cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Ezedin Sultan

Больше
Рекламные посты
781
Подписчики
+524 часа
+447 дней
+5230 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የምሽት ወግ😍 ከረመዳን መልስ ወደ ቆሎ ሱቄ (ድሬ) ስመለስ ብልፅግናው መንግስታችን (አንዳንዶች ፅ ትዋጣለች ብለዋል፣ እኔ አላልኩም ልጆቼን ላሳድግበት😁) ሶስት ትዕዛዝ አዟል። 1. በረንዳችሁ ላይ አበባ ትከሉ፣ ተክለናል ውሀውን ማነው የሚያጠጣው? የሚለው ባይመለስም? በሙቀቱ ምክንያት ለሰውም እያጠረ ነው! ደግሞ አንድ ገፅ በጥቅጥቁ የተፃፈ ቃል ማስገቢያ ወረቀት አስፈርመውናል እኮ🙄 2. ዲም ላይት አድርጉ፣ በማታ ከተማው እንዲንቦገቦግ ይመስለኛል (ይሄን ትዕዛዝ ከማዕከል ያስተላለፈው ሰው የከተማ ልጅ አለመሆኑን መገመት አይከብድም) ዲም ላይት እንዴት የከተማ ውበት መገለጫ እንደሆነ እስካሁን አልገባኝም 3. ካሜራ ግጠሙ(ጫን ያለው) ከቀበሌ የተወከሉ 3/4 ሰዎች ወደ ሱቃችን መጡ። ካሜራ ግጠሙ? አሉ (ስቅ እንኳ አላላቸውም😁 የት? ምኑ ጋር? ለምን? ግራ በመጋባት ጥያቄ አከታተልን ከመሀከላቸው አንዷ ሱቁን በደንብ ቃኘችና፣ "ቆሎ እየሰራ ካሜራ ግጠም ማለት ይከብዳል" አለቻቸው፣ አስከትላም "በቃ አከራዮቹ እንዲያስገቡ እንነግራቸዋለን" ብላ ይዛቸው ወጣች፣ አላህ ይስጥሽ አልኩ በውስጤ! . . . ትንሽ ቆየት፣ ነጠል ብላ ተመለሰችና፣ ቆሎ ስጡኝ አለች፣ እህ እንኳን ጠይቀሽን ብለን አፈፍ አድርገን ጅብት😁 የሁሉም ማስፈራሪያ "ይታሸጋል" ነው😥
Показать все...
መቆም የክስተቶች በፍጥነት መቀያየር ብዙዎቻችን ላይ ተፅእኖው የጎላ ነው። መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ያለው ሰው በእንዲህ ወቅቶች ይደቆሳል። እየተዶቀስን ነው። ተለዋዋጭና ተደራራቢ የመንግስት ፖሊሲ፣ የሰላም እጦት በከፍተኛ ሁኔታ የሽቀላውን መስመር አጣቦታል። ከኮሮና ወዲህ (ከ2012 ማብቂያ) የረጋ የንግድ ስርአት አለ ለማለት አያስደፍርም። በዛ ላይ ሀገራችን ላይ የተካሄዱና እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች ገበያው የሚያካለውን ስፍራ (Market Area) በጣም አጥበውታል። የሸማቹን ቁጥር አመናምነውታል። ጦርነቱ የሰውን የመግዛት አቅም ክፉኛ አሟጦታል። ሰው ከኮሮናና ከጦርነት በፊት ከሚሰራው ከግማሽ በታች(<50%) እየሰራ ነው። የሚገርመው ደግሞ ወጪው ከእጥፍ(>100%) በላይ ጨምሯል። የገቢና ወጭ አለመጣጣም ብዙዎቻችንን ያስጨነቀ ጉዳይ ነው። መፍትሄውስ? መቆም፣ መረጋጋትና ማሰብ ይፈልጋል። ሁል ጊዜ መሮጥ በራሱ የውጤታማነት መገለጫ አይደለም። ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት የሚኬዱ መንገዶችን በጥንቃቄ መምረጥ ግድ ይላል። ተጨማሪ ጦስ ህይወታችን ላይ ይዘው እንዳይመጡ በሰከነ መንፈስ መመርመር አስፈላጊ ነው። በተለይ 2 ነገር 1ኛ. ተጨማሪ ገቢ ለማግኘትና እራሳችንን ለማሻሻል ካለን ጉጉት የተነሳ የምንገባባቸውን ጉድጓዶች ርቀት መፈተሽ ግድ ይላል። የተለያዩ መጭበርበሮች ውስጥ እንዳንገባ ቆም ብሎ ማሰብ፣ ማውጣትና ማውረድ ተገቢ ነው። ይህንን ጉጉት ለግል ጥቅማቸው ለመጠቀም ያሰፈሰፉ አሸን ናቸው። በአጭሩ ትከብራለህ፣ ይህን ያህል ትርፍ ታጋብሳለህ፣ ውጭ ሀገር እንልካለን፣ ይህን ያህል ካመጣህ ይህን ያህል አተርፍልሀለሁ . . . የሚሉ ማምታቻዎች ተበራክተዋል። ጥንቃቄ ይሻል! 2ኛ. ገበያው ላይ ከፍተኛ የሆነ የካሽ እጥረት ተከስቷል። የካፒታል መዳከምም እንዲሁ። ገበያው መቀዛቀዙን ተንተርሶ የተከሰተው የካሽ እጥረት ለመቅረፍ ሸሪዐው የሚከለክላቸው መንገዶችን ከመጓዝ መቆጠብ አስፈላጊ ነው። በተለይ ወለድ ከባድ ጥንቃቄ ይሻል። ወለድ ከከባባድ ወንጀሎች ይመደባል። መንገዱ ሰፊ ነው። ዝቅተኛው የወለድ ወንጀል ክብደት "እናትን ከመገናኘት" ጋር እንደሚስተካከል ውዱ ነብይ ሙሀመድ ﷺ ነግረውናል። በጥቅሉ ነገራቶች በተጣበቡበት ጊዜ ሰከን፣ ረጋ ብሎ ማሰብ፣ ቅርብና ታማኝ የምንላቸውን ሰዎች ማማከር፣ በዱአ መበርታት አስፈላጊ ነው። አብሽሩ፣ ያበርታን! https://t.me/EzedinSultan14
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሀጅ መጠራት ነው (ኒያ ነው) ብዬ ሳወራ አንዱ አንድ ገራሚ ታሪክ አወጋኝ "አንዱ በጣም ታዋቂ ባለሀብት ነው። በስንት ጉትጎታና ግፊት ሀጅ አድርግ ተብሎ ይጓዛል። የአንድ ትልቅ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ነበር። ዑምራውን ፈፅሞ ሀጁን ሲጠባበቅ እዚህ እሱ ካልተገኘ የማይፈፀም ጉዳይ ይገጥመዋል። መጀመርያም በግፊ የሄደው ግለሰብ ሀጁን ሳያደርግ ተመለሰ። " አለኝ ለዛ ነው እኮ ሰዎች ዱዓ ሲያደርጉ "ጌታዬ ሆይ ወደ ቤትህ ጥራኝ" የሚሉት ብዙ ሀጅ የሄዱ ሰዎች ብትጠይቁ አብዛኛው በገንዘብ አቅም ሳይሆን በኒያው ሀይል የተጓዘ ነው። ሞልቶለት የሄደ ጥቂት ነው። አቤት ስንት 10፣ 20፣ 30 ፣ 40 ፣ 50 ሚልየን ቤት ላይ እየኖረ? የብዙ 100 ሚልየኖች ድርጅት እያስተዳደረ? 4፣ 5፣ 6፣ 7፣ 20፣ 25 ሚልየን መኪና እየነዳ ሀጅ ግን ለመሄድ ይሳነዋል። አላህ ፊት ምን ብሎ ይመልስ ይሆን? ያ ረብ፣ ወደ ቤትህ ሳትጠራን አትውሰደን🤲
Показать все...
