ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку 👈

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

Открыть в Telegram
924
Подписчики
Нет данных24 часа
+57 дней
+1030 дней
Архив постов
#ዜና ሹመት 1) ወ/ሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ 2) አቶ ያህያ ሱልጣን የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ 3) አቶ ታምራት ውድማ የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ 4) አቶ ነጋ አስፋው የጉራጌ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ ሆነው በሽግሽግና በምደባ ተሹመዋል!! መረጃው የጉራጌ ዞን ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው።

ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም ወረዳ አቀፍ የዳልጋ ከብቶችን በሆርሞን ማድራት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በዛሬው እለት በመሀል አምባ ከተማ ማስጀመሩን ገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በመረሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚፍታ አረቦ በበኩላቸው የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን አርሶ አደሩ ብልጽግናውን ማረጋገጥ የሚችለው የተሻሻሉ የከብት ዝርያዎችን መጠቀም ሲችል መሆኑን ተናግረዋል። የከብቶችን ዝርያ በማሻሻል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት በማሳደግ መንግስት በሌማት ትሩፋት መረሀ ግብር ባወረደው መሰረት አንድ አርሶ አደር አንድ የተሻሻለ ዝርያ እንዲኖረው በማድረግና የከብቶቹን ስርዓተ ምግብ በማሻሻል የወተት ምርትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። በዛሬው እለት ሆርሞን ማድራት ቴክኖሎጂ አማካኝነት አራት ቀበሌዎች በአደረጃጀት ከብቶችን የመለየት ስራ በመስራት በዛሬው እለት ንቅናቄ መጀመሩን አስታውቀዋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር መርጋ በዚህ ወቅት እንዳሉት በወረዳው እንስሳትን በሆርሞን በማድራትና በማዳቀል ዝርያ የማሻሻል ስራ ከተጀመረ በርካታ አመታት ማስቆጠሩና በዚህም አመርቂ ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል። ከዚህ በፊት በተሰሩ የከብት ዝርያ የማሻሻል ስራዎች ላይ የተሻለ አፈጻጸም መኖሩና በዘንድሮው አመትም አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ ስራውን በወረዳው መሀል አምባ ቀበሌ በንቅናቄ መጀመሩ አስታውቀዋል። የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የእንስሳትና አሳ ሀብት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፈድሉ ኡስማን የከብቶችን ዝርያ በማሻሻል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ አውስተው እስካሁን በወረዳው14 ሺህ 9 መቶ ዝርያቸው የተሻሸሉ ከብቶች መኖራቸውን ተናግረዋል። አቶ ፈድሉ ኡስማን አክለውም በወረዳው በዘንድሮው አመት በ3ቱ በዝርያ ማሻሻል ዘዴዎች ማለትም በተሻሻለ ኮርማ፣በሲንክሮናይዜሽን እና በመደበኛ ማዳቀል ስራ 2 ሺህ 6 መቶ 40 ከብቶችን ለማዳቀል ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸው በዚህም 8 ሺህ 205 ቶን የወተት ምርት እንደሚጠበቅና 1 ሺህ 5 መቶ 34 ዝርያቸው የተሻሻሉ ጥጃዎችን ለማግኘት ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። በዘንድሮ አመትም በሲንክሮናይዜሽን በወረዳው በአንድ ክላስተር በአራት ቀበሌዎች ከ250 ከብቶች በላይ ለማዳቀል ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል። በመጨረሻም ሆርሞን የተሰጣቸው ከብቶች ከበሬዎች ንክኪ በማራቅ ፍላጎት በሚያሳዩበት ቀን አርሶ አደሮች ከብቶቹን ማዕከል ማምጣት እንደሚጠበቅባቸውና በሶስተኛው ቀን ሁሉም ሆርሞን የተሰጣቸው ከብቶች ወደ ማዕከል ማምጣት እንዳለባቸው አቶ ፈድሉ ኡስማን መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በደነብ ቀበሌ የ2ኛ ዙር የሴቶች የልማት ህብረት ሞዴል ቀበሌ መመረቁን የወረዳው ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በምረቃው