1 321
Подписчики
+124 часа
+67 дней
+14830 дней
Архив постов
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+5
ከቴክኖሎጂ ፈጣሪነት እስከ አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት.........
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን በተሳተፉበት አለም አቀፍ ውድድር አሸናፊ ሆነዋል::
"የክህሎት ኢትዮጵያ" ፕሮግራም ተሳታፊ የሆኑት የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን በብሪክስ ቤልት ኤንድ ሮድ የቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ውድድር አገራችንን በመወከል አሸንፈዋል።
በውድድሩ በአጠቃላይ በ15 ዘርፎች በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያ 4 የብር ሜዳልያ እና 3 የነሀስ ሜዳልያ በማምጣት ቀዳሚ ሆናለች።
ከዚህም በተጨማሪ 10 የፈጠራ ሥራዎች የምርጥ ፈጠራ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን በተሳተፉበት የፈጠራ ስራ Advanced Manufacturing Designing Semi-Automatic Animal feed production Machine ዘርፍም ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የነሀስ ሜዳልያ በማምጣት ማሸነፍ ችለዋል::
በዚህ ከፍተኛ ውጤት የኮሌጁ ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! የኮሌጁ አመራሮች መምህራኖቻችን የፈጠራ ሃሳባቸውን ወደ መሬት ለማውረድ የሚያደርጉትን ጥረት በተሻለ መልኩ ድጋፍ የምናደርግ ይሆናል።
የኮሌጁ ዲን
አቶ ሰለሀዲን አብዱልሀሚድ
በአዲስ የተዘጋጁ የሙያ ደረጃዎች የትውውቅና ምክክር መርሃግብር ተካሄደ፡፡
ለኢንዱስትሪው ተፈላጊውን የሰው ሃይል ለማቅረብ በኢንዱስትሪው የተዘጋጀውን የሙያ ደረጃዎች ለማስተዋወቅ ከሙያ ደረጃ ጋር ተያይዞ የሚነሱና የሚያጋጥሙ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያስችል ዘንድ ሙያ ደረጃዎች በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ የዘርፍ መሪ መስሪያቤቶች፣ ማህበራት፣ ባለድርሻ አካላት፣ ማሰልጠኛ ተቋማት እና ስልጠናውን ለሚመሩ አካላት ማስተዋወቅ ተችሏል።
የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በገበያው ተፈላጊ የሆኑ ሙያዎች በመደበኛ የስልጠና ፕሮግራም በክህሎት የዳበረ በአስተሳሰብና በስነምግባር የበለጸገ የሰለጠነ የሰው ሃይል በማፍራት አስፈላጊውን ክህሎት በማስጨበጥ ለዜጎች በከተማና ገጠር የስራ ዕድሎች መፍጠር የሚያስችል ሥራዎች በመስራት ላይ ያለውና ለዚሁ ስራ ተግባራዊነት አስፈላጊ የሆኑ የስራ ገበያውን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተዘጋጁ የማሰልጠኛ መሳሪያዎች በአስተዳደሩ የሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ በኩል ለኮሌጆች በማሰራጨት ተግባራዊ እንዲሆኑ እየተደረገ ይገኛል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 12/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በአዲስ የተዘጋጁ የሙያ ደረጃዎች የትውውቅና ምክከክር መርሃግብር ተካሄደ፡፡

በአዲስ የተዘጋጁ የሙያ ደረጃዎች የትውውቅና ምክከር መርሃግብር ተካሄደ፡፡

Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ "ጥራት በተለየ እሳቤና ፈጠራ" በሚል መሪ ቃል 14ኛውን የዓለም ጥራት ሳምንት አስመልክቶ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው ኤግዚቢሽን ላይ እየተሳተፈ ይገኛል::
የISO የጥራት አስተዳደር ተሸላሚነትን ያገኙ ከ150 በላይ ድርጅቶችና ተቋማት በሚሳፉበት በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ ኮሌጃችን አጠቃላይ አገልግሎቶቹን ጨምሮ የተለያዩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎቹን እና ምርቶቹን እያስተዋወቀም ይገኛል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ህዳር 11/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
በድሬዳዋ አስተዳደር እየተካሄደ የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራን የሙያ ብቃት ምዘና ቀጥሎ የኮንስትራክሽን አሰልጣኝ መምህራን በደረጃ አራት እና አምስት በስትራክቸራል ኮንስትራክሽን ሙያ ምዘና መውሰዳቸው ተገለጸ።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 11/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+4
#ዜና|የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከተለያየ የትምህርት ክፍል ለተውጣጡ ሰልጣኝ ተማሪዎች ቻይና ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በAI tools and Modeling ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና በዛሬው እለት መስጠት ጀመረ፡፡
በስልጠናው ማስጀመሪያ እለት በመገኘት ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ኢ/ኤ/ቴ/ሽ ም/ዲን ወ/ሮ ትግስት በዙ ሲሆኑ በንግግራቸውም ጊዜው የAI ነው ስልዚህ የምንሰራቸውን ስራዎች በ AI የታገዙ እንዲሆኑ እንዲሁም የምናሰለጥናቸው ሰልጣኞች መጪውን ዘመን እንዲረዱ እንዲህ አይነት መሰል ስልጠናዎችን በመስጠት የሰልጣኞችን አቅም ማጎልበት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ም/ዲኗ አያይዘውም በኮሌጁ የሚሰለጥኑ ሰልጣኝ ተማሪዎች በቀጣይም ሀገር ውስጥ እንዲሁም ውጪ ሀገር ከሚገኙ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን የተለያዩ ስልጠናዎችን እንዲያገኙና ለስራው አለም ብቁ እና ዝግጁ ሆነው እንዲገኙ ኮሌጁ በትጋት የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡
በዛሬው እለት ቻይና ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ በመሆን የተጀመረው ስልጠና በኮሌጁ በተቋቋመው የICT ስልጠና ማእከል ውስጥ ሲሆን የመጀመሪያ ዙሩ ስልጠና ለ2 ቀን የሚቆይ ይሆናል እንዲሁም ሁለተኛ ዙሩ በቀጣይቀናት ለ 5 ቀናት የሚሰጥ እንደሆነ ስልጠናውን ከሚያስተባብሩት አካላት ለማወቅ ተችሏል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ህዳር 10/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
በአስተዳደሩ 600 ያህል ሰዎችን የማስተናገድ አቅም ያለው ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።
ዘመናዊ የመሠብሰቢያ አዳራሹ ዲዛይኑ ሙሉ በመሉ በውስጥ አቅም ባለሞያዎች መሰራቱ በወቅቱ ተገልጿል።
የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አዳራሹ ከ37 ሚለዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት ሙሉ በመሉ የመልሶ ግንባታ ሥራው የተከናወነ መሆኑን ገልፀው በመልሶ ግንባታው ስራ ፣ ዘመናዊ የድምፅ ማጉያዎች፣ ምቹ ወንበሮች ፣ የሙቀት መቆጣጠሪያ፣ መፀዳጃ ቤቶች ግንባታ ፣ መኪና ማቆሚያ ፣ የውጭ እግርኛ መንገድና አረንጓዴ ስፍራዎች ፣ ዘመናዊ መድረክ ግንባታ፣ አጠቃላይ የጣሪያና ዘመናዊ የብርሃን መቆጣጠሪያ እና ሌሎችንም ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።
ሃላፊው አክለውም ልዩ የእንግዳ ማረፊያው እና በልዩ ሁኔታ የተሰራ አካል ጉዳተኞችን ያማከለ ዘመናዊ መፀዳጃ ቤትና መንገዶችን ያካተተ መሆኑን ጠቁመዋል።
አዳራሹ ድሬዳዋን የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ ለሚደረገው ጥረት የራሱን ሚና ይጫወታል ብለዋል።
©️ DireTvአማርኛ | ህዳር 10 ፥2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+6
‹‹የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በmobile tvet እንቅስቀሴ የተለያዩ ወጣቶችን የሙያ ባለቤት ለማድረግ እየተጋ ያለ ኮሌጅ››
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በወረዳ 8 የሚገኙ ወጣቶችን በተለያዩ ሙያዎች በmobile tvet እንቅስቀሴ በአካባቢያቸው የስልጠና ጣቢያ በማቋቋም ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡
ኮሌጆች የስልጠና ቦታ ሳይገድባቸው ወጣቶችን በሚመቻቸው ቦታ በመንቀሳቀስ ስልጠናዎችን በመስጠት የስራ እድል ፈጠራውን እንዲሁም ዜጎች የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ የማድረግ ስራዎችን ሊሰሩ ይገባል ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ በዚህም የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግንባር ቀደም በመሆን ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የኮሌጁ ዲን አያይዘውም ኮሌጁ በወረዳ 8 የሚገኙ ወጣቶችን በኤሌክትሪክ ሙያ፣በ Finishing construction ሙያ እንዲሁም በህይወት ክህሎትና የኢንተርፕሩነርሺፕ ክህሎቶችን ወጣቶች በሚመቻቸው ቦታ ከወረዳው ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡
በቀጣይም በሌሎች ወረዳዎች መሰል ስልጠናዎችን በተለያዩ ሙያዎች የማሰልጠኑ ተግባር የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ህዳር 9/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
+1
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ማኔጅመንት ከEDI ከመጡ ባለሙያዎች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ::
የውይይት መድረኩ ኮሌጁ ከEntrepreneurship Development Institute(EDI) ጋር በመተባበር ለተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ሲሰጥ በቆየው የኢንተርፕርነርሺፕ ስልጠና መሰረት በቀጣይ እንደ ተቋም ወደ ተግባር ለማስገባት ያለመ መሆኑም ተገልፇል::
በዚህም በማኔጅመት ደረጃ ሊሰሩ የሚገባቸውን ተግባራት አስመልክቶ የቀጣይ ትግበራ ዝርዝር እቅድ እዘገጃጀት ላይ ውይይቶች የተካሄዱ ሲሆን የጋራ አቅጣጫ ማስቀመጥም ተችሏል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ህዳር 08/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
ታላቅ ቅናሽ
በእጀ ወርቆች የተመረተ ልዩ ልዩ ቦርሳዎችን፣ባህላዊና ዘመናዊ ልብሶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ታገኛላችሁ
ምርቶቻችን
💼 በቆዳ ውጤቶች የተማሪ ቦርሳ፣የላፕቶፕ ቦርሳ፣የሴቶች ቦርሳ፣ዋሌት፣ቀበቶ
👗 በአልባሳት የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ጋውን፣የ ሰራተኞች ቱታ፣የባህል አልባሳት፣የስፖርት ቁምጣ እና ቲሸርት፣የህትመት ቲሸርቶች፣ስካርፕ እንዲሁም ዘመናዊ አልባሳትን በትእዛዝ እናመርታለን
በቡድን ለሚመጡ ደንበኞች ልዩ ቅናሽ እናደርጋልን፡፡ጥራትና ቅልጥፍና መለያች ነው
ይምጡ ይዘዙን አድራሻችን ከድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ወደ ኤርፖርት በሚወስደው መንገድ 150 ሜትር ላይ እንገኛለን