cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

AI-IKHILAS

አላህ የፃፈልን ርዝቅ እየበላን ሞታችንን የምንጠብቅ የአላህ ባሮች አላህ ያድርገን

Больше
Рекламные посты
456
Подписчики
-124 часа
+37 дней
+1630 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
ጫት እና አደጋው ✅✅✅✅ 🏝 ከኡስታዝ አቡ ኢልሃም ቻነል ተወስዶ ወደ pdf በወንድም አቡ ዒምራን የተዘጋጀ ➽ ጫት ዱንያዊ የሆኑ ጉዳቶች ያሉት ሲሆን 1, በገንዘብ ላይ፣ 2, በጤና ላይ፣ 3, በጊዜ ላይ፣ 3, በቤተሰብ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ተዳሷል። በሌላ በኩል አኸራዊ ጉዳቶች ያለት ሲሆንለምሳላ ከፆም፣ ➻ ከሶላት፣ ➻ ወንጀል ከመዳፈር አንፃር፣ ➻ ከሽርክ ጋር በተያያዘ እና የመሳሰለት ተዳሰዋል። 🚥 የቃመ ተጠቀመ ሳይሆን የቃመ ተለቀመ ነው የሚባሆው አዎ የቃመ ጥርሱን ይለቅማል ቤተሰቡን ይበትናል፤ ወንጀል ያጠራቅማል፤ ራሱንም ቤተሰቡንም ዲኑንም ሀገሩንም ይጎዳል። ▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴ ⚙ 📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩ 🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣  ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️ https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy ሀሳብ  ካለዎ  ⤵️⤵️⤵️⤵️ https://t.me/AbuImranAselefybot
Показать все...
ጫት እና አደጋው.pdf2.09 MB
2, ከፆም ጋር በተያያዘ፦ ከፆም ጋር በተያያዘ ጫት ያለው ሁኔታ አስገራሚ ነው። በሀገራችን ሆን ተብሎ ይመስል ከሱና ፆሞች ጋር በተያያዘ ጫት ሲቃም ይስተዋላል። በቅድሚያ የሚታወሰን ሰኞ(ኢስነይን) ነው። ነቢዩ የተወለዱበት ቀን መሆኑን በመግለፅ ፁመውት፣ ሌሎችም እንዲፆሙት አዘው ነበር። ነገር ግን ከነቢዩ በተቃራኒ ሰዎች ሰኞ ቀንን በመብላት፣የሽርክ ስንኛችን በማንበብ ና ጫት በመቃም ሲያሳልፉት ምን ይባላል? ሌላው ሀሙስ(ኸሚስ) ቀን ነው ነቢዩ ይህንንም ቀን እንዲፆም ሲገፋፉ ሰዎች ግን በተለይ ለሊቱን በመቃም ሲያድሩ ይስተዋላል። ነቢዩ የጁሙዐን ምሽት(በኛ ሀሙስ ማታ) ብቻ ነጥሎ በኢባዳ ማሳለፍን ሲከለክሉ ሰዎች ግን ኢባዳውንም ትተው በባሰ ሁኔታበሽርክ ስንኝ ከጫት ጋር ሲጋተሩ ያድራሉ። ነቢዩ ይህን ቢያዩ ምን ይሉ ይሆን?