ru
Feedback
Learn Tigrigna with AFRO💊💊💊https://youtube.com/@learntigrignawithafro?si=BGiu7TTONxi2VeXC

Learn Tigrigna with AFRO💊💊💊https://youtube.com/@learntigrignawithafro?si=BGiu7TTONxi2VeXC

Открыть в Telegram

Learn Tigrigna with me, You will be fluent soon 💯💯💯 Join my YouTube channel.... https://youtube.com/@learntigrignawithafro?si=BGiu7TTONxi2VeXC

Больше
455
Подписчики
-124 часа
+47 дней
+830 дней
Архив постов
YouTube ላይpost bidereg yshalal ende😂

መልስ መልሲ ጅል የማይረባ/የማትረባ የትግራይ እናቶች ፀጉራቸው ከተሰሩ በኋላ መጨረሻ ላይ ሚሰሩት(will send u pic later) ሲኒ

እስከ ፯ ሰዓት ድረስ ሞክሩ

ዓሻ በኽቲ ድርማሞ ፍንጃል እነዚህን በትክክል የመለሰልኝ 1gb internet gift....https://t.me/tigrignaye

እንኳን አብሮ አደረሰን አዲሱ ዓመት የሠላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ፣ የመፈቃቀርና የመተዛዘን ይሆንልን ዘንድ እየተመኛው፣ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን!!

አቱም ሰባት ከመይ ቀኒኹም ጠፊአ ዶ?ስራሕ ትምርቲ ቢዚ ጌርኒ ከመይ አለኹም ኸ? ስሙኝማ ስልኮች እየሸጥኩ ነው(Samsung,tecno,infnix,apple,bontel) all r available on hand ምትፈልጉ ካላችሁ አዋሩኝ እስኪ inbox

ካነበብኩት ይህ ፅሁፍ ለወጣቶች ነው ፖለቲካ አይደለም ማእበሉ ሲመጣ መርከቡን ካልሰራህ አሊያም ምትሸሸግበት ዋሻ ከሌለህ ዋና መቻል ከማእበሉ አያስጥልህም ይበላሃል። ጦረኞች ያፏጫሉ ሟቾች ፈረሶቻቸውን ያስቀድማሉ አትወስወስ የፖለቲካ ጭቃ ያበላሸውን ወለል አፀዳለው ብለህ አትረገጥ። ወጣት ነህ? መብራት አስገቡልኝ በል ስልክህን ቻርጅ አድርግ ፣ ኔትዎርክ ይስተካከልልኝ በል Online Course ውሰድ ፣ አእምሮህ ሲደክም የስፖርት ማዘውተሪያ ይሰራልኝ በል ሰውነትህን አንቀሳቅሰው ፣ ኡኡኡ ውሃ ይግባልኝ በል ታጠብ ሰፈርህ ሰላም ካጣ ከየመኖች ተማር የሰፈር ህግ አውጣ የመን ውስጥ አንድ አዲስ ሰው ካየህ ስሙን እና አድራሻውን ማንም መጠየቅ ይችላል አደጋ ሊሆንብህ ይችላላ ካልተናገረ ፖሊስ ይዞልህ ይሄዳል። ሰላምህን ሳትጣላ ሳትጋጭ ጠብቅ። ወጣት ነህ? አሁን ጉልበት ሳለህ ተሯሯጥ እና ለኪስህም ለሳጥንህም ያንን መለኛ የሆነ ወረቀት አጭቅበት። እድሜህ ከሄደ በውሃላ የመጣ ገንዘብ እርዳታ ትሰጠው እንጂ ያማረህን ምግብ አትበላ ዶክተሩ ብዙ ምግብ ከልክሎሃል የተፈቀደልህንም አትበላ ጥርስህ አልቋል ጁስ መጠጣት ብቻ ምርጫህ ሳይሆን ገንዘብ ስራ መንገድ ካጣህ አንብብ ክህሎትህን አዳብር ከዛ ወደስራው ና። ወጣት ነህ? ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ሆነ መምጣት የሚፈልጉት ወንበራቸውን የሚያጠብቁት ቀጥቅጠው ባስገቧቸው እና ተጣመሙ ብለው በጣሏቸው ሚስማሮች ልክ ነው። ወጣት ለወንበሩ ሚስማር ነው እየተመታ ይይዛል ሲጣመም ይጣላል ከወንበሩም ሚታየው እንጨትና ቀለሙ እንጅ ስንት ሚስማር እንኳ እንደፈጀ አናፂው አያቀውም ። ታድያ ለምን ጀግና ልሁን ትላለህ? ለምን ነገን መኖር አትመኝም? ወጣት ሆይ አንድ ነገር ተረዳ እኛ መላእክቶች አይደለንም ለሰዎች አልተላክንም ሰዎችን ሁሉ መጠበቅ እና ማስደሰት አንችልም አለማችን ሁለት ህግ አላት። ህግ አንድ - ጥቂቶች ጌታ ብዙዎች ባሪያ ሆነው ሲኖሩባት ህግ ሁለት- ባሪያዎች ሚሞቱት ጥቂት ጌቶችን ለመተካት አሊያም አዲስ ጌታ ለመሆን ነው ሌሎቹ ግን ባሪያ እንደሆኑ ይቀጥላሉ ምክኒያቱም ህግ አንድ እንዲህ ይላል "ጥቂቶች ጌታ" Winter is Coming ለወጣቶች ማእበል እየመጣ ነው ሚያስብ ጭንቅላት ያለው ይሻገረዋል የሌለው ማያስበውንም ከማጣት ማንም አያግደውም። ማንም ይምጣ ማንም ይሾም ማንም ይውረድ ወጣት ከሆንክ መኖር ይገባሃል እና ከቻሉ ጠረጴዛ ላይ በመግለጫ ጋጋታ ይጨርሱት ካልቻሉ ፓርላማ ውስጥ ይደባደቡ። አንተ በቲቪ እያየህ ሳቅባቸው እንጅ አንድ ቃታ ባልሳቡ ጦርነት መሃል ሳይገቡ በሚቸከችኩ ሰዎች ተገፋፍተህ ለሞት እጅህን አትዘርጋ እውነተኛ ታጋይ ነኝ ካልክ ፌስቡክ ላይ ሆነ ዩትዩብ ላይ ለሚፎክረው ሰውዬ እንዲህ በለው "እኔ ወደግንባር ልሄድ ነው መንገዱን አንተ ስለምታውቀው ና ቅደም አንተ ምራኝ ያሆ"