ስነ ስርዓት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሚፍታ አረቦ እንደገለጹት የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሴቶችን በልማት ህብረት በማደራጀት የቁጠባ ባህላቸውን ማሳደግ ፣የጤና ፓኬጆችን መተግበር፣ እንዲሁም የግብርና ኢኒሼቲቮችን ለመጠቀም ወሳኝ ሚና እንዳለው ጠቅሠው ወደ ሁሉም ቀበሌዎች ማስፋት እንደሚገባ አሳስበዋል። የወረዳው ሴ/ህ/ጉ/ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈትያ መህዲ በበኩላቸው የሴቶች የልማት ህብረት አረደጃጀቱ ሴቶች የመደራጀት መብታቸውን የሚያረጋግጡበት እንደሆነ እና የአደረጃጀቱን በማጠናከር ሴቶች በግብርናው፣ በጤናው፣ በትምህርቱ ዘርፍ ንቁ ተሳታፊነታቸውንና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ብሎም ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ለማሳደግ በጋራ ቁጠባ ለማድረግ እንደሚያግዝ ገልጸው በዚህም አበረታች ለውጦች እየታዩ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በዘንድሮ በጀት ይህ ቀበሌዎችን የማስመረቅ ተግባር ልዩትኩረት በመስጠት ተቋማቸው እንደሚሰራ አንስተው የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራርና ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ወይዘሮ ፈትያ አክለው ገልጸዋል፡፡ በፕሮግራሙ የመስክ ጉብኝት እንዲሁም የእውቅናና ሽልማት ስነ ስርዓት የተካሄደ ሲሆን በዚህም የላቀ አስተዋጽኦ ያደረጉ የቀበሌ ባለሙያዎች፣ ሴቶች አንዲሁም የቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤቱ ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በመጨረሻም ለ3ኛ ዙር ሞዴል ቀበሌ ልየታ እና የ6 ተቋማት ኅላፊዎች የባለድርሻ አካላት የጋራ የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ በፕሮግራሙ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የዘርፍ ኃላፊዎች፣ የጤና ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የግብርና ጽ/ቤት ም/ኃላፊ፣ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽ/ቤት የማኔጅመንት አካላት፣ የቀበሌ ባለሙያዎች እና የሴቶች ልማት ህብረት አባላት ተገኝተዋል፡፡ መረጃው የወረዳው ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ነው።

ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት በተለያዩ ምክንያቶች ክትባት ጀምረው ያቋረጡ እና ምንም ያልጀመሩ ህፃናትን በመለየት ተገቢው የክትባት አገልግሎት እንዲያገኙ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ጽህፈት ቤቱ ከመጪው ሰኞ ጥቅምት 17/ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ ክትባት በዘመቻ ለመስጠት የሚያስችል ኦረንቴሽን ለጤና ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት ሰጥቷል። ኦረንቴሽኑን የሰጡት የገ/ጉ/ወ/ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙባሪክ ሰይፉ እንደተናገሩት በወረዳው ክትባት ያላገኙ እድሜያቸው ከ1 አመት በታች የሆኑ ህፃናት እና ክትባት ጀምረው በተለያዩ ምክንያቶች ያቋረጡ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑና  በሁሉም ቀበሌ በየልማት ቡድኑ ለተለዩ ህፃናት ይሰጣል ብለዋል። በወረዳ ደረጃ በሁሉም ቀበሌዎችና ከተሞች ከአንድ እስከ 5 አመት እድሜ ያላቸው ዜሮ ዶዝ 3 ሺህ 61፣ ተከትበው ያልጨረሱ አንደር ዶዝ 2 ሺህ 508 ህፃናት እንዲሁም የኩፍኝ ክትባት ላልወሰዱ 5 ሺህ 84 ህፃናት የክትባቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ ስለመሆኑ አቶ ሙባሪክ ሰይፉ አስታውቀዋል። የጤና ባለሙያዎች እና በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ዘመቻውን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በየትኛውም አካባቢ ክትባት ማግኘት ያለባቸውን በሙሉ የክትባቱ ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ አቶ ሙባሪክ አክለው አስገንዝበዋል። ክትባቱ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የገለፁት አቶ ሙባሪክ ዘመቻው በተጨማሪ ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ተግባራት የሚከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል። ይኸውም ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ሆኖ ክትባት ያልጀመሩና ጀምረው ያቋረጡ ህጻናትን በክትባት ተደራሽ ማድረግ፤ የስርዓተ-ምግብ ደረጃ ልየታና ህክምና እንዲሁም ፌስቱላና የማህጸን ወልቃት ልየታ በተቀናጀ መልኩ በዘመቻ መልክ ተጀምሮ በመደበኛነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። ኦረንቴሽኑ በጽህፈት ቤት ደረጃ ዛሬ የተሰጠ ሲሆን በመጪው ዕሁድ ደግሞ ለጤና ጣቢያ ባለሙያዎች እንደሚሰጥ ተገልጿል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።

ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም መንግስት በሚያወርዳቸው ህዝብን ተጠቃሚ በሚያደርጉ አሰራሮች ሴቶች መሪ ተዋናይ ሆነው የእድሉ ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሆነ የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የእሬሶ ቀበሌ የሴቶች ገንዘብ ቁጠባ ብድር መሰረታዊ ህብረት ስራ ሀላፊነቱ የተወሰነ የሴቶች የልማት ህብረት ወፍጮ ቤት እና በኦቼና አንቀዲን ቀበሌ የኢንሾላይ የሴቶች የልማት ህብረት ማሳ ተጎብኝቷል። የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ነጅቢያ ማህመድ በወረዳው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት ሴቶች በተለያዩ አደረጃጀቶች በማደራጀትና በማሳተፍ መብቶቻቸው እንዲያስከብሩና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀት 1ለ10 አባላት ያላቸው እንደሆነም ያመላከቱት ሀላፊዋ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት የበለጠ እንዲረጋገጥ እየተሰራ እንደሆነም አስረድተዋል። በዞኑ 7ሺህ 3 መቶ 95 የሴቶች የልማት ህብረትና ከ22 ሺህ በላይ የ1ለ10 አደረጃጀት እንዲሁም 2መቶ 7 ሺህ 103 አባላቶች በልማት ህብረት ተደራጅተው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያረጋገጡ እንደሆነም አመላክተዋል። በሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀት የሚፈለገው ውጤት እንዲመጣ የዞኑ መንግስትና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ትልቅ እገዛ እያደረጉላቸው ሲሆን ለዚህም ከፍተኛ ምስጋናም አቅርበዋል። መንግስት በሚያወርዳቸው ኢንሼቲቮች ሴቶች መሪ ተዋናይ ሆነው የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሰፋፊ ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱም አመላክተው የሴቶች የልማት ህብረት በመኽር እርሻ በበልግ እርሻ ፣በመስኖ ልማትና በሌማት ቱሩፋትና በሌሎችም ዘርፎች በርካታ ስራዎች መሰራቱና በተጨባጭ ውጤት ማምጣት ተችሏል ብለዋል። በ15ቱም መዋቅሮች በመኽር እርሻ በርካታ የወል መሬቶች በሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀት ማልማት እንደተቻለም ያስሩት ወይዘሮ ነጅቢያ ሴቶች በመስኖ ልማት ስራ ለሀገርም ተሞክሮ የሚህን ስራ እየሰሩም እንደሆነም አስረድተዋል። ከሌማት ቱሩፋት ጋር ተያይዞ 30 40 30 ኢንሼቲቭ በፍራፍሬና በጎሮ አትክልት ጎመን ፣ድንች ፣ቀይስር በማምረት ከራሳቸው አልፈው ለገበያ የሚያቀርቡ ሴቶች መፍጠር አስታውሰው የአንድ ቀንና የ45 ቀን ጫጩት ላይ ተሰማርተው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያረጋገጡ እንደሆነም አስረድተዋል። ሴቶች በእደ ጥበብ፣ በሸክላ ስራና ፣በእጅ ስራ ውጤቶች የጉራጌን ባህል በማስተዋወቅና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው ለማረጋገጥ ትልቅ ስራ እየሰሩ እንደህነም ጠቁመው ከዚህም ባሻገር ሴቶች በንግድ ስራ ፣በእርባታ ስራ የተሻለ ስራ እየሰሩ እንደሚገኝ ተናግረው በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በእሬሶ ቀበሌ ሴቶች ገንዘብ ቁጠባ ብድር መሰረታዊ ህብረት ስራ ሀላፊነቱ የተወሰነ ማህበር የሴቶች የልማት ህብረት ወፍጮ ቤት ከፍተውና በግብርና ስራ መስማራታቸውም ጠቁመው የእነዚህም ተሞክሮ ወደ ሌሎች አካባቢዎች መስፋት እንዳለበትም አስረድተዋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ፈቲያ መህዲ በበኩላቸው በወረዳው በሴቶች የልማት ህብረት