cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Don Bosco Catholic Primary School (1-8) A.A

Больше
Рекламные посты
1 757
Подписчики
+524 часа
+217 дней
+3530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

☑️ ውድ የዶን ቦስኮ ካቶሊክ የመ/ ደ / ት / ቤት የ 6 ኛ ክፍል ተማሪዎች ☑️ ➥ከነገ ( 12 / 10 / 2016 ዓ.ም እስከ ዓርብ ( 14 / 10 / 2016 ዓ.ም ) ድረስ የ 1 ኛ ደረጃ መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና እንደሚሰጥ ይታወቃል። ስለሆነም በተደረገላችሁ ገለፃ መሠረት ጧት 1:00 ሰዓት በዶን ቦስኮ ት/ቤት ተገኝታችሁ አድሚሽን ካርድ እንድትቀበሉ እናሳስባለን :: ☑️ የተከበራችሁ ወላጆች ☑️ ➧ ተማሪዎች ለፈተና አስፈላጊ የሆኑ የት /ት ቍሳቁሶችን ( እርሳስ ከነመ ጠባበቂያ ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ) እና የት/ ቤት መታወቂያ ( ሊብሬቶ) ከተሟላ የዩኒፎርም አለባበስ ጋር አሟልተው በጧት (1: 00 ሰዓት ) ዶን ቦስኮ ት/ቤት እንዲደርሱ ታደርጉ ዘንድ ከወዲሁ እናሳስባለን :: ➥ዓርብ ( 14 / 10 / 2016 ዓ.ም ) የመጨረሻው ፈተና እስከ 4: 00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይቆያል :: መልካም ጊዜ። ት/ቤቱ
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ለ ዶን በስኮ ካቶሊክ የመ/ ደ / ት/ቤት የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ነገ ( | | / 10 / 2016 ዓ.ም ) አጠቃላይ የፈተና ሂደቱን በተመለከተ ኦሬንቴሽን በባለሙያዎች ስለሚሰጥ ሁላችሁም በተለመደው የጠዋት የት/ቤት ሰዓት ( 1፡50 ) በዶን ቦስኮ ካቶሊክ ት/ቤት እንድትገኙ ከወዲሁ እናሳው ቃለን :: ማስታወሻ ለወላጆች ነገ ( ሰኔ | | / 2016 ዓ.ም. )ለ6ኛ ክፍል የሚሰጠው ኦሬንቴሽን እጅግ አስፈላጊ ስለሆነና ተማሪዎች የመፈተኛ ክፍላቸውንም የሚያዩበት ጊዜ ስለሆነ እንዳይቀሩ ፣ እንዳያረፍዱ ታደርጉ Hንድ በጥብቅ እናሳስባለን ።
Показать все...
ለተከበራችሁ የዶን ቦስኮ ካቶሊክ ት/ቤት እስልምና ተከታይ ተማሪዎችና ወላጆች / አሳዳጊዎች እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል- አድሃ ( አረፉ ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! ! በዓሉ የሰላም ፣ የጤና ፣ የፍቅር እና የአንድነት ይሆንላችሁ ዘንድ ከልብ እንመኛለን :: መልካም በዓል ! ት /ቤቱ
Показать все...
0 5 / 10 /2016 ዓ.ም ለተከበራችሁ የዶን ቦስኮ ካቶሊክ የመ/ ደ / ት / ቤት የ 6ኛ እና 8 ኛ ክፍል ተማሪዎችና ወላጆች / አሳዳጊዎች የ 6 ኛ እና 8 ኛ ክፍል ተማሪዎች የ4ኛውን ሩብ ዓመት ሞዴል ፈተና ውጤት የሚቀበሉትና ከ 100 % የሚገለፀላቸው ዓርብ ( 07 / 10 /2016 ዓ.ም) ብቻ ስለሆነ ተማሪዎች ት/ቤት መምጣት የሚኖርባቸው መሆኑን እየገለፀን እስከ 9 : 20 ሰዓት ሙሉ ቀን በት/ቤት የሚውሉ መሆኑን እናሳውቃለን :: ማሳሰቢያ፦ በዕለቱ ተማሪዎች ባለመገኘታቸው ለሚፈmረው ክፍተት ሁሉ ት/ቤቱ ኃላፊነቱን የማይወስድና የማይጠይቅ መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ እናሳውቃለን። ት/ቤቱ
Показать все...
Repost from N/a
የሚኒስትሪ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች ➊ የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡ ❷ በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን ክብ ብቻ መጠቆር አለበት፡፡ ➌ ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው ክብ ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡ ❹ ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን ክብ በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡ ❺ በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ ክብ ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡ ❻ ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ❼ ለመፃፍ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ተፅፎ ወይም ትንሽ ጭረት እና ነጥብ ከተገኘ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ሙሉ  በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ❽ መልስ በሚጠቆርበት ጊዜ እርሳሱ ከተሰጠው የክብ ሳጥን መውጣት የለበትም። ከወጣም በማጥፊያ (Eraser/Rubber) ማጥፋት ይጠበቅባችኋል። ❾ መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ ➓ ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram