ዞን ቴ/ሙ/ት/ስ/መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ስርገማ በጋራ የመሩት ሲሆን የዞን መምሪያ ሰወ ሃብት ዳይሬክቶሬት አቶ ተሾመ ተሰማ እና የወረዳ ቦርድ አባላት ተሳትፈዋል።
መጋቢት 03/2018 ዓ/ም
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የሚገኘው HLS አበባ ልማት ድርጅት አማካኝነት ለኤክስፖርት ገበያ
የተዘጋጁ የአበባ ምርቶች በምስል በከፊሉ:-
መጋቢት 03/2018 ዓ/ም
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ላጫ ጋሩማ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማና የተጓደሉ የአመራር ቦታዎችን መነሻ በማድረግ በሽግሽግና በምደባ የተለያዩ ሹመት ሰጥተዋል!!
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በዚህም መሰረት፦
1. አቶ መኩሪያ ተመስገን ፦የንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ
2. ወ/ሮ አርሽያ አህመድ ፦ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ
3. አቶ ታሪኩ ሃ/ማርያም ፦ የስራ እድል ፈጠራና የኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ም/ኃላፊና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኃላፊ
4. ማሬ ገ/መድህን ፦የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ም/ኃላፊና የቤቶች ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ
5, አቶ ታሪኩ ንዳ፦ የመልካም አስተዳደርና አካባቢ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ
6. ይብጌታ ንጋ፦ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ም/ኃላፊና የመሬት ልማት ማኔጅመንት ዘርፍ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል!!
መረጃው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ነወ።
የካቲት 03/2018 ዓ ም
የመንግስት የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ በማስተካከል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የ2018 በጀት ዓመት የ2ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም የስትሪንግ ኮሚቴ ከወረዳው አመራር ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ።
በሁሉም ተቋማት ለማህበረሰቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥ ሲቪል ሰርቫንት ለመፍጠር በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ጽ/ቤቱ አክሎ ገልጿል።
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ፋሪስ ከማል አማካኝነት የ2018 ዓ.ም በ2ኛ ሩብ አመት በሴክተሩ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት በዝርዝር ቀርቦ ከባለድርሻ አካላት ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን በተነሱ ጉዳዮች ምላሽና አስተያየቶች ተሰጥቶባቸዋል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ እንደገለፁት የሕዝቡን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት እና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲረጋገጥ የፐብሊክ ሰርቪስ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
የተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ለመፍታትና አገልግሎት አሰጣጡን ሊያረጋግጡ የሚችሉ አሰራሮችን በመዘርጋት በተገቢው መሰራት እንዳለበት ጠቅሰው
በመንግስት የተቀመጡ ስትራቴጂዎች፣ ግቦችና እቅዶች ተፈፃሚ እንዲሆኑና የአሰራር ስርአቱ ለማሻሻል የሲቪል ሰርቫንቱ ዝግጁነትና ቆራጥነት ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል።
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ፋሪስ ከማል ተቋማት የሚቀርቡ አቤቶታና ቅሬታዎች የመፍታት እና ሚፈለጉ መረጃ በወቅቱ ለሚመለከተው አካል ከማስተላለፍ አንጻር የማስተዋሉ ችግሮች በቀጣይ ሊታረሙ እንደሚገባ ተናግረዋል ።
በሁሉም ተቋምት ማህበረሰቡ ጥራት ያለው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በአግባቡ እንዲያገኝ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።
የአገልግሎት ፈላጊውን የማህበረሰብ ክፍል ፍላጎት ማሟላት የፐብሊክ ሠርቪስ ተቋም ብቻ ሳይሆን ሁሉም ተቋማት እና የሚመለከታቸው አካላት የድርሻቸውን ወስደው በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የወረዳው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
መጋቢት 02/2018 ዓ/ም
ጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ለ7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ የተወዳዳሪ እጩዎችን በይፋ አስተዋውቋል!!
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ለ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በወረዳው ምርጫ ክልል የሚወዳደሩ እጩዎችን በይፋ የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል።
በመድረኩ የተገኙት የፓርቲው አመራሮች እንደገለጹት፣ እጩዎቹ በስነ-ምግባር የታነጹ፣ ለህዝብ አገልግሎትና የልማት ተደራሽነት የሚተጉ እና የፓርቲውን ራዕይ በአግባቡ የሚያስፈጽሙ ብቁ ግለሰቦች መሆናቸውን ገልፀዋል።
የብልፅግና ፓርቲ በምርጫ ቅስቀሳው ወቅት የሰላም፣ የአንድነት፣ የልማት ፣የሁለቱ ውሃዎች፣ የዴሞክራሲ ግንባታ ጉዳዮችን እንደ ዋና አጀንዳ እንደሚይዝ ተገልጿል።
ፓርቲው የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የጀመራቸውን ስራዎች ለማጠናከር ዝግጁ መሆኑንም ተመላክቷል።
በመድረኩ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ፣የወረዳው ፓ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብድረሂም ርዳ ፣የጉራጌ ዞን ፋይናስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዱ ሀሰን እና የወረዳው ጠቅላላ አመራሮች ተሳትፈዋል!!