እሚገርመው ደግሞ ቀኑንም መሳሳታቸው ኸሚስ ማታ የሚሉት ለይለተል ጁምዓን ነው። ከዚህ በተጨማሪ አመት ጠብቀው የሚመጡ የሱና ፆሞችን ምክንያት በማድረግ ሰዎች ለመቃምና ለመብላት ሲሯሯጡ ይታያሉ። ለምሳሌ ነቢዩ የዐሹራ ቀን እንዲፆም እንጂ እንዲበላበትም ሆነ እንዲከበር አላዘዙም ሶሀቦቻቸውም አላደረጉትም። ነገር ግን አንዳድንድ አካባቢዎች ያለ ምንም ማስረጃ እንደ በዓል ሲያከብሩትና ከነቢዩ በተቃራኒ ሲፈፅሙ ይስተዋላል። ግን ለምን? አቡ ነጂ አል ኢርባዲ እንዳስተላለፉት ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል «…በሀይማኖት ውስጥ አዳዲስ ፈጠራዎችን ተጠንቀቁ። ምክንያቱም አዲስ ነገር ሁሉ ፈጠራ ነው፣ ፈጠራ ሁሉ ደግሞ ጥመት ነው፣ ጥመት ሁሉ ደግሞ ለእሳት ይዳርጋል።» አቡዳውድ ዘግበውታል ረመዳን ላይ የጫት ታሪክ የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን። ቀኑን ፆሞ የዋለው ሰው የጫት አምሮቱን የሚወጣው ለሊቱን እየቃመ በማደር ነው። ነቢዩ በረመዳን ለሊቱን በኢባዳ ህያው ያደርጉ ነበር፤ ነገር ግን በዘመናችን በነሽዳና በዘፈን፣ በጫት እየተደነሰ ይታደራል። በዚህ ቢበቃ ጥሩ ነቢዩ አበክረው እንድንመገብበት የነገሩንን የሱሁር ሰዓት አሳልፈው በባዶው የሚፆሙ ብዙ ናቸው። እንደ ማምሸታቸውም ሱብሂን ከነጋ በኋላ የሚሰግዱም አሉ። ይህ ፆመን ለአኼራችን መሰነቅ ሲገባን ጫት ግን አቅጣጫችንን ቀይሮ ለቅጣት እየዳረገን እንዳለ ያስገነዝበና: 3, በጫት ሳቢያ የሚከሰቱ ወንጀሎች በጫት ሳቢያ የሚፈፀሙ ወንጀሎች የትየለሌ ናቸው። ቢሆንም ራሳችንን ከጫት ለማራቅ ይረዳን ዘንድ የተወሰኑትን ልጥቀስ። በመጀመሪያ ጫት የሚቅም ሰው የሚፈፅመው ከምላስ ጋር በተያያዘ ነው፤ ብዙ ሰዎች በጫት ሰክረው እውነቱንም ውሸቱንም እየቀላቀሉ እያጋነኑ ሲናገሩ ይስተዋላሉ። ይህ ደግሞ ለማይታመኑና አቅል የማይቀበላቸው ታሪኮች(ቂሷዎች) መፈጠር ምክንያት ነው። ሌሎች ደግሞ እንዳሻቸው የወንደሞቻቸውን ስም እያነሱ ሲጥሉ ሲያሙና ሲያንቋሽሹ የአላህን ቃል ሲጥሱ ይገኛሉ። ጫት ለከባባድ ወንጀሎችም ያጋልጣል። በተለይ ወንዶችና ሴቶች እየተቀላቀሉ በሚቅሙባቸው ቤቶች በጫት ግፊት አስከፊ ቅጣትን የሚያስከትሉ የዝሙት ወንጀሎች ይፈፀማሉ። «ዝሙትን አትቅረቡት፤ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ስራ ነውና መንገድነቱም ከፋ» አል-ኢስራዕ፡32 ሌላው ጫት በሚቃምበት ወቅት የሚፈፀሙ አንዳንድ የምርቃና ኢባዳዎች ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ሲያመዝን ይስተዋላል። ብዙ ጊዜ የሚፈፀሙት ሶለዋት ማውረድ ዱዐ ማድረግና የመሳሰሉት ሲሆኑ መሰረታቸው ጥሩና የሚደገፍ ቢሆንም አተገባበራቸው ችግር እያስከተለና ከነቢዩ ሱና እያፈነገጠ ይገኛል። ለምሳሌ ሶለዋት የሚደረገው ለብቻ ሆኖ ሳለ ሰዎች ተጠባብቀው በአንድነት ሲፈፅሙና ከነቢዩ ትዕዛዝና ከሶሀቦቻቸው ስራ ያፈነገጠ የቢድዐ ተግባር ሲያደርጉ፤ ዱዐ ሲደረግ ደግሞ ለአላህ ተናንሰንና ድምፃችንን አሳንሰን መሆን ሲገባው ጫት ላይ ግን ከፍ ባሉ ድምፆች አላስፈላጊ የሆኑ ቃላትን (ሽርካዊ)ቃላትን በመጠቀም በዱዐ ላይ ድንበር ሲታለፍ ይታያል። ይህ ደግሞ አይቀጡ ቅጣትን የሚያስከትል ወንጀል ነው። እንዲሁም ጫት አንዳንዴ መጤ በዓላትን ታኮ ስለሚመጣ በሱስ ምክንያት የነዚህ ቢድዓ ተግባራት ተሳታፊ ሊያደርገን ይችላል። የምዕመናን እናት ኡሙ ዐብዲላህ(ረ.