924
Подписчики
Нет данных24 часа
+57 дней
+930 дней
Архив постов
ነሐሴ 28/2017 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ
"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በተሻገረ ህልም፣ በላቀ ትጋት፣ አስተማማኝ ነገን መስራት! በሚል መሪ ቃል ለሁለት ቀን የሚሰጠው በየ ደረጃው አባላት ስልጠና መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ግድቡ ተጠናቋል ሲባል ምን ማለት ነው ?
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአጠቃላይ ከ13 ተርባይኖች 5,150 ሜጋዋት ማመንጨት የሚችልበት አቅም ላይ ይገኛል።
- እስካሁን ከ71 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውሃ ተይዟል። ቀሪው 2.1 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በመጪዎቹ 7-10 ቀናት ውስጥ ይያዛል።
- በግድቡ የተያዘው ውሃ ወደኋላ ከ246 ኪሎ ሜትር በላይ ይተኛል፤ እስካሁን ባለው 240 ኪሎ ሜትር ላይ ተደርሷል። ርቀቱ ከአዲስ አበባ እስከ ሻሸመኔ ይሆናል።
ኢትዮጵያ ገንብታ ባጠናቀቀችው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አማካኝነት ኃይል እያገኘች ትገኛለች።
የኃይል ማመንጫ ግድቡ ነሐሴ 24/2017 ላይ 2530 ሜጋ ዋት በማመንጨት ኃይል መስጠት ችሏል።
- ግድቡ ተጠናቋል ሲባል ምን ማለት ነው ?
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋናው ግድብ በ1.8 ኪሎ ሜትር እርዝማኔና 145 ሜትር ከፍታ ተገንብቶ ተጠናቋል።
በአጠቃላይ ከ10 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር ያህል ኮንክሪት (RCC) ሙሌት ተካሂዷል።
የግድቡ የስረኛው ክፍል 150 ሜትር ስፋት አለው። የላይኛው ክፍል ደግሞ 11 ሜትር ስፋት ሲኖረው ሁለት መኪኖችን ጎን ለጎን ማሳለፍ ይችላል።
ኃይል ማመንጨት የሚችሉ 13 ተርባይኖች ተከላ የተጠናቀቀ ሲሆን ከእነዚህ ተርባይኖች 5150 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ይቻላል።
በግድቡ የውጨኛው ክፍል የሚታዩት የብረት አሸንዳዎች በግራ እና በቀኝ በኩል ላሉ ኃይል የሚያመነጩ ተርባይኖች ውኃ የሚተላለፍባቸው ሲሆን እያንዳንዳቸው 8.5 ሜትር ዲያሜትር ስፋት አላቸው። 300 ሜትር ኪዩብ በሰከንድ ማሳለፍ አቅም አላቸው።
በግራ የኃይል ማመንጫ 7 ተርባይኖች ሲኖሩ በቀኝ የኃይል ማመንጫ ደግሞ 6 ተርባይኖች ሙሉ ለሙሉ ተከላቸው ተጠናቋል።
ከዚህ ውስጥ 3ቱ የቅድመ ኃይል ተርባይኖች በመጠን አነስ ያሉ ሲሆን ቀሪዎቹ 10 ተርባይኖች እያንዳንዳቸው 400 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም አላቸው።
ግድቡ ያመነጨው ኃይል በሁለት መስመሮች ማለትም በጣና በለስ አድርጎ በደብረ ማርቆስ እንደዚሁም በአሶሳ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ብሔራዊ የኃይል ቋት በመግባት ላይ ይገኛል።
ከዋናው ግድብ በተጨማሪ የህዳሴ ግድቡ የኮሬቻ ግድብ (Saddle Dam) ከዋናው ግድብ በ15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።
ርዝመቱ 5.2 ኪሎ ሜትር እና 50 ሜትር ከፍታ ላይ ሆኖ ሙሉ ለሙሉ በ15 ሚሊየን ሜትሪክ ኪዩብ ድንጋይ የተሞላ ነው። የተያዘው ውሃ ሾልኮ እንዳያልፍ ከ30-40 ሴንቲ ሜትር ውፍረት ባለው ኮንክሪት ተለብጧል።
እስካሁን ከ71 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውሃ ተይዟል። አጠቃላይ ግድቡ የሚይዘው 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ነው፤ የሚቀረው ከ2.1 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ያልበለጠ ነው።
