cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የቡታጀራ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዐ

★የቻናሉ አላማ 1.በከተማችን ላሉ ሙስሊም ተማሪዎች የዲን ግንዛቤ መስጠት። 2.በከተማችን ለሚሰጡ ዳዐዋ ፕሮግራሞች እና ኮርሶች ማሳወቅ። 3.በተማሪዎች ለሚነሱው ጥያቄዎች በቂ፣መረጃ አቀፍ እና ፍትሀዊ በሁነ መንገድ መመለስ። ★ለጥያቄ፣አስታየት፣ቅሬታ፣ማስተካከያ @Abu_sufyan ወይም @Talib_ALilm

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
202
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

📌 ልጅ አገረድ አገባ ግን (ቢክር) ድንግል አላገኘባትም ?? ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) ተጠየቁ #ጥያቄ:- ሰውየው ልጅ አገረድ አግብቶ ድንግል ሁና ካላገኛት ምን ማድረግ ነው ያለበት ? #መልስ:- ይሄ ብዙ ምክኒያቶች ይኖሩታል : ድንግሏ ምናልባት ያለ ዝሙት ሊፈርስ ይችላል። የልጂቱ ውጫዊ ስብዕናዋ መልካም ከሆነ እናም በዲኗ የተስተካከለች ከሆነች በሷ ላይ ጥሩ ግምትና መልካም ጥርጣሬን ማሳደር የግድ ነው። በዚያ ላይ ጥሩ ጥርጣሬን ማሳደር ግድ ይላል። 🔸 ወይንም አፀያፊውን ዝሙት ሰርታ ከዚያ አላህ መርቷት ከሰራችሁ መጥፎ ተግባር ተፀፅታና ቶብታም ሊሆን ይችላል። ከዚያም ወደ ጥሩነትና መልካምነት ከተቀየረች (ቢክራ) ድንግል አለመኖሯ እሱን አይጐዳውም። 🔸 ምናልባትም ድንግሏ በወር አበባ ብርታት ምከንያት ፈርሶ ሊሆን ይችላል። ጠንካራ (ሃይድ) የወር አበባ (ቢክራን)ድንግልን ያፈርሳል። ይሄን ኡለሞች አውስተውታል። 🔸 ልክ እንደዚሁም በአንዳንድ ዝላዮች ድንግል ሊፈርስ ይችላል። ከሆነ ቦታ ወደሆነ ቦታ ስትዘል። ወይንም ከከፍተኛ ቦታ ወደ ዝቅተኛ ቦታ በምትወርድ ጊዜ በዚህ አጋጣሚ ድንግል ሊፈርስ ይችላል። ➪ ስለዚህ የድንግል መፍረስ የግድ በአፀያፊው ዝሙት ብቻ ሊሆን አይችልም በጭራሽ ከዝሙት ውጭ በሆነ ክስተት ነው ድንግሌ የፈረሰው ካለች ወይንም በዝሙት ነው ድንግሌ የፈረሰው ግን ተገድጄ እና ተደፍሬ ነው ካለች ይሄ እሱን አይጎዳውም። 🔸 ወይንም በፍላጎቷ ዝሙት ሰርታ ከሆነ ድንግሏ የፈረሰው ግን ያንን ያደረገችው በማታውቅበትና በመሃይምነቷ ጊዜ እንደሆነም እናም አሁን ከዚያ ቶብታና ተፀፅታ ከሆነ ይሄም እሱን አይጎዳውም። 🔸 ይሄን የሷን ሚስጥር ሊበትንባት እና ሊያሰራጭባት አይገባም ይልቁንስ ሊደብቅላት ይገባል። በእርሱ ግምት እውነተኛነቷንና ቅንነቷን እናም መስተካከሏን ካመነበት ከእርሱ ጋር ያስቀራታል። ካሎነ ግን በሷ ላይ ያደረበት ግምት ጥሩ ካልሆነ ይፈታታል የሷን ሚስጥር ከመደበቅና ከመጠበቅ ጋር በጭራሽ ሚስጥሯን ባደባባይ መግለፅ አይገባውም።
Показать все...
