cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

✍ዮኒ-ኣታን

ማሰብ ስታቆም ማመን ትጀምራለህ!

Больше
Рекламные посты
812
Подписчики
Нет данных24 часа
-67 дней
-2730 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

መልክአ ውቢት (ዲናኦል ሽፈራው)        ለዝክረ ስምኪ አባትሽ ተጨነቁ እናትሽ አማጡ ለዚ መሳይ ውበት ስምን ለመሰየም ቃላት እስኪያጡ ተጨንቀው ተጠበው ግራ ቢገባቸው እግዜር መለአኩን ልኮ በህልማቸው ይቺን ቆንጆ ጉብል ውቢት በሏት ብሎ እረፍትን ሰጣቸው          ለስእርተ ርስትኪ የፀጉርሽ ልስላሴው እጅጉን ቢገርመኝ ለመንካት ቢያጓጓኝ "እባክህ አምላኬ ማበጠሪያ አርገኝ" ብዬ ተማፀንኩኝ ይሄ ሉጫ ፀጉሯን ልክ ስታበጥር ማበጠሪያ ሆኜ በፀጉሮቿ መሀል እንድል ክንፍ ብ ር ር        ለገፅኪ አንቺዬ የፊትሽ ብርሀን እውርን ይመራል ለጨለመው አይኑ መንገድ ይሆነዋል ለኛ ላይናማዎቹማ አብረቅራቂው ፊትሽ መስታወታችን ነው አመዳም መልካችን አምሮ የሚታየን በፊትሽ ንጣት ነው       ለአይንትኪ እበቀደም ለታ አይንሽን እያየው እግዜርን ታዘብኩት እንዲ ስል ጠየኩት አዝኜም ለመንኩት "ማታዳላው አምላክ ማታዳላው ጌታ ምን ስትለው ፈጠር የኔ አይነቱን አይን ይሄንን ከርታታ አቤቱ አምላኬ በሰጠኸኝ አካል አዝኜ ባላውቅም ዛሬ ግን ውብ አይኗን አይቼ በኔ ስላፈርኩኝ መግለጥን አልቻልኩም እናም ደግሜ እንድገልጥ ካሳ እንዲሆነኝ ያሳፈረኝ አይኗ ብርታት እንዲሰጠኝ አንድ ግዜ መታ በውብ ከንፈሮቿ አይኔን ትሳምልኝ ከገለጥኩ በኋላም ለዘለአለሜ ስንቄ እንዲሆነኝ እንደ እመብርሐን ስዕል ባየኋትኝ ቁጥር ሐሴት እንዲሰማኝ ይቺን ቆንጆ ጉብል  ከእቅፌ አስቀርልኝ" ላእዛንኪ ለእናፍኪ ለአፍኪ ለከናፍርኪ ለልሳንኪ ለእስትንፋስኪ እያልኩ አድናቆቴን ባስብ ልቀጥለው ቃላቶች ቀለሉ ውበትሽን መግለፅ እጅግ ተሳናቸው አልችል አለ አቅማቸው ይኸውልሽ አለሜ ይሄን ውበትሽን የቃላቶች ጥምረት ሊገልፁት አይችሉም አቅሙ የላቸውም ምስጢረ ጥበቡ ለነርሱ አልተሰጠም በዚህች አለም ላይ ያንቺን ውበት ሊገልፅ ሀይሉ የተሰጠው ለአንድ ነገር ነው እርሱም በዝምታ ቃላት ሳያወጡ በልብ ማድነቅ ነው እናም አለሜዋ ዝምታ ስለሆነ ውበትሽን ገልጦ የልቤን የሚያደርስ ባፌ ዝም ብዬ በውስጤ አወራለው መልክአ ውቢት እያልኩ የውበትሽን ድርሳን ስደግም እኖራለው    ዲናኦል ሽፈራው(@ye_keraniyowa_tobiyaye)
Показать все...