ቀሪው 2.1 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በመጪዎቹ 7-10 ቀናት ውስጥ ይያዛል።
በግድቡ የተያዘው ውሃ ወደኋላ ከ246 ኪሎ ሜትር በላይ ይተኛል። እስካሁን ባለው 240 ኪሎ ሜትር ላይ ተደርሷል። ርቀቱ ከአዲስ አበባ እስከ ሻሸመኔ ያልፋል።
የኮሬቻ (saddle dam) 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ለመያዝ ወይም የሚያመነጨውን 5150 ሜጋዋት ለማመንጨት የሚያስፈልገውን የውሃ መጠን ለመያዝ በጣም አስፈላጊ ነው።
#ታላቁየኢትዮጵያህዳሴግድብ #Dam #EthiopianDam
ናሴ 28 2 ክም 17 ኢ/ዘማን
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረደ
በመጎራጉር ቀበሌ በልሞት ደር ያለይ የስረይ ሠኜ አሁ ያለቢ አህዋልከ በእንዥነ፦
በሚቀጥሉት ዓመታት እንደ ሕዳሴ ግድብ አይነት ትላልቅ ፕሮጀክቶች ይጀመራሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚቀጥሉት ከ5 እስከ 15 ዓመታት እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አይነት ትላልቅ ፕሮጀክቶች እንደሚጀመሩ አረጋገጡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የጉባ ላይ ወግ" በተሰኘ ልዩ ቃለ ምልልስ ላይ ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት ፥ ግድቡ በተሟላ ደረጃ አልቆ ሥራ ከጀመረበት ጀምሮ የኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካዊ ኩስመና ታሪክ አበቃ ማለት ነው።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ጂኦፖለቲክስ ቁመና አደገ ፤ተሻሻለ ማለት እንደሆነ በማንሳት ÷ ለኢትዮጵያ እስካሁን ባለፈችባቸው ጊዜያቶች ሁሉ ትልቁ ፈተና ከትልቁ ዓባይ ጋር የተያየዘ ነው ብለዋል።
ሌሎች ችግሮች በተለያዩ አካባቢዎች ችግር የሚፈጥሩ ባንዳዎች እንደሆኑ እና የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ እናት እና ባለቤት ትልቁ የሆነው ዓባይን ፈታች ማለት ትንንሾቹን ለመፍታት ቀላል እንደሆነ አመልክተዋል።
ቀይ ባሕር የዛሬ 30 ዓመት እኛ ጋር ነበር፤ የተፈጠረውም ስህተት የትናንት ስህተት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ይሄ ስህተት ነገ ይታረማል፤ ዓባይ ግን ለሺህ ዓመታት የዘለቀ ችግር የተፈታበት ነው ሲሉ አስረድተዋል።
የዓባይ ጉዳይ ከሌሎች ችግሮቻችን በሦስት ምክንያቶች በጣም የሚበልጥ እንደሆነ ገልጸው÷ የመጀመሪያው በግድቡ መገንባት እንጎዳለን ብለው የሚያስቡ ወንድሞቻችን እንደማይጎዱ ሲያዩ ነገሩ እንዲረግብ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል በባዕዳን መላክ ሱሳቸው የሆኑ ሃይሎች ባዕዳዎቹ ረገብ ሲሉ ባንዳዎቹ እንደሚመናመኑ እንዲሁም በሚቀጥሉት ከ5 እስከ 15 ባሉ ዓመታት እንደ ሕዳሴ ግድብ አይነት ትላልቅ ፕሮጀክቶች እንደሚጀመሩ አረጋግጠዋል።
አሁን ላይ ጀመረን መጨረስ እንደምንችል አይተናል፤ ትልቁ ዓባይን ማሳካት እና ችግሩን መፍታት ከቻልን ሌሎች ትንንሽ ችግሮችን መፍታት ማሳካት እንደሚቻል እና ይህም ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ቦታችንን እንዲስተካከል ያደርጋል ነው ያሉት።
በእያንዳንዷ ቀን ኢትዮጵያ ከፍ ያለ ጉዳይ ጀምራ እየጨረሰች ኢኮኖሚያዊ ስፍራዋን ታሻሽላለች፤ የድህነት እና የረሃብ ስሟም ይቀየራል ፤ ይህ ምንም ጥርጥር የለውም ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ የበለጸገች፣ ፍላጎቶቿን የምታስከብር፣ ከዓለም ስንዴ እና ፍትሕ የምትለምን ሳትሆን እራሷ የምታረጋግጥ እንደምትሆን አንስተው÷ ይሄም በዓባይ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፤ በሌሎቹምእየተደገመ ይሄዳል ብለዋል።
ከዚህ ባለፈም የጂኦፖለቲክስ ኩስመና ይሻሻላል፤ በከፍተኛ ፍጥነት በሁሉም ዘርፍ ሩጠን የመጨረሻዋን መስመር ቆርጠን ብልጽግናችንን እናረጋግጣለን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
ነሐሴ 26/2017 ዓ.ም
የጳጉሜ አምስቱ ቀናቶች አከባበርን አስመልክቶ በሚተገበሩ ተግባራት ከስተግባሪ ተቋማት ጋር ውይይት ተደረገ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በ2017 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት በወረዳ ደረጃ በተለያዩ ጉዳዮች ለማክበር እንዲያስችል ተቋማት ስለሚኖራቸው ተግባራትና ኃላፊነት እና የማስፈጸሚያ እቅድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
የጳጉሜን ቀናቶች አስመልክቶ የሚከናወኑ ተግባራት እቅድ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት የጳጉሜን ቀናቶች ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ከምትለይበት አንዱ የአስራ ሶስት ወራት ፀጋ ባለቤት አንዱ በመሆኗ በዕቅዱ መሰረት ለማከናወን አስተግባሪ ተቋማት ከወዲሁ በመዘጋጀት የሚከናወኑ ተግባራት በእቅዱ መሰረት መተግበር እንዳለበት አስገንዝበዋል።
የአመቱ መጠናቀቂያ ብቻም ሳይሆን የአዲስ ዓመት መቀበያ ከመሆኑ አንፃር በእቅዱ መሰረት ለማከናወን አስተግባሪ ተቋማትና ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን መስራትና በመቀናጃት ደማቅ ማድረግ እንደሚገባ አቶ አ/ረሂም ርዳ አክለው ገልጸዋል።
አምስቱ የጳጎሜ ቀናቶች የተለያዩ ስያሜዎች የተሰጣቸው ሲሆን ተለያዩ ፕሮግራሞች ማለትም ፓናል ውይይት፣የኪነ-ጥበብ ስራዎች፣የልማት ስራ ጉብኘት፣የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች፣የእግር ኳስ ውድድር፣ፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽን፣ዶክመንተሪ ፊልሞች ማሳየት፣ከፖሊስ እና ሌሎች ከጸጥታ አካላት ጋር የእግር ጉዞ፣ የሰንደቅ ዓላማ መስቀል እንዲሁም አጫጭር መልእክቶች ማስተላለፍ እና ሌሎችም መርሃ ግብሮች በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር በመግባባት ውይይቱ ተጠናቋል።
ነሐሴ 26/2017 ዓ.ም
የመልካም አሰተዳደር ችግሮችን በተግባር ለመፍታት በየደረጃው ያለው አመራር ዝግጁነቱንና ቁርጠኝነቱን ማሳደግ እንደሚጠበቅበት ተገለጸ።
፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "የአገልግሎት ልህቀት ለኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ የመልካም አስተዳደር የአመራር መድረክም ተካሄዷል።
በዚህ ወቅት የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚፍታ አረቦ የ2017 ዓ.ም ተለይተው የተፈቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የ2018 ዓ.ም የተለዩ የመልካም አስተዳደር እቅድ አቅርበዋ ውይይት ተደርጎበታል።
በመድረኩ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በየደረጃው የሚገኘው አመራር የመልካም አሰተዳደር ችግሮችን በተግባር ለመፍታት ዝግጁነቱንና ቁርጠኝነቱን ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የብልሹ አሠራሮች መነሻ የሆኑ ጉዳዮችን አስቀድሞ በውል መረዳት እንደሚገባና ተግባራዊ ምላሽም መስጠት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑን አቶ ሚፍታ አክለው ገልጸዋል።
የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ አመራሩ በየዘርፉ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተገቢው ለመመለስ ወቅቱን የሚመጥን የአመራር ስብዕና በማላበስ ከመቼውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባት ተናግረዋል።
አቶ አ/ረሂም ርዳ አክለውም ሁሉም አመራር የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በወሳኝ መልኩ ለማረጋገጥ በተሰማራበት መስክ አርበኛ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በመድረኩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በቅርብ ክትትልና ድጋፍ ለመፍታት የሚያግዙ የቀጣይ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።
ናሴ 26 2 ክም 17 ኢ/ዘማን
" ተታገዞት ሙርተኝነት " ቢላን ቡር ሁስብ በደሰ ቀበሌ በልሞት ደር ያለይ የስረይ ሠኜ አሁ ያለቢ አህዋልከ በምሴ፦
#ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር!
በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአመራሮች የውይይትና የስልጠና መድረክ ተጠናቀቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በመድረኩም ላይ ባለፉት ሰባት አመታት በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ስኬቶችን ይበልጥ ለማስቀጠል ፣ ጉድለቶችን በማረም እንደ ሀገር የጀመርነውን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ ማሳካት በሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ በመወያየት በላቀ ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት ለመፈፀም የጋራ መግባባት መፍጠር ተችሏል።
ባለፋት የለውጥ ዓመታት የገጠሙንን ፈተናዎች ወደ ድል በመቀየር የነበሩ ሀገራዊ ስብራቶቻችንን መጠገን የሚያስችል ሁለንተናዊ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉን በውይይቱ ተነስተዋል።
በወረዳችን የብልጽግና ተምሳሌት ፣ የተሞክሮ መቀመርያ ማዕከልና የሰላም ሰገነት ለማድረግ በተሰጠው ቁርጠኛ አመራር መላ ህዝቡን በተደራጀ አግባብ በማሳተፍ አመርቂ ስኬቶችን ማስመዝገብ እንደተቻለም በመድረኮቹ ተገልፀዋል።
ጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ፣ የመንግስት የማስፈፀም አቅም በማጎልበት ለጠንካራ ሀገር ግንባታ ወሳኝ መሆኑ ታምኖበት በተሰራው ሥራ ሀገራችን የጀመረችው የከፍታ ጉዞ ወደ ማንሰራራት የሚያደርሱ በርካታ ተምሳሌታዊ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችለናል።
የተደረገው ውይይት ፓርቲያችን የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን ለማድረግ የሰነቀውን ዓላማ እውን ለማድረግ በአመራሩ ዘንድ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት የፈጠረ መሆኑ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል።
በወረዳው የሚገኘው አመራር ወቅታዊ ሀገራዊ ፣አህጉራዊ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች በመረዳት የፓርቲያችንን ተልዕኮ በተቀናጀ መልኩ በብቃት ለመፈፀም አቅም እንደሚሆን በአመራሮቹ ተነስቷል።
በመጨረሻም ሁሉም አመራር የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተሰማራበት መስክ ሁሉ አርበኛ መሆን እንዳለበት የጋራ መግባባት በመፍጠር ውይይቱ ተጠናቋል።