‍ አላህ የማይወዳቸው አስር ዐይነት ሰዎች‼️ 1ኛ, ከሀዲያን ﴿قُل أَطيعُوا اللَّهَ وَالرَّسولَ فَإِن تَوَلَّوا فَإِنَّ اللَّهَ لا يُحِبُّ الكافِرينَ﴾ {(ሙሐመድ ሆይ) አላህንና መልእክተኛውን ታዘዙ በላቸው። ዘወር ካሉ አላህ ከሀዲያኖችን አይወድም} [አል_ዒምራን:32] 2ኛ, በዳዮች ﴿وَأَمَّا الَّذينَ آمَنوا وَعَمِلُوا الصّالِحاتِ فَيُوَفّيهِم أُجورَهُم وَاللَّهُ لا يُحِبُّ الظّالِمينَ﴾ {እነዝያ ያመኑትንና መልካም ስራ የሰሩትማ ምንዳቸውን ይሞላላቸዋል። አላህ በዳዮችን አይወድም} [አል_ዒምራን:57] 3ኛ, አታላዮች ﴿وَإِمّا تَخافَنَّ مِن قَومٍ خِيانَةً فَانبِذ إِلَيهِم عَلى سَواءٍ إِنَّ اللَّهَ لا يُحِبُّ الخائِنينَ﴾ {ከሕዝቦች ክህደትን (ማታለልን) ብትፈራ በመተካከል ላይ ሆናችሁ ቃል ኪዳናቸውን ወደነሱ ጣልላቸው። አላህ አታላዮችን አይወድም} [አል_አንፋል:58] 4ኛ, ድንበር አላፋዎች ﴿يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا لا تُحَرِّموا طَيِّباتِ ما أَحَلَّ اللَّهُ لَكُم وَلا تَعتَدوا إِنَّ اللَّهَ لا يُحِبُّ المُعتَدينَ﴾ {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ለእናንተ የፈቀደላችሁ ምርጦችን እርም አታድርጉ። ወሰን (ድንበርም) አትለፉ። አላህ ወሰን አላፊዎችን አይወድም} [አል_ማኢዳ:87] 5ኛ, አበላሺዎች (አጥፊዎች) { وَاللَّهُ لا يُحِبُّ المُفسِدينَ﴾ {አላህ አበላሺዎችን አይወድም} [አል_ማኢዳ:64] 6ኛ, ኩራተኞች ﴿إِنَّ اللَّهَ لا يُحِبُّ الفَرِحينَ} {አላህ ኩራተኞችን አይወድም} [አል_ቀሰስ:76] 7,ጉረኞች ﴿وَاللَّهُ لا يُحِبُّ كُلَّ مُختالٍ فَخورٍ} {አላህ ኩራተኛና ጉረኛን ሁሉ አይወድም} [አል_ኸዲድ:23] 8ኛ, ከዳተኛና ኃጢኣተኛ ﴿ إِنَّ اللَّهَ لا يُحِبُّ مَن كانَ خَوّانًا أَثيمًا﴾ {አላህ ከዳተኛና ኃጢኣተኛ የሆነን ሰው አይወድም} [አል_ኒሳእ:107] 9ኛ, ኩራተኛ ﴿لا جَرَمَ أَنَّ اللَّهَ يَعلَمُ ما يُسِرّونَ وَما يُعلِنونَ إِنَّهُ لا يُحِبُّ المُستَكبِرينَ﴾ {አላህ የሚደብቁትንም ግልፅ የሚያደርጉትንም የሚያውቅ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም። እሱ ኩራተኞችን አይወድም} [አል_ነሕል:23] 10ኛ, አባካኞች ﴿يا بَني آدَمَ خُذوا زينَتَكُم عِندَ كُلِّ مَسجِدٍ وَكُلوا وَاشرَبوا وَلا تُسرِفوا إِنَّهُ لا يُحِبُّ المُسرِفينَ﴾ {የኣደም ልጆች ሆይ! (ሀፍረተ ገላችሁን የምትደብቁበትን) ጌጣችሁ በመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ። ብሉም ጠጡም አታባክኑ። አላህ አባካኞችን አይወድምና} [አል_አዕራፍ:31] 🖊️ማስታወሻ❗ 6ኛ ላይ "الفَرِحينَ" ተብሎ የተቀመጠውና 9ኛ ላይ "المُستَكبِرينَ" ተብሎ የተቀመጠው ሁለቱም የኩራተኞች መገለጫ ሲሆኑ "الفَرِحينَ" ማለት አላህ ውለታ ውሎላቸው ለዝያ ውለታ ማመስገን ሲገባቸው አላህን በማመፅና ባሮቹ ላይ በመንቀባረር የሚኩራሩት ሲሆኑ፤ "المُستَكبِرينَ" ማለት ደግሞ በየትኛውም ዐይነት ሁኔታ የሚኩራሩትና የታወቀው “ኩራተኛ” የሚባሉት ሰዎች ናቸው።
Показать все...