🔥 3👍 1
#ተፈላጊ #ምዕራፍ_7 #ምስረታ ሳንድሮስ የተበተነው ፂሙን እያሻሸ "ወጣት ነበርክ ጋላሪዬስ....ትዝ ይልህ ይሆናል...ቪራ እንደዛሬው ሃያል አልነበረችም...ያኔ ከኢትዮጵያ ስንሰደድ በኤርትራ ነበር ያለፍነው..ትዝ አይልህም እንዲያውም ኤርትራ ያገኘነው ጥሩ ሰው ነበር አረጋዊ የሚባል 'የኛ እጣ ፋንታ ደረሰባችሁ' እያለን...ይገርማል እኮ" አለና ከተቀመጠበት ቦታ እየተስተካከለ..."ሄሊክስ አንቺ እንደኛ አልተሰደድሽም" አለና በጫትና ሲጋራ የነወዘውን ጥርሱን ገላለጠው... "አዎ አባባ ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ብወለድ ቤተሰቦቼ የ ፈረንሳይ ዜግነት ነው ያላቸው" አለች ፊትለፊቷ ላይ የተዘረጋውን ፀጉሯን በጆሮዋ እየሳገች..."ልክ ብለሻል አዎ...ያውም ጎንደሬ" አለና ሳቀ..የሱን ሳቅ ተከትላ እንደ በረዶ የነጣውን ጥርሷን አብለጨለጨችው...በጨለማም እንኳን ማብራቱን የማያቆመው ውብ ፈገግታዋ ከጨረቃ ይበልጣል...እነሱ ሲሳሳቁ ዶ/ር ጋላሪዬስ በትካዜ ከንፏል...........። "እና...."ብሎ ቀጠለ ሳንድሮስ.. "ያኔ ቪራ ላይ ያሉ ደሃ ጥቁሮች ነበሩ...እነሱ ለራሳቸው የሚሆን ነገር ሳይኖራቸው እኛን አንከብክበው አስተናገዱን...በዛን ጊዜ ከሀገራችን ሞትን ፈርተን የተሰደድነው ኢትዮጵያዊያን እልህ እና ንዴት ውስጥ ስለነበርን ቪራ ላይ ለመንገስ አሰብን...ማንም የኛ ሃገር ነው ተው አላለንም ነበር...የነበራት አገዛዝ የወደቀ ስለነበር የኛን ሃሳብ ከመቀበል ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበራቸውምና ተስማሙ.....ከዛን በኋላ ከተለያዩ የውጭ ሀገራት ባለስልጣኖች ጋር መደዋወል ጀመርን...." ወሬውን ሄሊክስ አቋርጣ "እንዴት ከነሱ ጋር...ማለቴ ከውጭ ሰዎች ጋር እንዴት ተገናኛችሁ..." አለች ... የስደታቸው ታሪክ በጣም አጓጉቷታል "አይ ሄሊክስ..ኢትዮጵያ እያለሁ የውጭ ሚኒስቴር እንደነበርኩ አላውቅም ለማለት ነው" አለና ቀጠለ "በብድር እና በእርዳታ አማካኝነት ቪራ በፍጥነት ማደግ ጀመረች..ለጊዜውም ቢሆን አንድ ቪራዊ ቪራን ቢመራትም..ሀገሪቷን ያሳየችውን ለውጥ አይቶ ስልጣኑን ለኔ አስተላለፈ እና ከስልጣኑ ወረደ...ከጊዜያት በኋላ አለም ላይ አሉ ከሚባሉ በኢኮኖሚ ሀብቷ ተርታ ተሰለፈች...ብድሯን ከፍላ ለዜጎቿ አመቺ ህይወት ፈጥራ አሁን ላይ ታኖራለች...ቅድም እንዳልኩት ከጣልያን ፣ ስፔን ፣ ፖርቹጋል ፣ እንግሊዝ ፣ አሜሪካ ፣ ጀርመን ፣ ፈረንሳይ ፣ ኩርድ በድህነት ሲቆራመቱ የነበሩት ዜጎች ቪራ አቀፈቻቸው...አሁን ላይ ድህነት ቪራ ውስጥ የለም... ሆኖም ግን ኢትየጵያ ላይ ያሉት አረመኔዎች አሁንም እኛን ላማሳደድ ተነስተዋል...እነሱ ካልጠፉ ቪራ ችግር ውስጥ ትገባለች...አላማቸው ኢትየጵያን መበታተን ነው..የኛ አላማ ደግሞ ኢትዮጵያን እንደ ቪራ አንድ ማድረግ..ሀያል ማድረግ ነው" "አባባ ያቀረቡት ድርድር እኮ ከባድ ነው...እስቲ ተመልከተን የኛን ህይወት..ከቤት እኔ ስወጣ በጠባቂ ታጅቤ...አንተ ጫካ ውስጥ ተደብቀህ ያው ቪራ ላይ..ለምን አባባ እንዳልከው ነፃነቷን እና አንድነቷን ያወጀች ከሆነ ለምን ቪራ ሁነን እንደበቃለን አባባ..." አለ ዶ/ር ጋላሪዬስ ያደረገውን ባርኔጣ አናቱ ላይ እያነሳ... "ጋላሪዬስ... ምንም ደህና ሀገር ውስጥ ብንገኝም እኛ ግን ደህና አይደለንም...እሰብ የአባትህን ሞት...ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለም እዚሁ ቪራ ውስጥ ነው...ለምን እንደሆነስ ታውቃለህ...ሰርጎ ገቦች ስላሉ ነው...አሁንም አሉ... እዚህ ጫካ ስትመጡ ያልተከተላችሁ ሰው አለመኖሩን በምን እርግጠኞች ናችሁ...በምንም!...ሁሌም አስተውል ጋላሪዬስ...አባትህ አንተን አደራ ብሎ ያረፈው ለኔ ነው..ለወንድሙ ያንተንም የኔንም ስም ያስቀየርኩት ሆን ብዬ ነው...ግን እንደዛም ሁኖ በካርቶን ጠቅልለው ቤትህ ድረስ አመጡልህ...ስምህ ተቀይሮም እንኳን ያውቁሃል እኔንም እንደዛው ጋላሪዬስ"። ከ ዶ/ር ጋላሪዬስ አይን የ እንባ ዘለላዎች ወረዱ። ከትንሽ ሰዓታት በኋላ ዶ/ር ጋላሪዬስ እና ወ/ሮ ሄሊክስ ለስንብት ተነሱ። ዶ/ር ጋላሪዬስ ወደ መውጫ በሩ እንዳመራ "አባባ የግሪክ ቃል ማንበብ ትችላለህ እንዴ.." አለው "አልችልም..እያወከኝ" አለውና ፈገግ አለ። ...................................................... ይቀጥላል.. ዮኒ      ኣታን @yonatoz Share @Yonny_Athan Share @Yonny_Athan
Показать все...