መጋቢት 01/2018 ዓ.ም
በሳይንስና ቴክኖሎጂ የዳበረ ትውልድ በመፍጠር የሀገር ብልፅግና ማረጋገጥ እንደሚገባ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ከገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር "አዲስ እይታ ለአዲስ ፈጠራ ለተሻለ ውጤት "በሚል መሪ ቃል የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ ቀን በገደባኖ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከብሮ ዋለ።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሳይንስ ና ቴክኖሎጂ ፅህፈት ቤት የፈጠራ ስራ ሂደት ባለሙያ አቶ ከይረዲን መሀመድ እንደገለፁት ተማሪዎች የሰሩትን የፈጠራ ስራ አስፈላጊና ችግር ፈቺ መሆኑን ተናገረው የፈጠራ ስራ ለመስራት ሲሞክሩ የሳይንስ መምህራን ድጋፍ መጠየቅ እንደሚገባቸውና የፈጠራ ስራ ባለቤት እንደሚችሉ ገልፀው ዛሬ የሞከሩት የፈጠራ ስራ ለነገ የተሻለ ለመስራት መነሳሳት መቻል እንዳለባቸውና ተማሪዎች የፈጠራ በትምህርት በተግባር ማረጋገጥ ይኖርበታል ብለዋል ።
ባለሙያው አክለውም ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች መነሻው ትምህርት ቤት በመሆናቸው በሳይንስና ቴክኖሎጂ የዳበረ ትውልድ በማፍራት የሀገር ብልፅግና ለማረጋገጥ ሁሉም ትምህርት ቤቶችና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለዘርፉ ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ፅህፈት ቤት የመምህራን ትምህርት አመራር ስራ ሂደት ባለ ሙያ አቶ ሞላ አስፋ እንደተናገሩት የፈጠራ ስራ ሰዎች ባለመዱት መልኩ ማሳየት መሆኑ ተናግረው እያንዳንዱ የፈጠራ ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ ማሻሻል ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ተማሪዎች የሰሩት የፈጠራ ስራ ማንዋል በማዘጋጀት ገለፃ ማድረግ እንደሚገባቸው ገልፀው ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ እንደ ሀገር ከፍተኛ ተኩረት ተሰጥቶ እየተሰራበት ያለ ዘርፍ በመሆኑ ይህ ዘርፍ ትልቅ ትኩረት የሚሻ በመሆኑ በአንድ ተቋም ብቻ የሚተው ጉዳይ ባለመሆኑ ሁሉም የሚመለከተው አካላት በጋራ ተቀናጅተው በመስራት ዘርፉ ውጤታማ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
የገደባኖ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህር አቶ ዳንኤል እምዩ ባስተላለፉት መልዕክት የፈጠራ ትንሽ ሚባል እንደሌለ ሊበረታታ የሚገባው በመሆኑ እንደ ትምህርት ቤት ለፈጠራ ስራ ለሚሰሩ ተማሪዎች የሚያበረታቱ መሆኑ ተናገረው ተማሪዎች የትምህርት ቤት ብቻ ተወዳዳሪ ሳይሆኑ እንደ ሀገር ተወዳዳሪ ለመሆን ጠንክራችሁ በመስራት በፈጠራ ስራ ውጤታማ መሆን እንደሚገባቸው አስታውሰው ከሳይንስ መምህራን ድጋፍ በማግኘት ያላችሁ የዕውቀት ክህሎት በማስፋት በፈጠራ ስራ ውጤታማ መሆን እንደሚገባቸው እና በፈጠራ ስራ የተሸለ ተሳትፎ ላደረጉ ተማሪዎች በአመቱ መጨረሻ የማበረታቻ ሽልማት እንደሚዘጋጅ ገልፀዋል።
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ ቀን አስመልክቶ ተማሪዎች የሰሯቸው የፈጠራ ስራዎቻቸው ያቀረቡ ሲሆን በፈጠራ ስራ ለተሳተፉ ተማሪዎች የዕውቀትና ሰርተፍኬት የተበረከተላቸው ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ በተማሪዎች ግጥም እና ዜና ቀርቧል።
መጋቢት 01/2018 ዓ/ም
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በእንስሳት ሀብት ልማት የተጀመረውን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማጠናከር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ከወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል ድጋፍ የተገኘ 300 ኮኮስ የዶሮዎች ዝርያዎች ለሰፋቶ ቀርሳ ቀበሌ እና ለመሀል አምባ ከተማ መሰራጨቱን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አክሎ አስታውቋል።
እነዚህ ኮኮስ ዝርያዎች በምርታማነታቸው የታወቁና የተኛውም በሽታ መቋቋም የሚችሉ ሲሆኑ ለሁለቱ ቀበሌዎች ለ70 አባወራዎች በሌማት ትሩፋት መንደር በድጋፍ መልክ መሰራጨቱ ተመላክቷል።