‍ አላህ የማይወዳቸው አስር ዐይነት ሰዎች‼️ 1ኛ, ከሀዲያን ﴿قُل أَطيعُوا اللَّهَ وَالرَّسولَ فَإِن تَوَلَّوا فَإِنَّ اللَّهَ لا يُحِبُّ الكافِرينَ﴾ {(ሙሐመድ ሆይ) አላህንና መልእክተኛውን ታዘዙ በላቸው። ዘወር ካሉ አላህ ከሀዲያኖችን አይወድም} [አል_ዒምራን:32] 2ኛ, በዳዮች ﴿وَأَمَّا الَّذينَ آمَنوا وَعَمِلُوا الصّالِحاتِ فَيُوَفّيهِم أُجورَهُم وَاللَّهُ لا يُحِبُّ الظّالِمينَ﴾ {እነዝያ ያመኑትንና መልካም ስራ የሰሩትማ ምንዳቸውን ይሞላላቸዋል። አላህ በዳዮችን አይወድም} [አል_ዒምራን:57] 3ኛ, አታላዮች ﴿وَإِمّا تَخافَنَّ مِن قَومٍ خِيانَةً فَانبِذ إِلَيهِم عَلى سَواءٍ إِنَّ اللَّهَ لا يُحِبُّ الخائِنينَ﴾ {ከሕዝቦች ክህደትን (ማታለልን) ብትፈራ በመተካከል ላይ ሆናችሁ ቃል ኪዳናቸውን ወደነሱ ጣልላቸው። አላህ አታላዮችን አይወድም} [አል_አንፋል:58] 4ኛ, ድንበር አላፋዎች ﴿يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا لا تُحَرِّموا طَيِّباتِ ما أَحَلَّ اللَّهُ لَكُم وَلا تَعتَدوا إِنَّ اللَّهَ لا يُحِبُّ المُعتَدينَ﴾ {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ለእናንተ የፈቀደላችሁ ምርጦችን እርም አታድርጉ። ወሰን (ድንበርም) አትለፉ። አላህ ወሰን አላፊዎችን አይወድም} [አል_ማኢዳ:87] 5ኛ, አበላሺዎች (አጥፊዎች) { وَاللَّهُ لا يُحِبُّ المُفسِدينَ﴾ {አላህ አበላሺዎችን አይወድም} [አል_ማኢዳ:64] 6ኛ, ኩራተኞች ﴿إِنَّ اللَّهَ لا يُحِبُّ الفَرِحينَ} {አላህ ኩራተኞችን አይወድም} [አል_ቀሰስ:76] 7,ጉረኞች ﴿وَاللَّهُ لا يُحِبُّ كُلَّ مُختالٍ فَخورٍ} {አላህ ኩራተኛና ጉረኛን ሁሉ አይወድም} [አል_ኸዲድ:23] 8ኛ, ከዳተኛና ኃጢኣተኛ ﴿ إِنَّ اللَّهَ لا يُحِبُّ مَن كانَ خَوّانًا أَثيمًا﴾ {አላህ ከዳተኛና ኃጢኣተኛ የሆነን ሰው አይወድም} [አል_ኒሳእ:107] 9ኛ, ኩራተኛ ﴿لا جَرَمَ أَنَّ اللَّهَ يَعلَمُ ما يُسِرّونَ وَما يُعلِنونَ إِنَّهُ لا يُحِبُّ المُستَكبِرينَ﴾ {አላህ የሚደብቁትንም ግልፅ የሚያደርጉትንም የሚያውቅ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም። እሱ ኩራተኞችን አይወድም} [አል_ነሕል:23] 10ኛ, አባካኞች ﴿يا بَني آدَمَ خُذوا زينَتَكُم عِندَ كُلِّ مَسجِدٍ وَكُلوا وَاشرَبوا وَلا تُسرِفوا إِنَّهُ لا يُحِبُّ المُسرِفينَ﴾ {የኣደም ልጆች ሆይ! (ሀፍረተ ገላችሁን የምትደብቁበትን) ጌጣችሁ በመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ። ብሉም ጠጡም አታባክኑ። አላህ አባካኞችን አይወድምና} [አል_አዕራፍ:31] 🖊️ማስታወሻ❗ 6ኛ ላይ "الفَرِحينَ" ተብሎ የተቀመጠውና 9ኛ ላይ "المُستَكبِرينَ" ተብሎ የተቀመጠው ሁለቱም የኩራተኞች መገለጫ ሲሆኑ "الفَرِحينَ" ማለት አላህ ውለታ ውሎላቸው ለዝያ ውለታ ማመስገን ሲገባቸው አላህን በማመፅና ባሮቹ ላይ በመንቀባረር የሚኩራሩት ሲሆኑ፤ "المُستَكبِرينَ" ማለት ደግሞ በየትኛውም ዐይነት ሁኔታ የሚኩራሩትና የታወቀው “ኩራተኛ” የሚባሉት ሰዎች ናቸው። https://t.me/Pointing_to_the_True_Religion
Показать все...
ክርስቲያን መሆን ጉዳቱና ጉዱ

ይህ ቻናል በአላህ ፍቃድ ወደ ትክክለኛውና ወደ ተፈጠርንለት ሀይማኖት ማመላከት ነው

አደራ! እናንተ እውቀት ፈላጊ ወንድም እህቶች ኪታብ ላይ አደራ!! ምንም እንኳ ሸቅለን አዳሪ ብንሆን ጧትና ማታ ላይ እንጠንክር قال العلامة ابن مانع رحمه الله لا بد لطالب العلم من المواظبة على الدرس والتكرار فى أول الليل وآخره ولهذا يقال من أسهر نفسه بالليل فقد فرح قلبه بالنهار ነፍሱን በለሊት እንቅልፍ ያሳጣ ሰው በቀን ላይ ልቡ በእርግጥ ይደሰታል ከሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም ተቅሪር የተወሰደ
Показать все...
አደራ! እናንተ እውቀት ፈላጊ ወንድም እህቶች ኪታብ ላይ አደራ!! ምንም እንኳ ሸቅለን አዳሪ ብንሆን ጧትና ማታ ላይ እንጠንክር قال العلامة ابن مانع رحمه الله لا بد لطالب العلم من المواظبة على الدرس والتكرار فى أول الليل وآخره ولهذا يقال من أسهر نفسه بالليل فقد فرح قلبه بالنهار ነፍሱን በለሊት እንቅልፍ ያሳጣ ሰው በቀን ላይ ልቡ በእርግጥ ይደሰታል ከሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም ተቅሪር የተወሰደ
Показать все...
ከተላመዳቸው ኃጢያቶች በሸዕባን ወር ላይ መቆጠብ ያልቻለ ሙስሊም ረመዳን ሲገባ በአንድ ጊዜ ማቆሙ እንዴት ይቻለዋል? ሸዕባን የቅድመ ዝግጅትና የመለማመጃ ወር መሆኑን እናስታውስ።
Показать все...
#በገጠሬው_አነጋገር_አትገረምም!? ------------------------------------------------- "ቂያማ መቃረቧ በምን ማወቅ እንችላለን!?" ብለው#ገጠሬውን ሲጠይቁት..... ➻"#እውነት_ተናጋሪ____; እውነት በመናገሩ ዋጋ የሚከፍል ከሆነና ➻#ውሸትተናጋሪ___; ውሸት በመናገሩ ዋጋ የሚከፈለው ከሆነ በእርግጥም ቂያማ ተቃርቧል!!" አላቸው። እውነት አልተናገረም ትላላችሁ!?
Показать все...
"ጊዜውን ለአላህ ያላደረገ ከሕይወት ይልቅ ሞት ለሱ የተሻለ ነው።"ኢብኑል ቀይም[አዳኡ ወደዋእ፡ 186]
Показать все...