ሁላቹም ሞክሩት የምር ይከፍላል ።start ማለት ብቻ ከዛ account መላክ ያን ያህል ቀላል ነው ሁላቹም ተጠቀሙበት✌️
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
⚡️እኛም ተቀላቅለናል⚡️ እጅዎ ላይ ባለው #ስልክ📱 ብቻ ወደ #ሀብት_ማማ ይውጡ ዛሬውኑ ይጀምሩ ከፍታን #ከሂጅራ_ጋር_ያጣጥሙ 🎊 #የሂጅራ_ባንክ ቦትን ተጠቅመው ሲመዘገቡ የ 1,000 ብር ስጦታ በተጨማሪም 1 ሰዉ ወደ ቦቱ ሲጋብዙ የ 125 ብር ሽልማት ያግኙ🎁 ይህ ማለት 40 ሰዎችን ወደ ቦቱ ሲጋብዙ 5000+1000 ብር #አካውንቶ ላይ ገቢ ይደረጋል ማለት ነው መልካም እድል ይሁንልዎ 🙏 እርስዎም አሁኑኑ ወደ ሀብት ማማ ጉዞ ይጀምሩ👇 https://t.me/Hijira_bank_Bot?start=r05862705180 https://t.me/Hijira_bank_Bot?start=r05862705180
Показать все...
ሁላቹም ሞክሩት የምር ይከፍላል ።start ማለት ብቻ ከዛ account መላክ ያን ያህል ቀላል ነው ሁላቹም ተጠቀሙበት✌️
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
⚡️እኛም ተቀላቅለናል⚡️ እጅዎ ላይ ባለው #ስልክ📱 ብቻ ወደ #ሀብት_ማማ ይውጡ ዛሬውኑ ይጀምሩ ከፍታን #ከሂጅራ_ጋር_ያጣጥሙ 🎊 #የሂጅራ_ባንክ ቦትን ተጠቅመው ሲመዘገቡ የ 1,000 ብር ስጦታ በተጨማሪም 1 ሰዉ ወደ ቦቱ ሲጋብዙ የ 125 ብር ሽልማት ያግኙ🎁 ይህ ማለት 40 ሰዎችን ወደ ቦቱ ሲጋብዙ 5000+1000 ብር #አካውንቶ ላይ ገቢ ይደረጋል ማለት ነው መልካም እድል ይሁንልዎ 🙏 እርስዎም አሁኑኑ ወደ ሀብት ማማ ጉዞ ይጀምሩ👇 https://t.me/Hijira_bank_Bot?start=r05862705180 https://t.me/Hijira_bank_Bot?start=r05862705180
Показать все...