👍 11 1
ወንድሜ Muhammed Seid Abx አንድ ጥያቄ ጠይቆ ነበር . . . "ብዙ ሙስሊሞች ግን ትምህርት የምትጠሉት ለምንድነው ?" ጥያቄው የተወሰነ ቢታረም ጥሩ ይመስለኛል። "ብዙ ሙስሊሞች ለምንድነው ትምህርት ላይ የማትዘልቁት? በተማራችሁበት የማትሰሩትስ ለምንድነው?" ይህ የሚያወያይና የሚያከራክር ጥያቄ ነው። እንደ አንድ ትምህርቱን በዲግሪ ብቻ እንደተወሰነና በተማረበት እንዳልሰራበት ሰው ራሴን ወክዬ ምክንያቴን ልግለፅ . . . ------------- 2007 እንደተመረቅኩ ድሬ፣ ሀረር ወይም ጅግጅጋ የመስራት ፍላጎት ስለነበረኝ ማስታወቂያ ማሰስ ጀመርኩ። የድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ቢሮ የስራ ማስታወቂያ አውጥቶ ተመለከትኩ። CV አዘጋጅቼ ላመለክት ወደ ቢሮ አቀናሁ። የሳይት ተቆጣጣሪ ( supervision ) ነበር። ፀሀፊዋ በፈገግታ ተቀበለችኝ። (ፊቴ አሳፍሮኝ አያውቅም😁፣ ሰው ቶሎ ያዝንልኛል😍)። የስራ ማስታወቂያ የወጣበትን ዝርዝር ሰጠችኝና የማስገባበትን ዘርፍ አስመረጠችኝ። ልቤ የመታው ይሄኔ ነው፣ ክው አልኩ ደሞዙ 2300 ብር ነበር። ሲቆረጥ ወደ 1800 አከባቢ ይወርዳል። በጊዜው የተከራየሁት ቤት 600 ብር ነበር። 1800-600=1200 ብር በ1200 ብር ህይወቴን መመስረት አለብኝ። ምግብ፣ ካርድ(ላጤ ስለሆንኩ😁)፣ ትራንስፖርት፣ ህክምና የመሳሰሉትን መሸፈን አለበት። የበጀት መጓደል ሲፈጠር የግድ ወደ ጉቦ/ሙስና ማምራት አይቀርም። ይህ ደግሞ ሀራም(ክልክል) ነው። በግንባታ አለም ውስጥ ሳይት ቁጥጥር አንደኛ ሙሰኛ ቦታ ነው። ስለዚህ? የቅጥርን ህይወት እርም አልኩት። ተመልሼ ለፈተናም ይሁን ቃለ-መጠይቅ ሳልሄድ ቀረሁ። ---------- ነገሩን ከጥላቻ ብቻ ሳይሆን በሌላ አቅጣጫም እንመልከተው ለማለት ነው። ተምረህ የምታገኘው ደሞዝ ህይወትህን ለመምራት በቂ አይደለም። ጉቦ ለመብላት እምነትህ አይፈቅድም። ያስተማረህን እንድትረዳና እንድታግዝ(ቤተሰብ/አሳዳጊ) ሀይማኖትህ ያዘሀል። ጊዜው የፈተና ነውና በጊዜ ወደ ትዳር እንድትሰበሰብ ህሊናህ ይመራሀል። ይህን ሁሉ ሀላፊነት ተምሮ በሚገኝ ገቢ ማስኬዱ አዳጋች ነው ተብሎ ስለሚታሰብ ለትምህርት ቀዝቃዛ አመለካከት ይፈጥራል። የተማረውም በተማረው ፕሮፌሽናል እንዳይሆንና እራሱን የበለጠ በትምህርት እንዲያሻሽል አይጋብዝም። እኔ ለዚህ ይመስለኛል፣ እናንተስ? (ትምህርት አስፈላጊነት ላይ በጣም የከረረ አቋም ካላቸው ሰዎች ውስጥ ነው የምመደበው)
Показать все...
