cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Poem

ግጥምን ከእውነታ ጋር የያዘ ፍቅርን 💓 ሀዘንን 😔😭 ምኞትን 😑 ሀሳብን 🤔 የሚገልፅ ምርጥ ቻናል❣️❣️❣️ ቻናላችን ምስረታ ላይ ስላለ ቶሎ ይቀላቀሉን

Больше
Рекламные посты
252
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

አሞኛል😞 መናገር ከብዶኛል የውስጤን ነውጥቼ የሀሳብን መንጋ በጀርባዬ አንግቼ ሳቄን መልስልኝ በዛ በልጅነት የነፈከኝን ያ ምስኪኑ ልቤ ሀዘን የማያውቀው ያ ምስኪኑ አይኔ እንባ ያላዘለው ያ ምስኪኑ ጥርሴ የእውነት ፈገግታ ከፊቱ የማይለው ያ ንፁህ አዕምሮ ምንም ያልበረዘው ያ ስብዕና ክፋት ያላወቀው ያ ንፁህ አንደበት ክፋ የማይወጣው ገብተህ አሳመምከው አመሰቃቀልከው በዛ በልጅነት በደስታ ታጅቤ ፍቅሬን ሳጣጥማት እንደ ንብ ስንቀስማት ጊዜዬን ሳዜማት ሳድግ እያልኩ ሳስብ ስቀኝለት ቅኔ አመሰቃቀልከው ልኑር ብለህ ከጎኔ እንዲህ ነበርኩ ያኔ ቆይ እሺ ጠቀመህ ከስሜትህ አልፎ ህመሜ አሳመመህ ያ ንፁህ ልቤ ዝም ባለ አንደበት ልብህ ክፋት እንዳዘለ እኔ መች አወኩት አሁንማ አደኩ ልቤ ሳይታከም ቁስሌም ሳይሸርልኝ የልቤን ጠባሳ ማንም ሳያውቅልኝ ያለሁበትን ህመም ማንም ሳይረዳልኝ ትራሴን በእንባ በለቅሶ እያራስኩኝ አመታት አለፊኝ ያጨለምከውን ህይወት እኔ እንዴት ላብራው ለሰውስ ሄጄ ምን ብዬ ላስረዳው እንዴት ብዬ ልርሳው ያነባሁትን እንባ የለመንኩህን ልመና ሆድክ እንዲባባ አመመኝ ያልኩትን አዝነህ እንድትተወኝ ልጅ እኮ ናት ብለህ እንድትራራልኝ መርሳት እኮ አልቻልኩም መኖርም መብላትም መደሰትም አልቻልኩም ከዛን ቀን ጀምሮ ለዚህ ሁሉ አመታት ከልቤ አልሳኩም በዛች እድሜዬ የወሰድክብኝን ሳቄን መልስልኝ😔 @chrsti1 በልጅነታቸው ብዙ ለተሰቃዩ እህቶቻችን🥺
Показать все...
2.60 MB
🔥 3
ዕድሌ ነው... . ዕድሌ ነው... በሚስት ልወሰን፣ እኔ ትዳር ሲያምረኝ፤ ሳታገባ 'ምትቆይ፣ አንድም ሴት አትገኝ . ዕድሌ ነው... እኔ ዲግሪ ስይዝ፣ ዲግሪ ዋጋ ያጣል፤ ገንዘብ ያለው ሁሉ፣ ዶክትሬት ያመጣል . ዕድሌ ነው... እኔ መድረክ ስይዝ፣ ይፈታል ጉባኤ፤ እኔ መጾም ሲያምረኝ፣ ይሆናል ትንሣኤ። . ዕድሌ ነው... በቁርባን ለመኖር፣ ንሰሐ ስገባ፤ አቁራቢው ፖትልኮ፣ ቤተመንግሥት ገባ። . ዕድሌ ነው... እኔ ኳስ ስገዛ፣ ሜዳው ይታረሳል፤ እኔ ቤት ሲኖረኝ፣ ሰፈሬ ይፈርሳል። . ዕድሌ ነው... ለተሾመ ሁሉ፣ እንዳልኖርሁ ስለፋ፤ እኔ አለቃ ስሆን፣ የሚታዘዝ ጠፋ። . ዕድሌ ነውና... ከዕለታት አንድ ቀን፣ መንገሤ ባይቀርም፤ እኔ ንጉሥ ስሆን፣ ሀገሪቱ አትኖርም።
Показать все...
👏 3👍 2🤔 2
➺አብረን እንሞታለን                                                                    ግድ የለሽም እንጀምር ያማረ ይሆናል እጅግ የሚያምር እንዝለቅ አልፋ ብለን  እስከ ኦሜጋ አትፍሪ ነይ ወደ እኔ ከኔጋ እናንጽ ፍቅራችንን  ከአለት ላይ ከፍ በአለም ብለን እንድንታይ ሁሌም ተጨባብጠን መዳፍሽ ከመዳፌ እንኑር ምግብ እየሆነኝ ከንፈርሽ ለአፌ እንደ አባታችን አብርሃም ሳራ ''የኔ ጌታ'' የኔ ንግሥት ስንባባል በየተራ ብዙ አመታትን ኖረን ኖረን ኖረን እሽ በይኝ በልጆቻችን ተከብረን አብረን እንሞታለን።
Показать все...
🥰 4🤮 4👍 1