#ተፈላጊ #ምዕራፍ_6 #ጥንስስ_ሴራ_3 ዶ/ር ጋላሪዬስ ካርቶኑን አገላብጦ አየውና በያዘው ሴንጢ ቀደደው...ጥቁር ሳጥን እና ከላዩ ላይ ትንሽዬ ወረቀት ተቀምጧል....ወረቀቱን አነሳውና አየው... "Χειριστείτε αυτό το αντικείμενο προσεκτικά... ποτέ η γυναίκα σας ξέρει αυτή τη γλώσσα"....ይላል...ዶ/ር ጋላሪዬስ ወደ ሄሊክስ ዞር አለና... "ሄሊክስ የምን ጽሁፍ ነው ይሄ..." "ብዙ ሀገራት ዙረህ እንዴት አታውቀውም" በማሾፍ መልኩ እያለች ወረቀቱን ተቀበለችውና የአይን መነፀሯን አስተካክላ ለበሰች....ለትንሽ ደቂቃዎች ዝም ብላ ቆየችና.... "ጽሁፉ የ ግሪክ ነው...ነገር ግን የግሪክን ጽሁፍ ማንበብ አልችልም" አለችውና ወረቀቱን መለሰችለት... "ከኔ የበለጠ ሀገር ምትዞሪው አንቺ..." አለና ወረቀቱን ተቀብሎ ከኪሱ ከተተው...ከካርቶኑ ውስጥ የተቀመጠውን ሳጥን አነሳውና አየው...ተቆልፏል.. "በምን ልክፈተው አሁን ይሄን" አለና ከካርቶኑ መልሶ ከተተው....ወ/ሮ ሄሊክስ በትዝብት ካየቺው በኋላ...."አባባ ሳንድሮስ ጋር እንሂድ እኔም ናፍቀውኛል..." አለችው... ልክ ነሽ መሄድ አለብን ውድ ሄሊክስ" ብሎ ተነሳና ሳጥኑን በሌላ መያዣ አንግቦ ተያይዘው ወጡ። #ጎንዳር "ወደ ቪራ ከተማ መሄድ ሳይኖርብን አይቀርም ካዳክ..." "ይሻላል ወንድሜ...ቲያጎ እኮ ቪራ ውስጥ ነው ያለው...ማክሰንም እዛው ነው ያለው እኮ" "ልክ ነህ....ግን ቲያጎን ልናምነው አንችልም...ማክሰን ብቻውን አደጋ ውስጥ ሊገባ ይችላል....እና መሄድ ይኖርብናል" "ለነገሩ እኮ አንተ ካልክ የሚቀየር ነገር የለም ዶ/ር ከሱር" አለና ሳቅ አለ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ "ሄሊክስ..ደውለሽ እንኳን ደህንነቴን አትጠይቂኝም ልጄ...ይሄ ባልሽ እንደሆነ በቃ ካለመጨቃጨቅ ሌላ ነገር የለውም" እያሉ መጫወት ጀመሩ "አይ አባባ ሳልፈልግ ቀርቼ እኮ አይደለም...ስራዬን ታውቀው የለ" "ኻኻ...የጎንደሬዎች አማርኛ አልጠፋብሽም...ጉደኛ ነሽ" "እትብቴ እዛው አይደል እንዴ የተቀበረው እንዴት ይጠፋኛል ብለው ነው"....መሳሳቅ ጀመሩ....ከ ሳንድሮስ ጋር ቀኑን ሙሉ ሲጨዋወቱ ዋሉና...የዶ/ር ጋላሪዬስን ሳጥን በጥበቆቹ አስከፍተው ማየት ጀመሩ....ሳጥኑ ውስጥ...የኢትዮጵያ ባንዲራ እና ካርታ ተቀምጧል...ከካርታው በስተጀርባ "ብንስማማ ይሻላል" ይላል። "አባባ ምንድነው ይሄ...አልገባኝም" ግራ በተጋባ መንፈስ ሳንድሮስን እየተመለከተው... "ጋላሪዬስ...ይሄ ጉዳይ አስከፊ ነገር ያመጣል...ሀገሪቷን ለመከፋፈልና ለመገነጣጠል አስበዋል ማለት ነው።...ይሄ ደግሞ አንዷን ሀገር ለ አራት ወይም ለ አምስት ከፋፍለው 'ኢትዮጵያ' የሚለውን ስም ለማጥፋት ነው የታሰበው...እንዲህ ሲያደርጉ ደግሞ አንተ ዝም እንደማትላቸው ያውቃሉ...ለዛም ነው ድርድር ውስጥ ሊያስገቡህ የፈለጉት" "ይሄ እኮ ድርድር አያስፈልገውም  አባባ" "አይ ጋላሪዬስ...