የ"ላ ኢላሃ ኢለሏህ" ቃል! በሙሓደራዪ ውስጥ የነሼ ዘንጋ፦ ① የላ ኢላሃ ኢለሏህ ተፍሲር ② የላ ኢላሃ ኢለሏህ ዋጂብነት ③ የላ ኢላሃ ኢለሏህ ፈዷኢል • መስቃን ገዌ አትበር፤ ውዶ ተፈያ ላኝ፤ የሰልማን፣ የጋሼኝ፤ የፈቱረሕማን፣ የእማማ ትትጌብር አትንበር! 🎤 ጎቤያሁ፦ አቡ ሰዒድ! https://t.me/butajira_Qirat_daewa_group/675
Показать все...
كلمة لا اله الا الله.mp35.96 MB
‍ 🇸🇦ሳዑዲን ብቻ ለምን❓ 🇪🇹በሀገራችን፦ የሀገራችን ዜጎች አደባባይ ላይ ተዘቅዝቀው ተገድለዋል። 🇪🇹በሀገራችን፦ የሀገራችን ዜጎች በጅምላ እንደ በግ ታርደዋል። 🇪🇹በሀገራችን፦ የሀገራችን ዜጎች ተገድለው ሬሳቸው በመኪና ተጎትቷል። 🇪🇹በሀገራችን፦ የሀገራችን ዜጎች መስጂዳቸው አቃጥለውባቸው ሆያሆዬ ሲጨፍሩ አይተናል። 🇪🇹በሀገራችን፦ እናት ልጆቿ ፊት እንደ ተደፈረች ተነግሮናል። 🇪🇹በሀገራችን፦ “ወደድኩሽ አፈቀርኩሽ ስላት ፍቅሬን አልተቀበለችኝም” በሚል ስንት ሴቶች ተቀጥቅጠው ተጨፍጭፈው ተገድለዋል❓ 🇪🇹በሀገራችን፦ ዜጎች በሀገራቸው ላይ ሞተው በእምነታቸው ም/ት መቀበሪያ ተከልክለው አስራ ምናምን ኪ.ሜ ሬሳ ተሸክመው ይጓዛሉ። 🇪🇹በሀገራችን፦ ከተናጋሪው በፊት ለሰሚው የሚሰቀጥጡ ስንትና ስንት ወንጀሎች ተፈፅመዋል❓ ታድያ በሀገራችን የሀገራችን ዜጋ ሆነው ይህንን ሁሉ በደልና ግፍ እየተፈፀመባቸው ዛሬ ሳዑዲ ላይ ያለ ሀገሪቷ ፍቃድ የገቡ ስደተኞች ላይ በደልና ግፍ ሲደርስ እኛን ቅዱስ ሳዑዲን እርኩስ አድርጎ መሳል ለምን አስፈለገ❓ ምን አልባትም አንድ ፍሬሽ ፖለቲከኛ ይመጣና “እኛ ሀገር በግለሰብ ነው የተፈፀመው ሳዑዲ ግን በመንግስት ነው” ሊል ይችላል። እንዲህ ዐይነቱ ፖለቲከኛ ፖለቲካ እስኪገባው ምላሽ አይሰጠውም! አዎን እናዝናለን ያመናል‼️ በሳዑዲ እርስ ቤት ውስጥ የሚሰቃዩት ሀበሻዎች ስለ ሆኑ ሳይሆን የሰው ልጅ በመሆናቸው የሚደርስባቸው ስቃይ ውስጣችን ይረብሸዋል። ይህንን ቀዳዳ አገኘሁ ብለን ግን ሳዑዲን ጥላሸት የሚቀባ የጠቆረ ልብ የለንም። ማወቅ ያለብን የጥፋቱ ጀማሪ ሳዑዲ ሳትሆን ስደተኞቹ ናቸው❗ያለ ሀገራቸው ፍቃድ ተደብቀው ወጡ፤ ያለ ሳዑዲ ፍቃድ ጥሰው ገቡ። ገብተውም ሀገሪቷን የሚያበላሹ ሆኑ (ሁሉም ባይሆኑም)። ሳዑዲ ውስጥ የሚሰርቀው ሀበሻ ነው፤ ተደብቆ ኸምር ሚነግደው ሀበሻ ነው። በዚህ ጊዜ ለቀው እንዲወጡ እድል ሰጠቻቸው። አልተቀበሉም። በመጨረሻም እርምጃ ወሰደች። እርምጃዋ አንደግፈውም። ለእነርሱም እናዝናለን። አላህ በሰላም ወደ ሀገራቸው እንዲመልሳቸው እንማፀነዋለን እንጂ የተከበረችውና የተቀደሰችዋ ትልቋ ሳዑዲ “ህገ ወጥ” ባለቻቸው ላይ በወሰደችው እርምጃ ምክንያት ልንጠላትና ልናንቋሽሻት አንችልም‼️ በነገራችን ላይ ስለ “ህገ ወጥ” ከተወራ በሀገራችንም እኮ “ህገ ወጥ” ወይም “የጨረቃ” ናችሁ በሚል ስንትና ስንት ቤተሰቦች ናቸው ወደ ጎዳና የተወረወሩት❓❓ ሳዑዲ ኢትዮጵያዊያኖች “ህገ ወጥ” ብላ እስር ቤት አስገባቻቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ኢትዮጵያዊያኖች “ህገ ወጥ (የጨረቃ)” ናችሁ ተብለው ወደ ጎዳና ነው የሚወረወሩት‼️ ትልቁ መርሳት የሌለብን ነገር 🇪🇹ሀገራችን ጠንካራ የዲፕሎማሲ አሰራር ያለው መንግስት ስለ ሌላት ነው ዜጎቿን እንዲህ ለስቃይና ለእንግልት የሚዳረጉት‼️‼️ ስለዚህ በክስተቱ መወቀስ ያለበት 1ኛ, በህገ ወጥ የሄዱት በአጠቃላይ፤ 2ኛ, ዜጎቿን ማስተዳደር ያቃታት ድሃ ሀገራችንና ዜጎቹን ከጭቆና መታደግ ያቃተው መንግስታችን፤ ምክንያቱም፦ ኢኽዋንዮች ዲንም ሰብዓዊነትም የላቸውም። ዲናቸውም ሰብዓዊነታቸው ያለው 🪑በወንበር ዙሪያ ነው። በመጨረሻም ዛሬ ላይ ይህንን ቀዳዳ አገኘሁ ብሎ የሚቀደደው የኢኸዋን ፊክራ የተቆጣጠረው አይተህ እውነትም ለጭቁኖች የታዘነ መስሎህ የምታራግብ ካለህ ነቃ በል❗ እውነትም ለጭቁኖች ታዝኖ ሳይሆን በአሁን ሰዓት ከየትኛውም ሀገር በተሻለ መልኩ ተውሒድና ሱና የበላይ ሆኖ የሚተገበርባት፣ዘመናዊነት ለበላቸው ሰዎችና ለዲሞክራሲ እንደ ሌሎች ያላጎነበደደች እስላማዊ ሀገር በመሆኗ ብቻና ብቻ ነው‼️ እንጂማ👇 የገጠሩ ክፍል በድርቅና በረሀብ እያለቀ፤ የከብቱን መኖ አልቆ የቤቱን ክዳን አራግፎ ከብቶቹን እየታደገ ለዚህ ህዝብ መድረስ ሲቻል ከተማ ውስጥ እዚህ ግባ ለማይባሉ ግንባታዎችና ፕሮግራሞች በሚሊየን ቤት ብር እየፈሰሰ ምድረ ብሶታም ይመጣና “የኢትዮጵያ ዜጎች በሳዑዲ…” እያለ ያላዝናል። ሶማሌ ክልል በድርቅ የሚያልቀው ህዝብና በየ ክልሉ የሚጨፈጨፈው ህዝብ ዜጋ አይደለም❓❓ ወይንስ የተፈለገው የሳዑዲን ክብር ከሙስሊሞች ልብ ላይ መፋቅ ነው⁉️ 🇸🇦አላህ መሪዎቿንና ህዝቦቿን ያስተካክልላት🤲 🇸🇦ከኢኽዋንና መሰል ጠላቶቿ ሴራ አላህ ይታደጋት🤲 🇪🇹በእስር ላይ ያሉ ዜጎቻችንም አላህ በሰላም ለሀገራቸው ያብቃቸው🤲
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.