ዐንሀ) እንዳወሩት ነቢዩ እዲህ ብለዋል «የእኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ድርጊት የሰራ እርሱ(ስራው) ውድቅ ነው።» ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል 4, ከሽርክ ጋር በተያያዘ፦ ከጫት ጋር በተያያዘ ከሚነሱት ጉዳቶች ሁሉ አስከፊው የሽርክ ወንጀል ነው። ሽርክ ከኢስላም የሚያስወጣ የዘልአለማዊውን ህይወት የሚያጨልምና ለዝንትአለም እሳት የሚዳርግ አስከፊ ወንጀል ነው። ሸይጧን ግን ሰዎችን ወደ እሳት ለማስገባት ካለው ከፍተኛ ፍለጎት የተነሳ ጫትን ታኮ ሰዎችን ወደ ሽርክ እየጨመራቸው ይገኛል። በጫት ላይ በሚነገሩ የሐሰት ታሪኮች በመማረክ ብዙዎች ወደ ሽርክ ገብተዋል እየገቡም ነው። እነዚህ ቂመሐ ላይ የሚነገሩ ታሪኮችና ጀብዱዎች በጫት የተበረዘውን የሰው አእምሮ ታሪኩ ለተወራለት ሰው(ጂን፣ወሊይ፣ ሸህ…) ተገዥ እንዲሆን ብሎም ይረዱኛል በሚል ስሜት እነርሱን እንዲያመልክ ያደርገዋል። በእንደዚህ አይነት ወንጀል ላይ ደግሞ አላህ ምህረት የለውም!!! «አላህ በርሱ ማጋራትን በፍፁም አይምርም፤ ከዚህ ሌላ ያለውን(ኃጠዓት) ለሚሻው ሰው ይምራል» አል-ኒሳዕ፥48 በአላህ ፈቃድ መጠነ ሰፊ ከሆነው የጫት ጉዳት የተወሰነውን ለማሳየት ሞክረናል። ከላይ እንደቀረበው ጫት በግለሰቦች፣ በቤተሰብ፣ በማህበረሰብና ብሎም በሀገር ላይ ውድቀትን የሚያመጣ መሆኑን ተረድተናል። ዋናው ጉዳይ ስለጫት ማወቃችን አይደለም ይልቁንም ራሳችንን ከጫት እንዴት ማራቅ እንችላለን የሚለው ላይ ነው። በአላህ ወይም በነቢዩ ቀጥታ ካልተነገረ በስተቀር አንደን ነገር ሀላል ወይም ሀራም ማለት ክልክል ነው። «በአላህ ላይ ውሸትን ልትቀጣጥፉ ምላሶቻችሁ በሚመጠኑት ውሸት ይህ የተፈቀደ ነው፣ የህ እርም ነው አትበሉ» አል-ነህል፥116 ይሁን እንጂ ኢስላም እንደ ጫት ባሉ ነገሮች ራስን መጉዳት አስቀድሞውኑ ከልክሏል፤ ከሚያመጡት ውጤት አንፃር። ለዚህ ደግሞ ከላይ የዘረዘርናቸው የጫት ጉዳቶችና ውጤቶች በቂ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ አላህና መልዕክተኛው ኸምርን ከልክለዋል። ኸምር ሚለው ቃል ኸመረ ከሚለው ስርወ ቃል የመጣ ሲሆን አእምሮን የሚሸፍን ማለት ነው። ቃሉ በመጠጥ ብቻ የተገደበ አይደለም። አስካሪ እስከሆነና ከአቅል ውጪ እስከሚያደርግ ድረስ የሚበላም ሆነ የሚጠጣ ነገር በዚህ ውስጥ ይጠቃለላል። እናም ጫት ሰዎችን ከኖርማል አስተሳሰብ አውጥቶ የሚያናውዝ በመሆኑ በዚህ ክልከላ ውስጥ ይካተታል ማለት ነው። «እናንተ ሰዎች ሆይ! በምድር ካለው ነገር የተፈቀደ ጣፋጭ ሲሆን ብሉ።» አል በቀራህ፥168 ሰዎች ሆይ! ጫትና መሰል ነገሮችን በመጠቀም ህይወታችንን ለዱኒያም ሆነ ለአኸይራ ኪሳራ ከምንዳርጋት አላህ በሰጠን የተፈቀደ ነገር እንብቃቃ!!! https://t.me/sunah123 https://t.me/sunah123 https://t.me/sunah123 https://t.me/sunah123
Показать все...
አቡ ኢልሐም አስ_ሰለፊ (የኡስታዝ ሙሀመድ ኑር)ያለቁ ና እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን መልቀቂያ ቻናል

