cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የመ/ቅ/ኢ/ወሐና/ወ/ዋ/መ/ሰ/ት/ቤት ልማት እና በጎ አድራጎት ክፍል

ይህ የመካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤተ ክርስቲያን ወልድ ዋህድ ሰንበት ትምህርት ቤት ልማት እና በጎ አድራጎት ክፍል መረጃ መለዋወጫ ገጽ ነው 👉 ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት👈 @NEBIYOU1112

Больше
Рекламные посты
223
Подписчики
Нет данных24 часа
-27 дней
-330 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
🌹የምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን ጉባኤ🌹      🌹    ሁለት ቀናት ቀሩት       🌹         🌹  ጥር 26/2016   🌹            🌹 4:00-6:00  🌹            🌹መካነ ቅዱሳን🌹
Показать все...
🔔እናስተዋውቃችሁ🔔   📖አባ ኢየሱስ ሞዐ ቤተመጻሕፍት 📖 ዛሬ ልናስተዋውቃችሁ የወደድ ነው በፃድቁ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ስም የተሰየመውን  የሰንበት ትምህርት ቤታችን  ቤተ መጽሐፍት ነው አብራችሁን ቆዩ። አባ ኢየሱስ ሞዐ ማን ናቸው? 📖እግዚአብሔር በ13ኛው መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው:: ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 📖እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው አገራችን በወንጌል ትምህርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ  ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ::📖 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 📖አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር: የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል::📖 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 📖ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምህርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን (ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው) ይህቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ::📖 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 📖አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምህርት: የምናኔ ማእከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ። ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ 📖አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ: ሲፈጩ: ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ::📖 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 📖በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ: ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው:: ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 📖በአንዴም ከዳሞ (ትግራይ) ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ (ወሎ) አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ: በስብከተ ወንጌል: በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ::📖 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 📖ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:📖 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 📖ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት አገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ (ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው) ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ::📖 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 በአገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምህርት አብስለው አመነኮሱና "ሂዱ! አገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው::📖 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 📖ከእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትንአቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የኋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ::📖 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 📖ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለአገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በኋላ አቅንተዋል:: ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 📖እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ: በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም:: "እንዘ የሃሊ ዘበሰማያት ዐስቦ:: መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል::📖 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 📖ከዚህ በኋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው ህዳር 26 (በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ) በ1292 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: <<ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው!!>> ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሰንበት ትምህርት ቤታችን ይህን ውለታ በማሰብ እንዲሁም ከጻድቁ ረድኤት በረከት ለመሳተፍ   ቤተመጽሐፍቱን በፃድቁ አባ ኢየሱስ ስም ሰይማ ምዕመናንን የእግዚአብሔር ቃል እንዲያነቡ እያደረገች ያለችሁ። አባ ኢየሱስ ሞዐ ቤተመጽሐፍት የአገልግሎት ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከቀኑ11:30-1:30 እንዲሁም ቅዳሜ 3:00-1:30
Показать все...
👏 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
፵ኛ ዓመት የኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ወልድ ዋህድ ሰንበት ትምህርት ቤት በ 1976 ዓ.ም ግንቦት ወር በእግዚአብሔር አምላክ መልካም ፈቃድ ተመሠረተ። ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከተመሰረተበት ግዜ አንስቶ በርካታ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን እያገለገለ ቆይቷል፡፡ በመንፈሳዊ አገልግሎት እህት ከሆኑ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር ጥሩ የሆነ መንፈሳዊ ቅርበት በመፍጠር በበርካታ የጋራ አገልግሎቶች ላይ መሳተፍ ተችሏል፡፡        ባለፉት 40 ዓመታት በሰንበት ትምህርት ቤታችን በስነምግባር ተኮትኩተው ፤ ጥሩ መንፈሳዊ ህይወት ያላቸው ፤ በዘመናቸው እግዚአብሔርን በፍርሀት ማገልግል የቻሉ በቁጥር በርካታ የሆኑ እህት እና ወንድሞች የፈሩ ሲሆን  አሁን ላይ ያለውም ትውልድ ይህንን ሰፊ የሆነ የአገልግሎት መዳረሻ በመረከብ እግዚአብሔር አምላክ በወደደ እና በፈቀደ መጠን የሰንበት ትምህርት ቤቷን አገልግሎቶች በሰፊው እያስቀጠሉ ይገኛሉ፡፡        በሰንበት ትምህርት ቤታችን ዘመን ተሻጋሪ ከሆኑ አገልግሎቶች መካከል የመንፈሳዊ ትምህርት እና የዝማሬ አገልግሎቶች ሰፊውን ቦታ ይይዛሉ፡፡ ምዕመናንን ብሎም አባለትን መሰረት በማድረግ ላለፉት 40 ዓመታት በሰንበት ትምህርት ቤታችን ውሰጥ ሰፋ ያለ የቃለ እግዚአብሔርማዕድ ማዘጋጀት እና መመገብ ተችሏል::
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
"ኃጢአት በሚሰረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን።”         🌹ጸሎተ ሃይማኖት🌹    🌹ሳምንታዊው የረቡዕ ጉባኤ🌹     🌷ርዕስ ምሥጢረ ጥምቀት🌷       🌹  ሰዓት 12:00-1:30🌹           🌷 ጥር 8/2016🌷   ቦታ  በወልድ ዋህድ ሰንበት ትምህርት ቤት
Показать все...
ነገ የገሀድ ጾም እስከ ስንት ሰዓት ነው? ለበዓሉ የሚቆርቡ እንዴት ነው የሚጾሙት? መልስ፦ ነገ ሰንበት ስለሆነ ከምግብ በመታቀብ ጾም የለውም ነገር ግን ዘወትር በአዋጅ አጽዋማት ላይ እንደሚውሉ ቅዳሜና እሁድ (ሰንበት) የጾም ምግብ በመብላት  ከጥሉላት ምግብ ብቻ በመከልከል ይጾማል :: -> ለበዓሉ የሚቆርቡ ግን ለቅዳሴው 15 ለቁርባን 18 ሰዓት በማስላት ከምግብ ይከለከላሉ። ይህም ማለት ከቅዳሜ ረፋድ 3 ሰዓት በኋላ ምግብ ያቆማሉ ማለት ነው ። ይህም ጠዋት ስለ ተመገቡ ሰንበትን ሽረው ጾሙ አያሰኝም ።
Показать все...
👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
❝ እግዚአብሔር ቃል ወደዚህ ዓለም ይመጣ ዘንድ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ይዋሐድ ዘንድ ምን አተጋው ? በጨርቅ ይጠቀለል ዘንድ በበረት ይጣል ዘንድ ምን አተጋው ? ... በፍዳ ተይዘን የነበርን እኛን ያድነን ዘንድ አይደለምን ? ❞ ️      ቅዱስ እለእስክንድሮስ
Показать все...
ልዩ የሕይወት ጉዞ በሰበታ ቤተ ደናግል እንደዚህ አለፈ
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ደረሰ
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.