ውጤታማ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ተናግረው ሴቶች በቁጠባ ፣በጤና ፣በትምህርትና በሌሎችም ዘርፎ በመወያየት ዘርፈ ብዙ ችግሮች እየቀረፉ እንደሆነም አመላክተዋል። በወረዳው የሴቶች የቁጠባ ባህል እያደገ ሲሆን አሁን ላይ በሴቶች የልማት ህብረት ካፒታልን ሳይጨምር ከ9 ሚሊየን ብር በላይ በሴቶች የልማት ህብረት መቆጠብ ማቻሉም ተናግረዋል። በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በእሬሶ ቀበሌ የሴቶች ገንዘብ ቁጠባ ብድር መሰረታዊ ህብረት ስራ ሀላፊነቱ የተወሰነ የልማት ህብረት ሰብሳቢ ወይዘሮ ውሉጌ ሀጅ ከድር እንዳሉት በናፍጣ የሚሰራ ወፍጮ ቤት ከፍተው ለአካባቢው ሰው አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነ አብራርተዋል። በተመሳሳይ ኦቼና አንቀዲን ቀበሌ ኢንሾላይ የሴቶች የልማት ህብረት ሰብሳቢ ወይዘሮ ሲቲ ሀይደር እንዳሉት የልማት ህብረታቸው ሶስት ሄክታር መሬት በገብስ ማሳ መሸፈናቸው ተናግረው በዚህም በሄክታር እስከ 30 ኩንታል ምርት እንደሚጠብቁም አስረድተዋል ። በየ15 ቀኑ የልማት ህብረት አባላቶች የሚቆጥቡ እንደሆነና በህብረት ስራ ተደራጅተው መስራት ከጀመሩ ጀምሮ ከ250 ሺህ ብር በላይ መቆጠባቸውና በቀጣይ ወፍጮ ቤት ለመክፈትም እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል።

ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የተቋማትና የፈጻሚዎች የእውቅናና ሽልማት መርሃ-ግብር ዛሬ ማካሄዱ ተገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በመድረኩም በሃገራችን በሁሉም መስኮች እየተመዘገበ ያለው ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ ስኬት የፐብሊክ ሰርቫንቱ ሚና የላቀ መሆኑ ተገልጿል። በዕውቅና ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ሃገራችን የጀመረችዉ የብልጽግና ጉዞ መሳካት የፐብሊክ ሰርቫንቱ ሚና የላቀ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች ለተመዘገበዉ ስኬት የፐብሊክ ሰርቫንቱ የአንበሳዉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ አውስተዋል። ይህንን ተጨባጭ ዉጤት በተሻለ ደረጃ ማሳደግ ይቻል ዘንድ ፐ/ሰርቪሱ የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመንና የተገልጋዩን ህብረተሰብ እርካታና አመኔታ ማረጋገጥ እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል። የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋሪስ ከማል የአንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። አክለውም ፐ/ሰርቫንቱ 1 ቀን እንደ 5 ቀን፣ 1 ሰዓት እንደ 5 ሰዓት በማገልገል በወረዳችንና በሃገራችን እየተካሄደ ያለውን የብልጽግና ጉዞ ማረጋገጥ እንደሚጠበቅበት መልዕክት አስተላልፈዋል። የፅህፈት ቤቱ ባለሙያ አቶ ሙስጠፍ ሺፋ የ2017 ዓ/ም የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። በመጨረሻም ጽ/ቤቱ በ2017 ዓ/ም የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማትና ፈጻሚዎች የእውቅናና ምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል። በዚህ መሰረትም በተቋም ደረጃ:- 1ኛ/ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፍርድ ቤት 2ኛ/ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት 3ኛ/ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፍይናንስ ጽ/ቤት እና የወረዳው ሴ/ህ ጉዳይ ፅ/ቤቶች በእኩል ዉጤት በማምጣት 3ኛ ደረጃ በመውጣት ተሸልመዋል። ከፈጻሚዎች በወረዳ ደረጃ:- 1ኛ/ በህሩ ሰማን ከውሃ ጽ/ቤት 2ኛ/ እንደሻው ከመንገድ ጽ/ቤት 3ኛ/ አሰፋ ማሩ ከፍርድ ቤት ከፐብሊክ ሰርቪስ ፅ/ቤት በጽ/ቤት ደረጃ:- 1ኛ/ ሀያት ባሀሩ 2ኛ/ ሙስጠፋ ሻፊ 3ኛ/ አባበል ምትኩ ከቀበሌ ስራ አስኪያጆች 1ኛ/ አ/በር ነጋሽ ከዘ/ሰፋቶ ቀበሌ 2ኛ/ ሰኢድ ነጋሽ ከቤደር ቀበሌ 3ኛ/ ረምዚያ በንቲ ከደነብ ቀበሌ ተሸልመዋል። ከሳይት ባለሙያ:- 1ኛ/ አ/ሃቅ አ/ፈታ ጅማ ጤና ጣቢያ ባለሙያ 2ኛ/ እስማኤል ፈድሉ ከኢንተርፕራይዝ 3ኛ/ ዳንኤል እምዩ ተሸሊሚ መሆን ችለዋል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወረዳ የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።