የአቡ ኢልሐም (ኡስታዝ ሙሀመድኑር) ፉሪ በሀምዛ መስጂድ ተቀርተው ያለቁ እና እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን መልቀቂያ ቻናል። 👇👇👇👇👇

https://t.me/sunah123

ጫት እና አደጋው ብዙ ሰዎች ጫትን ራሳቸውን ለማነቃቃት፣ ለማንበብና ጊዜያቸውን ለማሳለፍ …እንደመዝናኛም ይጠቀሙበታል። ጫት እንደ glycosides, tannins, more than 40 alkaloids, amino acids, vitamins, minerals & amphetamine, caffeine, Catharine, Cathinone, eduline and ephedrine ያሉ ንጥረነገሮችን በመያዙ ሰውነታችን በተለይ አእምሮአችን ከሚችለው በላይ የሆነ ስራን እንዲያከናውን ይረዱታል። ሆኖም አዕምሮአችን ለጥቂት ጊዜ ፈጣን ከሆነ በኋላ በጫት ሱስ እየተጠመደ ይሄድና በስተመጨረሻ ያለ ጫት የማይንቀሳቀስ ፉርጎ ይሆናል። ጫት ወጣቱን ፣ሽማግሌውን፣ ወንዱን፣ሴቱን ፣ማህበረሰቡን በጠቅላላ ና የሀገርንየሰው ሀይል እያቆረቆዘ የሚገኝ መጥፎ መሳሪያ ነው። መጥፎ ስራን መቃወም ከእምነት ጭምር ነውና በጫት ላይ ያሉ የተወሰኑ የጫት ጉዳቶችን በማቅረብ ምን ያህል ጎጂና በኢስላምም የተወገዘ መሆኑን ለማሳየት እወዳለሁ። የጫትን ጉዳቶች ለመረዳት እንዲያመቸን ዱኒያዊና አኸይራዊ በማለት ለሁለት ከፍለን እናየዋለን። ዱንያዊ፦ በዚህ ርዕስ ስር ጫት በተጠቃሚውና በአካባቢው ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለማሳየት እንደሚከተለው ከፋፍለን እናየዋለን። 1, በገንዘብ ላይ፦ ሰዎች ከልጆቻቸው ና ከቤተሰባቸው አፍ በመንጠቅ ገንዘባቸውን ለጫት ሲያውሉ ይስተዋላል። ይህ ደግሞ አባወራዎች አላህ የጣለባቸውን ቤተሰብን የማሰተዳደር ሀላፊነት ባለመወጣት ለተጠያቂነት ይዳርጋቸዋል። ነቢዩ እንዲህ ብለዋል «ሁላችሁም እረኞች ናችሁ፤ ከረኝነታችሁም ትጠየቃላችሁ።» በሌላ በኩል ችግረኞች እያሉ እነሱ ገንዘባቸውን በጫት ላይ ማዋላቸው ለተጠያቂነት ይዳርጋቸዋል። አላህ በቁርዓኑ አባካኞችን ከሸይጧን ጋር አቆራኝቷቸዋልና። «አታባክን፣ አባካኝ የሸይጧን ጓደኛ ነውና»እቤት ውስጥ ወጭ ሲጠየቅ አሻፈረኝ ያለው ሰው እጫት ተራ ሲሄድ ምን ያክል እንደሚያወጣ ለእናንተ ልተወው....... 2, በጤና ላይ ጤና በአብዘኞቻችን እጅ ያለ ያላወቅነው ትልቁ ሀብታችንና ፀጋችን ነው። ይህን ፀጋ የሚያው ነተነጠቀው ብቻ ነው። ለዚህም ነው ነቢዩ በተለያዩ ሀዲሶቻቸው የጤናን ደረጃ የገለፁት። ጫት በቅድሚያ ከፍተኛ ችግር የሚያስከትለው በጥርስ ላይ ነው። ጥርስ ራሱን መተካት የማይችል በመሆኑ በቀላሉ ከተጎዳ ዳግም ተፈጥሮአዊ በሆነ መልኩ መጠገኑ የማይቻል ነው። ነቢዩም ጥርሳቸውን ከመንከባከብ አልፈው ተከታዮቻቸውንም ያዙ ነበር።