cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

አንድ ላይ 😊

😊selam sewoch #አንድላይ nen bezi channel gtmochen yehiwot tekami eytawochen ena psychology .............

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
189
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

00:18
Видео недоступноПоказать в Telegram
90650ebef01649b0a098d09657a5fa35.mp48.52 KB
.4⃣.......የመጨረሻው ••• አስተውል ... ••• ሁለተኛውን ከመረጥክ ልክ እንደ ንስሩ አምስት ዋጋዎችን መክፈል አለብህና ዝግጁ ሁን ... ፩ኛ. ራስህን ከመጥፎ ነገሮች አርቀህ በፅሞና ሃሳብህን መግራት ጀምር ...ንስር አሞራው ከፍተኛ ተራራ ላይ የሚወጣው ከሁሉም ንስሮች እርቆ ለህይወቱ ዋጋ ለመክፈል ነው ... ይህን አይነት መላ ምሁራኑ "የስኬት ሱባኤ" ይሉታል። ፪ኛ. አንገብጋቢ ችግርህን ለመፍታት ቁርጥ ያለ አቋም ይዘህ እስከ ሞት የሚያደርስ መስዋትነት መክፈል። ንስሩ አፉ ላይ ያለውን ምግብ ማምጫ መንቁሩን እንደሚያስወግደው ሁሉ። ፫ኛ. መስዋት የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትዕግስት መጠበቅ ... ይህ ደግሞ ንስሩ መንቁሩ እስኪያድግለት ድረስ ምግብ ሳይበላ እንደሚኖረው ሁሉ አንተም ዋጋ የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትእግስት እና እምነት መጠበቅ። ፬ኛ. በትእግስት ጠብቀህ ያሰብከው ነገር ከመጣ በዋላ ህይወትህን ጠፍንገው የያዙህን ነገሮች መፍታት ... ልክ ንስሩ መንቁሩ እንዳደገለት የእግሩን ጥፍሮች በመንቁሩ እየወጋ እንደሚያስወግዳቸው ሁሉ። ፭ኛ. ሁሉን ካሳካህ በዋላ ወደ ህልምህ መብረር ... ይህ ማለት ንስሩ የእግሮቹን ጥፍር አስወግዶ እና አሮጌ ክንፎቹን አስወግዶ ከጠበቀ በኋላ አዲስ ክንፍ ፣ አዲስ መንቁር እና አዲስ ጥፍር ካበቀለ በዋላ እንደ አዲስ ጉልበታም ንስር ቀሪ ዘመኑን ይኖራል። ሲጠቃለል ... አንተም ፣ አንቺም ፣ እኔም በዚህ ሁሉ መንገድ አልፈን ከባዱን ጊዜ ካለፍን በዋላ በአዲስ የህይወት መንቁር ፣ የተስፋ ጥፍር እና የስኬት ክንፍ ከፍ ብለን እንበር ዘንድ ..... ኑ ንስር አሞራን እንምሰል። #ለዚህ ነው ንስር የጥንካሬ የአይበገሬነት እና የከፍታ የመታደስ የአትኩሮት የሐያልነት ምልክት የሆነ ልዩ ፍጡር በመሆኑ በርካታ ሐገሮች ንስርን ምልክታቸው በማድረግ የሚጠቀሙት!! @fitsumhelina
Показать все...
3⃣ ፭ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል። ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡ • • • ወዳጄ ሆይ:- ችግር ገጠመኝ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል ፣ ችግሬ ... ችግሬ ... እያልክም ነጠላ ዜማ አትልቀቅ ፣ ፊትህንም ችግር ፊት አታስመስል ፣ ጥቅም ላይ እያፈጠጠ የሚከተል ሰው በበዛበት አለም ላይ መውደቅህን መጥሪያ ካርድ አታሰራበት ፣ መራብ መጠማትህን ፖስት ለማድረግ አትቸኩል ፣ መገፋትህን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረህ ኡኡኡ አትበል ፣ ስንት ነገር መስራት የምትችልበትን አዕምሮ ለሃሜትና "አሉ ... አለች" መሳሪያ በመጠቀም "የውሸት እየኖርክ - የእውነት አትሙት" ...በቃ! ... ልክ እንደ ንስር አሞራ በህይወትህ አጋማሽ ላይ ምርጫ መቶልሃል ... ፩ኛ. ችግሩን ታቅፎ መሞት ፪ኛ. ለችግሩ መስዋትነት ከፍሎ ማለፍ ....... @fitsumhelina
Показать все...
1⃣ #ንስር ስለ ንስር አሞራ ስነግርህ ከሚገርም መሳጭ ታሪክ ጋር ነው ... እውነት እውነት እልሃለሁ የንስር አሞራ ታሪክ በሁላችንም ህይወት ውስጥ አለና ከራስህ ጋር እያዛመድክ ካነበብከው ለለውጥህ ስንቅ ይሆንሀል ። * ንስር አሞራ ፀሐይን ቀጥ ብሎ ማየት የሚችል ወደ ጸሐይ አቅጣጫ ጨረሩን እያየ መብረር የሚችል ብቸኛው የአለማችን ፍጥረት ነው ። አንድ ንስር በመብረር ላይ እያለ ቁራወች ጭልፊቶች 100 ወይም 200 ሁነው ከበው ሲጮሁበት ወደጸሐይ እያየ ከፍ ብሎ ይበራል ሌሎቹ ፍጥረቶች ወደ ጸሐይ እያዩ መብረር ስለማይችሉ ይጠፋቸዋል!! * ንስር ከሰው አይን 8 እጥፍ የተሻለ ማየት ይችላል ፣ * ንስር ከ5-7 ኪሜ ያለን ለማደን የሚፈልገውን