ሳልነግርሽ… . አፍቅሬ እንዳጣሁሽ… በነብያቶች አፍ፣ ፍልስፍና ሚመስል፣ትንቢት ተነገረ ታምር የሚሰራ…          ጎትቶ ጎትቶ፣        በመርፌ ቀዳዳ፣ግመል አሻገረ ግመሉ ሲሻገር፣መርፌው ተሰበረ፡፡ በሰባራ መርፌ…. ፍቅርሽን ከፍቅሬ፣ባንድነት ልሰፋ ይኸው እደክማለሁ… ክር ሆነሽ እያጠርሽ፣              ኖራለሁ ስለፋ፡፡ …………………………………. ሳልነግርሽ…. የኔ አለም ያላንቺ፣ እንደሆነ ራቁት ባንቺ እንደነበር        ቀን ና ሌሊቴ የሚፈራረቁት፡፡ እንደተለየሽኝ… አለም ባዶ ሆና፣        መኖር እንዳስጠላኝ ፍቅርሽ እከክ ሆኖ… በልቤ ተተክሎ፣ነፍሴን እንደበላኝ፡፡ ………………………………… ሳልነግርሽ…. የነብያት ትንቢት፣       በኔ መፈፀሙን ‹‹ታምሪያለሽ››እያልሁኝ፣          ‹‹ተአምር››  ማክተሙን የተለየሽኝ ለት… ምፅአት መምጣቱን፣          የኔአለም መቆሙን፡፡ ………………………………………… ሳልነግርሽ…. ካጣሁሽ በኋላ….     ባለፍኩት ጭንቅ ዓለም                     ፣የስቃዬን መአት   አፍቅሮ ማጣት ነው…       በሰባራ መርፌ፣ እውነትን መስፋት ነው        ፣ለካንስ ምፅአት፡:
Показать все...
🔥 2 1
❣️ እውነት ናፍቀኸኛል ❣️ ይዤህ ጥፍት ብል እሩቅ ካለ ቦታ ሰው ከሌለበት እኔና አንተ ብቻ ደረትህ ላይ ተኝቼ ክንድህን ብንተራሰው ትንፋሽህን ተንፍሼ አይንህን እያየው አለምን ብንተዋት ጊዜን አቁመነው ቢያሻን እየበላን ሲያሻን እየጠጣን ያሻንን አድርገን በርቀት በቦታ በሰዉ ጫጫታ የተፈተነውን ይህን  ፍቅራችንን ምናለ ብንክሰው ? ጆሮ ዳባ አልብሰን ልባችንን ብቻ ብናስተናግደው የፍቅራችንን ጥግ ኖረን ብንኖረው እንኳንስ ሰዉ እንኳንስ ጨረቃ ይቀናብን ነበር ምንተኛበት ሶፋ ❣️
Показать все...
6
ውሰድልን ቅዱስ አርጎ ፈጥሮት ፡ ቀርፆት በዐምሳሉ አውርሶት ሲያበቃ ፡ ምድሪቷን በሙሉ ደስታ ስላጣበት ፡ እርሱን ተመልክቶ እርሷን ፈጠረለት ፡ ከአጥንቱ መርጦ። ታዲያ...ማ ያዳም ማዘን ፡ ለኟም ተረፈና አጥንቱ በእሾህ ፡ ተቀየረችና አሁን ያዳም ልጆች  ፡ በሷ ሰላዘንን በተገላቢጦሽ ፡ እርሷን ውሰድልን
Показать все...
👍 1
01:02
Видео недоступноПоказать в Telegram
11.03 MB
2🥰 2
Показать все...
1.07 MB
2👍 1
Arsuya🥺😍👏 @PrincessGirl216
Показать все...
1.60 MB
🚶‍♀️🚶‍♀️  ሒጂ🚶‍♀️🚶‍♀️ መሄድን ካማረሽ ልብሽ ከተነሳ ጓዙን አሰባስቦ ለመሄድ ካነሳ የትላንት ትዝታን ያን ያሳለፍነው ሁሉ አልተውህ ዘላለም ከተረሳ ቃሉ ግድ የለም እራቂ ካሻሽ ቦታ ሂጂ ልብሽ ከፈቀደ ሌላን ሰው ልመጂ ሂጂ ሸኝሻለው በእንባ እየታጠብኩ መርሳትን እንዲችል ልቤን እያሳመንኩ የመተውን አቅም ካንቺው እያስተማርኩ ሂጂ ግድ የለሽም ልብሽ ከቆረጠ ባንድ የፍቅር መንገድ ሁለት ከረገጠ አንድን እየገፋ ሌላን ከጨበጠ ካስከረመው ይልቅ መጪን ካስበለጠ ሂጂ ግድ የለሽም ባያስችለኝ እንኳን ከጎኔ ስትርቂ ልረሳሽ ባልችልም ከልቤ ብጠልቂ ሂጂ ግድ የለሽም ልቤ አያዝንብሽም ለኔማ እኮ በቂ መኖር በትዝታሽ የእውነት በነበረው በትላንቱ እሺታሽ ዛሬ ምን ተገኝቶ ልብሽ መሄድ ቢያምረው አቲጂ አልልም የወሰነን ማስቆም ትርፉ ኪሳራ ነው አሁንም የምልሽ ሂጂ ካሻሽ ቦታ ነገን ይስመርልሽ ልብሽን ከረታ ሂጂ የእውነት ይቅናልሽ መንገዱ ለኔ አላለሽም አልሆነም ፍቃዱ እናም ሂጂ አንቺ የኔው ፍቅር ምርጫ እሱ ካልፈቀደ አይሆን በኔ ብልጫ ሂጂ ግድ የለሽም ለምቴጂው እንጂ ለኔ አልተሰጠሽም የኔው መሻት እንጂ የሱ አልነበርሽም ሂጂ ግድ የለሽም ለምትኖሪው እንጂ ለኖርሽው አይደለሽም ሂጂ ግድ የለሽም 🚶‍♀️🚶‍♀️🚶‍♀️🚶‍♀️
Показать все...
👍 3🔥 2 1
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.