ለምን ወደ ቪራ ከተማ መጣን ታድያ...ለ ሰላሳ አመታት ያህል እኮ ቪራ ውስጥ ነው ያሳለፍነው... የቪራ አስተዳዳሪ እያለው ቪራን ኢትየጵያን ለማስመሰል ሞክሬያለው...እስቲ ከተማዋን እያት የሚሰሩት ህንፃዎቿ እኮ እያንዳንዳቸውን ብሄሮች ለማሳየት ታስቦ ነበር...ግን ከጊዜያት በኋላ ከጣልያን ፣ ስፔን ፣ ፖርቹጋል ፣ እንግሊዝ ፣ አሜሪካ ፣ ጀርመን ፣ ፈረንሳይ ፣ ኩርድ...የሚገኙ ዜጎች ወደ ቪራ ከተማ ገቡ...እነሱ ከገቡ ከአመታት በኋላ አንተ የቪራ ዋና አስተዳዳሪ ሆንክ...አንተ ስልጣን ላይ ከወጣህ በኋላ ግን ቪራ እንደነበረችው አልቆየችም ጋላሪዬስ...ያንተ ልብ ክፋትን አያውቅም...ከኢትዮጵያ ውጭ ላሉ ዜጎችም ነፃ የህንፃ ዲዛይን እድል ሰጠኻቸው...." "አባባ እንደሱ እኮ ያደረኩት የቪራ ከተማ በተለያዩ የህንፃ ንድፍ ጎልታ እንድትታይ ነው" "ልክ ነህ ጋላሪዬስ ጥፋት የለብህም....የሁሉንም የሀገሪቷን ዜጎች በአንድነት እንዲኖሩ አድርገሃል....መቼም ከኢትዮጰያ ለምን እንደወጣን ታውቃለህ..እነዛ ኣረመኔዎች ባመጡት ሃሳብ ስላልተስማማን አንድ ኢትየጵያን ስላልን ነው ሊገሉን ያሳድዱን የነበረው" አሉና በረጅሙ ተነፈሱ። ...................................................... ይቀጥላል... ዮኒ      ኣታን @yonatoz Share @Yonny_Athan Share @Yonny_Athan
Показать все...
#ተፈላጊ #ምዕራፍ_5 #ጥንስስ_ሴራ_2 "ሄሎ ዶ/ር ከሱር እቃውን ለጥበቆቹ እንዲሰጡት አድርጌያለው....ስራዬን መቼ ልጀምር" "ካዳክ በ ቴክስት ይልክልሃል" ፀሃዯ ለመውጣት ገና ከማኮብኮቧ ማክሰን የተላከውን እቃ ለጥበቆቹ ሰጥቶ ዞር አለ። ዶ/ር ጋላሪዬስ ከመኝታው ሲነሳ ከጎኑ ሚስቱን ሄሊክስን አጣት....መታጠቢያ ክፍል ገብቶ ተጣጥቦ ወደ ሳሎኑ አመራ...የ ብርቱካን ጭማቂዋን እየጠጣች "እሺ ዶ/ሩ በጠዋት መነሳት አለመደብህም እንዴት ዛሬ ነቃህ..." "ጎኔን ብርድ ሲመታኝ የትኛው እንቅልፍ ይውሰደኝ..." "እስከዛሬ ያልበረደህ እንዴት ዛሬ?..." "ውድ ሄሊክስ ስፔናዊያኖች ነገር ነው እንዴ ያሰለጠኑሽ...." ከጥበቆቹ አንዱ...."አለቃ የሆነ ሰው ይሄንን እቃ ለእርሶ አስቀምጧል...'ማንነቴን እርሱ ያውቀኛል' ብሏል" አለና በእጁ የታቀፈውን በካርቶን የታሸገውን ከፊትለፊት ጠረንጴዛ ላይ አስቀመጠው። "ስሙን ማን ነበር ያለኝ...." እያለ መብሰልሰል ጀመረ.... "ይልቁንስ....ዛሬ ካንቺ ጋር ነው ቪራ ከተማን ምንዞረው ልዕልቴ" እያለ ወደሷ ቀረበ.....ወ/ሮ ሄሊክስ በአንድ እጇ እየገፋችው.... "ኽ...ልክ ነህ ጋላሪዬስ....ቪራን እሽከረከራታለው" "ሄሊክስ...ግን ታውቆሻል..ከመጣሽ ጀምሮ በጣም እየገፋሽኝ ነው.... ትላንት ስላረፈድኩ ይቅርታ ጠየኩሽ...እሱንም ምክንያቴን ነገሬሻለሁ...ከወራት በኋላ መጥተሽ ከኔጋ ለመሆን ጊዜ አጣሽ...ዛሬም እንደሌሎቹ ወራት ብቻዬን አስተኛሽኝ" ሲል የ ወ/ሮ ሄሊክስ ፊት እንደመሳቅ እና እንደመኮሳተር እያለ... "ሁሌም ብቻህን አይደል የምታኛው....