ነገር በደንብ ለይቶ ማየት ይችላል፣ * ንስር ለአደን እስከ 120 km አካሎ ይበራል፣ * ንስር መመጠለያ ከሌለበት አካባቢ ሁኖ ሃይለኛ ዝናብ ቢመጣ ወደላይ በምጠቅ ከደመና በላይ በሮ ዝናብና ወጀቡን ከስር ያደርጋል እንጂ በዝናብ አይቀጠቀጥም፣ * ንስር አድኖ እንጂ ጭራሽ የሞተ አይበላም፣ * ንስር ሲታመም ጸሐይን አተኩሮ በማየት ነው ህክምና የሚያገኘው፣ * ንስር 340° ማየት ይችላል። ሰው 180° አካባቢ ነው ማየት የሚችለው፣ * ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው ካልክ ልክ ነህ ... ግና 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል ... - የመጀመሪያው :- ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል ... - ሁለተኛው :- አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ(መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል ... @fitsumhelina
Показать все...
2⃣ - ሶስተኛው:- ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል። እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው። 1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ? 2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ? የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል። ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን እነዚህን አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል። ፩ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል። ፪ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል። ፫ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡ ፬ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል። @fitsumhelina
Показать все...
00:15
Видео недоступноПоказать в Telegram
13.17 MB
I am creating contents on tiktok support 🙏😊
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Take the time to judge. A beautiful little girl was holding two apples in her hands. Her mother walked into the room and gently, with a smile, asked her little princess, "Honey, would you mind giving your mommy one of the two apples?" The little girl looked at her mother for a few seconds and then suddenly took a bite of one apple, followed quickly by another. The woman felt a smile harden on her face and tried very hard not to show her disappointment. She was upset that her beloved daughter was not willing to share with her. Suddenly the little girl held out one of the bitten apples and said: "Mama, take this one, it's sweeter!" Moral: No matter how mature, experienced and knowledgeable you are, never rush to judge others. Give them a chance to explain themselves. What you see can be very misleading. Often seeing only the big picture will mislead us as to the true motives for the other person's actions. Join us for more -> @psychologiesi 💡
Показать все...
00:15
Видео недоступноПоказать в Telegram
7.42 MB
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.