👍 6
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንወያይበት ስለ መኪና ሲነሳ ሁሌ ጥያቄ የሚሆንብኝ አንድ ጉዳይ አለ። የህግ ሰዎች፣ የመንግስት አካላት(መንገድ ትራንስፖርት) ሌሎችም ትኖራላችሁ እና መልሱልኝ እስቲ . . . በአደጋ ሙሉ በሙሉ የወደሙ (Damage ) ወይም በእሳት አደጋ ሙሉ አካላቸው ከጥቅም ውጭ የሆኑ መኪኖች እጣቸው ምንድነው? ለብዙሀኑ ግልፅ እንዲሆን ትንሽ ላፍታታው . . . መኪና ማለት ሁለት ነገር ነው። አንደኛው መኪናው (እቃው) ራሱ ሲሆን፣ ሁለተኛው ህጋዊነቱ የሚረጋገጥበት ዶክመንት ነው። በዋነኝነት መኪናው ላይ የሚገኘው ሻንሲ እና ሞተር ቁጥሩ የባለቤትነት ደብተር ማረጋገጫው ላይ ቁጥራቸው ይመዘገባል። መኪናው የናንተ መሆኑ የሚለየው በዚህ መልኩ ነው። አንድ መኪና በከባድ አደጋ/መገልበጥ አሊያ ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ቢወድምና መልሶ ለማሰራት የማይቻል ከሆነ ህጉ ምን ይላል ነው? የኔ ጥያቄ እንደ ቀላል የሚታይ ጉዳይ አይደለም። ባለ ንብረቱ መኪናውን አጥቶ ዶክመንቱን ይዞ ብቻ ይቀመጣል። ይህ ደግሞ አላስፈላጊ ለሆኑ ህገ-ወጥ ተግባራት ይመራል። የመኪና ስርቆት መበራከትም ከዚሁ ጋር በቀጥታ ይዛመዳል። እና መፍትሄው?
Показать все...
👍 3
ምርቱ መስፈርቱን አሟልቶ ከገባና ገበያ ከወጣ ቡኋላ አትጠቀሙ ማለት ምን ማለት ነው? የንግድ አሻጢር ማለት ይህ አይነት ነው። 👇👇👇👇👇 #እንድታውቁት🚨 2 የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈቶች አሟልተው ባለመገኘታቸው ምክንያት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ማሳሰቢያ ተላለፈ። 1ኛ. #Sultan Instant Full Cream Milk Powder (400g) , (PD 19/02/2024, & Exp 18/02/2026 B.NO.56 2ኛ. #Nura Super Instant Full Cream Milk Powder (400g) PD 01/11/2023 እና Exp 31/10/2025 BT 23246006 LOT No. 230915 291123003127 የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈርቶች ያላሟሉ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የንግድና ቀጠናዊ ትስስስር ሚኒስቴር አሳስቧል። @tikvahethiopia
Показать все...
👍 3
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት🚨 2 የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈቶች አሟልተው ባለመገኘታቸው ምክንያት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ማሳሰቢያ ተላለፈ። 1ኛ. #Sultan Instant Full Cream Milk Powder (400g) , (PD 19/02/2024, & Exp 18/02/2026 B.NO.56 2ኛ. #Nura Super Instant Full Cream Milk Powder (400g) PD 01/11/2023 እና Exp 31/10/2025 BT 23246006 LOT No. 230915 291123003127 የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈርቶች ያላሟሉ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የንግድና ቀጠናዊ ትስስስር ሚኒስቴር አሳስቧል። @tikvahethiopia
Показать все...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
Фото недоступноПоказать в Telegram
Repost from N/a
ውድ የገፃችን ተከታታዬች በቴሌግራም የተከታዬቻችን ብዛት 100 በመሻገሩ ሁላችሁንም ልናመሰግን እንወዳለን! ሌሎች ወዳጆችዎን ወደዚህ ቻናል በመጋበዝ ተደራሽነቱን እንዲያሰፉልን በአክብሮት እንጠይቃለን! https://t.me/sofibaltena
Показать все...