«ባላጠብቅባችሁ ኖሮ በየውዱዑ በመፋቂያ አዛችሁ ነበር» ነቢዩ በሌላ በኩል ጫት ውስጣዊ አካላት ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከመጀመሪያው የከፋ ነው። ጉበት፣ ኩላሊትና የሽንት ፊኛ በጫት ኬሞካሎች  የሚጎዱ ሲሆን ከረጅም አመታት በኋላ ደግሞ እንደ ምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ የስነልቦና ችግርና ሽንተ ማጥ ላሉ ከፍተኛና ብሎም ለሞት ለሚያደርሱ በሽታዎች ያጋልጣል። በጫት ዙሪያ በተደረጉ ጥናቶች መሰረት ጫት በመተንፈሻ አካለት ፣ በደም ዝውውር አካላት፣ Gastrointestinal sys.፣ Hepatobiliary sys.፣ Genitourinary sys.፣ Obstetric effects፣ Metabolic and endocrine effects፣ በነርቭ አካላት ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳቶችን ያስከትላል። ይህ ብቻ አይደለም ጫት አእምሮን ክፉኛ የሚያደነዝዝ፣ በሱስ ከተያዙ በቀላሉ እንዳይላቀቁ የሚያደርግና ድብርትን የሚያመጣ ነው።ይህ ደግሞ ጤነኛ የነበረውን የሰዎች አስተሳሰብ አዛብቶ ለተበላሸ ማህበራዊ ህይወትና ለተቃወሰ ጤና ይዳርጋል። እንዲሁም በጫት ሱስ ተጠምደው ብዙ ጊዜያትን ያሳለፉ ወንዶች ስሜታቸው ይቀንሳል ብሎም ያጡታል። 3, በጊዜ ላይ አረቦች ጊዜ ከሂዎት በላይ ነው ይላሉ። እውነት ነው፣ ጊዜ እጅግ ውድ ሀብታችን ነው። ብዙ ነገሮች በጊዜ ይወጠናሉ በጊዜ ይፈፀማሉ። ጊዜን በትክክል ካልተጠቀምንበት ግን በወቅቱ ማግኘት የሚገባንን ነገር እነድናጣና ብሎም ለኪሳራ እንድንዳረግ ያደርግናል። አንዱ ተጠቃሽ ጫት ነው። ሰዎች ጧት የጀበና ሲሉ ቆይተው ስራው ሳያልቅ ከሰዐት ደግሞ ለጫት ሲቀመጡ ይስተዋላል። ሌሎች ደግሞ ከጧት እስከማታ ሲጠምዱት ይታያሉ። ይህ ስራቸውን በጊዜ ፈፅመው ኖሮአቸውን እንዳያሻሽሉ የሚያደርግ የድህነት ማነቆ ነው። በሌላ በኩል ጫት፣ ሰው በጊዜው ለአኸይራ ቤቱ የሚሆን ስንቅ እንዳይሰንቅ ያደርገዋል። ይኸኛው ከቀደሙት የባሰ መጥፎ የጫት ገፅታ ነው። ጊዜያችንን በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ደግሞ አላህ ዘንድ ከሚጠብቁን አራቱ ጥያቄዎች ሁለቱን መመለስ አልቻልንም ማለት ነው። አንዱ ሀብትህን በምን አዋልከው? የሚልና በጊዜህ ምን ሰራህበት? በጫት….. 4, በቤተሰብ ላይ በቤተሰብ መዋቅር ውስጥ የቅድሚያውን ቦታ ሚይዙት ወላጆች ናቸው። ወላጆች ወልደው እንደማሳደጋቸው ሁሉ ምንም እንኳን ሀቃቸውን ባይመልስም እነርሱን ማገልገል መርዳት እና ለነርሱ ዝቅ ማለት በቁርዐን የተጣለብን ግዴታ ነው።      «…ለወላጆቻችሁም መልካም ስሩ በአንተ ዘንድ ኾነው አንዳቸውንም ይሁን ሁለታቸውን ኡፍ አትበላቸው አትገላምጣቸውም መልካም ቃልም ተናገራቸው» ኢስራዕ 23 ሆኖም ጫት መንከባከብ የሚገባንን ቤተሰቦቻችንን እንድንረሳና ቁርዐንን እንድንጥስ ምክንያት ይሆነናል። ይህን እየተመለከቱ የሚያድጉት ታናናሾቻችንም ከዚህ በከፋ መልኩ ስርዓት አልባና ጋጠወጥ እንዲሆኑ በር ይከፍታል። ✅ሚስት ሌላዋ ተጠቂ ናት። ባሏ የጫት ሱሰኛ ከሆነ ለልጆቹም ሆነ ለርሷ ማድረግ የሚገባውን እንክብካቤ አይፈፅምም። ከዚህ በተጨማሪም የሚስቱን ሀቅ ሊያጓድልና ግዴታዎቹንም ሊዘነጋ ይችላል። ይህ ደግሞ በቤተሰብና በግለሰቡ ላይ የሚያሳድረው ስንልቦናዊ መቃወስ ይህ ነው ተብሎ የሚገለፅ አይደለም። ልጆችም በለጋነታቸው ሱሰኞች የሚሆኑበት አጋጣሚም ይከሰታል። ሲገፋ ደግሞ ቤተሰብ እስከ መበተንም ይደርሳል። ✅✅አኸይራዊ በዚህ ርዕስ ስር ጫት ምን ያህል አኸይራችንን ሊጎዳ እንደሚችል እናያለን። በቅድሚያ በሶላት ዙሪያ የሚያስከትለውን ችግር እንመልከት። 1, ከሶላት ጋር በተያያዘ፦ በአብዘኛው የጫት ሱሰኛ የሆነ ሰው አንድ ጊዜ ከተቀመጠ በኋላ እስከሚረካ ለምንም ቢሆን ዳግም መነሳቱ ይከብደዋል። ይህ ባህሪ ደግሞ ቀርተዋል(ስለዲን ዕውቀት አላቸው) የሚባሉ ሰዎች ላይ ሳይቀር የሚስተዋል ነው። እንግዲህ ጫትን እየቃመ ያለ ሰው ሶላት ሲደርስ ተነስቶ መስገድ ከከበደው አደጋው እዚህ ጋር ነው። በብዛት ሰዎች ጫትን የሚቅሙት(የሚፈርሹት) ከዝሁር በኋላ ሲሆን በምርቃና ተውጠው የአሱር ሶላት ሲያልፋቸው ይስተዋላል። ትንሽ ጠንካራ የሚባሉት ጀመዓ ቢያመልጣቸውም ተነስተው በሰዓቱ የሚሰግዱ ሲሆን ሌሎቹ ግን ሶላታቸውን አዘግይተው ሲሰግዱ ጥቂቶች ደግሞ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ከመግሪብ ጋር ያዳብሉታል። ይህ ችግር የሰዎችን ዘልዐለማዊ ቤት ክፉኛ የሚጎዳ ነው። አላህ ግን የአሱር ሶላትን እድንጠባበቃት አዞን ነበር። «በሶላታችሁ ተጠባበቁ በተለይ በመካከለኛይቱ ሶላት፤ ታዛዦች ሆናችሁ ለአላህ ቁሙ» ቁርዓን በቀራህ
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
👍 2
⚡️⚡️السلام عليكم ورحمة الله وبركاته⚡️⚡️ ታላቅ ብስራት(ቡሽራ)  ለዕውቀት ፈላጊዎች በሙሉ        ልዩ የክረምት ኮርስ (የቂርአት) ፕሮግራም አዘጋጅ የቢላል ኢብኑ ረባህ ተማሪዎች እንደሚታወቀው  ቢላል ኢብኑ ረባህ መድረሳ ለሙስሊሙ ኡማ በተለያየ የፕሮግራም(ሰዓት) አማራጭ ኢስላማዊ እውቀት በማስገንዘብ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡አሁን ደግሞ የተማሪዋች እረፍት (የትምህርት መዘጋትን) አስመልክቶ በአይነቱ ልዩ የሆነ የክረምት ኮርስ አዘጋጅተን የናንተን መምጣት በጉጉት እየተጠባበቅን እንገኛለን፡፡ 📆 የመመዝገቢያ ወቅት ከሰኔ 23 እስከ ሰኔ 28 📔 ደርሱ የሚጀመርበት ቀን ሀምሌ1 🌸 ትምህርቱ የሚያካትተው         🔹 ቁርአን በነዝር             🔹 ቁርአን በሂፍዝ                🔹 የተጅዊድ ትምህርት 🔹 የአቂዳ ኪታቦች      🔹 የፊቂህ ኪታቦች          🔹 የአዳብ እና የተርቢያ ትምህርት    ማሳሰቢያ፦ 1. ሸሪዓዊ ህግና ደንብ ማክበር ይጠበቅበዎታል 2. ኢስላማዊ አለበበስ መልበስ ይኖርበዎታል። 3. የመድረሳው መግቢያና መውጫ ሰአት መከበር አለበት። ☎️ ለበለጠ መረጃ፦0921566720                        0912635372                        0947145727 ☎️ በሴቶች በኩል:-  0947023241 አድራሻ፦ካራቆሬ  ውሀልማት አጠገበብ ቢላል  ኢብኑ ረባህ https://t.me/bilalibnurebahmedresa https://t.me/bilalibnurebahmedresa
Показать все...
ቢላል ኢብኑ ረባህ መድረሳ