እኔ ስመጣ ብቻ ነው እንጂ ብቸኝነትህን የምትረሳው አይደለ?...... ለኔ ክብር ቢኖርህና ብታስብ ከኢትዮጵያ ያመጣሁልህን ሰዓት ለውድ ጋላሪዬስ ይመጥናል ብዬ ያመጣሁልህን ሰዓት ከአንዲት ምናምቲያም ሰራተኛ ክፍል ውስጥ አታስቀምጠው ነበር..ጋላሪዬስ" አለችና ከቆመበት ጥላው ወደ መኝታ ቤት አመራች። ዶ/ር ጋላሪዬስ ፊቱ ላይ የተደፋውን ነጭ ፂም እያፍተለተለ...."እንዴት...." እያለ ማልጎምጎም ጀመረ....በድንገት "ስናፍቅሽ" ብሎ ተጣራ.... "ኧዬ ጋሼ..." "ትላንት ማታ ሄሊክስ ስትመጣ አንቺ የት ነበርሽ..." "እእ....ለ አትዬ የሚሆን አበባ በጓሮ እየቀጠፍኩ ነበር....ምነው" "የእጅ ሰዓቴን ከክፍልሽ አጊንታዋለች" አለና ከጠረንጴዛ ላይ ተየቀመጠውን የጭማኪ ጆክ ወደብርጭቆ እየገለበጠ መጠጣት ጀመረ። "እና ጋሼ ምን አስባ ነው..." አለች ስናፍቅሽ አይኗ በእንባ እየተሞላ.... ""አብረን እንዳደርን....ሂጂ አሁን ወደስራሽ" አለና ወደ መኝታ ቤቱ አመራ። የቁርስ ማዕድ ከጠረጴዛ ላይ ተነስቶ በረንዳ ላይ ቡና እየተፈላ ነበር..የ ዶ/ር ጋላሪዬስ  ስልክ መጮህ ጀመረ...ዶ/ር ጋላሪዬስ ስልኩን አነሳና.. "ሄሎ..." አለ "ዶ/ር ጋላሪዬስ እንዴት አረፈድክ" "እግዚአብሔር ይመስገን...ማን ልበል" "የኢትዮጵያ ወዳጅህ....ስጦታዬን አልወደድከውም እንዴ..." "የምን ስጦታ...ማነህ" "በቃ ስትወደው ደውል"...አለና ጆሮው ላይ ዘጋው.... ወ/ሮ ሄሊክስ የ ዶ/ር ጋላሪዬስን ፊት እያየች..."ያንተ ችግር ማብቂያ የለውም አይደል?... በካርቶን የመጣልህስ ምንድነው.." አለች ትኩረት ያልሰጠችው በመምሰል...ዶ/ር ጋላሪዬሴ ከኪሱ ሴንጢ እያወጣ..."ስናፍቅሽ...ሂጅና ካርቶኑን አምጪው" አላት። ......................................................... ይቀጥላል ዮኒ      ኣታን @yonatoz Share @Yonny_Athan Share @Yonny_Athan
Показать все...
#ተፈላጊ #ምዕራፍ_4 #ጥንስስ_ሴራ "አለቃ....ወ/ሮ ሄሊክስ መጥታለች...." "ኧኧኧ...እሺ አመሰግናለሁ" ዶ/ር ጋላሪዬስ ከግቢው በር ላይ ያቆመውን መኪናውን ለ ጠባቂዎቹ ሰጥቶ ወደ ቤቱ ውስጥ ገባ.... የመመገቢያ ጠረንጴዛው በምግብ ተሞልቷል የ ፈረንሳይ ወይን እና ውስኪ ከ ጠረንጴዛው መሃል ላይ ቁመዋል.... "ኦኦው..... ለ ውድ ሄሊክስ ነው ይሄ ሁሉ ምግብ...ይገርማል" እያለ ወደ ክፍሉ አመራ....ወ/ሮ ሄሊክስ ከመኝታ ቤታቸው በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ በአረንጓዴ እና በፀጥታ የተሞላውን የቪራን አየር ትኮመኩማለች...."ውድ ሄሊክስ...."እያለ የክፍሉን በር ከፍቶ ገባ....ወ/ሮ ሄሊክስ ከተቀመጠችበት እየተነሳች...."የኔ ብኩን ሰው....ኤርፖርት ድረስ መጥተህ ስለተቀበልከኝ አመሰግናለሁ" "ኣ....ምን ሁነሻል ሄሊክስ....ላንቺ ሚሆን ስጦታ እየፈለኩ ነው የዘገየሁት ሆኖም ግን መጥቼ ነበር ጥለሺኝ መጣሽ እንጂ....ደሞ እንዴት ነው ያማረብሽ ልዕልቴ" ...እያለ አቀፋት.....ከካፖርት ኪሱ በዕንቁ የተለበጠ የእጅ አንባር እያወጣ አጇ ላይ አደረገላት...ምንም አላለችውም "ልዕልቴ....ምነው ዝም አልሽ አልወደድሺውም..." "አይደለም....ስተኛ ስተኛ አውልቄ የት እንደማስቀምጠው እያሰብኩ ነው" አለችና ከቆመበት ጥላው ወደ ሳሎን ወረደች። " ስፔናዊያኖች ቁጠኛ አድርገውሻል ውድ ሄሊክስ" አለና ሳቀ...."ይልቁንስ ከ ስፔን የሚመጣ እንግዳ አለን" አለችው እና ከውስኪው 1 ብርጭቆ ቀድታ ጨለጠችው.... "ልዕልቴ ምን ሆነሻል...ይሄን ያህል ስላረፈድኩ አዝነሽብኛል እንዴ..." "የተከበሩ ዶ/ር ጋላሪዬስ...አታስብ በስራ ጉዳይ ነው...ግን...ጥያቄ አታብዛብኝ እንግዳችን Mr.Carlos ይባላል እና ለ እረፍት ወደ ቪራ ጋብዤው ነው"...ብላ ወደውጭ ወደ ሚያሳየው የመስታወት ግድግዳ ፊቷን አዞረች እና እጇን አጣምራ ቆመች.... "ውድ ሄሊክስ ከ 3 ወራት በኋላ ተገናኝተን ፊትሽን አትጣይብኛ...."እያለ እጆቹን በጀርባዋ በኩል ላከ እና..."ጠረንሽ ናፍቆኝ ነበር ልዕልቴ..."እያለ አንገቷ ውስጥ ገባ...."እንግዳ ይመጣል አልኩህ እንግዲህ ከዛ በኋላ እናወራለን ጋላሪዬስ" ብላ ሶፋ ላይ ሄዳ ቁጭ አለች። ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ የቤቱ ደዎል ጠራ...ዶ/ር ጋላሪዬስ በ ግራ እጁ ውስኪ የያዘ ጉርድ ብርጭቆ ጨብጦ በሩ ላይ የሰቀለውን የደህንነት ካሜራ አየ..."ሄሊክስ.. ሚስተር ካርሎስ ይሄ ነው?" ብሎ ወደ እሷ ዞር አለ....ፈጠን አለችና ወደሱ ተጠግታ የመጣውን ሰው ተመለከተች....በሩ ላይ ተገትራ ክፈቺ ወይንም አትክፈቺ የሚል ትዕዛዝ የምትጠብቀው ስናፍቅሽ የጌታዋን እና የእመቤቷን አይን ትጠባበቃለች.... ወ/ሮ ሄሊክስ ወደ ስናፍቅሽ ዞር ብላ የክፈቺ ምልክት ሰጠቻት.... "Bienvenido Sr.Carlos" አለችና ከብረት የፈረጠመ እጆቹን ጨበጠችው... "De nada, señora Helix" አለ ከበረዶ የነጣውን ጥርሱን እያብለጨለጨ...ወ/ሮ ሊክስ ፈጠን ብላ.... "Este es mi esposo Dr. Gallerias" አለችና ወደ ባለቤቷ ጠቆመቺው...ምን እንደሚሉ ፈፅሞ ያልገባው ዶ/ር ጋላሪዬስ ከመካከላቸው እየተቁለጨለጨ ያያቸው ነበር..... "Encantado de conocerlo Dr. Gallerias" አለና ካርሎስ እጁን ዘረጋለት....ዶ/ር ጋላሪዬስም በፈገግታ አንገቱን እያነቃነቀ ጨበጠው። ሰፊ የ እራት ምሽት እና ጨዋታ ካስተናገዱ በኋላ እኩለ ለሊት ላይ  ካርሎስ ለመሄድ ተነሳ...ዶ/ር ጋላሪዬስም አብረው ጥበቃዎቹን ልኮ ሸኘው። ........................................................ ይቀጥላል... ዮኒ      ኣታን @yonatoz Share @Yonny_Athan Share @Yonny_Athan
Показать все...