ይህ የቢላል ኢብኑ ረባህ መድረሳ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በአላህ ፍቃድ፦ - በመድረሳው የሚሰጡ የተለያዩ ቂርአቶች፣ - ዳዐዋዎች እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን እንለዋወጥበታለን ሀሳብ እና አስተያየት ለመስጠት ይህን ቦት ይጠቀሙ ~ @billalmedresa_bot

ልዩ እና ገራሚ ሙሐደራ 🔍🔍🔍🔍🔍🔍 እያንዳንዱ ሰው ስላለበት አማና ✅ አደራን የመወጣት አስፈላጊነት ➜ ይህ ሙሐደራ    ➧ ኡስታዝ ያለበት አደራ    ➧ ሚስት ያለባት አማና    ➧ ዶክተር ስላለበት አማና    ➧ ተማሪ ስላለበት አደራ    ➧ ሰራተኞች ስላለባቸው አማና    ➧ የሀገር አስተዳዳሪ ስላለበት አማና    ➧ በየትኛውም ሙያ፤ እድሜ ሁኔታ ወዘተ ያለ ማንኛውም ሰው ስላለበት ሀላፊነት በዝርዝር ተዳሷል።    ➹ ሌሎችም በሚገርም አቀራረብ ተካተዋል። 🎙 በተከበሩ ሸይኽ አቡ ዐብዱልሃሊም ዐብዱልሐሚድ ብን  ያሲን አል'ለተሚይ አሱኒይ አስሰ'ለፊይ አላህ ይጠብቃቸው 🏝 ይሄን ሁሉ ትንታኔ ያቀረቡት ሸይኹ በሂፍዛቸው ነው። በጣም ትልቅ ብቃት አላህ ሰጥቷቸዋል። በጣም አስገራሚ አሊም ናቸው። ▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴ ⚙ 📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩ 🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣  ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️ https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy ሀሳብ  ካለዎ  ⤵️⤵️⤵️⤵️ https://t.me/AbuImranAselefybot
Показать все...
የዲን አማናዎችን መጠበቅ.mp327.58 MB
ሰበር ዜና አሰላሙዓለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድ የአል-ኢስላሕ ቤተሰቦች ነገ ጁሙዓህ ሰኔ 21 /10/2016 በኡስታዝ ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሐመዊያህ) ከመግሪብ እስከ ዒሻእ የዳዕዋህ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል። በጊዜ በመገኘት ተጠቃሚ ይሁኑ!!!! የመድረሳችን ቻናል join በማለት ተጠቃሚ ይሁኑ ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ https://t.me/medresetulislah
Показать все...
مدرسة الإصلاح (አል ኢስላሕ መድረሳ)

ይህ ቻናል ከፉሪ ሕይወት ፋና ወደ ዑመር ኢብኑ ዓብዱልዐዚዝ መስጂድ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ ኑሪ ሜዳ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የአል ኢስላሕ መድረሳ ኦፊሺያል የቴሌግራም ቻናል ነው። በአላህ ፍቃድ በመድረሳው የሚሰጡና በተለያዩ የሰለፊያህ ዱዓቶች፣ ኡስታዞችና መሻኢኾች የሚተላለፉ መልዕክቶች (በድምፅም ይሁን በፅሑፍ) ይተላለፉበታል።

https://t.me/medresetulislah

2_5469754169873141215.ogg3.96 MB
Показать все...
AI-IKHILAS

አላህ የፃፈልን ርዝቅ እየበላን ሞታችንን የምንጠብቅ የአላህ ባሮች አላህ ያድርገን

Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.