#ተፈላጊ #ምዕራፍ_3 #ንጉስ_እና_ንጉስ ሰዓቱ 12:00 ገደማ ላይ ነው...የጎንደር የዳር መብራቶች በየቦታው ፈክተዋል...ከ ስልሳ አመታት በላይ ካስቆጠረው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፊት ለፊት ላንድ ክሩዘር(land cruiser) መኪና ያቆመ ጎልማሳ ሰውዬ ከ ኮሌጁ ጋራ በአንክሮ ተፋጠዋል......ቡኒ ሌዘር ጃኬት በውስጥ ደግሞ ጥቁር ሸሚዝ ያነገተ...በርገንዲ ካኪ ሱሪ የታጠቀ..ጥቁር ሌዘር ጫማ የተጫመተ...መኪናውን ዳር አቁሞ ህንፃውን ለረዥም ሰዓታት ሲመለከተው ቆዬ....ይህንን የታዘበው የግል ጓደኛውም ከመኪናው አንገቱን አውጥቶ...."ወንድም ከሱር....ይሄን ያህል መፋጠጥ አይበቃም....በል ና ግባ" "ልክ ነህ ካዳክ....ይበቃል...ስራችንን መጀመር እንዳለብን እየተሰማኝ ነው" እያለ ወደ መኪናው አምርቶ ገባ..... "ለ ዶ/ር ጋላሪዬስ የላከው መልዕክት ደረሰ እንዴ?" "አዎ..... ማክሰን ቪራ ከተማ ውስጥ ደርሷል እቃውን ግን አልሰጠውም...." "ታድያ እስኪሰጠው እንጠብቅ እንጂ....እራሱ ወደ እቅዳችን ዘሎ ይገባልናል እኮ ዶ/ር ከሱር"አለና በረጅሙ ሳቀ። ካዳክ የ ዶ/ር ከሱር የልብ ጓደኛ ነው...ብዙ ስራዎችን አብረው ነው ሚሰሩት...ከአመታት በፊት በ ሳይኮሎጂ (psychology) የመጀመሪያ ድግሪውን እና በ ማኔጅመንት(manegement) ሁለተኛ ድግሪውን ይዞ ዶ/ር ከሱር ከከፈተው የግል ሆስፒታል ውስጥ የዳይሬክተርነት ቦታ ይዞ ይሰራል.....አቋሙ ጠየም ያለ ፂም አልባ..መካከለኛ ቁመት ያለው ደንዳና ሰውነት ይዟል...። #ቪራ_ኢንተርናሽናል_ኤርፖርት "ወ/ሮ ሄሊክስ እንኳን ደህና መጣች" አጠር ብላ ቀላ ያለች...ውበቷ ታይቶ የማትጠገብ አሪፍ የሰውነት ቅርፅ ያላት...ወርቃማ ፀጉር አናቷ ላይ የደፋች ወይዘሮ...አካባቢውን እያጤነች.... "ኽኽ...ጋላሪዬስ አልመጣም" አለች በመገረም አይኗ ላይ የተንጠለጠለውን መነፀሯን እያወለቀች..... "እመቤት አሁን ይደርሳል...." "ይሆናል....." አለችና ክንዷ ላይ ካንጠለጠለችው ነጭ የእጅ ቦርሳዋ ውስጥ ስልኳን እያወጣች.... "ለመሆኑ የምገባበትን ሰዓት አልነገራችሁትም?" "ጠዋት እንደምትገቢ ያውቅ ነበር....ነገር ግን የበረራ ሰዓትሽ መራዘሙን በ ቴክስት ልከንለት ነበር...ያው ስራውን ታውቂው አይደል...." "ይሁን እስቲ አሁን ቤት አድረሰኝ...እንሂድ" "ግን...ትንሽ አንጠብቀውም እመቤት" "እንሂድ አልኩ እንሂድ ነው....ያዘዝኩህን አድርግ" እየተነጫነጨች ለሷ ተብሎ ወደተዘጋጀው ነጭ BMW መኪና አመራች። በምሽት ሰዓት ከአካባቢው ተለይቶ የተንቆጠቆጠው የ ዶ/ር ጋላሪዬስ የመኖሪያ ስፍራ የ ወ/ሮ ሄሊክስን መኪና አስተናገደች...የግቢው ጥበቃዎች ወደ መኪናዋ ከበው... "እንኳን በደህና መጣሽ የኔ እመቤት...." "አመሰግናለሁ ጀግኖች...እንዴት ቆያችሁ...." አለችና ወደ ቤቱ ገባች.....ቦርሳዋን ሶፋ ላይ ወረወረች እና በደከመ መንፈስ ሶፋው ላይ ተዘረፈጠች...."ስናፍቅሽ..."......"ኧረ ስናፍቅሽ"....ስናፍቅሽን ብትጠራትም አቤት የሚል መልስ አልተቀበላትም....ወ/ሮ ሄሊክስ ወደ ስናፍቅሽ ክፍል አመራች.... "ኳኳኳ.....ኳኳኳ...ኳኳኳ"...የማከፍታት አልነበረም... ወ/ሮ ሄሊክስ የበሩን እጀታ ከፍታ ገባች...ማንም የለም ከጠረጴዛው ላይ ከተቀመጣው አብረቅራቂ የእጅ ሰዓት ውጪ...ወ/ሮ ሄሊክስ የእጅ ሰዓቱን አንስታ አየችው..... ለ 53ኛ አመቱ ለባለቤቷ የሰጠቺው ስጦታ። .......................................................... ይቀጥላል... ዮኒ      ኣታን @yonatoz Share @Yonny_Athan Share @Yonny_Athan
Показать все...
👏 1
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.